Ethiopian TipsÂŽ
100 subscribers
121 photos
2 videos
2 files
126 links
Under New Tips:
#Health tip
#Book tip
#Psychology tip
#Technology tip
#Idea tip
#Poem tip
#Quote tip
#Question tip

... and others.

👇👇👇
@ETtips
https://t.me/ETtips
Download Telegram
ዋሌት በኋላ ኪስ ማስቀመጥ የሚያስከትለው ጉዳት፦

ብዙ ወንዶች ዋሌት በኋላ ኪሳችን ማኖር እና ዘወትራለን።

እንደ ሴቶች ቦርሳ ስለማንይዝም መታወቂያችንን እና ፎቶግራፎችን ጨምሮ ሌሎች ለዘወትር አገልግሎት አስፈላጊ የሆኑና ያልሆኑ ነገሮችን በዋሌታችን እንይዛለን።

ይሄው የዋሌታችን መጠን በተለቀ ቁጥርም ስንቀመጥም ሆነ መኪና ስናሽከረክር የአከርካሪ አጥንታችን ከተፈጥሯዊዉ ሁኔታ በተለየ መልኩ የመዛነፍ ሁኔታ ያሳያል፡፡
የደም ዝውውራችንም በተወሰነ መልኩ እንዲስተጓጎል ያደርጋል።

በዚህም ምክንያት ለወገብ ህመምና እንደ ዲስክ መንሸራተት ለመሳሰሉ ህመሞች እንጋለጣለን።

ባለሙያዎች እንደሚሉት ዋሌት በኋላ ኪስ ማስቀመጥና በአንድ እግራችን ትልቅ ሂል ጫማ መጫማትና በሌላው ስስ ሶል ያለው ጫማ ማድረግ አንድ ናቸው።

በተመሳሳይ ሴቶችም ከባድ ቦርሳ አዘውትረው በአንድ በኩል የሚይዙ ከሆነ የጀርባ አጥንታቸው እንዲዛባና ያልተስተካከለ አቋም እንዲኖራቸው ያደርጋል።

ባለሙያዎቹ ለወንዶቹ እንደ መፍትሄ ያስቀመጡት የዋሌታችንን የውፍረት መጠን በተቻለ መጠን ስስ በማድረግ ሳንሰላች በፊት ኪስ መያዝ መልመድን ነው።

የዋሌት ቦርሳችንን በአሰስ ገሰሱ ከመሙላት ይልቅ እጅግ በጣም የሚያስፈልጉንን ብቻ መያዝም ለዚህ ይረዳናል።

ሴቶችም ልክ እንደ ወንዶቹ ባይሆንም በቦርሳችን በጣም ከባድ ነገሮችን ከመያዝ መቆጠብና በሁለቱም ጎናችን እያፈራረቅን መያዝ ተገቢ ነው ።

https://t.me/ETtips
➢በቂ እንቅልፍ አለመተኛት የሚያስከትላቸው ዋና ዋና የጤና ችግሮች የሚከተሉት ናቸው።

በቂ እንቅልፍ አለማግኘት (Sleep Deprivation) በአጭርም ሆነ በረጅም ጊዜ በጤናችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። የሰውነታችን የተለያዩ ክፍሎች ራሳቸውን የሚያድሱትና የሚጠግኑት በእንቅልፍ ወቅት በመሆኑ፣ እንቅልፍ ማጣት እንደ መኪና ያለ ዘይት የመንዳት ያህል አደገኛ ነው።

​1. በአዕምሮና በሥነ-ልቦና ላይ የሚመጡ ችግሮች
​የትኩረት ማጣት፦ አዲስ ነገር የመማር፣ የማስታወስ እና ውሳኔ የመስጠት ብቃት ይቀንሳል።
​የስሜት መለዋወጥ፦ ለጭንቀት (Anxiety)፣ ለድብርት (Depression) እና ለተቆጭነት ስሜት ያጋልጣል።
​የእውቀት መቀነስ፦ የአዕምሮ ሴሎች መረጃን የማቀናጀት አቅማቸው ስለሚዳከም ለስህተት ተጋላጭነትን ይጨምራል።

​2. በልብና በደም ዝውውር ላይ የሚመጡ ችግሮች
​የደም ግፊት መጨመር፦ እንቅልፍ ማጣት የደም ግፊትን ሊጨምር ይችላል፣ ይህም ለልብ ድካም መንስኤ ይሆናል።
​የልብ ሕመም፦ በቂ እንቅልፍ የማያገኙ ሰዎች ለልብ ምት መዛባትና ለድንገተኛ የልብ ሕመም የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።

​3. በሰውነት ክብደትና በሜታቦሊዝም ላይ የሚመጡ ችግሮች
​ከመጠን ያለፈ ውፍረት፦ እንቅልፍ ማጣት የረሃብ ስሜትን የሚቆጣጠሩ ሆርሞኖችን (Leptin እና Ghrelin) ያዛባል። ይህም የምግብ ፍላጎት እንዲጨምርና ሰውነታችን ካሎሪን የማቃጠል አቅሙ እንዲቀንስ ያደርጋል።
​የስኳር በሽታ፦ ሰውነታችን የደም ስኳርን የሚቆጣጠርበትን መንገድ (Insulin sensitivity) ስለሚያዛባው ለዓይነት 2 ስኳር በሽታ ያጋልጣል።

​4. በበሽታ የመከላከል አቅም ላይ የሚመጡ ችግሮች
​የመከላከል አቅም መዳከም፦ ሰውነታችን በሽታን የሚከላከሉ "ሳይቶኪን" (Cytokines) የተባሉ ፕሮቲኖችን የሚያመነጨው ተኝተን ሳለን ነው። እንቅልፍ ካጣን በቀላሉ በጉንፋንና በተላላፊ በሽታዎች እንጠቃለን።

​5. ሌሎች አካላዊ ችግሮች
​የቆዳ መበላሸት፦ የቆዳ መጨማደድ፣ የአይን ማበጥ እና የቆዳ መገርጣት (Stress hormone በመጨመሩ ምክንያት)።
​የአደጋ ተጋላጭነት፦ እንቅልፍ ማጣት ልክ እንደ አልኮል መጠጥ ሁሉ የአካል ቅንጅትንና ንቃትን ስለሚቀንስ ለመኪና እና ለሥራ ላይ አደጋዎች ያጋልጣል።

​ምን ያህል ሰዓት መተኛት አለብን?
​የእንቅልፍ ፍላጎት እንደ እድሜ ቢለያይም፣ በአማካይ ለአዋቂ ሰው ከ 7 እስከ 9 ሰዓት ጥራት ያለው እንቅልፍ ያስፈልጋል።

​ማሳሰቢያ፦ የእንቅልፍ እጦቱ ረጅም ጊዜ የቆየና የዕለት ተዕለት ኑሮዎን እየነካ ከሆነ የሕክምና ባለሙያ ማማከር አስፈላጊ ነው።

https://t.me/ETtips
የተመረዘ ምግብ መብላታችሁን የሚያሳዩ ምልክቶች፦

በተለምዶ የምግብ መመረዝ ተብሎ የሚጠራው የምግብ ወለድ በሽታ የተበከለ፣ የተበላሸ ወይም መርዛማ ምግብ የመብላት ውጤት ነው።

የተለመዱ የምግብ መመረዝ ምልክቶች መካከል ጥቂቶቹ:-

🥙 የሆድ ቁርጠት

▪ተቅማጥ

▪ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ

▪የምግብ ፍላጎት ማጣት

▪ቀላል ትኩሳት

▪ድክመት

ለሕይወት አስጊ የሆኑ የምግብ መመረዝ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-

▪ከ 3 ቀናት በላይ የሚቆይ ተቅማጥ

▪ከ 38.9°C በላይ የሆነ ትኩሳት

▪የማየት ወይም የመናገር ችግር

▪የከባድ ድርቀት ምልክቶች፣ ይህም የአፍ መድረቅ፣

▪ደም የቀላቀለዉ ሽንት

ማሳሰቢያ

ከእነዚህ ምልክቶች መካከል አንዱ ካጋጠመዎት ሐኪም ያነጋግሩ ወይም ወዲያውኑ ወደ ሕክምና ይሂዱ።

https://t.me/ETtips
በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ (Diaper Dermatitis) ምንድነው?

በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ፣ በጨቅላ ወሸፃናት እንዲሁም ታዳጊዎች ላይ የሚከሰት በጣም የተለመደ የቆዳ ሽፍታ ሲሆን ይህም ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው ከዳይፐር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ባላቸው የውጨኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲሆን በዋነኝነትም መቀመጫዎች፣ የታችኛው የሆድ ክፍል፣ ብልት አካባቢ እና የላይኛው ጭን አካባቢ ላይ በብዛት ይስተዋላል።

በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ (Diaper Dermatitis ) እነማን ላይ ይከሰታል?

ዳይፐር dermatitis እድሜያቸው አንድ ሳምንት ከሞሉ ጨቅላ ህፃናት ጀምሮ ሚከሰት ቢሆንም, ነገር ግን ከፍተኛው የመከሰቱ አጋጣሚ እድሜያቸው ከ9 እስከ 12 ወራት ባሉ ህፃናት ላይ ይበልጥኑ ይስተዋላል። በተሰሩ ጥናቶች መሰረት ከአራት ልጆች መካከል አንዱ ላይ የሚከሰት ሲሆን በፐርሰንት ሲቀመጥ ስርጭቱ ከ7 እስከ 40 በመቶ ይደርሳል ይህም እንደ የዳይፐር አጠቃቀም፣ የሽንት ቤት ሥልጠና፣ የንጽህና አጠባበቅ እና የሕፃናት አስተዳደግ ልምምዶች ሊለያይ ይችላል።

በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ (Diaper Dermatitis ) ለምን ይከሰታል?

1) ከመጠን በላይ እርጥበት - በዳይፐር አካባቢ ውስጥ ያለው የእርጥበት መጠን መጨመር በዋነኝነት ሽንትን እና ሰገራን አምቆ ስለሚዝ ውስጣቸው ባለው ኬሚካል አማካኝነት የውጨኛውን የቆዳ ክፍል (stratum corneum)በመጉዳት ለሽፍታው ተጋላጭ ያደርጋል።

2) ፍትጊያ (Friction) - የውስጠኛውን የቆዳ ክፍል ተጋላጭ በማድረግ ከዳይፐሩ በሚኖራቸው ፍትጊያ ኬሚካሎቹ አልፈው በመግባት የቆዳ መቆጣትን ከማባባስ አልፎ ለኢንፌክሽን ተጋላጭ ያደርጋል።

3) የቆዳ ፒኤች መጨመር እና የቆዳ ማይክሮባዮም ለውጥ -ሽንት በራሱ አሲዳማ ስለሆነ ቆዳ ላይ ያለውን አሲድ ይበልጥ ከፍ በማድረግ በቆዳው ላይ የሚገኘውን ጠቃሚ ባክቴርያዎች በማጥፋት ጎጂ ለሆኑ ባክቴሪያዎች (S.Aureus, Strep.Pyogens, Candida Albican)፣ ተጋላጭ በማድረግ ችግሩን ያባብሱታል ።

4) አመጋገብ - ጡት የሚጠቡ ጨቅላ ህጻናት ፎርሙላ ከሚመገቡት ጨቅላዎች ባነሰ ለዳይፐር dermatitis ተጋላጭ ናቸው።

5) የቅርብ ጊዜ ተደጋጋሚ የአንቲባዮቲክ ሕክምና - በቅርብ ጊዜ ሰፋ ያሉ-ስፔክትረም ያላቸውን አንቲባዮቲኮችን መጠቀም ጨቅላ ሕፃናትን ለተቅማጥ እና የፈንገስ ኢንፌክሽን የመያዝ እድላቸውን በመጨመር ለዳይፐር dermatitis አጋላጭ ሊያደርጋቸው ይችላል።

6) ዳይፐርን በጊዜው አለመቀየር

7) ለረጅም ጊዜ የቆየ የተቅማጥ ህመም

በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ (Diaper Dermatitis ) ምልክቶቹ ምንድናቸው?

ቀጥተኛ ግንኙነት ባላቸው የውጨኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ይህም መቀመጫዎች፣ የታችኛው የሆድ ክፍል፣ ብልት አካባቢ እና የላይኛው ጭን ጨምሮ የሚታይ በጣም የቀላ (Intense Erythema), ሲዳሰስ ሸካራና ከቆዳ ከፋ ያለ (Macules and Papules) ፣እርስ በርሳቸዉ የተያያዙ ትናንሽ ዕብጠት (Coalesce plaques) አንዳንዴም ቅርፊት (Scaling) ሚመስል ነገር ሊኖራቸው ይችላል።
ከላይ ከተጠቀሱት ችግሮች ጋር ተያይዞም ያለማቋረጥ ማልቀስ ፣ ምቾት ማጣት ፣ለማከክ መሞከር የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ።

በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ (Diaper Dermatitis) ህክምናው ምንድነው?

የዳይፐር dermatitis ህክምና በዋነኝነት አጠቃላይ የቆዳ እንክብካቤ, ዳይፐር ምርጫ, እና የውጨኛው የቆዳ ክፍል ላይ የሚቀቡ መድሀኒቶችን በዋናነት ይይዛል

፩ ዳይፐርን ቶሎ ቶሎ መቀየር - ዳይፐርን ቶሎ ቶሎ መቀየር ቆዳው ከሰገራ እና ከሽንት የሚኖረውን የተራዘመ ጊዜ በመቀነስ ዳይፐር dermatitis የመፈጠሩን ዕድል ይቀንሰዋል።

፪ ያለ ዳይፐር የእረፍት ጊዜያቶችን መስጠት - ዳይፐር dermatitis ያለበት ህጻን ያለ ዳይፐር የእረፍት ጊዜ (ለምሳሌ በቀን ጥቂት ሰዓታት) እንዲቆይ ማድረግ፣ ይህም ቆዳ በቀጥታ ለአየር እንዲጋለጥ ያስችላል።

፫ ቀስ ብሎ በለስላሳው ቦታውን ማጽዳት - የዳይፐር ቦታው ለብ ባለ ውሃ እና በትንሽ መጠን ወይም በፊዚዮሎጂክ ፒኤች ባላቸው ንፅህና መጠበቂያዎች መፀዳት አለበት. እንደ አማራጭ ከሽቶ-ነጻ እና ከአልኮል ነጻ የሆኑ የህጻናት መጥረጊያዎች መጠቀም ይቻላል ነገር ግን በዚህ ወቅት ቆዳው ይበልጥ ሽፍ ካለ አለርጂክ ሊሆንባቸው ስለሚችል ቶሎ ማቆም ያስፈልጋል ፤ ከነዚህም መካከል እንደ methylisothiazolinone ያሉ መከላከያዎች የአለርጂ ንክኪ dermatitis ሊያስከትሉ ይችላሉ።

፬ ጎጂ ምርቶችን ማስወገድ -በተለምዶ ቦታው ላይ የሚደረጉ ከበቆሎ የሚሰሩ ግን ለሌላ ጥቅም የሚውሉ Poweders ለምሳሌ cornstarch or talcum powder ከፍተኛ የሆነ የመተንፈሻ አካል አደጋ ሊያመጡ ስለሚችሉ ባንጠቀም ይመከራል። ከነዚህም በተጨማሪ እንደ ቤኪንግ ሶዳ እና ቦሪ አሲድ ዱቄቶች Percutaneous Absorb ስለ ሚደረጉ ሌሎች አካላት ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

፭ የዳይፐር ምርጫ - በሕፃናት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውለው ከሁሉ የተሻለው የዳይፐር ምርጫ አከራካሪ ጉዳይ ነው.ነገር ግን የተራቀቀ የዳይፐር ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚሆን ዳይፐር (Disposables ) ዳይፐር dermatitis በሚታከምበት ጊዜ ብንጠቀማቸው ይመከራሉ ምክንያቱም ከፍተኛ የመምጠጥ አቅማቸው ቆዳውን ለሽንት እና ለኬሚካሎች የመጋለጥን ዕድልን ስለሚቀንስ ነው።

፮ ቆዳ ላይ ሚቀቡ መከላከያ ቅባቶች-ከቀላል እስከ መካከለኛ ለሆነ ዳይፐር dermatitis ክሬሞች እንዲሁም ቅባቶች እንደ መጀመሪያ ሕክምና ያገለግላሉ። እያንዳንዱን ዳይፐር በምንለውጥበት ወቅት እነዚህን ቅባቶች መጠቀም ይኖርብናል። እነዚህ መከላከያዎች በዋነኝነት ኬሚካሎቹ እንዲሁም እርጥበትን ከቆዳ ጋር እንዳይገናኙ ያደርጋሉ።

ከነዚህ መከላከያዎች መካከል ፔትሮላተም፣ ዚንክ ኦክሳይድ ወይም ሁለቱንም ያካተቱ ይገኙበታል። አንዳንዶቹ ደግሞ ላኖሊን፣ ፓራፊን ወይም ዲሜቲክኮን (የሲሊኮን ዘይት) ይይዛሉ።

ለተጨማሪ ጤና መረጃ የቴሌግራም ቻላናች ይቀላቀሉ ።
https://t.me/ETtips
✍ በቀን ስንት ጊዜ መሽናት አለብን?

መቼ ነው የህመም ምልክት የሚሆነው?

👉በቀን እና በማታ የሚኖረን የሽንት ብዛት ፣ ቀለም እንዲሁም ሽንት የመያዝ አቅማችን ስለጤንነታችን የተለያዩ ነገሮችን ይጠቁመናል። ባለሙያዎች እንደሚገልጹት ከ80% በላይ የሚሆኑ የሽንት ፊኛ ችግሮች ከሽንት ፊኛ ውጪ ባሉ ችግሮች ምክንያት የሚፈጠሩ ናቸው። በዋናነት ከሚጠቀሱ ችግሮች መሃከል ከልብ ጋር ተያይዘው የሚፈጠሩና ከነርቭ ችግር ጋር የሚያያዙ ይጠቀሳሉ ።

👉👉 የትኞቹ ችግሮች ካሉ ህክምና ማግኘት አለብን ፡-

🔹 ሽንት ስንሸና የህመም ስሜት መፈጠር የሽንት ቀለም ከወትሮ መቀየር/ደም መቀላቀል ካለ የሽንት መጠን መጨመር / ከበቂ በታች መሆን ሽንታችን መጥቶ ለማስወገድ ከተቸገርን

👉👉 የሽንት ትቦ/ መስመር ላይ ችግር እንዳለ የሚያሳዩ ምልክቶች ፡-

🔹 ቶሎ ቶሎ ለሽንት መመላለስ በ24 ሰዐት ከ6-8 ጊዜ ሽንትን መሽናት የተለመደ ነው ። ከዛ በላይ መመላለስ ከፍተኛ ፈሳሽ ከመውሰድ ጋር አልያም ከመጠን በላይ ቡናን ከመውሰድ ጋር ሊያያዝ ይችላል። ነገር ግን የጤና ችግርም ሊሆን እንደሚችል ማስተዋል ይኖርብናል ከነዚህም መሃከል፡- የሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን ፣ የፕሮስቴት ህመም፣ የልብ በሽታ ፣ ስኳር ህመም እንዲሁም ሌሎች... ካሉ ሊፈጠር ይችላል። አንዳንዴም የሽንት ፊኛ ከሚፈለገው በላይ መስራት ቶሎ ቶሎ ሽንት ለመሽናት መንስኤ ይሆናል ለዚህም እንደነርቭ ጉዳት ፣ የመድሃኒቶች ተጽእኖ ፣ኢንፌክሽን ፣ ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት መኖር እንዲሁም የኢስትሮጅን ሆርሞን እጥረት አጋላጭ ይሆናሉ። በሴቶች ላይ በተጨማሪም የሽንት ፊኛ በተገቢው ቦታ ላይ አለመቀመጥ (bladder prolapse) / ይህ ችግርም ከወሊድ በኋላ ሊያጋጥም ይችላል እድሜ ፡- አብዛኛውን ጊዜ እድሜ ከፍ እያለ ሲመጣ በምሽት ቶሎ ቶሎ ሽንት የመምጣት ስሜት የሚኖራቸው ሲሆን 60 ዎቹን እየዘለሉ ሲመጡ ግን በምሽት ከሁለት ጊዜ በላይ የመሽናት ልምድ አይኖርም ካለ ግን የበሽታዎች ምልክት ሊሆን ስለሚችል ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው ።

🔹ሮዝ፣ ቡኒ/ ቀይ ቀለም ያለው ሽንት (urine colour change) እነዚህ ምልክቶች መታየት ሽንት ላይ ደም መቀላቀሉን የሚያመላክቱ ናቸው ። ምን ጊዜም ቢሆን ሽንት ላይ ደም መቀላቀል እንደ ቀላል ችግር የሚታለፍ አይሆንም ስለሆነም በቶሎ የህክምና ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው ። ቡናማ ቀለም ያለው ሽንት በሰውነታችን በቂ ፈሳሽ እንደሌለ ይጠቁመናል፤ በዚህ ወቅት የምንወስደውን የፈሰሻ መጠን መጨመርና እንደ ቡና ያሉትን ተወት ማድረግ ፍቱን ነው ።

🔹 ሽንትን መቋጠር አለመቻል(incontinence) ሽንትን መቋጠር አለመቻል በዋናነት በሁለት የሚከፈል ሲሆን በጫና ምክንያት የሚፈጠር (stress incontinence) እና የሽንት ስሜትን መቆጣጠር አለመቻል (urge incontinence) በመባል ይታወቃሉ።

🔹 ጫናን አለመቆጣጠር (stress incontinence) ፡- ይህ አይነቱ ሳል ሲሳል፣ ሲሳቅ ፣ ሲነጠስ ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሲሰራ የሚፈጠር የሽንት ማምለጥ ነው።በተጨማሪም ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ከመኖር ጋር ተያይዞ ሊፈጠር ይችለል። ክብደት ሲጨምር የሽንት ትቦን የሚደግፉ ጡንቻዎች ላይ ጫና በመፍጠር ሽንት እንዳንቋጥር ያደርገናል።

🔹 የሽንት ስሜትን መቆጣጠር አለመቻል (urge incontinence) ፡- ይህ አይነቱ ችግር ሽንት ቤት እሰኪደረስ እንኳን መቆጣጠር አለመቻል ያስከትላል። ለዚህ ችግር ከሚያጋለጡ ነገሮች መሃከል በከፍተኛ መጠን የሚሰራ ፊኛ ይጠቀሳል ። በዚህ ወቅት በፍጥነት መኮማተር ይጀምራል።

https://t.me/ETtips
Adult Literacy Rates in Africa

1) 🇸🇨 Seychelles ~ 96%
2) 🇬🇶 Equatorial Guinea ~ 95%
3) 🇸🇹 São Tomé & Príncipe ~ 94%
4) 🇿🇦 South Africa ~ 91–95%
5) 🇳🇦 Namibia ~ 92%
6) 🇲🇺 Mauritius ~ 92–93%
7) 🇱🇾 Libya ~ 91%
8) 🇿🇼 Zimbabwe ~ 90%
9) 🇨🇻 Cabo Verde ~ 90%
10) 🇸🇿 Eswatini ~ 89%
11) 🇧🇼 Botswana ~ 89%
12) 🇿🇲 Zambia ~ 87%
13) 🇬🇦 Gabon ~ 86–89%
14) 🇱🇸 Lesotho ~ 82–85%
15) 🇰🇪 Kenya ~ 83%
16) 🇹🇳 Tunisia ~ 82–83%
17) 🇹🇿 Tanzania ~ 82%
18) 🇩🇿 Algeria ~ 81%
19) 🇬🇭 Ghana ~ 80%
20) 🇺🇬 Uganda ~ 80%
21) 🇨🇬 Republic of the Congo ~ 80–85%
22) 🇪🇬 Egypt ~ 78%
23) 🇨🇩 DR Congo ~ 77–80%
24) 🇨🇲 Cameroon ~ 77–80%
25) 🇷🇼 Rwanda ~ 73–79%
26) 🇲🇦 Morocco ~ 75%
27) 🇲🇬 Madagascar ~ 75%
28) 🇪🇷 Eritrea ~ 75%
29) 🇦🇴 Angola ~ 75%
30) 🇩🇯 Djibouti ~ 70–75%
31) 🇳🇬 Nigeria ~ 62–77%
32) 🇲🇼 Malawi ~ 68%
33) 🇧🇮 Burundi ~ 68%
34) 🇸🇩 Sudan ~ 60–65%
35) 🇹🇬 Togo ~ 65%
36) 🇲🇿 Mozambique ~ 63–64%
37) 🇰🇲 Comoros ~ 60–62%
38) 🇸🇳 Senegal ~ 55–58%
39) 🇲🇷 Mauritania ~ 53–55%
40) 🇨🇮 Côte d’Ivoire ~ 54–60%
41) 🇬🇲 Gambia ~ 50–55%
42) 🇬🇼 Guinea-Bissau ~ 50–56%
43) 🇱🇷 Liberia ~ 48%
44) 🇬🇳 Guinea ~ 45–48%
45) 🇧🇯 Benin ~ 45–58%
46) 🇸🇱 Sierra Leone ~ 45–60%
47) 🇸🇴 Somalia ~ 40–55%
48) 🇨🇫 Central African Republic ~ 37–39%
49) 🇧🇫 Burkina Faso ~ 37–41%
50) 🇳🇪 Niger ~ 35–38%
51) 🇸🇸 South Sudan ~ 34–35%
52) 🇲🇱 Mali ~ 31–35%
53) 🇹🇩 Chad ~ 27–34%

Source: UNESCO (UIS), World Bank, CIA World Factbook (2020–2025)

https://t.me/ETtips
"የጥርስ ሳሙናን መጠቀም መጥፎ የአፍ ጠረን ያመጣልና አልጠቀምም!"

ይህ የበርካታ ታካሚዎች ፍላጎት ሲሆን ዳሩ ግን ቀድሞ የነበረንን ጠረን ስለሚያጠፋ እንጂ ለአዲስ መጥፎ የአፍ ጠረን አይዳርገንም።

ብዙን ጊዜ የአፋችንን ንፅህና ከመጠበቅ በምንሰንፍበት ጊዜ ልማም እና ሻሃላ(Plaque & calculus) የመከማቸት ዕድልን ስለሚያሰፋ ይህ ክምችት ድድ እና የመንጋጋ አጥንትን ከመብላት እና የድድ እና የመንጋጋ አጥንት ኢንፌክሽን ከማምጣትም ባለፈ ለመጥፎ የአፍ ጠረን ይዳርጋል።

በተለምዶ ሽቶ ስንጠቀም ከሰዓታት በኋላ ለሽቶው ጠረን አፍንጫችን ለማዳ ይሆንና ልዩነቱ ብዙም አይታወቀንም ለሌላ ሰው ግን የሽቶው መዓዛ እንደ አዲስ የሚሸት ሲሆን መጥፎ የአፍ ጠረንም እንደዛው የአፍ ንፅህናችን ሳንጠብቅ ስንቀር አፍንጫችን ይለምደውና መጥፎ የአፍ ጠረን ያለንም አይመስለንም።

ነገር ግን የጥርስ ሳሙና ከይዘቶቹ መካከል ጥሩ መዓዛ ሰጪ ይዘት(Flavoring Agent) አንዱ ሲሆን ጥርሳችንን በምንቦርሽበት ወቅት አፋችን ጥሩ ጠረን ይኖረውና ለቀናት በጥርስ ሳሙና መቦረሽ ስናቋርጥ እንደ አዲስ ለሚመጣው መጥፎ የአፍ ጠረን አፍንጫችን መልመድ ስለሚጀምር ጠረኑ የመጣው ባለመቦረሻችን ሳይሆን በጥርስ ሳሙናው ይመስለናል እንጂ የጥርስ ሳሙና መጥፎ የአፍ ጠረን ያጥፋ እንጂ አያባብስም።

በመጨረሻም የአፋችንን ንፅህና የጥርስ ሳሙናና ለስላሳ የጥርስ ብሩሽ ተጠቅመን ጠዋት ከቁርስ በኋላ እና ማታ ከመኝታ በፊት መቦረሽ ይመከራል።

https://t.me/ETtips
የስልክ ባትሪ እድሜን ይጨምራሉ ተብለው የሚታሰቡ 3 የውሸት (Fake) ልምዶችና እውነታው!

📌ብዙዎቻችን ስልካችንን ስንጠቀም "ባትሪ ለመቆጠብ" ብለን የምናደርጋቸው ነገሮች ባትሪውን የበለጠ እየጎዱት እንደሆነ ያውቃሉ? ዛሬ በቴክኖሎጂው ዓለም የተሳሳቱ ግን ደግሞ የተለመዱ 3 ልምዶችን እና እውነታውን እነግራችኋለሁ።

1. አፖችን "Close" ማድረግ (Swipe up አድርጎ ማጥፋት)

📌 አንድ ልምድ አለ ይህም...አፖችን ዝግት አድርገን ስናጠፋ ባትሪ ይቆጥባል ብለን እናስባለን አፖችን በየደቂቃው መዝጋት ባትሪውን የበለጠ ይበላዋል። ምክንያቱም ስልኩ ያንን አፕ ድጋሚ ሲከፍተው ከዜሮ ለመነሳት ከፍተኛ ኃይል ስለሚጠቀም ነው ። አፖችን ስልኩ ራሱ እንዲያስተዳድራቸው መተው ይሻላል።

2. ባትሪ 0% እስኪሆን ጠብቆ ቻርጅ ማድረግ

📌 "ባትሪው ሙሉ በሙሉ አልቆ ቢጠፋና ቻርጅ ቢደረግ ይቆያል" የሚል የተሳሳተ እምነት አለ ።

📌 አሁን ያሉት የሊቲየም (Lithium-ion) ባትሪዎች 0% መውረድ በጣም ይጎዳቸዋል። ባትሪዎ 20% ሲደርስ ቻርጅ ማድረግ እና 80% ሲደርስ መንቀል የባትሪውን እድሜ በ 2 እጥፍ ያራዝመዋል።

3. አዲስ ስልክ ሲገዛ 8 ሰዓት ቻርጅ ማድረግ

📌 "አዲስ ስልክ ሲገዛ ባትሪው እንዲለምድ4/ 8 ሰዓት መቆየት አለበት"ይባላል ።

ይህ ድሮ ለነበሩ ባትሪዎች እንጂ ለአሁኑ ስልኮች አይሰራም። አዲስ ስልክ ሲገዙ 100% ሲሞላ ወዲያውኑ መጠቀም መጀመር ይችላሉ፤ 8 ሰዓት ማቆየት ለውጥ የለውም !

❗️ ለባትሪ ዋናው ጠላት "ሙቀት" ነው ። ስልካችን ቻርጅ እያደረገ ጌም (Game) የሚጫወቱ ከሆነ ወይም ከባድ አፖችን የሚጠቀሙ ከሆነ ስልኩ ይሞቃል። ይህ ሙቀት የባትሪውን ሴሎች በቋሚነት ስለሚገድላቸው፣ ቻርጅ እያደረጉ ስልክ አለመጠቀም ከምንም በላይ የባትሪውን ጤና ይጠብቃል ።

🎯 ይልቅ ለስልካችን አንድ original ቻርጀር ብቻ በመጠቀም መሙላትና የስልኩን ና ባትሪውን ደህነት መጠበቅ ይገባናል !

📌 የቴሌግራም ቻናላችን ፦ 👇

https://t.me/ETtips
➢ፎረፎርን በዘላቂነት ለማጥፋት የሚረዱ 10 ምርጥ የቤት ውስጥ መላዎች፦

ፎረፎር አስቸግሮዎታል?  እንግዲያውስ በፍጹም አይጨነቁ!

ፎረፎርን በተፈጥሯዊ እና በቀላል የቤት ውስጥ መላዎች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ ይቻላል።

እመኑኝ፤ እኔም በወጣትነቴ የፎረፎር ችግር ነበረብኝ እና በቀላሉ በቤት ውስጥ በማዘጋጃቸው ውህዶች አስወግጄዋለሁ።

✅ የፎረፎር ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የፎረፎር ዋነኛ ምልክቶች በፀጉር ስር የሚታዩ ነጫጭ ቅርፊቶች እና ከፍተኛ የማሳከክ ስሜት ናቸው።

በኔ ላይ የታየው መጠነኛ ማሳከክ እና ቅርፊት ነበር፤ የቤት ውስጥ መላዎችን መጠቀም ስጀምር ግን ወዲያውኑ ለውጥ አይቻለሁ።

✅ ፎረፎር ለምን ይከሰታል?

👉 ፎረፎር በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል። ከእነዚህም መካከል:-

🧅 ውጥረት (Stress)
🧅 የተመጣጠነ ምግብ እጥረት
🧅 የፈንገስ ኢንፌክሽን
🧅 ፀጉርን አዘውትሮ አለመታጠብ
🧅 የተወሰኑ መድኃኒቶች ጭምር ፎረፎርን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

✅ በባህል የተለመዱ የፎረፎር መድኃኒቶች፦

በተለያዩ ባህሎች ውስጥ ለፎረፎር መላ ተብለው ለዘመናት ያገለገሉ በርካታ ተፈጥሯዊ መላዎች አሉ። ለምሳሌ ያህል:-

🍓 አብሽ (Fenugreek):- አብሽ ለፎረፎር በጣም ውጤታማ ከሆኑ የባህል መላዎች አንዱ ነው። ነገር ግን ለሁሉም ሰው ላይስማማ ይችላል፤ ምክንያቱም ሰውነትን የማቀዝቀዝ ባህሪ አለው።

🍓 ሎሚ (Lemon):- ሎሚ ሌላኛው ለዘመናት የቆየ ቀላልና ውጤታማ መላ ነው። ፎረፎርን ከማጥፋቱም ባሻገር በጭንቅላት ላይ የሚከሰት ማሳከክን ያስታግሳል።

🍓 ኒም (Neem):- የኒም ቅጠል በየትኛውም አጠቃቀሙ ለፎረፎር ፍቱን መድኃኒት ነው።

✅ እነዚህን መላዎች እንዴት እንጠቀም?

ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መላዎች ውስጥ አንዱን ይምረጡና ችግሩ እስኪጠፋ ድረስ ቢያንስ በሳምንት ሦስት ጊዜ ይጠቀሙ።

ፎረፎሩ ከጠፋ በኋላ ደግሞ ችግሩ ተመልሶ እንዳይመጣ ለመከላከል በሳምንት አንድ ጊዜ መጠቀሙን ይቀጥሉ።

✅ ፎረፎርን በዘላቂነት የሚያጠፉ 10 ምርጥ መላዎች፦

1️⃣ ሬት ለፎረፎር (Aloe Vera)
�አንድ የሾርባ ማንኪያ ንጹሕ የሬት ጄል ላይ የግማሽ ሎሚ ጭማቂ ጨምረው እንደ ፀጉር ማስክ ይቀቡት።

ሬትም ሆነ ሎሚ ፎረፎርን የሚያስከትሉ ባክቴሪያዎችን እና ፈንገሶችን በፍጥነት በመዋጋት ፎረፎርን ለማከም ይረዳሉ።

2️⃣ አብሽ ለፎረፎር (Fenugreek)
�አንድ የሾርባ ማንኪያ የአብሽ ዱቄት ላይ በቂ እርጎ በመጨመር ለ30 ደቂቃ ያህል ያስቀምጡት። ይህም አብሹ እንዲወፍር ይረዳዋል።

በደንብ ከመቱት በኋላ እንደ ፀጉር ማስክ ይጠቀሙ።

(ይህ ውህድ የሳይነስ ችግር ላለባቸው ሰዎች አይመከርም)።

3️⃣ የኒም ቅጠል ውህድ (Neem Rinse)
�አንድ ጥቅል የኒም ቅጠልን ከውኃ ጋር አፍልተው የውኃው ቀለም ሲቀየር ያውጡት።

ከቀዘቀዘ በኋላ አጥልለው የግማሽ ሎሚ ጭማቂ ጨምረውበት ፀጉርዎን ለመጨረሻ ጊዜ ይለቃለቁበት።

ይህ ውህድ ፎረፎርን ለማጥፋት በጣም ውጤታማ ነው።

4️⃣ አምላ ለፎረፎር (Amla)
�አንድ የሾርባ ማንኪያ የአምላ ዱቄት ላይ ንጹሕ የሬት ጄል ቀላቅለው እንደ ማስክ ይቀቡት።

ለ20 ደቂቃ አቆይተው በሻምፖ ይታጠቡ።

ይህ ማስክ ፎረፎርን ከማጥፋቱም በላይ የፀጉር እድገትን ያበረታታል።

5️⃣ የአፕል ሳይደር ኮምጣጤ እና ሎሚ (Apple Cider Vinegar & Lemon)
�እኩል መጠን ያለው የሎሚ ጭማቂ እና የአፕል ሳይደር ኮምጣጤ ይቀላቅሉ።

ከዚያ አንድ የሾርባ ማንኪያ ከዚህ ውህድ ወስደው ከአንድ ኩባያ ውሃ ጋር በመበጥበጥ ፀጉርዎን ይለቃለቁበት።

ይህ ፎረፎርን ለማከም አስደናቂ መላ ነው።

6️⃣ ሎሚ እና የኮኮናት ዘይት (Lemon & Coconut Oil)
�አንድ የሾርባ ማንኪያ የኮኮናት ዘይት ላይ እኩል መጠን ያለው የሎሚ ጭማቂ ጨምረው ያዋህዱ።

በጥጥ እየነከሩ የራስ ቅልዎን በደንብ ይቀቡት። ለ15 ደቂቃ አቆይተው ይታጠቡ።

ማሳከክን በመጀመሪያ ዙር ሲጠቀሙት ያስቆማል፤ ደጋግመው ሲጠቀሙት ደግሞ ፎረፎሩ ሙሉ በሙሉ ያጠፋል።

7️⃣ የጥብስ ቅጠል ውህድ (Rosemary Rinse)
�የጥብስ ቅጠል (Rosemary) ለፀጉር ጤንነት በሀገራችን በስፋት ከሚታወቁ መላዎች አንዱ ነው።

ጥቂት የጥብስ ቅጠሎችን በውኃ ውስጥ ለጥቂት ደቂቃዎች ያፍሉት።

ውኃው ከቀዘቀዘ በኋላ አጥልለው ፀጉርዎን ከታጠቡ በኋላ በመጨረሻ ይለቃለቁበት።

ፎረፎርን ከመከላከልም ባሻገር ለፀጉርዎ ጥሩ ልስላሴ ይሰጣል።

8️⃣ እንቁላል እና የኮኮናት ዘይት (Egg & Coconut Oil)
�የእንቁላል ማስክ ፎረፎርን ለማከም በጣም ጥሩ ነው። አንድ እንቁላል ሰብረው ከአንድ የሻይ ማንኪያ ንጹሕ የኮኮናት ዘይት ጋር በደንብ ይምቱት።

ይህንን ውህድ በብሩሽ ፀጉርዎን ተቀብተው ለ15 ደቂቃ ያህል ካቆዩ በኋላ ይታጠቡት።

9️⃣ የሻይ ዛፍ ዘይት (Tea Tree Oil)

�ይህ ዘይት ፎረፎርን የሚያስከትሉ ፈንገሶችን እና ባክቴሪያዎችን በመዋጋት ይታወቃል።

3 ጠብታ የሻይ ዛፍ ዘይትን ከአንድ የሾርባ ማንኪያ የኮኮናት ዘይት ጋር ቀላቅለው የራስ ቅልዎን ይቀቡ። ለተሻለ ውጤት በሳምንት ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ።

🔟 የከሪ ቅጠል (Curry Leaf) 🍃

�(ማሳሰቢያ:- ይህ ቅጠል በሀገራችን የተለመደ አይደለም፤ ነገር ግን በውጭ ሀገራት ለሚኖሩ ወይም በልዩ መደብሮች ለሚያገኙት ይጠቅማል)።

አንድ እፍኝ የከሪ ቅጠልን ከእርጎ እና ከጥቂት የሎሚ ጭማቂ ጋር በመፍጨት እንደ ማስክ ይጠቀሙ። በሳምንት ሦስት ጊዜ በመጠቀም አስደናቂ ለውጥ ያያሉ።

https://t.me/ETtips
ጠቃሚ ጤና መረጃ ለነብሰ ጡሮች እንሆ

ፎሊክ አሲድን መውሰድ ችላ አትበል !!

ማንኛዋም እርጉዝ ሴት ወይም ለማርገዝ የምታስብ እናት በቂ የሆነ የፎሊክ አሲድ ንጥረ ነገር ማግኘት ይኖርባታል ፡፡

በእርግዝና ጊዜ ፎሊክ አሲድ ባለመወሰዱ ምክንያት በልጁ ላይ የሚመጡ ችግሮች
- ጭንቅላት ሳይኖር መወለድ (Anencephaly)
- የአከርካሪ አጥንት እብጠት (spinal bifida)
- የአንጎልና ነርቭ እክል (Neural tube defect)
ፎሊክ አሲድ በእርግዝና ክትትል ወቅት ከሚሰጥ መድሀኒት በተጨማሪም በምግብ ውስጥ ማግኘት እንችላለን፡፡
በፎሊክ አሲድ የበለፀጉ ምግቦች
- ብርቱካን
- ባቄላ
- ሩዝ
- ፓስታ
- ጉበት
- ሙዝ
- ቲማቲም
- ፓፓያ
- አቮካዶ
- ጎመን፣ ሰላጣ
ተገቢ እና ተመጣጣኝ የፎሊክ አሲድ የወሰደች እናት ደህና ልጅም ጤና!

https://t.me/ETtips
#ጆሮዬ ይጮሃል!!!

ለምን?

ምክንያቱ ምንድነው?

ለመሆኑ የጆሮ ጩኸት ስንል ምን ማለታችን ነው???

በምን ምክኒያትስ ይህ ችግር ሊከሰት ይችላል???

👉 ውድ ቤተሰቦች የጆሮ ጬኸት ማለት ምንም አይነት ድምጽ በአካባቢው ላይ ሳይኖር ነገር ግን ጆሮአችን ውስጥ የምንሰማው ድምጽ ሲኖር ማለት ነው ።

👉 በጆሮ የሚሰሙት ድምጾች አብዛኛው ጊዜ ይህንን ይመስላሉ፡-
• የደውል አይነት ድምጽ
• እስ የሚል ድምጽ
• የማቃጨል አይነት ድምጽ
• የእንግግታ ድምጽ የመሳሰሉትን …
👉እነዚህ ድምጾች በትንሽ / በትልቁ ፣ በአንድ ጆሮ ወይም በሁለቱም ጆሮ ሊሰማ ይችላል።

👉 በምን ምክንያት ሊመጡ ይችላሉ??

• ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ችግር

• ለከፍተኛ ድምጽ መጋለጥ

• በጆሮ ኩክ መብዛት ምክኒያት መደፈን

• የጭንቅላት እና የአንገት አደጋ

• እባጭ

• የጆሮ ጡንቻዎች መሸማቀቅ

• የደም ስር ትቦ መዘጋት

• የጭንቅላት እና የአንገት እባጭ

• ከፍተኛ የደም ግፊት

• የደም ማነስ

👉 አጋላጭ ሁሌታዎች፡-

• ለከፍተኛ ድምጽ መጋለጥ

• የእድሜ መግፋት

• ወንዶች ከ ሴቶች ይልቅ ተጋላጭ ናቸው

• የልብ እና የደም ስሮች ችግር

• ማጨስ

👉 ይህ ችግር እየቆ ሲመጣ ሊየስከትላቸው የሚችላቸው ችግሮች፡-

• ለጭንቀት ይዳርጋል

• እንቅልፍ ለመተኛት መቸገር

• አካባቢው ላይ ላለው ነገር ትኩረት አለመስጠት

• የማስታወስ ችግር

• ድካም

• ፍርሃት እና ብስጭት

👉 ይህንን ችግር እንዴት መከላከል እንችላለን???

• ከፍተኛ የሆነ ድምጽ የጆሮን ነርቮች ስለሚጎዳ እና ይህ ችግር ለመስማት ችግር እና ለጆሮ ጩኸት ስለሚጋልጥ የድምጽ መከላከያ መጠቀም ይኖርብናል፡፡ በተለይ ሙዚቀኞች እና ኢንዱስትሪ ሰራቶች ይህንን መጠቀም ይኖርባቸዋል።

• ለረጅም ጊዜ ድምጹ ከፍ ያለ አምፕሊፋየር እና ኤርፎን መጠቀም ለመስማት ችግር እና ለጆሮ ጩኸት ችግር ስለሚጋልጥ ቀንሶ መጠቀም ይኖርብናል።

• ለልብ እና ደም ስሮች ችግር እንዳንጋለጥ እንቅስቃሴ ማድረግ ፣ አመጋገብን እና የኑሮ ዘይቤን ማስተካከል ይኖርብናል።

• በተጨማሪም ለችግሩ አጋለጭ የሆኑ በሽታዎች ቶሎ መታከም ይኖርብናል።

https://t.me/ETtips
Ethiopian Tips® pinned «#ጆሮዬ ይጮሃል!!! ለምን? ምክንያቱ ምንድነው? ለመሆኑ የጆሮ ጩኸት ስንል ምን ማለታችን ነው??? በምን ምክኒያትስ ይህ ችግር ሊከሰት ይችላል??? 👉 ውድ ቤተሰቦች የጆሮ ጬኸት ማለት ምንም አይነት ድምጽ በአካባቢው ላይ ሳይኖር ነገር ግን ጆሮአችን ውስጥ የምንሰማው ድምጽ ሲኖር ማለት ነው ። 👉 በጆሮ የሚሰሙት ድምጾች አብዛኛው ጊዜ ይህንን ይመስላሉ፡- • የደውል አይነት ድምጽ…»
✍ በቀን ስንት ጊዜ መሽናት አለብን?

መቼ ነው የህመም ምልክት የሚሆነው?

👉በቀን እና በማታ የሚኖረን የሽንት ብዛት ፣ ቀለም እንዲሁም ሽንት የመያዝ አቅማችን ስለጤንነታችን የተለያዩ ነገሮችን ይጠቁመናል። ባለሙያዎች እንደሚገልጹት ከ80% በላይ የሚሆኑ የሽንት ፊኛ ችግሮች ከሽንት ፊኛ ውጪ ባሉ ችግሮች ምክንያት የሚፈጠሩ ናቸው። በዋናነት ከሚጠቀሱ ችግሮች መሃከል ከልብ ጋር ተያይዘው የሚፈጠሩና ከነርቭ ችግር ጋር የሚያያዙ ይጠቀሳሉ ።

👉👉 የትኞቹ ችግሮች ካሉ ህክምና ማግኘት አለብን ፡-

🔹 ሽንት ስንሸና የህመም ስሜት መፈጠር የሽንት ቀለም ከወትሮ መቀየር/ደም መቀላቀል ካለ የሽንት መጠን መጨመር / ከበቂ በታች መሆን ሽንታችን መጥቶ ለማስወገድ ከተቸገርን

👉👉 የሽንት ትቦ/ መስመር ላይ ችግር እንዳለ የሚያሳዩ ምልክቶች ፡-

🔹 ቶሎ ቶሎ ለሽንት መመላለስ በ24 ሰዐት ከ6-8 ጊዜ ሽንትን መሽናት የተለመደ ነው ። ከዛ በላይ መመላለስ ከፍተኛ ፈሳሽ ከመውሰድ ጋር አልያም ከመጠን በላይ ቡናን ከመውሰድ ጋር ሊያያዝ ይችላል። ነገር ግን የጤና ችግርም ሊሆን እንደሚችል ማስተዋል ይኖርብናል ከነዚህም መሃከል፡- የሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን ፣ የፕሮስቴት ህመም፣ የልብ በሽታ ፣ ስኳር ህመም እንዲሁም ሌሎች... ካሉ ሊፈጠር ይችላል። አንዳንዴም የሽንት ፊኛ ከሚፈለገው በላይ መስራት ቶሎ ቶሎ ሽንት ለመሽናት መንስኤ ይሆናል ለዚህም እንደነርቭ ጉዳት ፣ የመድሃኒቶች ተጽእኖ ፣ኢንፌክሽን ፣ ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት መኖር እንዲሁም የኢስትሮጅን ሆርሞን እጥረት አጋላጭ ይሆናሉ። በሴቶች ላይ በተጨማሪም የሽንት ፊኛ በተገቢው ቦታ ላይ አለመቀመጥ (bladder prolapse) / ይህ ችግርም ከወሊድ በኋላ ሊያጋጥም ይችላል እድሜ ፡- አብዛኛውን ጊዜ እድሜ ከፍ እያለ ሲመጣ በምሽት ቶሎ ቶሎ ሽንት የመምጣት ስሜት የሚኖራቸው ሲሆን 60 ዎቹን እየዘለሉ ሲመጡ ግን በምሽት ከሁለት ጊዜ በላይ የመሽናት ልምድ አይኖርም ካለ ግን የበሽታዎች ምልክት ሊሆን ስለሚችል ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው ።

🔹ሮዝ፣ ቡኒ/ ቀይ ቀለም ያለው ሽንት (urine colour change) እነዚህ ምልክቶች መታየት ሽንት ላይ ደም መቀላቀሉን የሚያመላክቱ ናቸው ። ምን ጊዜም ቢሆን ሽንት ላይ ደም መቀላቀል እንደ ቀላል ችግር የሚታለፍ አይሆንም ስለሆነም በቶሎ የህክምና ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው ። ቡናማ ቀለም ያለው ሽንት በሰውነታችን በቂ ፈሳሽ እንደሌለ ይጠቁመናል፤ በዚህ ወቅት የምንወስደውን የፈሰሻ መጠን መጨመርና እንደ ቡና ያሉትን ተወት ማድረግ ፍቱን ነው ።

🔹 ሽንትን መቋጠር አለመቻል(incontinence) ሽንትን መቋጠር አለመቻል በዋናነት በሁለት የሚከፈል ሲሆን በጫና ምክንያት የሚፈጠር (stress incontinence) እና የሽንት ስሜትን መቆጣጠር አለመቻል (urge incontinence) በመባል ይታወቃሉ።

🔹 ጫናን አለመቆጣጠር (stress incontinence) ፡- ይህ አይነቱ ሳል ሲሳል፣ ሲሳቅ ፣ ሲነጠስ ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሲሰራ የሚፈጠር የሽንት ማምለጥ ነው።በተጨማሪም ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ከመኖር ጋር ተያይዞ ሊፈጠር ይችለል። ክብደት ሲጨምር የሽንት ትቦን የሚደግፉ ጡንቻዎች ላይ ጫና በመፍጠር ሽንት እንዳንቋጥር ያደርገናል።

🔹 የሽንት ስሜትን መቆጣጠር አለመቻል (urge incontinence) ፡- ይህ አይነቱ ችግር ሽንት ቤት እሰኪደረስ እንኳን መቆጣጠር አለመቻል ያስከትላል። ለዚህ ችግር ከሚያጋለጡ ነገሮች መሃከል በከፍተኛ መጠን የሚሰራ ፊኛ ይጠቀሳል ። በዚህ ወቅት በፍጥነት መኮማተር ይጀምራል።


https://t.me/ETtips
የነስር መንስኤዎች

ነስር (epistaxis) ድንገተኛ የሆነ አስደንጋጭ ከአፍንጫ ደም መፍሰስ ሲሆን በአብዛኛው ለከፋ አደጋ የማይዳርግ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ነስርን ከሚነሳበት ክፍል በመነሳት በሁለት ይከፈላል፡፡

1, ከፊተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Anterior Nosebleeds)
ከአፍንጫ ቀደዳዎች መካከል አካባቢ የሚገኙ የደም ስሮች ሲጎዱ የሚከሰት ሲሆን ከ90 በመቶ በላይ ለሚከሰት የነስር ዓይነት ምክንያት ነው፡፡አብዛኛዉን ጊዜ ህፃናት ላይ ይከሰታል እንዲሁም በቀላሉ መቆጣጠር ይቻላል፡፡
2, ከኋለኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Posterior Nosebleeds)
በአብዛኘው በዕድሜ በገፉ ሰዎች ላይ ይከሰታል፡፡ ወደ ዉስጥ ካሉ የደም ስሮች የሚመጣ መጠኑ በዛ ያለ ደም ይኖረዋል እናም የተለየ ሕክምና የሚያስፈልገው እና ውስብስብ ነው፡፡

ነስርን የሚያመጡ መንስኤዎች

📌 በአፍንጫ ላይ አደጋ/ አፍንጫ መጎርጎር
📌 የደም ግፊት መጨመር
📌 የደም መርጋት ችግር
📌 የደም ማቅጠኛ መድሐኒቶች
📌 የመተንፈሻ አካላት ህመም
📌 ቀዘቃዛ እና ደረቅ የአየር ንብረት
📌 ለኬሚካል ተጋላጭ መሆን
📌 አልኮል እና በአፍንጫ የሚወሰዱ አደንዛዥ እጽ
📌 እርግዝና

ነስርን መከላከያ መንገዶች

📌 በአብዛኛው ነስር የሚከሰተው በቀዘቀዘ እና በደረቅ የአየር ንብረት ስለሆነ አፍንጫ እንዳይደርቅ ቫዝሊን (Petroleum jelly) መጠቀም
📌 አፍንጫዎን በጣትዎ አለመነካካት
📌 የነስር መንስኤ ከሌላ የጤና ችግር ጋር ተያያዥነት ካለው ሐኪም ማማከር
📌 ሲጋራ ከማጨስ መቆጠብ

ነስር ከተከሰተ በኋላ ወደ ሐኪም መሄድ የሚያስፈልገው

📌 አፍንጫዎን ለ10 ደቂቃ ያህል ይዘው ቆይተው ነስሩ ካልቆመ
📌 ወዲያዉኑ ወዲዉኑ በተደጋጋሚ የሚነስር ከሆነ
📌 ለነስሩ ጋር ተያይዞ ደም ማስመለስ ካለ
📌 ራስ ማዞር ወይንም ራስ መሳት ካለዉ
📌 ከፍተኛ ትኩሳት ካለ
📌 የልብ ምት የሚጨምር ከሆነ እና ለመተንፈስ መቸገር ካለ
📌 ሰውነት ላይ ሽፍታ/መበለዝ ካለ
📌 ከአፍንጫ ሌላ ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች ደም መፍሰስ ካለ
📌 ደምን ለማቅጠን የሚጠቅሙ መድኃኒቶችን የሚወስዱ ከሆነ
📌 የደም መርጋትን የሚያስተጓጉሉ ማንኛውንም ዓይንት ሕመም ካለ
📌 የኬሞቴራፒ ሕክምና በቅርቡ ወስደው ከነበረ

ነስር እንዴት ይቆማል

📌 ከጭንቅላትዎ ጎንበስ ማለት (ጭንቅላትን ወደ ላይ ቀና ማድረግ የሚፈሰውን ደም ወደ ጉሮሮ በማምጣት ጉዳት ያስከትላል)
📌 ቀጥ ብለው መቀመጥ
📌 ሁለቱም የአፍንጫ ቀዳዳዎች በአውራ ጣት እና በጠቋሚ ጣት ግጥም አድርጎ ለአስር ደቂቃ ይዞ ማቆየት
📌 በአፍ የሚመጣን ደም መትፋት
📌 ነስሩ ካቆመ በኋላ አፍንጫዎን አለመነካካት
📌 ቢያንስ ለ24 ሰአታት ያህል ሞቅ ያሉ መጠጦችን አለመጠቀም

የነስር ህክምና

📌 ደም በሚፈስበት ቦታ የአፍንጫ እስፖንጅ ማስገባት እና ከ 24-48 ሰአት ማቆየት(የሚገባዉም ሆነ የሚዎጣዉም በጤና ባለሙያ እርዳታ ነዉ፡፡)
📌 ለደም መርጋት የሚሆኑ መድሀኒቶች
📌 የተቀደዱ የደም ስሮችን ካሉ በኬሚካል(ሲሊቨር ናይትሬት በመጠቀም) እና በቀዶ ህክምና ማስተካከል ይገኙበታል።

https://t.me/ETtips
❤1
Ethiopian Tips® pinned «የነስር መንስኤዎች ነስር (epistaxis) ድንገተኛ የሆነ አስደንጋጭ ከአፍንጫ ደም መፍሰስ ሲሆን በአብዛኛው ለከፋ አደጋ የማይዳርግ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ነስርን ከሚነሳበት ክፍል በመነሳት በሁለት ይከፈላል፡፡ 1, ከፊተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Anterior Nosebleeds) ከአፍንጫ ቀደዳዎች መካከል አካባቢ የሚገኙ የደም ስሮች ሲጎዱ የሚከሰት ሲሆን ከ90 በመቶ በላይ ለሚከሰት…»
የግዕዝ ቁጥር ከ 1 እስከ 1ቢሊዮን፦

አልቦ 0
፩ አሐዱ 1
፪ ክልኤቱ 2
፫ ሠለስቱ 3
፬ አርባዕቱ 4
፭ ሐምስቱ 5
፮ ስድስቱ 6
፯ ስብዓቱ 7
፰ ስመንቱ 8
፱ ተሰዓቱ............. 9
፲ አሠርቱ .............10
፲፩ አሠርቱ ወአሐዱ 11
፲፪ አሠርቱ ወክልኤቱ 12
፲፫ አሠርቱ ወሠለስቱ 13
፲፬ አሠርቱ ወአርባዕቱ 14
፲፭ አሠርቱ ወሐምስቱ 15
፲፮ አሠርቱ ወስድስቱ 16
፲፯ አሠርቱ ወሰብዓቱ 17
፲፰ አሠርቱ ወስመንቱ 18
፲፱ አሠርቱ ወተሰዓቱ 19
፳ እስራ 20
፳፩ እስራ ወአሐዱ 21
፳፪ እስራ ወክልኤቱ 22
፳፫ እስራ ወሠለስቱ 23
፳፬ እስራ ወአርባዕቱ 24
፳፭ እስራ ወሐምስቱ 25
፳፮ እስራ ወስድስቱ 26
፳፯ እስራ ወሰብዓቱ 27
፳፰ እስራ ወሰመንቱ 28
፳፱ እስራ ወተሰዓቱ 29
፴ ሠላሳ 30
፴፩ ሠላሳ ወአሐዱ 31
፴፪ ሠላሳ ወክልኤቱ 32
፴፫ ሠላሳ ወሠለስቱ 33
፴፬ ሠላሳ ወአርባዕቱ 34
፴፭ ሠላሳ ወሐምስቱ 35
፴፮ ሠላሳ ወስድስቱ 36
፴፯ ሠላሳ ወሰብዓቱ 37
፴፰ ሠላሳ ወሰመንቱ 38
፴፱ ሠላሳ ወተሰዓቱ 39
፵ አርብዓ 40
፶ ሃምሳ 50
፷ ስድሳ 60
፸ ሰብዓ 70
፹ ሰማንያ 80
፺ ተሰዓ 90
፻ ምዕት 100
፻፩ ምዕት ወአሐዱ 101
፻፪ ምዕት ወክልኤቱ 102
፻፫ ምዕት ወሠለስቱ 103
፻፬ ምዕት ወአርባዕቱ 104
፻፭ መዕት ወሐምስቱ 105
፻፮ ምዕት ወስድስቱ 106
፻፯ ምዕት ወሰብዓቱ 107
፻፰ ምዕት ወስመንቱ 108
፻፱ ምዕት ወተሰዓቱ 109
፻፲ ምዕት ወአሠርቱ 110
፻፲ወ፩ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 111
፻፲ወ፪ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 112
፻፲ወ፫ ምዕት አሠርቱ ወሠለስቱ 113
፻፲ወ፬ ምዕት አሠርቱ ወአርባዕቱ 114
፻፲ወ፭ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 115
፻፲ወ፮ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 116
፻፲ወ፯ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 117
፻፲ወ፰ ምዕት አሠርቱ ወስመንቱ 118
፻፲ወ፱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 119
፻፳ ምዕት ወእስራ 120
፻፴ ምዕት ወሠላሳ 130
፻፵ ምዕት ወአርብዓ 140
፻፶ ምዕት ወሃምሳ 150
፻፷ ምዕት ወስድሳ 160
፻፸ ምዕት ወሰብዓ 170
፻፹ ምዕት ወሰማንያ 180
፻፺ ምዕት ወተሰዓ 190
፪፻ ክልኤቱ ምዕት 200
፪፻ወ፩ ክልኤቱ ምዕት ወአሐዱ 201
፪፻ወ፪ ክልኤቱ ምዕት ወክልኤቱ 202
፪፻ወ፫ ክልኤቱ ምዕት ወሠለስቱ 203
፪፻ወ፬ ክልኤቱ ምዕት ወአርባዕቱ 204
፪፻ወ፭ ክልኤቱ ምዕት ወሐምስቱ 205
፪፻ወ፮ ክልኤቱ ምዕት ወስድስቱ 206
፪፻ወ፯ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓቱ 207
፪፻ወ፰ ክለኤቱ ምዕት ወስመንቱ 208
፪፻ወ፱ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓቱ 209
፪፻ወ፲ ክልኤቱ ምዕት ወአሠርቱ 210
፪፻፲ወ፩ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 211
፪፻፲ወ፪ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 212
፪፻፲ወ፫ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሠልስቱ 213
፪፻፲ወ፬ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአርባቱ 214
፪፻፲ወ፭ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 215
፪፻፲ወ፮ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 216
፪፻፲ወ፯ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 217
፪፻፲ወ፰ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰመንቱ 218
፪፻፲ወ፱ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 219
፪፻፳ ክልኤቱ ምዕት ወእስራ 220
፪፻፴ ክልኤቱ ምሪዕት ወሠላሳ 230
፪፻፵ ክልኤቱ ምዕት ወአርብዓ 240
፪፻፶ ክልኤቱ ምዕት ወሃምሳ 250
፪፻፷ ክልኤቱ ምዕት ወስድሳ 260
፪፻፸ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓ 270
፪፻፹ ክልኤቱ ምዕት ወሰማንያ 280
፪፻፺ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓ 290
፫፻ ሠለስቱ ምዕት 300
፬፻ አርባዕቱ ምዕት 400
፭፻ ሐምስቱ ምዕት 500
፮፻ ስድስቱ ምዕት 600
፯፻ ስብዓቱ ምዕት 700
፰፻ ስመንቱ ምዕት 800
፱፻ ተሰዓቱ ምዕት 900
፲፻ አሠርቱ ምዕት 1000
፳፻ እስራ ምዕት 2000
፴፻ ሠላሳ ምዕት 3000
፵፻ አርብዓ ምዕት 4000
፶፻ ሃምሳ ምዕት 5000
፷፻ ሳድስ ምዕት 6000
፸፻ ሰብዓ ምዕት 7000
፹፻ ሰማንያ ምዕት 8000
፺፻ ተሰዓ ምዕት 9000
፻፻ እልፍ 10,000
፪፻፻ ክልኤቱ እልፍ 20,000
፫፻፻ ሠለስቱ እልፍ 30,000
፬፻፻ አርባዕቱ እልፍ 40,000
፭፻፻ ሐምስቱ እልፍ 50,000
፮፻፻ ስድስቱ እልፍ 60,000
፯፻፻ ሰብዓቱ እልፍ 70,000
፰፻፻ ስመንቱ እልፍ 80,000
፱፻፻ ተሰዓቱ እልፍ 90,000
፲፻፻ አሠርቱ እልፍ 100,000
፳፻፻ እስራ እልፍ 200,000
፴፻፻ ሠላሳ እልፍ 300,000
፵፻፻ አርብዓ እልፍ 400,000
፶፻፻ ሃምሳ እልፍ 500,000
፷፻፻ ስድሳ እልፍ 600,000
፸፻፻ ሰብዓ እልፍ 700,000
፹፻፻ ሰማንያ እልፍ 800,000
፺፻፻ ተሰዓ እልፍ 900,000
፻፻፻ አእላፋት 1,000,000
፲፻፻፻ ትእልፊት 10,000,000
፻፻፻፻ ትልፊታት 100,000,000
፲፻፻፻፻ ምእልፊት 1,000,000,000

https://t.me/ETtips
ስልካችን ስቶሬጅ (Storage) ከሞላ ዋናው መፍትሔ ይህን አፕ መጠቀም ነው !

📌 ስለ Storage problem ከዚህ በፊት post አድርገናል ግን ይህን ዘዴ እንድትጠቀሙት እንመክራለን !

📌 ብዙ ሰው ከስልኩ አለ ግን የማንጠቀመው ዘዴ !

[በነገራችን ላይ እኔ የምመርጠው ቀዳሚ መፍትሔ ነው ! ]

📌 Flash ,Memory .... ከመግዛትና ከማስቀመጥ ብዙ እጥፍ ይሻላልም ይመከራልም !

~ Google "drive" በሚል application የተለያዩ file አችንን እንድናስቀምጥ የሚያደርግ system አለው !

📌 በዚህ የ Google App ውስጥ...

🎯ፈቶ፣video delete ማድረግ አይጠበቅባችሁም
🎯ስልካችሁ ቢጠፋ ፋይላችሁን ማግኘት ትችላላችሁ
🎯 በአንድ email account ብቻ 15 GB ቦታ ይሰጣችኋል 😍
🎯5 Email ቢኖራችሁ 15x5 =75GB ከስልካችሁ storage ውጭ Google ይሰጣችኋል !

~ ከናንተ ሚጠበቀው email address ና password በጥንቃቄ መያዝ ነው !

~ 100% አስተማማኝ ነው ማንም የግል መረጃችሁን አያይም !

📌 ከ Google ምርት አንዱ የሆነው ና በ Drive storage የሚጋራው Google photos ደግሞ ዋና የፈቶ ማስቀመፃ App ነው...

📌" አብዛኛው ሰው የማይጠቀመው ግን እያንዳንዱ አንድሮይድ ስልክ ውስጥ ያለ አንድ ድንቅ መተግበሪያ አለ ። እሱም "Google Photos" ይባላል ።

📌 ይህም አፕ ፎቶዎችን ማስቀመጫ ብቻ ሳይሆን የስልካችሁን ቦታ ነፃ ማድረጊያ ምርጡ ዘዴ ነው !

[አሰራሩ በቅደም ተከተል ...👇 ]

1) Google Photos አፕ ውስጥ ይግቡ።

2) ከላይ የፕሮፋይል ምልክታችሁን ንኩና "Photos settings" ውስጥ ግቡ።

3) "Backup" የሚለውን አብሩት (ይህ ፎቶዎቻችሁን ወደ Google cloud storage upload ያደርገዋል ) ።

4) አሁን ዋናው ሚስጥር እዚህ ጋር ነው፦ "Free up space" የሚለውን በመጫን በጣም ብዙ free storage ማግኘት ትችላላችሁ !

📌 ስልካችሁ ወደ ጎግል የተሰቀሉትን (Backup የተደረጉትን) ፎቶዎች ከስልካችሁ "Internal Storage" ላይ ብቻ ነው delete የሚያደርጋቸው ። ፎቶዎቹ ግን አሁንም በ "Google Photos" ውስጥ ይኖራሉ ።

🎯 ስልካችሁ ቢሰረቅ ወይም ቢጠፋ እንኳ፣ አዲስ ስልክ ገዝታችሁ የድሮ የኢሜል (Gmail) አድራሻችሁን ስታስገቡ፣ የድሮ ፎቶዎቻችሁ በሙሉ እንደነበሩ ተመልሰው ይመጣላችኋል ።

📌 የመጨረሻ Tip ፦ ከናንተ ሚጠበቀው ነገር email address እና password አለመርሳት ነው ! ፓስወርዳችሁንና email address ሳችሁን በተለያየ ቦታዎች አስቀምጡ !
ለምሳሌ በ Telegran Saved message ,Other cloud app ወይም ቶሎ ከምታገኙበት ቦታ !

#Backup
#Google_photos
#storage_full

https://t.me/ETtips
ስለ ቴሌግራም ይህን ማወቅ አለባችሁ !

📌 1. የኮድ ችግር መፍትሄ ፦ ቴሌግራም በድጋሚ ሲገቡ ኮድ አልመጣ ካለዎት፣ Telegram X አውርዱና ስልክ ቁጥሩን አስገብታችሁ በ SMS ሳይሆን "Get code via call" የሚለውን በመምረጥ በስልክ ጥሪ ኮዱ እንዲነገራችሁ አድርጉ ። ፈጣን መፍትሄ ነው!

📌 2. ኢንተርኔት መቆጠቢያ፦ ቴሌግራም ያለምክንያት ዳታ እንዳይጨርስባችሁ Settings > Data and Storage ውስጥ ገብታችሁ "Automatic Media Download" የሚሉትን 3ቱንም አማራጮች አጥፏቸው (Off አድርጓቸው) ። ቪዲዮና ፎቶ በራሱ መውረድ ያቆማል!

📌 3. ስልክ ቁጥርን መደበቅ፦ ማንም ሰው በእርስዎ ፈቃድ ቁጥርዎን እንዳያይ Settings > Privacy and Security > Phone Number ውስጥ ገብታችሁ "Nobody" የሚለውን ይምረጡ። በዚህም ደህንነታችሁን መጠበቅ ትችላላችሁ።

📌 4. ለራስ መልእክት መላክ (Cloud Storage)፦ ቴሌግራም ላይ "Saved Messages" የሚባለው ክፍል ለእርስዎ ብቻ የተዘጋጀ የ24 ሰዓት ማከማቻ ነው። ማንኛውንም ፎቶ፣ ቪዲዮ ወይም ፋይል እዚያ ላይ በመላክ ለዘላለም ማስቀመጥ እና ከማንኛውም ስልክ ማግኘት ትችላላችሁ ።
(እችን እምኳ ገላግሌ በሏት ብዙ መረጃ ሚይዝልን ነው 😍)

📌 5. በስም ብቻ ሰውን መፈለግ፦ የሰው ስልክ ቁጥር ሳይኖራችሁ በቴሌግራም መገናኘት ትችላላችሁ። Settings > Username ውስጥ ገብታችሁ የራሳችሁን ስም (ለምሳሌ @ETtips ) ፍጠሩ። ቁጥራችሁን ሳይሰጡ በዚህ ስም ብቻ ሰዎች እንዲያገኟችሁ ማድረግ ትችላላችሁ ።

📌 6. የመልእክት ሰዓት መወሰን (Scheduled Messages)፦ ለአንድ ሰው መልእክት መላክ ፈልገው ግን ሰዓቱ ካልደረሰ፣ የመላኪያ (Send) ቁልፉን ጫን አድርገው በመያዝ "Schedule Message" የሚለውን በመምረጥ እንዲላክ የሚፈልጉበትን ቀንና ሰዓት መወሰን ይችላሉ።

📌 7. ፎቶን ሳይደበዝዝ መላክ ( በQuality)፦ ፎቶ ስትልኩ ጥራቱ እንዳይቀንስ ከፈለጋችሁ እንደ ፎቶ ሳይሆን "File" የሚለውን መርጣችሁ ላኩት። ፎቶው ልክ እንደተነሳበት ጥራት ይደርሳል!

📌 8. ቪዲዮን ወደ GIF መቀየር፦ ቪዲዮ ለሰው ሲልኩ ድምፁን "Mute" (ማጥፊያ) ምልክቱን ከነካችሁት፣ ቪዲዮው ወዲያውኑ ወደ GIF ይቀየራል፤ ይህም በጣም አነስተኛ ዳታ (MB) እንዲጠቀም ያደርገዋል ።

📌 9. በስውር መልእክት ማንበብ ፦ የመጣላችሁን መልእክት የላከው ሰው ሳያውቅ (ሁለት ምልክት ሳይበራ) ለማንበብ፣ የሰውየውን ፎቶ (Profile) ጫን አድርገው ይያዙት ። መልእክቱ በትንሽ መስኮት ተከፍቶ ይታያችኋል 🙄!

📌 10. የቴሌግራም መጠለፍ በፍጥነት ለመመለስ ፦ አካውንታችሁ በሌላ ሰው መከፈቱን ለማወቅ Settings > Devices ውስጥ ይግቡ ። ከእርስዎ ስልክ ውጪ ሌላ መሳሪያ ካዩ "Terminate all other sessions" የሚለውን በመጫን ሌላ ሰው በናንተ account እየተጠቀመ ከሆነ እንዳይጠቀም ማድረግ ትችላላችሁ !

🎯 Tip ፦ ቴሌግራማችሁን 100% አስተማማኝ ለማድረግ Two-Step Verification የሚለው ማብራታችሁን እንዳትረሱ!

#TelegramTips #TelegramHacks
#DigitalLife

https://t.me/ETtips
❤1
አዲስ ስልክ ለመግዛት ሲያስቡ እነዚህን ነጥቦች የግድ ይፈትሹ!

ስልክ መግዛት ዝም ብሎ ፎቶ ማየት ወይም ብራንድ መምረጥ አይደለም። የገንዘብዎ ዋጋ እንዲመለስልዎትና ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግልዎት የሚከተሉትን 7 ወሳኝ ነጥቦች ልብ ይበሉ፦

📌 1) ፕሮሰሰር (Processor)፦ የስልኩ "አንጎል" ነው። ስልኩ እንዳይቆራረጥ (Lag እንዳያደርግ) ጠንካራ ፕሮሰሰር ያለው መሆኑን ያረጋግጡ። ለምሳሌ ለጌም ወይም ለከባድ ስራ Snapdragon ወይም Apple Bionic የተሻሉ ናቸው።

📌 2) ራም (RAM)፦ ስልኩ በአንድ ጊዜ ብዙ አፖችን የመክፈት አቅሙን ይወስናል። ዛሬ ላይ ቢያንስ 6GB ወይም 8GB RAM ያለው ስልክ መግዛት ለፍጥነትዎ አስተማማኝ ነው።

📌 3) ስክሪን (Display Quality) ፦ ቀኑን ሙሉ የምናየው ስክሪኑን ስለሆነ AMOLED ወይም OLED ስክሪን ያላቸውን ይምረጡ። ቀለማቸው ጥራት ያለውና ለዓይን የማይደክሙ ናቸው።

📌 4) ባትሪ (Battery Life) ፦ ከቻርጅ ጋር ተጣብቀው መኖር ካልፈለጉ ቢያንስ 5000mAh ባትሪ ያለውና Fast Charging (በፍጥነት ቻርጅ የሚያደርግ) መሆኑን ያረጋግጡ ።

📌 5) ካሜራ (Camera Quality) ፦ የሜጋፒክሰል (MP) ብዛት ብቻውን ጥራት አይሰጥም ። በዩቲዩብ ላይ የስልኩን የካሜራ "Sample" ቪዲዮዎች በማየት ትክክለኛ ጥራቱን ያረጋግጡ ።

📌 6) ስቶሬጅ (Internal Storage) ፦ ዛሬ ላይ አፖችና ፎቶዎች ትልቅ ቦታ ስለሚይዙ ቢያንስ 128GB ያለው ስልክ ይመረጣል ። "Memory Full" ከሚል ጭንቀት ያርፉበታል ።

📌 7) የገበያ ዋጋ ፦ ሁሌም ዋጋውን ካሰቡት በጀት ጋር አገናዝቡ። አንዳንድ ጊዜ በስሙ ብቻ ... ውድ ከሆነ ስልክ ይልቅ፣ በተመሳሳይ ዋጋ የተሻለ አቅም (Specs) ያላቸው ሌሎች ብራንዶችን ማግኘት እንደሚቻል ታሳቢ አድርጉ።

🎯 አንድ ሚስጥር ፦

ስልክ ከመግዛታችሁ በፊት 'Google' ላይ በመግባት የስልኩን ስም ጽፋችሁ መጨረሻ ላይ 'GSMarena' ብላችሁ ፈልጉ። ስለ ስልኩ እያንዳንዱን ዝርዝር መረጃ (Specs) እዚያ ላይ በግልጽ ታገኛላችሁ!

https://t.me/ETtips
Ethiopian Tips® pinned «አዲስ ስልክ ለመግዛት ሲያስቡ እነዚህን ነጥቦች የግድ ይፈትሹ! ስልክ መግዛት ዝም ብሎ ፎቶ ማየት ወይም ብራንድ መምረጥ አይደለም። የገንዘብዎ ዋጋ እንዲመለስልዎትና ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግልዎት የሚከተሉትን 7 ወሳኝ ነጥቦች ልብ ይበሉ፦ 📌 1) ፕሮሰሰር (Processor)፦ የስልኩ "አንጎል" ነው። ስልኩ እንዳይቆራረጥ (Lag እንዳያደርግ) ጠንካራ ፕሮሰሰር ያለው መሆኑን ያረጋግጡ። ለምሳሌ ለጌም ወይም…»
ቴሌግራም በኮምፒውተር እየተጠቀሙ አማርኛ አላነብ ብሎታል ?

ከሰሞኑ የቴሌግራም መተግበሪያ የዊንዶው ቨርዥን አማርኛ ጹሑፎችን ለማንበብ ሲያስቸገር ተስተውሏል።

ቴሌግራም በኮምፒውተር የምትጠቀሙ  ተከታዩን ቅደም ተከተል በመጠቀም አማርኛ እንዲያነብላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።

Setting > Chat Setting > Font Family > ከሚመጣላችሁ ዝርዝር ውስጥ የሚፈልጉትን የአማርኛ ፎንት ይምረጡ (ለምሳሌ፦ Power Geez Unicode1, Ebrima, Nyala , Noto sans . . .) > Save > Restart

አማርኛ ፎንት በአማራጭ ውስጥ የማያገኙ ከሆነ የሚፈልጉትን ፎንት ቀጥታ ካወረዳችሁ በኋላ ቴሌግራማችሁን እንደ አዲስ በመክፈት መምረጥና ማስተካከል ይችላሉ።

ለአብነትም፥ Noto sans የተሰኘውን ፎንት https://fonts.google.com/noto/specimen/Noto+Sans+Ethiopic ላይ ማውረድ ይችላሉ። 

አማርኛ ፎንት ስለመረጡ አማርኛ ብቻ ነው የሚያነበው ማለት አይደለም የላቲን ፊደላትንም ማንበብ ያስችላችኋል።

https://t.me/ETtips
❤1