TIKVAH-ETHIO
709 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ : በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት የጤና መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡

በአማራ ክልል የደብረ ዘቢጥ ጤና ጣቢያ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት አገልግሎት መስጠት አቁሟል፡፡ በዚህም ህሙማን በህክምና እና መድኃኒት እጥረት #እየሞቱ ይገኛሉ፡፡

የህክምና መሰረተ ልማቶች እና ባለሞያዎች የጦርነት ኢላማ መሆን የለባቸውም፡፡

#ICRCEthiopia

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በህ/ተ/ም/ቤት ፀደቀ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ6 ወራት ተፈጻሚ የሚሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርምሮ አፅድቋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአንድ ድምጽ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው።

#ተጨማሪ_መረጃ ፦ ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባላት ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አፅድቋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድን ፤ አቶ ለማ ተሰማ - በሰብሳቢነት ፤ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ- በም/ሰብሳቢነት ይመሩታል።

መርማሪ ቦርዱ ሌሎች አምስት አባላት አሉት።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ፎቶ ፦ ፌልትማን ኢትዮጵያ ገብተዋል።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ጄፍሪ ፌልትማን ዛሬ ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) ገብተዋል፤ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ በኃላም ከሙሳ ፋኪ ማሃመት ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ፌልትማንን በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ጄፍሪ ፌልትማንን በቢሯቸው ተቀብለው በ #ኢትዮጵያ እና #ሱዳን ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን አሳውቀዋል።

Credit : Moussa Faki Mahamat (Twitter)

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#ማስጠንቀቂያ

በሀረሪ ክልል የህክምና ቁሳቁሶችን ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የሚሸጡ መድሃኒት መደብሮችን ከእኩይ ተግባራቸድ እንዲቆጠቡ የክልሉ ጤና ቢሮ አሥጠንቅቋል።

ቢሮው ፥ በጤና ባለሞያዎች የታዘዙ የመድሃኒት ምርቱ እያለ የለም በማለት እና ለህብረተሰቡ በተጋነነ ዋጋ በማቅረብ የግል ጥቅማቸውን የሚያሯሩጡ መድሀኒት መደብሮች ከዚህ እኩይ ተግባር ሊቆጠቡ ይገባል ብሏል።

በተያያዘ በጤና ባለሞያዎች ያልታዘዙ መድሃኒቶችን በግድ የለሽነት የሚሸጡ የግል መድሃኒት መደብሮች ህጋዊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ቢሮው አሳውቋል።

መድሀኒት ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የሚሸጡ መድሃኒት መደብሮችን ህብረተሰቡ በማጋለጥ የበኩሉን እንዲወጣ ሲል የክልሉ ጤና ቢሮ መልዕክት አስተላልፏል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#HappeningNow

ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ማብራሪያ እየተሰጠ ነው።

በአሁን ሰዓት መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላይ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እየተሰጠ ይገኛል።

ማብራሪያው በኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና በፍትህ ሚንስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ነው እየተሰጠ የሚገኘው።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ማብራሪያው የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ብዥታውን ለማጥራት ይረዳል ብለዋል። በሃገሪቱ ላይ የተጋረጠውን ፈተና ለመከላከል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ እንዳስፈለገም ተናግረዋል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ የፍትህ ሚንስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

Credit : ኤፍቢሲ

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
የተማሪዎች ምደባ ይፋ ሆኗል።

በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጊዚያዊ ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ተከታዩን ሊንክ በመከተል የዩኒቨርሲቲ መለያ ቁጥር እና ሙሉ ስም በማስገባት ጊዚያዊ ምደባቸውን መመልከት ይችላሉ፦ http://Placement.ethernet.edu.et

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
የዩኒቨርሲቲ ምደባ !

በመቐለ ፣ አክሱም ፣ ዓዲግራት ፤ ራያ እንዲሁም ወልዲያ ዩኒቨርስቲ ሲማሩ የነበሩና በፀጥታ ችግር ትምህርታቸውን መቀጠል ላልቻሉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ጊዜያዊ ምደባ ዛሬ ይፋ ሆኗል።

ምደባውን በዚህ http://Placement.ethernet.edu.et መመልከት ይቻላል።

• ምደባዉ እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም. የነበረዉን የትምህርት ጊዜ ሰሌዳን ጨርሰው የወጡት ተማሪዎችን ብቻ ይመለከታል፡፡

• ምደባዉ የተካሄደዉ መረጃዎችን በትክክል ላሰገቡ ተማሪዎች ሲሆን፣ በተጠየቀዉ መሰረት መረጃዎችን በትክክል ያላስገቡ ተማሪዎችና የኦን ላይን ፎርሙን በተለያየ ምክንያት በወቅቱ መሙላት ያልቻሉ ተማሪዎች ስማቸውን ኦንላይን ምደባ በሚረጋገጥበት ሶፍትዌር ላያገኙ ስለሚችሉ፣ በነበሩበት የትምህርት ክፍልና ዩኒቨርሲቲን መነሻ በማድረግ በዲፓርትመንት ስለተመደቡ፤ የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል።

• ተመዝግበው ሳይመደቡ የቀሩ ተማሪዎች በቂና ግልፅ መረጃ ያላቀረቡ መሆኑን በመገንዘብ ትምህርት ክፍላቸው የተመደበበትን ዩነቨርስቲ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል።

• ያልተመዘገቡ እንዲሁም ቅሬታ ወይም አቤቱታ ያላቸው ተማሪዎች በቴሌግራም ቦት (@moeplacementbot) አቤቱታቸውን ማቅረብ ይችላሉ። ትምህርት ሚኒስቴር አቤቱታዎችን በአካል እንደማያስተናግድ በጥብቅ አሳስቧል።

• በዩኒቨርስቲዎች ተፈቅዶላቸው እረፍት (Withdrawal) ላይ የነበሩ ተማሪዎች የትምህርት ክፍላቸው ለተመደበበት ዩኒቨርስቲ ማስረጃቸውን አቅርበው የሚታይላቸዉ ይሆናል ተብሏል።

NB : ተማሪዎች የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ጥሪ ሲያደርግ ብቻ ነው በአካል ቀርበው ሪፖርት የሚያደርጉት።

#MoE

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
animation.gif
7.9 KB
" ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር አልዘጋችም " - የኬንያ ፖሊስ አገልግሎት

‘Citizen TV’ የተባለው የኬንያ ቴሌቪዝን ጣቢያ በትናንትናው ዕለት “ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች” የሚል መረጃ አስረጭቶ ነበር። የቴሌቪዥን ጣቢያው ኬንያ ከ800 ኪሎሜትር በላይ የሚረዝመውን የሁለቱን ሀገራት ድንበር ላልተወሰነ ጊዜ መዝጋቷን ለዘገበበት ዜና ምንጭ አልጠቀሰም።

የኬንያ ፖሊስ አገልግሎት (Kenya Police Service) ዛሬ እንዳስታወቀው የኬንያ-ኢትዮጵያ ድንበር መዝጋቱን በተመለከተ በሚዲያ የተሰራጨው መልዕክት #የተሳሳተ መሆኑን አስታውቋል።

“አንዳንድ ሚዲያዎች በተሳሳተ መንገድ እንደዘገቡት ሳይሆን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስነው ድንበር አልተዘጋም” ያለው የኬንያ ፖሊስ “ያደረግነው በድንበር አካባቢ ያለውን የጸጥታ ቁመናችንን ማጠናከር ነው” ሲል አብራርቷል። የኬንያ ፖሊስ በተጨማሪም በድንበር አካባቢ ያለው ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑን ገልጿል።

የኬኒያ ፖሊስ በትናንትናው ዕለት “አጎራባች” ባላቸው ሀገሮች እየታዩ ነው ካላቸው የጸጥታ ሁኔታዎች አኳያ አምስት ነጥቦችን የያዘ መግለጫ አውጥቶ የነበረ ሲሆን ከነጥቦቹ መካከል በድንበር አካባቢ የጸጥታ ቁጥጥርን ማጠናከር የሚል ይገኝበታል።

Credit : ኢትዮጵያ ቼክ

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
" በአማራ ክልል 33 ሺህ ተማሪዎች የ12 ክፍል መልቀቂያ አይፈተኑም " - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

በጦርነት ምክንያት በአማራ ክልል ከሚገኙ 357 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል በ112ቱ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እንደማይሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ይህ ያሳወቀው ለጀርመን ሬድዮ በሰጠው ቃል ነው።

በአማራ ክልል ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡ 164 ሺህ ተማሪዎች መካከል ጦርነቱ በፈጠረው ችግር ምክንያት 33 ሺህ ተማሪዎች መፈተን አይችሉም።

የአማራ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሙላው አበበ እንደተናገሩት ፦
• በሰሜን ወሎ 42፣
• በዋግኽምራ 16፣
• በደቡብ ወሎ 48
• በደሴ ከተማ አስተዳደር 3፣
• በሰሜን ጎንደር 3 ሁለተኛ ት/ቤቶች ተማሪዎቻቸውን አያስፈትኑም፡፡

በክልሉ ለፈተናው የሚቀመጡት 131 ሺህ 167 ተማሪዎች ብቻ ሲሆኑ 123 ሺህ 159 በመደበኛ፣ 8 ሺህ 8 ደግሞ የግል ተፈታኞች መሆናቸውን ቢሮው ለሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከፊታችን ጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2/2014 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ ይሰጣል፡፡

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተራዘመ !

ህዳር 5 በቀጣይ ሳምንት እሁድ ሊያኬድ የነበረው የ 2014 ቶታል ኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መራዘሙ ተገልጿል ።

" በ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት ህዳር 5 ቀን ሊካሄድ የነበረውን የ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላልተወሰነ ጊዜ ለማራዘም መወሰናችንን እናሳውቃለን " ሲል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስነብቧል ።

የ ውድድሩን ተለዋጭ ቀን በቅርብ ሳምንታት ውስጥ እንደሚያሳውቁ አዘጋጆቹ ገልፀዋል ።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
" በአማራ ክልል 33 ሺህ ተማሪዎች የ12 ክፍል መልቀቂያ አይፈተኑም " - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

በጦርነት ምክንያት በአማራ ክልል ከሚገኙ 357 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል በ112ቱ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እንደማይሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ይህ ያሳወቀው ለጀርመን ሬድዮ በሰጠው ቃል ነው።

በአማራ ክልል ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡ 164 ሺህ ተማሪዎች መካከል ጦርነቱ በፈጠረው ችግር ምክንያት 33 ሺህ ተማሪዎች መፈተን አይችሉም።

የአማራ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሙላው አበበ እንደተናገሩት ፦
• በሰሜን ወሎ 42፣
• በዋግኽምራ 16፣
• በደቡብ ወሎ 48
• በደሴ ከተማ አስተዳደር 3፣
• በሰሜን ጎንደር 3 ሁለተኛ ት/ቤቶች ተማሪዎቻቸውን አያስፈትኑም፡፡

በክልሉ ለፈተናው የሚቀመጡት 131 ሺህ 167 ተማሪዎች ብቻ ሲሆኑ 123 ሺህ 159 በመደበኛ፣ 8 ሺህ 8 ደግሞ የግል ተፈታኞች መሆናቸውን ቢሮው ለሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከፊታችን ጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2/2014 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ ይሰጣል፡፡

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
👆የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ (5 /2014) መምሪያ ዕዝ መዋቅር እና አደረጃጀት መመሪያ ቁጥር 1/2014

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
" የጦር መሳሪያ የጫነ ተሽከርካሪ ወደ ሆሳዕና ከተማ ገብቷል ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው " - የሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ

የሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጥቅምት 24/2014 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት አካባቢ መነሻውን ከአዲስ አበባ ያደረገ ኮድ 3 ሰሌዳ ቁጥር 19331 ደ.ህ የሆነ ተሽከርካሪ የጦር መሳሪያ ጭኖ በወልቂጤ ከተማ በኩል ወደ በሆሳዕና ገብቷል ተብሎ የሚሰራጨው ወሬ ሀሰት መሆኑን ገልጿል።

ይሁንና ተሽከርካሪው በፍጥነት እያሽከረከረ ስለነበረ ሆሳዕና ከተማ ናረሞ አከባቢ በስራ ላይ የነበሩ ትራፊክ ፖሊሶች ለማስቆም ሲሞክሩ ጥሶ በማለፍ በ2 ሞተረኞች ላይ የአካል ጉዳት አድርሷል።

አሽከርካሪው ጉዳት አድርሶ ለማምለጥ ጥረት ቢያደርግም በአከባቢው ህበረተሰብና በፀጥታ አካላት ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገልጿል።

በተጎጂዎቹም ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት በመድረሱ በንግስት እሌኒ መህመድ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው።

ጉዳቱን ባደረሰው አሽከርካሪ ምርመራ በማድረግ የማጣራት ስራ እያከናወነ ይገኛል።

ጉዳዩ ይህ ቢሆንም የጦር መሳሪያ የጫነ ተሽከርካሪ ወደ ሆሳዕና ገብቷል ተብሎ የሀሰት መረጃ የተሰራጨ ሲሆን ፖሊስ መረጃው ሀሰተኛ ነው ብሏል።

ህብረተሰቡ ትክክለኛነቱ ባልተረጋገጠ ወሬ ሳይረበሽ አካባቢውን ከፀጥታ አካለት ጋር በመተባበር በመጠበቅ ወንጀልን በጋራ እንዲከላከል ጥሪ ቀርቧል።

ነዋሪዎች ማንኛውም ጥርጣሬ ውስጥ የሚያስገባ ነገር ካጋጠማቸው 046550330 በመደወል ለፖሊስ መረጃ እንዲሰጡ ተጠይቋል።

(የሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ)

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#የመንግስት_ማስጠንቀቂያ

የኢትዮጵያ መንግስት ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀ።

ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ያወጣው የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል አስጠንቅቋል።

መንግስት በመግለጫው "የሽብር ቡድኑ ማሽኖችና በሽርክና የሚሰሩ ሚዲያዎች የሽብር ወሬ እያሰራጩ ናቸው" ብሏል። ቁልፍ ኢላማቸው ደግሞ በአመራሩና ፣ በህዝቡና በወገን ጦር መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር ፍርሃትም እንዲነግስ ማሸበር ነው ሲል ገልጿል።

በተለያየ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ያሉ ተላላኪዎቻቸው የፀጥታ ችግር እንዳለ በማስመሰል የግል ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ የማግባባት ስራ እየሰሩ ይገኛሉም ብሏል።

በህዝቡና በወገኑ ጦር ውስጥ ጥርጣሪዎችን ለመፍጠር የመንግስት ባለስልጣናት ቪዛ እየጠየቁ ነው በሚል የውሸት ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ናቸውም ሲል ገልጿል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን በመግለጫው ከዲፕሎማሲ መርህ ውጪ የአንዳንድ ሃገር ኤምባሲዎች አዲስ አበባ እንደ ተከበበች በማስመሰልና ያሰቡት ውጥን እንዲሳካ በኤምባሲያቸው የሚሰሩ ዜጎቻቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እያሳሰቡ ይገኛሉ ብሏል።

በእንዲህ አይነት መንገድ ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰበው መንግስት በሀገር ጉዳይ ቀልድ የለምና ከድርጊቱ ባልተቆጠቡት ላይ የማያዳግም ርምጃ ይወሰዳል ሲል አስጠንቅቋል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 15 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,341 የላብራቶሪ ምርመራ 327 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 420 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ተጨማሪ አዳዲስ የደንብ ልብሶችን ስራ ላይ ማዋሉን ዛሬ አሳውቋል።

ነባሩን የደንብ ልብስ መጠቀም ማቆሙን ተቋሙ ገልጿል፡፡

ከዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ አዳዲሶቹ የደንብ አልባሳትን ብቻ መጠቀም እንደሚገባ እና ነባሩ የደንብ ልብስ ሙሉ በሙሉ መቀየሩ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ አሮጌውን የደንብ ልብስ ለብሶ የተገኘ አመራር እና አባል ላይ ጠንከር ያለ የዲስፕሊን እርምጃ ይወሰድበታል ተብሏል።

ህብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካላት አሮጌው የደንብ ልብስ ሙሉ በሙሉ በአዳዲሶቹ መቀየሩን ተገንዝበው አሮጌውን የደንብ ልብስ የለበሰ የፖሊስ አባል ሲያጋጥማቸው መረጃ በመስጠት እንዲተባበሩ ጥሪ ቀርቧል።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ፖሊስ ስራ ላይ ካዋላቸው አዳዲስ የደንብ አልባሳት ጋር ወይም ከሌሎች የፀጥታ አካላት የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ዩኒፎርም መጠቀም ክልክል መሆኑ በህግ የተደገገ ስለሆነ ከአ/አ ፖሊስ የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ዩኒፎርም የሚጠቀሙ አካላት ማስተካከያ እንዲያደርጉ ተቋሙ መልዕክቱን አስተላልፏል።

#AddisAbabaPolice

#Share #ሼር

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#ETHIOPIA

ማንኛውም የፀጥታ ችግር እንቅስቃሴ ሲመለከቱ ወይም ደግሞ ጥቆማ ለመስጠት ከፈለጉ ከላይ በተቀመጡት የስልክ መስመሮች ፈጥነው እንዲደውሉ የፌዴራል ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

#ሼር #Share

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#AddisAbaba

በእጃቹ ያለውን መሳሪያ እስከ ጥቅምት 27 / 2014 ደረስ ማስመዝገብ ትችላላችሁ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ በተለያዩ ምክንያቶች የጦር መሳሪያ ምዝገባው እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2014 ዓ/ም በድጋሚ መራዘሙን አሳውቋል።

የጦር መሳሪያ በእጁ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ በአስራ አንዱ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያዎችና በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች በግንባር በመገኘት እንዲያስመዘግብ መልዕክት መተላለፉን ተከትሎ በርካታ ግለሰቦች በእጃቸው ላይ የሚገኝን የጦር መሳሪያ ለተከታታይ 3 ቀናት ማስመዝገባቸው ተገልጿል።

መሳሪያ በእጃቸው ላይ ያለ ሰዎች የማስመዝገብ ፍላጎቱ እያላቸው የምዝገባ ቀኑ በማጠሩ ፣ ያላቸውን የጦር መሳሪያ ሌላ ቦታ በማስቀመጣቸው እና ማስመዝገብ እንደሚቻል በቂ መረጃ ያልሰሙ ግለሰቦች በመኖራቸው ምክንያት ምዝገባው እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2014 ዓ/ም መራዘሙ ተገልጿል።

በእጁ ላይ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ያላስመዘገበ ማንኛውም ግለሰብ የተጨመረውን ቀን ተጠቅሞ እንዲያስመዘግብ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#SNNPRS

በደቡብ ክልል መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በ5 ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግብ ጥሪ ቀረበ።

ይህ ጥሪ የተላለፈው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ትናንት ያካሔዱትን ውይይት መድረክ ተከትሎ ነው።

በዚህም መሰረት ማንኛውም የጦር መሳሪያ የታጠቀ አካል ከዛሬ ከጥቅምት 26 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በአካባቢው በሚገኙ የፖሊስ ጣቢያዎች ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ ማንኛውም #መታወቂያ የሚሰጥ አካል አዲስ መታወቂያ መስጠት አልያም የመታወቂያ እድሳት ማካሔድ ክልክል መሆኑ ተገልጿል።

አስቸጋሪ ሁኔታ ቢፈጠር እና መታወቂያ ማግኘት ግዴታ ሆኖ ከተገኘ ግን የክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ እዝ አውቆት ውሳኔ ሊሰጥበት ይችላል ተብሏል።

መረጃው ከደቡብ ክልል ኮሚኒኬሽን ያገኘነው ነው።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 ጀምሮ ይሰጣል።

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል የአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቅያ ፈተና (የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና) ከጥቅምት 29 - ህዳር 2/2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ገልጿል።

የብሄራዊ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናው በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ የሚሰጥ መሆኑን በማወቅ በተረጋጋ ስነ-ልቦና ቅድመ-ዝግጅታቸውን እንዲያደርጉ ኤጀንሲው አሳስቧል።

በሌላ በኩል ፥ አጠቃላይ የፈተናውን ቅድመ ዝግጅት እና አጠቃላይ ሁኔታ በተመለከተ ነገ ቅዳሜ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በኤጀንሲው ተወካይ ዋና ዳይሬክተር በኩል መግለጫ ይሰጣል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA