Ethiopian TipsÂŽ
100 subscribers
121 photos
2 videos
2 files
126 links
Under New Tips:
#Health tip
#Book tip
#Psychology tip
#Technology tip
#Idea tip
#Poem tip
#Quote tip
#Question tip

... and others.

👇👇👇
@ETtips
https://t.me/ETtips
Download Telegram
የግዕዝ ቁጥር ከ 1 እስከ 1ቢሊዮን፦

አልቦ 0
፩ አሐዱ 1
፪ ክልኤቱ 2
፫ ሠለስቱ 3
፬ አርባዕቱ 4
፭ ሐምስቱ 5
፮ ስድስቱ 6
፯ ስብዓቱ 7
፰ ስመንቱ 8
፱ ተሰዓቱ............. 9
፲ አሠርቱ .............10
፲፩ አሠርቱ ወአሐዱ 11
፲፪ አሠርቱ ወክልኤቱ 12
፲፫ አሠርቱ ወሠለስቱ 13
፲፬ አሠርቱ ወአርባዕቱ 14
፲፭ አሠርቱ ወሐምስቱ 15
፲፮ አሠርቱ ወስድስቱ 16
፲፯ አሠርቱ ወሰብዓቱ 17
፲፰ አሠርቱ ወስመንቱ 18
፲፱ አሠርቱ ወተሰዓቱ 19
፳ እስራ 20
፳፩ እስራ ወአሐዱ 21
፳፪ እስራ ወክልኤቱ 22
፳፫ እስራ ወሠለስቱ 23
፳፬ እስራ ወአርባዕቱ 24
፳፭ እስራ ወሐምስቱ 25
፳፮ እስራ ወስድስቱ 26
፳፯ እስራ ወሰብዓቱ 27
፳፰ እስራ ወሰመንቱ 28
፳፱ እስራ ወተሰዓቱ 29
፴ ሠላሳ 30
፴፩ ሠላሳ ወአሐዱ 31
፴፪ ሠላሳ ወክልኤቱ 32
፴፫ ሠላሳ ወሠለስቱ 33
፴፬ ሠላሳ ወአርባዕቱ 34
፴፭ ሠላሳ ወሐምስቱ 35
፴፮ ሠላሳ ወስድስቱ 36
፴፯ ሠላሳ ወሰብዓቱ 37
፴፰ ሠላሳ ወሰመንቱ 38
፴፱ ሠላሳ ወተሰዓቱ 39
፵ አርብዓ 40
፶ ሃምሳ 50
፷ ስድሳ 60
፸ ሰብዓ 70
፹ ሰማንያ 80
፺ ተሰዓ 90
፻ ምዕት 100
፻፩ ምዕት ወአሐዱ 101
፻፪ ምዕት ወክልኤቱ 102
፻፫ ምዕት ወሠለስቱ 103
፻፬ ምዕት ወአርባዕቱ 104
፻፭ መዕት ወሐምስቱ 105
፻፮ ምዕት ወስድስቱ 106
፻፯ ምዕት ወሰብዓቱ 107
፻፰ ምዕት ወስመንቱ 108
፻፱ ምዕት ወተሰዓቱ 109
፻፲ ምዕት ወአሠርቱ 110
፻፲ወ፩ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 111
፻፲ወ፪ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 112
፻፲ወ፫ ምዕት አሠርቱ ወሠለስቱ 113
፻፲ወ፬ ምዕት አሠርቱ ወአርባዕቱ 114
፻፲ወ፭ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 115
፻፲ወ፮ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 116
፻፲ወ፯ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 117
፻፲ወ፰ ምዕት አሠርቱ ወስመንቱ 118
፻፲ወ፱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 119
፻፳ ምዕት ወእስራ 120
፻፴ ምዕት ወሠላሳ 130
፻፵ ምዕት ወአርብዓ 140
፻፶ ምዕት ወሃምሳ 150
፻፷ ምዕት ወስድሳ 160
፻፸ ምዕት ወሰብዓ 170
፻፹ ምዕት ወሰማንያ 180
፻፺ ምዕት ወተሰዓ 190
፪፻ ክልኤቱ ምዕት 200
፪፻ወ፩ ክልኤቱ ምዕት ወአሐዱ 201
፪፻ወ፪ ክልኤቱ ምዕት ወክልኤቱ 202
፪፻ወ፫ ክልኤቱ ምዕት ወሠለስቱ 203
፪፻ወ፬ ክልኤቱ ምዕት ወአርባዕቱ 204
፪፻ወ፭ ክልኤቱ ምዕት ወሐምስቱ 205
፪፻ወ፮ ክልኤቱ ምዕት ወስድስቱ 206
፪፻ወ፯ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓቱ 207
፪፻ወ፰ ክለኤቱ ምዕት ወስመንቱ 208
፪፻ወ፱ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓቱ 209
፪፻ወ፲ ክልኤቱ ምዕት ወአሠርቱ 210
፪፻፲ወ፩ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 211
፪፻፲ወ፪ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 212
፪፻፲ወ፫ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሠልስቱ 213
፪፻፲ወ፬ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአርባቱ 214
፪፻፲ወ፭ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 215
፪፻፲ወ፮ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 216
፪፻፲ወ፯ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 217
፪፻፲ወ፰ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰመንቱ 218
፪፻፲ወ፱ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 219
፪፻፳ ክልኤቱ ምዕት ወእስራ 220
፪፻፴ ክልኤቱ ምሪዕት ወሠላሳ 230
፪፻፵ ክልኤቱ ምዕት ወአርብዓ 240
፪፻፶ ክልኤቱ ምዕት ወሃምሳ 250
፪፻፷ ክልኤቱ ምዕት ወስድሳ 260
፪፻፸ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓ 270
፪፻፹ ክልኤቱ ምዕት ወሰማንያ 280
፪፻፺ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓ 290
፫፻ ሠለስቱ ምዕት 300
፬፻ አርባዕቱ ምዕት 400
፭፻ ሐምስቱ ምዕት 500
፮፻ ስድስቱ ምዕት 600
፯፻ ስብዓቱ ምዕት 700
፰፻ ስመንቱ ምዕት 800
፱፻ ተሰዓቱ ምዕት 900
፲፻ አሠርቱ ምዕት 1000
፳፻ እስራ ምዕት 2000
፴፻ ሠላሳ ምዕት 3000
፵፻ አርብዓ ምዕት 4000
፶፻ ሃምሳ ምዕት 5000
፷፻ ሳድስ ምዕት 6000
፸፻ ሰብዓ ምዕት 7000
፹፻ ሰማንያ ምዕት 8000
፺፻ ተሰዓ ምዕት 9000
፻፻ እልፍ 10,000
፪፻፻ ክልኤቱ እልፍ 20,000
፫፻፻ ሠለስቱ እልፍ 30,000
፬፻፻ አርባዕቱ እልፍ 40,000
፭፻፻ ሐምስቱ እልፍ 50,000
፮፻፻ ስድስቱ እልፍ 60,000
፯፻፻ ሰብዓቱ እልፍ 70,000
፰፻፻ ስመንቱ እልፍ 80,000
፱፻፻ ተሰዓቱ እልፍ 90,000
፲፻፻ አሠርቱ እልፍ 100,000
፳፻፻ እስራ እልፍ 200,000
፴፻፻ ሠላሳ እልፍ 300,000
፵፻፻ አርብዓ እልፍ 400,000
፶፻፻ ሃምሳ እልፍ 500,000
፷፻፻ ስድሳ እልፍ 600,000
፸፻፻ ሰብዓ እልፍ 700,000
፹፻፻ ሰማንያ እልፍ 800,000
፺፻፻ ተሰዓ እልፍ 900,000
፻፻፻ አእላፋት 1,000,000
፲፻፻፻ ትእልፊት 10,000,000
፻፻፻፻ ትልፊታት 100,000,000
፲፻፻፻፻ ምእልፊት 1,000,000,000

https://t.me/ETtips
ስልካችን ስቶሬጅ (Storage) ከሞላ ዋናው መፍትሔ ይህን አፕ መጠቀም ነው !

📌 ስለ Storage problem ከዚህ በፊት post አድርገናል ግን ይህን ዘዴ እንድትጠቀሙት እንመክራለን !

📌 ብዙ ሰው ከስልኩ አለ ግን የማንጠቀመው ዘዴ !

[በነገራችን ላይ እኔ የምመርጠው ቀዳሚ መፍትሔ ነው ! ]

📌 Flash ,Memory .... ከመግዛትና ከማስቀመጥ ብዙ እጥፍ ይሻላልም ይመከራልም !

~ Google "drive" በሚል application የተለያዩ file አችንን እንድናስቀምጥ የሚያደርግ system አለው !

📌 በዚህ የ Google App ውስጥ...

🎯ፈቶ፣video delete ማድረግ አይጠበቅባችሁም
🎯ስልካችሁ ቢጠፋ ፋይላችሁን ማግኘት ትችላላችሁ
🎯 በአንድ email account ብቻ 15 GB ቦታ ይሰጣችኋል 😍
🎯5 Email ቢኖራችሁ 15x5 =75GB ከስልካችሁ storage ውጭ Google ይሰጣችኋል !

~ ከናንተ ሚጠበቀው email address ና password በጥንቃቄ መያዝ ነው !

~ 100% አስተማማኝ ነው ማንም የግል መረጃችሁን አያይም !

📌 ከ Google ምርት አንዱ የሆነው ና በ Drive storage የሚጋራው Google photos ደግሞ ዋና የፈቶ ማስቀመፃ App ነው...

📌" አብዛኛው ሰው የማይጠቀመው ግን እያንዳንዱ አንድሮይድ ስልክ ውስጥ ያለ አንድ ድንቅ መተግበሪያ አለ ። እሱም "Google Photos" ይባላል ።

📌 ይህም አፕ ፎቶዎችን ማስቀመጫ ብቻ ሳይሆን የስልካችሁን ቦታ ነፃ ማድረጊያ ምርጡ ዘዴ ነው !

[አሰራሩ በቅደም ተከተል ...👇 ]

1) Google Photos አፕ ውስጥ ይግቡ።

2) ከላይ የፕሮፋይል ምልክታችሁን ንኩና "Photos settings" ውስጥ ግቡ።

3) "Backup" የሚለውን አብሩት (ይህ ፎቶዎቻችሁን ወደ Google cloud storage upload ያደርገዋል ) ።

4) አሁን ዋናው ሚስጥር እዚህ ጋር ነው፦ "Free up space" የሚለውን በመጫን በጣም ብዙ free storage ማግኘት ትችላላችሁ !

📌 ስልካችሁ ወደ ጎግል የተሰቀሉትን (Backup የተደረጉትን) ፎቶዎች ከስልካችሁ "Internal Storage" ላይ ብቻ ነው delete የሚያደርጋቸው ። ፎቶዎቹ ግን አሁንም በ "Google Photos" ውስጥ ይኖራሉ ።

🎯 ስልካችሁ ቢሰረቅ ወይም ቢጠፋ እንኳ፣ አዲስ ስልክ ገዝታችሁ የድሮ የኢሜል (Gmail) አድራሻችሁን ስታስገቡ፣ የድሮ ፎቶዎቻችሁ በሙሉ እንደነበሩ ተመልሰው ይመጣላችኋል ።

📌 የመጨረሻ Tip ፦ ከናንተ ሚጠበቀው ነገር email address እና password አለመርሳት ነው ! ፓስወርዳችሁንና email address ሳችሁን በተለያየ ቦታዎች አስቀምጡ !
ለምሳሌ በ Telegran Saved message ,Other cloud app ወይም ቶሎ ከምታገኙበት ቦታ !

#Backup
#Google_photos
#storage_full

https://t.me/ETtips
ስለ ቴሌግራም ይህን ማወቅ አለባችሁ !

📌 1. የኮድ ችግር መፍትሄ ፦ ቴሌግራም በድጋሚ ሲገቡ ኮድ አልመጣ ካለዎት፣ Telegram X አውርዱና ስልክ ቁጥሩን አስገብታችሁ በ SMS ሳይሆን "Get code via call" የሚለውን በመምረጥ በስልክ ጥሪ ኮዱ እንዲነገራችሁ አድርጉ ። ፈጣን መፍትሄ ነው!

📌 2. ኢንተርኔት መቆጠቢያ፦ ቴሌግራም ያለምክንያት ዳታ እንዳይጨርስባችሁ Settings > Data and Storage ውስጥ ገብታችሁ "Automatic Media Download" የሚሉትን 3ቱንም አማራጮች አጥፏቸው (Off አድርጓቸው) ። ቪዲዮና ፎቶ በራሱ መውረድ ያቆማል!

📌 3. ስልክ ቁጥርን መደበቅ፦ ማንም ሰው በእርስዎ ፈቃድ ቁጥርዎን እንዳያይ Settings > Privacy and Security > Phone Number ውስጥ ገብታችሁ "Nobody" የሚለውን ይምረጡ። በዚህም ደህንነታችሁን መጠበቅ ትችላላችሁ።

📌 4. ለራስ መልእክት መላክ (Cloud Storage)፦ ቴሌግራም ላይ "Saved Messages" የሚባለው ክፍል ለእርስዎ ብቻ የተዘጋጀ የ24 ሰዓት ማከማቻ ነው። ማንኛውንም ፎቶ፣ ቪዲዮ ወይም ፋይል እዚያ ላይ በመላክ ለዘላለም ማስቀመጥ እና ከማንኛውም ስልክ ማግኘት ትችላላችሁ ።
(እችን እምኳ ገላግሌ በሏት ብዙ መረጃ ሚይዝልን ነው 😍)

📌 5. በስም ብቻ ሰውን መፈለግ፦ የሰው ስልክ ቁጥር ሳይኖራችሁ በቴሌግራም መገናኘት ትችላላችሁ። Settings > Username ውስጥ ገብታችሁ የራሳችሁን ስም (ለምሳሌ @ETtips ) ፍጠሩ። ቁጥራችሁን ሳይሰጡ በዚህ ስም ብቻ ሰዎች እንዲያገኟችሁ ማድረግ ትችላላችሁ ።

📌 6. የመልእክት ሰዓት መወሰን (Scheduled Messages)፦ ለአንድ ሰው መልእክት መላክ ፈልገው ግን ሰዓቱ ካልደረሰ፣ የመላኪያ (Send) ቁልፉን ጫን አድርገው በመያዝ "Schedule Message" የሚለውን በመምረጥ እንዲላክ የሚፈልጉበትን ቀንና ሰዓት መወሰን ይችላሉ።

📌 7. ፎቶን ሳይደበዝዝ መላክ ( በQuality)፦ ፎቶ ስትልኩ ጥራቱ እንዳይቀንስ ከፈለጋችሁ እንደ ፎቶ ሳይሆን "File" የሚለውን መርጣችሁ ላኩት። ፎቶው ልክ እንደተነሳበት ጥራት ይደርሳል!

📌 8. ቪዲዮን ወደ GIF መቀየር፦ ቪዲዮ ለሰው ሲልኩ ድምፁን "Mute" (ማጥፊያ) ምልክቱን ከነካችሁት፣ ቪዲዮው ወዲያውኑ ወደ GIF ይቀየራል፤ ይህም በጣም አነስተኛ ዳታ (MB) እንዲጠቀም ያደርገዋል ።

📌 9. በስውር መልእክት ማንበብ ፦ የመጣላችሁን መልእክት የላከው ሰው ሳያውቅ (ሁለት ምልክት ሳይበራ) ለማንበብ፣ የሰውየውን ፎቶ (Profile) ጫን አድርገው ይያዙት ። መልእክቱ በትንሽ መስኮት ተከፍቶ ይታያችኋል 🙄!

📌 10. የቴሌግራም መጠለፍ በፍጥነት ለመመለስ ፦ አካውንታችሁ በሌላ ሰው መከፈቱን ለማወቅ Settings > Devices ውስጥ ይግቡ ። ከእርስዎ ስልክ ውጪ ሌላ መሳሪያ ካዩ "Terminate all other sessions" የሚለውን በመጫን ሌላ ሰው በናንተ account እየተጠቀመ ከሆነ እንዳይጠቀም ማድረግ ትችላላችሁ !

🎯 Tip ፦ ቴሌግራማችሁን 100% አስተማማኝ ለማድረግ Two-Step Verification የሚለው ማብራታችሁን እንዳትረሱ!

#TelegramTips #TelegramHacks
#DigitalLife

https://t.me/ETtips
❤1
አዲስ ስልክ ለመግዛት ሲያስቡ እነዚህን ነጥቦች የግድ ይፈትሹ!

ስልክ መግዛት ዝም ብሎ ፎቶ ማየት ወይም ብራንድ መምረጥ አይደለም። የገንዘብዎ ዋጋ እንዲመለስልዎትና ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግልዎት የሚከተሉትን 7 ወሳኝ ነጥቦች ልብ ይበሉ፦

📌 1) ፕሮሰሰር (Processor)፦ የስልኩ "አንጎል" ነው። ስልኩ እንዳይቆራረጥ (Lag እንዳያደርግ) ጠንካራ ፕሮሰሰር ያለው መሆኑን ያረጋግጡ። ለምሳሌ ለጌም ወይም ለከባድ ስራ Snapdragon ወይም Apple Bionic የተሻሉ ናቸው።

📌 2) ራም (RAM)፦ ስልኩ በአንድ ጊዜ ብዙ አፖችን የመክፈት አቅሙን ይወስናል። ዛሬ ላይ ቢያንስ 6GB ወይም 8GB RAM ያለው ስልክ መግዛት ለፍጥነትዎ አስተማማኝ ነው።

📌 3) ስክሪን (Display Quality) ፦ ቀኑን ሙሉ የምናየው ስክሪኑን ስለሆነ AMOLED ወይም OLED ስክሪን ያላቸውን ይምረጡ። ቀለማቸው ጥራት ያለውና ለዓይን የማይደክሙ ናቸው።

📌 4) ባትሪ (Battery Life) ፦ ከቻርጅ ጋር ተጣብቀው መኖር ካልፈለጉ ቢያንስ 5000mAh ባትሪ ያለውና Fast Charging (በፍጥነት ቻርጅ የሚያደርግ) መሆኑን ያረጋግጡ ።

📌 5) ካሜራ (Camera Quality) ፦ የሜጋፒክሰል (MP) ብዛት ብቻውን ጥራት አይሰጥም ። በዩቲዩብ ላይ የስልኩን የካሜራ "Sample" ቪዲዮዎች በማየት ትክክለኛ ጥራቱን ያረጋግጡ ።

📌 6) ስቶሬጅ (Internal Storage) ፦ ዛሬ ላይ አፖችና ፎቶዎች ትልቅ ቦታ ስለሚይዙ ቢያንስ 128GB ያለው ስልክ ይመረጣል ። "Memory Full" ከሚል ጭንቀት ያርፉበታል ።

📌 7) የገበያ ዋጋ ፦ ሁሌም ዋጋውን ካሰቡት በጀት ጋር አገናዝቡ። አንዳንድ ጊዜ በስሙ ብቻ ... ውድ ከሆነ ስልክ ይልቅ፣ በተመሳሳይ ዋጋ የተሻለ አቅም (Specs) ያላቸው ሌሎች ብራንዶችን ማግኘት እንደሚቻል ታሳቢ አድርጉ።

🎯 አንድ ሚስጥር ፦

ስልክ ከመግዛታችሁ በፊት 'Google' ላይ በመግባት የስልኩን ስም ጽፋችሁ መጨረሻ ላይ 'GSMarena' ብላችሁ ፈልጉ። ስለ ስልኩ እያንዳንዱን ዝርዝር መረጃ (Specs) እዚያ ላይ በግልጽ ታገኛላችሁ!

https://t.me/ETtips
Ethiopian Tips® pinned «አዲስ ስልክ ለመግዛት ሲያስቡ እነዚህን ነጥቦች የግድ ይፈትሹ! ስልክ መግዛት ዝም ብሎ ፎቶ ማየት ወይም ብራንድ መምረጥ አይደለም። የገንዘብዎ ዋጋ እንዲመለስልዎትና ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግልዎት የሚከተሉትን 7 ወሳኝ ነጥቦች ልብ ይበሉ፦ 📌 1) ፕሮሰሰር (Processor)፦ የስልኩ "አንጎል" ነው። ስልኩ እንዳይቆራረጥ (Lag እንዳያደርግ) ጠንካራ ፕሮሰሰር ያለው መሆኑን ያረጋግጡ። ለምሳሌ ለጌም ወይም…»
ቴሌግራም በኮምፒውተር እየተጠቀሙ አማርኛ አላነብ ብሎታል ?

ከሰሞኑ የቴሌግራም መተግበሪያ የዊንዶው ቨርዥን አማርኛ ጹሑፎችን ለማንበብ ሲያስቸገር ተስተውሏል።

ቴሌግራም በኮምፒውተር የምትጠቀሙ  ተከታዩን ቅደም ተከተል በመጠቀም አማርኛ እንዲያነብላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።

Setting > Chat Setting > Font Family > ከሚመጣላችሁ ዝርዝር ውስጥ የሚፈልጉትን የአማርኛ ፎንት ይምረጡ (ለምሳሌ፦ Power Geez Unicode1, Ebrima, Nyala , Noto sans . . .) > Save > Restart

አማርኛ ፎንት በአማራጭ ውስጥ የማያገኙ ከሆነ የሚፈልጉትን ፎንት ቀጥታ ካወረዳችሁ በኋላ ቴሌግራማችሁን እንደ አዲስ በመክፈት መምረጥና ማስተካከል ይችላሉ።

ለአብነትም፥ Noto sans የተሰኘውን ፎንት https://fonts.google.com/noto/specimen/Noto+Sans+Ethiopic ላይ ማውረድ ይችላሉ። 

አማርኛ ፎንት ስለመረጡ አማርኛ ብቻ ነው የሚያነበው ማለት አይደለም የላቲን ፊደላትንም ማንበብ ያስችላችኋል።

https://t.me/ETtips
❤1
የባንክ ሒሳብን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር አላጣመሩም? ጊዜው እየሄደ ስለሆነ በቀጥታ ካሉበት ሆነው ኦንላይን ያጣምሩ።

💸 ዘመን ባንክ: https://fayda.zemenbank.com

💸 ሒጅራ ባንክ: https://apps.hijradigital.com/fayda/v2

💸 ሕብረት ባንክ : https://services.hibretbank.com.et/fayda

💸 ብርሀን ባንክ: https://nationalidharmonization.berhanonline.et:9095/fayda-login

💸 አዲስ ባንክ: https://fayda.addisbank.com.et

💸 አቢሲኒያ ባንክ: https://cs.bankofabyssinia.com/fayda_connect 

💸 አዋሽ ባንክ : https://fayda.awashbank.com

💸 የኦሮሚያ ህብረት ሾል ባንክ: https://my.coopbankoromiasc.com/harmonization 

💸 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡  https://cbefayda.cbe.com.et/

💸 ኦሮሚያ ባንክ ፡ https://obfayda.oromiabank.com/

💸 ወጋገን ባንክ : https://fayda.wegagenbanksc.com.et/harmonization

💸 ንብ ባንክ፡ https://fayda.nibbank.com.et/

💸 ፀሀይ ባንክ፡https://fayda.tsehaybank.com.et/FAYDA/home

💸  ስንቄ ባንክ : https://fayda.siinqeebank.com:7443

💸  ዘምዘም ባንክ : https://fayda.zamzambank.com.et

💸  አማራ ባንክ : https://fayda.amharabank.com.et

https://t.me/ETtips
​🛑 ባለሙያዎቹ ብቻ የሚያውቋቸው ድብቅ የቴክኖሎጂ እውነታዎች!
​
ሰዎች በልምድ "ጥሩ ነው" ብለው
የሚያደርጓቸው፣ ግን እንዲያውም ስልካቸውን የሚጎዱ ወይም የማይጠቅሙ ድብቅ ሚስጥሮችን፦

​1️⃣ "Auto-Brightness" ባትሪ ይቆጥባል?
​
ብዙ ሰው ስልኩ ራሱ ብርሃኑን እንዲያስተካክል (Auto-Brightness) ማድረጉ ባትሪ ይቆጥባል ብሎ ያስባል።

​📌 እውነታው፦ ይህን ለማድረግ ስልኩ ሁልጊዜ የላይት ሴንሰሩን (Light Sensor) ማሰራት አለበት። ሴንሰሩ በየሰከንዱ የአካባቢውን ብርሃን ስለሚለካ የራሱ የሆነ ባትሪ ይበላል። ብርሃኑን በራሳችሁ እጅ ማስተካከል ከሴንሰሩ በላይ ባትሪ ይቆጥባል!

​2️⃣ "Battery Saver" ሁልጊዜ ማብራት
​
አንዳንድ ሰዎች ባትሪው ሳይቀንስ ገና 100% እያለ ባትሪ ለመቆጠብ በማሰብ "Battery Saver" ያበራሉ።

​📌 እውነታው፦ ይህ ሲሆን ስልኩ የፕሮሰሰሩን (CPU) ፍጥነት በሃይል ይቀንሳል፣ ኖቲፊኬሽኖችን ያዘገያል፣ እና ስልኩ እንዲጨናነቅ (Lag) ያደርገዋል። ይህ አማራጭ ባትሪ ከ20% በታች ሲወርድ እንጂ ሁልጊዜ መጠቀም ስልኩን ያደክመዋል!

​3️⃣ ስልክን በ "Vibrate" (ንዝረት) ማድረግ
​ስልካችን ድምፅ እንዳያሰማ ብለን ሁልጊዜ ንዝረት (Vibration) ላይ እናደርጋለን።

​📌 እውነታው፦ በስልኩ ውስጥ ያለው የንዝረት ሞተር (Vibration Motor) ከስልኩ ስፒከር በላይ ከፍተኛ ሀይል ይፈልጋል። ስልኩ እንዲርገበገብ ትልቅ ጉልበት ስለሚጠይቅ ባትሪዎን በፍጥነት ይጨርሰዋል። ባትሪ ለመቆጠብ ወይ ድምፅ አብሩ ወይም ሙሉ በሙሉ "Silent" አድርጉት!

​💡እነዚህን ትናንሽ ስህተቶች በማስተካከል የስልክዎን እድሜ እና የባትሪ ቆይታ ያራዝሙ!

​#TechSecret
#BatteryLife
#CPU
#TechTip

https://t.me/ETtips
AI ፣ ML እና DL ያላቸውን ግንኙነት በሶስት አጭር አረፍተ ነገሮች እንዲህ መረዳት ይቻላል፡

1️⃣ AI (Artificial Intelligence): ኮምፒውተሮች እንደ ሰው እንዲያስቡና ውሳኔ እንዲሰጡ የሚያስችል ሰፊው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ነው።

2️⃣ ML (Machine Learning): ኮምፒውተሮች በግልጽ ትዕዛዝ ሳይሰጣቸው፣ ከመረጃ (Data) በመነሳት ራሳቸውን እንዲያስተምሩ የሚያደርግ የ AI ንዑስ ክፍል ነው።

3️⃣ DL (Deep Learning): በሰው ልጅ የነርቭ ሥርዓት ተመስሎ የተሰራ፣ በጣም ውስብስብ የሆኑ መረጃዎችን ለመተንተን የሚያገለግል የ ML ጥልቅ ዘርፍ ነው።

https://t.me/ETtips
#ሲም_ካርድዎ እውነተኛ ወርቅ እንዳለው ያውቃሉ?

📌በሲም ካርዶች ውስጥ የሚገኘው የወርቅ ምስጢር እና የቴክኖሎጂ ፋይዳው

በዘመናዊው የኮሙኒኬሽን ዓለም ውስጥ በየቀኑ የምንጠቀምባቸው ሲም ካርዶች በውስጣቸው እውነተኛ ወርቅ እንደሚይዙና ይህም ለቴክኖሎጂው ስኬት ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገለጸ።

ብዙዎች የሲም ካርድ ወርቃማ ቀለም ለጌጥ ወይም ለቀለም የተቀባ ቢመስላቸውም የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት በካርዱ ላይ የሚታየው ስስ ሽፋን እውነተኛ የወርቅ ማዕድን ነው።

ሲም ካርዶች ወርቅን የሚጠቀሙት ለቴክኖሎጂያዊ ጠቀሜታው ሲሆን ወርቅ ከሌሎች ማዕድናት በተለየ መልኩ የማይዝግ በመሆኑ ስልካችን ውስጥ ለረጅም ጊዜ ቢቆይም ከአየርና ከእርጥበት ጋር ተገናኝቶ ሳይበላሽ አስተማማኝ ግንኙነት እንዲፈጥር ይረዳል።

በተጨማሪም ማዕድኑ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ አስተላላፊ በመሆኑ መረጃዎች ከሲም ካርዱ ወደ ስልኩ ያለምንም መቆራረጥና በከፍተኛ ፍጥነት እንዲሸጋገሩ ያስችላል።

ምንም እንኳን በካርዶቹ ላይ የሚገኘው ወርቅ እውነተኛ ቢሆንም መጠኑ ግን እጅግ በጣም አነስተኛ መሆኑ ተመልክቷል። በጥናት መሠረት አንድ ግራም ወርቅ ለማግኘት በሺዎች የሚቆጠሩ አሮጌ ሲም ካርዶችን መሰብሰብና ማቅለጥ ያስፈልጋል።

ይህንን ተከትሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤሌክትሮኒክስ ብክነትን ለመቀነስ አሮጌ ስልኮችንና ሲም ካርዶችን መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ሥራ ትልቅ ትኩረት እየተሰጠው ይገኛል። በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሲም ካርዶች ሲሰበሰቡ ከፍተኛ መጠን ያለው ወርቅ፣ ብር እና ፓላዲየም የተባሉ ውድ ማዕድናትን ማውጣት እንደሚቻል ተረጋግጧል።

በመሆኑም ተጠቃሚዎች አሮጌ ሲም ካርዶችን ዝም ብሎ ከመጣል ይልቅ ለኤሌክትሮኒክስ ማዕከላት ቢሰጡ ለተፈጥሮ ጥበቃና ለኢኮኖሚው ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ተገልጿል።

https://t.me/ETtips
#E-SIM ምንድን ነው?

E-SIM (Embedded SIM) ማለት በቀላሉ ሲነገር "የተቀበረ" ወይም በስልካችን ውስጥ ተገጥሞ የሚመጣ የዲጂታል ሲም ካርድ ዓይነት ነው። እንደለመድነው የሚገባና የሚወጣ የሚታይ ካርድ ሳይሆን፣ በስልኩ ሰሌዳ (Motherboard) ላይ ተገጥሞ የሚመጣ ጥቃቅን ቺፕ ነው።
​ኢ-ሲም (eSIM) ከወትሮው ሲም ካርድ የሚለይባቸው ዋና ዋና ነጥቦች እነዚህ ናቸው፦

​1. ካርድ ማስገባት አያስፈልግም
​ስልኩ ውስጥ አስቀድሞ ስላለ፣ አዲስ ቁጥር ለማስጀመር ካርድ መግዛትና በስልኩ ቀዳዳ በኩል መክተት አያስፈልግዎትም። በኢንተርኔት አማካኝነት የሚሰጠውን QR Code ስካን በማድረግ ብቻ አገልግሎቱን መጀመር ይቻላል።
​2. ብዙ ቁጥሮችን በአንድ ስልክ
​በአንድ ኢ-ሲም ላይ ከአንድ በላይ የሆኑ የተለያዩ ኦፕሬተሮችን ቁጥር መያዝ ይቻላል። ለምሳሌ ለስራ እና ለግል የሚሆኑ ቁጥሮችን በቀላሉ እየቀያየሩ ለመጠቀም ይመቻል።
​3. ለደህንነት የተሻለ ነው
​ስልክዎ ቢጠፋ ወይም ቢሰረቅ፣ ሌባው ሲም ካርዱን አውጥቶ ሊጥለው አይችልም። ይህም ስልኩን ለማግኘት ወይም ለመቆለፍ የተሻለ እድል ይሰጣል።
​4. ቦታ አይይዝም
​ሲም ካርድ የሚገባበትን ቀዳዳ ስለሚያስቀር፣ የስልክ አምራቾች ያን ክፍት ቦታ ለትልቅ ባትሪ ወይም ለሌላ ዘመናዊ መገልገያ እንዲጠቀሙበት ይረዳቸዋል።
​ማወቅ ያለብዎት፦
​የስልክዎ አይነት፦ ሁሉም ስልኮች ኢ-ሲም አይቀበሉም። አብዛኛውን ጊዜ ከአይፎን 11 (iPhone 11) እና ከሳምሰንግ S20 (Samsung S20) በኋላ የወጡ ስልኮች ይህንን ቴክኖሎጂ ይደግፋሉ።
​የአገልግሎት ሰጪው ዝግጁነት፦ ኢ-ሲም ለመጠቀም የሚጠቀሙበት የቴሌኮም ድርጅት (ለምሳሌ ኢትዮ ቴሌኮም ወይም ሳፋሪኮም) አገልግሎቱን መጀመራቸውን ማረጋገጥ አለብዎት።

https://t.me/ETtips
🖥️ Computer Related Parts That You Must Know! 🤔💯
.
.
.
#computer #computersetup #accesorios #pcparts #pcsetup #computertech #techtips

https://t.me/ETtips
📝 MS Word Shortcut Keys: Must Know & Boost Your Typing Skill 😍💯
.
.
.
#msword #MSWordTips #mswordtricks #MSWORDtutorial #microsoftWord #tipsandtricks #tech #pctips #typing

https://t.me/ETtips
#5 ምርጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መተግበሪያዎች፦

1. Perplexity AI (https://www.perplexity.ai) – ለተረጋገጠ መረጃ ፍለጋ

👍 Googleን ከመሳሰሉ የመረጃ መፈለጊያዎች ምንጮች (Sources) አሰባስቦ በዝርዝር የሚገልጽ Ai ነው። ማንኛውንም ጥያቄ ሲጠይቁት፣ መልሱን ከተለያዩ ድረ-ገጾች አቀናጅቶ ከመስጠቱም በላይ፣ መረጃውን ከየትኛው ገጽ እንዳገኘው ሊንኩን ያስቀምጣል። ይህም መረጃው ትክክል መሆኑን ራሳችን ለማረጋገጥና ተጨማሪ ንባብ ለማድረግ እድል ይሰጠናል።

👉 የነፃ አገልግሎት (Free): መደበኛ ጥያቄዎችን ለመጠየቅና ምንጮችን ለማየት ሁልጊዜም ነፃ ነው።

👉 የክፍያ አገልግሎት (Paid): 'Perplexity Pro' በወር $20 ያህል።

👉 ጥቅሙ: ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው መረጃዎች ከተለያዩ ምንጮች ለማግኘትና ለማጣራት ያስችላል።

👌 አጠቃቀም: እንደ Google ማንኛውንም ርዕስ ጻፉ። መተግበሪያው ወቅታዊ መረጃዎችን ከኢንተርኔት አፈላልጎ ምንጮችን (Links) ጠቅሶ ይመልሳል።

👌 ምሳሌ: "በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ያለው የባንክ ወለድ መጠን ስንት ነው?"

👌 ጠቃሚ ነጥብ: "Focus" የሚለውን በመጫን ፍለጋችሁ በዩቲዩብ፣ በአካዳሚክ ጽሁፎች ወይም በዜና ላይ ብቻ እንዲያተኩር ማድረግ ትችላላችሁ።
.
.
.
2. Gamma AI (https://gamma.app) -- ለPowerPoint ስላይዶች

👍 የርዕስ ስም ብቻ በመስጠት ፕሮፌሽናል የPowerPoint (Presentation) ስላይዶችን በሰከንዶች ውስጥ ለማዘጋጀት ይጠቅማል። ጽሁፉን፣ ምስሎችንና ዲዛይኑን በራሱ የሚያቀናጅ ሲሆን፣ እንደ አስፈላጊነቱ በቀላሉ ማስተካከል ይቻላል። ለስብሰባዎች ወይም ለክፍል ውስጥ ገለጻዎች ውብና ሳቢ ስላይዶችን ያለ ድካም ለማዘጋጀት ለሚፈልግ ሰው ተመራጭ Ai ነው።

👉 የነፃ አገልግሎት (Free): መጀመሪያ ሲመዘገቡ 400 Credits ይሰጥዎታል። ይህም ጥቂት ስላይዶችን በነፃ ለመስራት ይበቃል።

👉 የክፍያ አገልግሎት (Paid): በወር $8 (Starter) ወይም $15 (Pro) ይጀምራል።

👉 ጥቅሙ: የክፍያው የGamma ምልክት (Watermark) ለማጥፋትና ያልተገደበ ስላይዶችን ለመስራት ያስችላል።

👌 አጠቃቀም: "Create New" የሚለውን በመጫን "Presentation" ምረጡ። ከዚያም የርዕሳችሁን ስም ጻፉ፤ (ለምሳሌ፦ "ስለ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጥቅሞች")።

👌 ምሳሌ: AIው ዝርዝር አጀንዳዎችን ያወጣል፤ "Continue" ስትሉት በሰከንዶች ውስጥ ምስልና ጽሁፍ ያለው ስላይድ ያዘጋጃል።

👌 ጠቃሚ ነጥብ: ዲዛይኑን ለመቀየር "Edit with AI" የሚለውን በመጫን "ምስሎቹን ወደ ካርቱን ቀይርልኝ" ብላችሁ ማዘዝ ትችላላችሁ።
.
.
.
3. ChatPDF (https://www.chatpdf.com) – ከፋይሎች ጋር ለመወያየት

👍 ከፒዲኤፍ ፋይሎች ጋር እንደ ሰው "ቻት" ለማድረግና ፋይሉን ለማጠቃለል የሚያስችል Ai ነው። መጽሃፍትን፣ የጥናት ጽሁፎችን ወይም ማንኛውንም ሰነድ በመጫን፣ በውስጡ ስላለው ጉዳይ ጥያቄዎችን መጠየቅ ይችላሉ። ፋይሉን በደንብ ለሚረዳ ሰው ጥያቄ እንደማቅረብ ይቆጠራል፤ ይህም ረጅም ጽሁፎችን የማንበብ አሰልቺ ሂደት በውይይት እንዲተካ ያደርገዋል።

👉 የነፃ አገልግሎት (Free): በቀን 2 ፒዲኤፍ (እስከ 120 ገጽ) እና 50 ጥያቄዎችን በነፃ ማቅረብ ይቻላል።
👉 የክፍያ አገልግሎት (Paid): በወር $15 አካባቢ።
👉 የክፍያ ጥቅሙ: በቀን እስከ 50 ፒዲኤፍ ፋይሎችን (እስከ 2,000 ገጽ) ለመተንተንና ያልተገደበ ጥያቄ ለመጠየቅ ያስችላል::

👌 አጠቃቀም: ማንኛውንም የፒዲኤፍ ፋይል ድረ-ገጹ ላይ ጎትቶ ማስገባት (Drag and Drop)።

👉 ምሳሌ: "ከዚህ ሰነድ ውስጥ 5 የፈተና ጥያቄዎችን አውጣልኝ" ወይም "ይህንን ፋይል በ10 ነጥቦች አሳጥርልኝ" በማለት ማዘዝ ይቻላል::
👉 ጠቃሚ ነጥብ: ለፈተና ለሚዘጋጁ ተማሪዎች መጽሐፍን በቀላሉ ለመረዳት በጣም ይረዳል።
.
.
.
4. Otter.ai (https://otter.ai) -- ንግግርን ወደ ጽሁፍ ለመቀየር

👍 ኦተር በስብሰባዎች ወይም በትምህርት ክፍለ ጊዜ የሚነገሩ ንግግሮችን በቀጥታ ወደ ጽሁፍ (Transcription) የሚቀይር ድንቅ Ai ነው። ንግግሩን ከመጻፍ ባለፈ፣ ዋና ዋና ነጥቦችን ለይቶ በማውጣት ማጠቃለያ ያዘጋጃል። በስራ ስብሰባ ላይ ቃለ-ጉባኤ መያዝ ሳያስፈልግ፣ በውይይቱ ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ በኋላ ላይ የተባለውን ሁሉ በጽሁፍ ለማግኘት ያስችላል።

👉 የነፃ አገልግሎት (Free): በወር 300 ደቂቃ የንግግር ትርጉም (Transcription) በነፃ ይሰጣል።
👉 የክፍያ አገልግሎት (Paid): በወር $10 አካባቢ ይጀምራል።
👉 የክፍያው ጥቅሙ ብዙ ደቂቃዎችን ለመጠቀም፣ የቪዲዮ ስብሰባዎችን (Zoom/Teams) በጥራት ቀድቶ ወደ ጽሁፍ ለመቀየር የላቀ እድል ይሰጣል።

👌 አጠቃቀም: በስብሰባ ወይም በትምህርት ሰዓት "Record" የሚለውን መጫን
👌 ምሳሌ: መተግበሪያው የሚነገረውን ሁሉ በጽሁፍ ይጽፋል፤ ስብሰባው ሲያልቅ ደግሞ "ማን ምን አለ?" የሚል ማጠቃለያ ያወጣል።
👌 ጠቃሚ ነጥብ: በZoom ወይም Google Meet ስብሰባዎች ላይ እንደ ረዳት ገብቶ ቃለ-ጉባኤ እንዲይዝ ማድረግ ይቻላል።
.
.
.
5. WolframAlpha (https://www.wolframalpha.com) -- ለሂሳብ እና ሳይንስ

👍 ይህ መተግበሪያ ለሂሳብ፣ ለሳይንስና ለዳታ ትንታኔ ተብሎ የተሰራ "የእውቀት ሞተር" ነው። ውስብስብ የሆኑ የሂሳብ ቀመሮችን በደረጃ በማስላት ከመፍታቱም በላይ፣ ስለ ስታቲስቲክስ፣ ፊዚክስና ኬሚስትሪ ትክክለኛ መረጃዎችን ይሰጣል። ተማሪዎችና መሃንዲሶች ለስሌት ስራዎችና ለሳይንሳዊ ጥያቄዎች አስተማማኝ መልስ ለማግኘት በስፋት የሚጠቀሙበት የላቀ የቴክኖሎጂ ውጤት ነው።

👉 የነፃ አገልግሎት (Free): ለብዙዎቹ የሂሳብና የሳይንስ ጥያቄዎች መልሱን በነፃ ይሰጣል።
👉 የክፍያ አገልግሎት (Paid): 'Pro' ስሪቱ በወር $5 USD አካባቢ (ለተማሪዎች) ወይም $7 USD (ለሌሎች) ነው።
👉 ጥቅሙ: ጥያቄው እንዴት ደረጃ በደረጃ (Step-by-step) እንደተሰራ ለማየትና ውጤቱን በፋይል ለማውረድ ያስችላል።

👌 አጠቃቀም: በሳጥኑ ውስጥ ማንኛውንም ስሌት ወይም ሳይንሳዊ ጥያቄ ጻፉ።
👌 ምሳሌ: Derivative of log(x) * cos(x) ብላችሁ ስትጽፉ ደረጃ በደረጃ አሰራሩንና ግራፉን ያሳያችኋል።
👌 ጠቃሚ ነጥብ: ስለ ሀገራት መረጃ ለማግኘትም ይጠቅማል፤ ለምሳሌ Ethiopia GDP vs Kenya GDP ካሉት የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚ በግራፍ ያነጻጽራል።
.
.
.
#ጠቃሚ_ማሳሰቢያ
ለእነዚህ አገልግሎቶች ክፍያ ለመፈጸም በኢትዮጵያ ብር በቀጥታ መክፈል አይቻልም። የግድ የቪዛ (Visa) ወይም የማስተር ካርድ (Mastercard) ተጠቃሚ መሆን ያስፈልጋል።

https://t.me/ETtips
#አልጀዚራ የኢራንን የጦር እና የኒውክሌር ተቋማት የሚያሳዩ የሳተላይት ምስሎችን ይፋ አደረገ::

"አዲሶቹ የሳተላይት ምስሎች እንደሚያሳዩት፣ ኢራን በአካባቢው እየጨመረ ከመጣው የአሜሪካ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ የጦር እና የኒውክሌር ጣቢያዎቿን እያጠናከረችና እየመሸገች ትገኛለች።"

እንደ አልጀዚራ ዘገባ ከሆነ በኢራን እና በአሜሪካ መካከል የሚደረገው ቀጥተኛ ያልሆነ የኒውክሌር ድርድር ቴህራን የሚሳኤል እና የኒውክሌር ማዕከላቶቿን በፍጥነት እንድታጠናክር ዕድል ሰጥቷታል።

ይህም ሊሰነዘርባት ለሚችል ለማንኛውም የአሜሪካ ወይም የእስራኤል ጥቃት የመከላከያ እርምጃዎችን ለመውሰድ ጊዜ አግኝታለች::
--
ምንጭ - #AlJazeeraEnglish

https://t.me/ETtips
የሲም ካርድ ፒን (PIN) ኮድ መቀየር ወይም መጠቀም ለስልክዎ ደህንነት እጅግ አስፈላጊ ነው። ብዙ ሰዎች የሲም ካርዱን ኦሪጅናል ኮድ (ብዙውን ጊዜ 0000 ወይም 1234) ሳይቀይሩት ይተዉታል፤ ይህም ለጥቃት ያጋልጣል።
​ፒን ኮድ መቀየር የሚጠቅምባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች እነሆ፦
​1. የግል መረጃን ለመጠበቅ
​ስልክዎ ቢጠፋ ወይም ቢሰረቅ፣ ሌባው ሲም ካርድዎን አውጥቶ በሌላ ስልክ ላይ ቢከተው የእርስዎን የስልክ ቁጥሮች (Contacts) እና በሲም ካርዱ ላይ የተቀመጡ መልዕክቶችን እንዳያገኝ ይከለክለዋል።
​2. የገንዘብ ዝውውር ደህንነት (Mobile Money)
​በአሁኑ ጊዜ እንደ Telebirr ወይም M-Pesa ያሉ አገልግሎቶች ከሲም ካርድ ጋር የተያያዙ ናቸው። ምንም እንኳን እነዚህ መተግበሪያዎች የራሳቸው የይለፍ ቃል ቢኖራቸውም፣ ሲም ካርድዎ በሌላ ሰው እጅ ከገባ የተለያዩ የማረጋገጫ መልዕክቶችን (OTP) በመቀበል አካውንትዎን ለመስበር ሊሞክሩ ይችላሉ። የሲም ፒን ካለ ግን ሲም ካርዱን መክፈት አይችሉም።
​3. የማንነት ስርቆትን ለመከላከል
​የእርስዎን ስልክ ቁጥር በመጠቀም ሌሎች ሰዎች የእርስዎን ስም በማጥፋት መልዕክት እንዳይልኩ ወይም ወደ ተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች (Telegram, WhatsApp) ገብተው መረጃዎን እንዳይሰርቁ ይረዳል።
​ማስታወስ ያለብዎት ነጥቦች፦
​የማይረሱትን ቁጥር ይምረጡ፦ ፒን ኮዱን 3 ጊዜ ተሳስተው ካስገቡ ሲም ካርዱ ይቆለፋል (ለማስከፈት የ PUK ኮድ ይጠይቃል)።
​ቀላል ቁጥሮችን አይጠቀሙ፦ እንደ 1111 ወይም 1234 ያሉ በቀላሉ የሚገመቱ ቁጥሮችን አይምረጡ።
​የሲም ካርድዎን ፒን ኮድ በስልክዎ Settings ውስጥ "Security" ወይም "SIM Card Lock" የሚለውን በመፈለግ በቀላሉ መቀየር ይችላሉ።

https://t.me/ETtips
የጆሮ ማዳመጫዎ ሙዚቃ ብቻ ሳይሆን "አደጋ" ሊሆን እንደሚችል ያውቃሉ?

​🎯 ​ብዙዎቻችን ማዳመጫ (Earphones/Airpods) ስንገዛ ድምጽ ካወጣ ብቻ "ጥሩ ነው" ብለን እናስባለን። ነገር ግን ጥራቱን ያልጠበቀ ማዳመጫ ከድምጽ መበላሸት ባለፈ በጤናዎ እና በስልክዎ ላይ ከፍተኛ ጥፋት ያደርሳል።
​
​ኦሪጅናል ማዳመጫን ከፌክ (Fake) ለመለየት እነዚህን ወሳኝ ነጥቦች ይመልከቱ፦

​📌​1) የቀዳዳዎቹ (Grills) ጥራት፦ ኦሪጅናል ማዳመጫዎች ጥቃቅንና ንጹህ በሆነ ብረት የተሸፈኑ ቀዳዳዎች አሏቸው። ፌክ ከሆነ ግን ቀዳዳዎቹ ሰፋ ያሉና ቀለማቸው ቶሎ የሚለቅ ነው።

📌2)​ ​ክብደት፦ ኦሪጅናል ኤርፖዶች (Airpods) ውስጥ ጥራት ያለው ባትሪና ማግኔት ስላለ "ከበድ" ይላሉ። ፌክ ከሆነ ግን ላስቲክ ስለሚበዛው በጣም ቀላል ነው።

📌​​ 3) የድምፅ ጥራት፦ ኦሪጅናል ማዳመጫ ድምፁ ቢጨምርም አይንጫጫም፤ ጥልቅ የሆነ የባስ (Bass) ድምፅ አለው። ፌክ ከሆነ ግን እንደ ቆርቆሮ ይንጫጫል፤ ድምፁም ወደ ውጭ ይወጣል።

📌​ ​4) የባትሪ አጠቃቀም፦ ኦሪጅናል ማዳመጫዎች ጥቂት ኃይል ብቻ ይጠቀማሉ። ፌኮች ግን ከስልኩ ጋር ለመገናኘት ብቻ ከፍተኛ ኃይል በመሳብ የስልኩን ባትሪ ያዳክማሉ።

​📌 ​5) የደህንነት ሲስተም፦ ኦሪጅናል ማዳመጫ የሰው ልጅ ጆሮ ሊሸከመው የሚችለውን የድምፅ መጠን (Decibel) ለመቆጣጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂ አለው። ፌኩ ግን ይህ ስለሌለው ጆሮን በቀላሉ ይጎዳል።

​❗️ ​ጥራቱን ያልጠበቀ ማዳመጫ ሲጠቀሙ ጆሮዎ ውስጥ የማቃጠል ስሜት ወይም ከፍተኛ ሙቀት የሚሰማዎት ከሆነ፣ አሁኑኑ መጠቀም ያቁሙ! ይህ የኤሌክትሪክ ፍሰቱ ስህተት መሆኑን እና ጆሮአችንን ሊያቆስለው እንደሚችል ምልክት ነው።

#Earphones​#Airpods
​#FakeVsOriginal
https://t.me/ETtips
‎ከልክ ያለፈ ላብ ያልበኛል ምክንያቱ ምን ይሆን?
‎
‎ላብ ሰዉነታችንን ለማቀዝቀዝ እና ከሰዉነታችን አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለማስወገድ በተለይም ሞቃት በሆነ የአየር ንብረት እና እንቅስቃሴ ሲደረግ የነርቭ ስርአታእን ወደ ላብ እጢ መልእክት ሲልክ የሚፈጠር ፈሳሽ ነዉ፤ ሆኖም ግን ከሙቀት እና ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዉጪ የሰዉነት ላብ ሲበዛ ከልክ ያለፈ ላብ (Hyperhidrosis) ሲባል የጤና ችግሮች እንዳለ ይጠቁመናል፡፡
‎
‎ከልክ ያለፈ ላብ ብዙዉን ጊዜ የሚከሰተዉ በእጅ መዳፍ፤ በእግር መዳፍ (የዉስጥ እግር) ና ብብት ዉስጥ ሲሆን እንደ ጤና ችግር የሚቆጠረዉ የእረስዎን የእለት ከእለት እንቅስቃሴዎትን የሚያስተጓጉል ከሆነ ነዉ፡፡
‎
‎ከልክ ያለፈ ላብ የእለት ከዕለት እንቅስቃሴዎትን ከማስተጓጎሉም በተጨማሪ ማህበራዊ ጭንቀትንና እፍረትን ሊያስከትል ይችላል፡፡
‎
‎ከልክ ያለፈ ላብ የሚያስከትሉ መንስኤዎች
‎
‎📌 የስኳር ህመም
‎📌 የወር አበባ መዛባት
‎📌 ማረጥ
‎📌 የላብ አመንጪ እጢ ችግር
‎📌 የታይሮይድ ሆርሞን መዛባት
‎📌 በደም ዉስጥ የስኳር መጠን መቀነስ
‎📌 የካንሰር ህመም
‎📌 የልብ ህመም
‎📌 የነርቭ ችግር
‎📌 የክብደት መጨመር/ከልክ ያለፈ የስብ ክምችት
‎📌 ከልክ ያለፈ ጭንቀት
‎📌 ኢንፌክሽን
‎📌 መድሐኒቶች (እንደ ከፍተኛ ደም ግፊት፣ ድባቴ እና የመርሳት ችግር የሚታዘዙ)
‎
‎ሃኪሞትን ማማከር የሚገባዎት መቼ ነዉ?
‎
‎📌 ላቡ የእለት ከእለት እንቅስቃሴዎትን ካስተስጓጎሎት
‎📌 ያልተለመደ ከበፊቱ የተለየ ብዙ የሚያልቦት ከሆነ
‎📌 ምክንያቱን ያላወቁት ማታ ማታ ላብ ካለዎት
‎📌 ይኸንን ችግር ለማሻሻል ከሚረዱ ዘዴዎች፦
‎
‎ — ዋነኛዉ የላብን መመረት የሚቀንሱ መድሀኒቶችን መጠቀም ሲሆን
‎ — ችግሩ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ ከሆነ ደግሞ ላብን ከመጠን በላይ የሚያመርቱትን የላብ ዕጢዎች ወይም ወደ ላብ ዕጢዎች የሚሄዱትን ነርቮች በቀዶጥገና እንዲስተካከል ማድረግ ይቻላል፡፡
‎
‎አጠቃላይ ምክሮች
‎
‎📌 በየቀኑ መታጠብ፡ ይህን ማድረግዎ በሰዉነትዎ ላይ ያሉትን የባክቴሪያ መጠን ይቀንሳል፡፡
‎
‎📌 ሻወር ከወሰዱ በኃላ እግሮትን በደንብ ማድረቅ፡ በጣትዎት መካከል በደንብ ማድረቅ፤ ፓዉደር መጠቀም።
‎📌 የሚጠቀሙትን ጫማና ካልሲ መምረጥ፡ ጫማዎትንና የጫማዎትን ሶል ከቆዳ የተሰራ ቢሆን ይመረጣል፡፡
‎
‎📌 ጫማዎትን መቀያየር፡ አንድን ጫማ ከሁለት ቀን በላይ ያለማድረግ፡፡
‎
‎📌 የሚጠቀሙት ካልሲ ጥጥነት ወይም ሱፍነት ያለዉ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ከጥጥ ወይም ከሱፍ የተሰሩ ካልሲዎች እርጥበትን የመምጠጥ ባህሪይ ያላቸዉ ሲሆን እንቅስቃሴ በጣም በሚያበዙበት ወቅት ደግሞ እርጥበትን በደንብ ሊመጡ የሚችሉ የአትሌት ካልሲ የሚባሉትን መጠቀም ይመረጣል፡፡
‎
‎📌 እግሮት አየር እንዲያገኝ ማድረግ፡ በሚመቾት ሰዓት እግሮትን ከጫማ ማዉጣትና ማናፈስ፤እቤት ዉስጥ ደግሞ ባዶ እግር ወይም ነጠላ ጫማ ማድረግ፡፡
‎
‎📌 ከጥጥ፤ ሱፍ ወይም ናይለን የተሰሩ ልብሶችን ማዘዉተር፡ እነዚህ አየር በደንብ እንዲዘዋወር ያደርጋሉ፡፡
‎
‎📌 ቅባት የበዛባቸዉ ምግቦች እና አልኮል ከመዉሰድ መቆጠብ።
‎
‎📌 ለችግሩ መንስኤ የሆኑ የጤና እክሎችን በወቅቱ መታከም።

https://t.me/ETtips
⛈️⛈️⛈️ መብረቅ  ⛈️⛈️
=======New Tips=======
➥አንድ የመብረቅ ብልጭታ ከፀሐይ ገጽታ በ 5 እጥፍ ይበልጥ ይሞቃል።
​የፀሐይ ገጽታ ሙቀት 5,500°C ገደማ ሲሆን፣ የመብረቅ ሙቀት ግን እስከ 30,000°C ሊደርስ ይችላል።

➥መብረቅ አሸዋን ወደ "ብርጭቆ" ይቀይራል።
​መብረቅ አሸዋማ መሬት ላይ ሲያርፍ፣ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት አሸዋውን ወዲያውኑ አቅልጦ ወደ ብርጭቆነት ይቀይረዋል። ይህ የተፈጠረው የብርጭቆ ቅርጽ "ፉልጉራይት" (Fulgurite) ወይም "የመብረቅ ቅሪተ አካል" ተብሎ ይጠራል። እነዚህ ድንጋዮች ልክ እንደ ዛፍ ቅርንጫፍ የተቆላለፉና ውስጣቸው ባዶ የሆኑ ቱቦዎችን ይመስላሉ።
➥መብረቅ አንድን ሰው ወይም ቁስ ሲመታ፣ በላዩ ላይ እንደ ዛፍ ቅርንጫፍ የተቆላለፈ መስመር ይተዋል። ይህ "ሊክተንበርግ ፊገር" ይባላል። ይህ የሚሆነው የኤሌክትሪክ ኃይሉ በቆዳ ስር ባሉ የደም ስሮች ውስጥ ሲያልፍ በሚፈጥረው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ነው።

➥መብረቅ ለአፈር ማዳበሪያ ነው።
​መብረቅ አደገኛ ቢሆንም ለተፈጥሮ ትልቅ ጥቅም አለው። በመብረቅ ጊዜ ያለው ከፍተኛ ሙቀት በአየር ውስጥ ያለውን ናይትሮጅን (Nitrogen) ይሰብረዋል። ይህ ናይትሮጅን ከዝናብ ጋር ወደ መሬት ሲወርድ ለተክሎች እጅግ ጠቃሚ የሆነ ተፈጥሯዊ ማዳበሪያ ይሆናል።

➥አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን በአማካይ በዓመት አንድ ጊዜ በመብረቅ ይመታል። ነገር ግን አውሮፕላኖች የተሰሩበት ብረት (Aluminium) ኤሌክትሪኩን በውጭ በኩል አሳልፎ ወደ መሬት ስለሚሰደው፣ በውስጥ ያሉት መንገደኞች ምንም አደጋ አይደርስባቸውም፤ እንዲያውም ብዙ ጊዜ መመታታቸውን እንኳ አያውቁም።

➥የመብረቅ ብልጭታ የሚጓዝበት ፍጥነት በሰከንድ 360,000 ኪሎ ሜትር ገደማ ነው።
​ይህ ማለት መብረቅ በአንድ ሰከንድ ውስጥ መላውን ዓለም 8 ጊዜ ሊዞር ይችላል ማለት ነው። ብርሃን ከሚያደርገው ጉዞ ጋር ይቀራረባል።

➥መብረቅ እና የሰው ልጅ "አእምሮ"፦
​አንድ ሰው በመብረቅ ተመትቶ በሕይወት ቢተርፍ (90% የሚሆኑት ይተርፋሉ)፣ በአእምሮው ላይ የሚገርም ለውጥ ሊመጣ ይችላል።
​"Savant Syndrome" የሚባል ክስተት ሊፈጠር ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ከመመታታቸው በፊት ያልነበራቸው ልዩ ችሎታ (ለምሳሌ ፒያኖ የመጫወት ወይም አስገራሚ የሒሳብ ስሌት የማስላት ብቃት) በድንገት ሲያገኙ ታይተዋል። ይህ የሚሆነው የኤሌክትሪክ ኃይሉ የአእምሮን የነርቭ መስመሮች ስለሚቀይራቸው ነው።

➥መብረቅ በዝናብ ደመና ውስጥ ብቻ ሳይሆን፣ በ እሳተ ገሞራ ፍንዳታ እና በ ትላልቅ የሰደድ እሳቶች ጊዜ ሊከሰት ይችላል። በእሳተ ገሞራ አመድ ውስጥ ያሉ ቅንጣቶች እርስ በእርሳቸው ሲጋጩ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ይፈጥራሉ፤ ይህም "የእሳተ ገሞራ መብረቅ" (Volcanic Lightning) ይባላል።

➥መብረቅ ረጅም ዛፎችን የሚመርጠው ወደ መሬት ለመድረስ አጭር መንገድ ስለሚሆኑ ነው።
​ነገር ግን መብረቅ ዛፍ ላይ ሲያርፍ፣ በዛፉ ውስጥ ያለው እርጥበት (ውኃ) ወዲያውኑ ወደ ትነት (Steam) ይቀየራል።
​ይህ ድንገተኛ ትነት ዛፉ በከፍተኛ ግፊት እንዲፈነዳ ወይም ቅርፊቱ ተላጥቶ እንዲወድቅ ያደርገዋል።

➥መብረቅ ሁልጊዜ ወደ መሬት ለመድረስ ቀላሉን እና አጭሩን መንገድ ይመርጣል። አንድ ቦታ አንድ ጊዜ ከተመታ፣ ያ ቦታ ለኤሌክትሪክ ፍሰት አመቺ መሆኑን ያሳያል።
​ለምሳሌ፦ በኒው ዮርክ የሚገኘው "ኢምፓየር ስቴት ቢልዲንግ" (Empire State Building) በዓመት በአማካይ ከ20 እስከ 25 ጊዜ በመብረቅ ይመታል።
​በአንድ ወቅት ደግሞ በአንድ የነጎድጓድ ማዕበል ውስጥ ብቻ ይህ ሕንፃ 8 ጊዜ ተመትቶ ያውቃል።


#መብረቅ
#Fulgurite
#New_Tips

https://t.me/ETtips