Facebook ➡️ Meta
ፌስቡክ ኩባንያ ስሙን ወደ ሜታ (Meta) እንደሚቀይር የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ማርክ ዙከርበርግ ዛሬ አሳውቀዋል።
በኩባንያው ስር የሚገኙት ፦
- ፌስቡክ፣
- ዋትስአፕ፣
- ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር የቀደመ ስማቸውን ይዘው ይቀጥላሉ።
ምንጭ፦ The Verge
@ETHIO_TIKVHA

#AGOA : የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አማካሪና ዋና የንግድ ተደራዳሪ ማሞ ምህረቱ ኢትዮጵያ ከAGOA እንድትወጣ ከሚሰሩት መካከል የሕወሃት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች እንዲሁም አንዳንድ አሜሪካ መንግስት ውስጥ ያሉ ሰዎችም እንደሚገኙበት ተናግረዋል።
አቶ ማሞ ይህን ያሉት ከአል ዓይን አማርኛው ክፍል ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ነው።
ኢትዮጵያ ከAGOA እንድትወጣ የሚሰሩት እንነማን እንደሆኑ ? ከዜና ወኪሉ የተጠየቁት የጠ/ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ ፦ አንደኛ የሕወሃት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች እንደሆኑ አመልክተዋል።
እነዚህ ሰዎች የሚከራከሩ ሰዎችን በመቅጠር በአሜሪካ ውስጥ ያሉ የኮንግረንስ ሰዎችን እንዲያሳምኑ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ በይፋ የሚታወቅ ነው ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም አንዳንድ ሰዎች (አሜሪካ መንግስት ውስጥ ያሉ ሰዎችም) እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት ትግራይን አስመከልክቶ ባለው ግጭት ውስጥ የተለያዩ የፖለቲካ ሃሳቦችን፤ የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎቶች እንዲሟሉ በማድረግ AGOAን እንደ አንድ የውጭ ፖሊሲ መሳሪያ አድርጎ የማስቀረት ጉዳይ አለ ሲሉ አቶ ማሞ ተናግረዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ማሞ ፥ " በእኛ እምነት የፖለቲካ ሂደቱን በተመለከተ AGOA ትክክለኛው መሳሪያ ነው ብለን አናምንም፤ ምክንያቱም AGOA ከተነሳ የሚጎዱት በዋነኛነት በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚሰሩ ሰራተኞች ናቸው በተለይ ሴቶች ናቸው የሚጎዱት " ብለዋል።
አክለውም ፥ "አንድ ሀገር የፖለቲካ መሳሪያውን ለማሳካት ሲባል ከጦርነቱ /ከግጭቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ሰዎች መጉዳት ትክክለኛ ነው ብለን አናምንም፡፡ ይህ እንዳይሆንም የበኩላችንን ጥረት እያደረግን ነው" ሲሉ አሳውቀዋል።

#SafaricomEthiopia
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ “አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Home Grown Economic Reform) ምሰሶዎች የሆኑትን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ሥራ ዕድል ፈጠራ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ።
በአዲስ አበባ ለ2 ቀናት በተካሄደው 18ኛው የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን መርሃግብር ላይ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከፍተኛ አመራሮች በዋና ሥራ አስፈጻሚው ሚስተር አንዋር ሱሳ መሪነት በመገኘት የኢትዮጵያን አገራዊ የዲጂታል እድገት ለውጥ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ በንግግራቸው “ወደገበያ ለመግባት እየተዘጋጀንበት ባለበት በዚህ ወሳኝ ምዕራፍ የኢትዮጵያ መንግስት ላደረገልን አበረታች ድጋፍ ላመሰግን እወዳለሁ። በኢትይጵያ ድንቅ አቅም እንዳለ ተመልክተናል። ተጨማሪ የሥራ ዕድሎችን ማመቻቸት፣ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ የዲጂታል ክህሎት ስልጠናዎችን መስጠት እንዲሁም የኢትዮጵያን የዲጂታል 2025 ዕቅድ ከግብ ለማድረስ የሚያስችል ስነምህዳር መገንባትን እንቀጥላለን” ብለዋል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/Safaricom-Ethiopia-10-28

Telegraph
Safaricom Ethiopia
#ETHIOPIA ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ “አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Home Grown Ecoonomic Reform) ምሰሶዎች የሆኑትን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ሥራ ዕድል ፈጠራ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ። በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት በተካሄደው 18ኛው የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን መርሃግብር ላይ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከፍተኛ አመራሮች በዋና ሥራ አስፈጻሚው ሚስተር አንዋር ሱሳ…
#የምርመራ_ሪፖርት
ፍትህ ሚኒስቴር በአማራ ክልል በሰሜን እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እንዲሁም በአፋር ክልል በሚገኙ ወረዳዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ወንጀል ምርመራንና የመጀመሪያ ደረጃ ግኝቶችን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
ምርመራው የተካሄደው በህወሃት ተይዘው በነበሩና በኃላም ነጻ በወጡ አካባቢዎች ነው።
በዚህ መሰረት ህወሓት በሰሜን ጎንደር ዞን ለጊዜው በዝርዝር ማስረጃ የተለዩ፦
- የ96 ሰዎች ሞት
- 53 የአካል ጉዳት
- 29 አስገድዶ መደፈር
- 11 ኢ-ሰብዓዊ አያያዝ
- 6 እገታ እንዲሁም የመንግስት፣ የግልና የሀይማኖት የተለያዩ ተቋማት ንብረቶች ላይ መጠነ ሰፊ ዘረፋና ውደመት ፈፅሟል ሲል ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
በደቡብ ጎንደር ዞን ባሉ አምስት ወረዳዎች በድምሩ፦
- የ129 ሰዎች ሞት
- የ54 ሰዎች የአካል ጉዳት
- በንፋስ መውጫ ከተማ ብቻ የ73 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንዲሁም በርካታ ግለሰቦች ንብረት ላይ ውድመት መድረሱ ተገልጿል።
በአፋር ክልል ነሃሴ 29/2013 ዓ.ም በጋሊኮማ ቀበሌ መጠለያ ጣቢያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት፦
- የ240 ሰዎች ሞት
- 42 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በቀሪዎቹ ሶስት ወረዳዎች ደግሞ የ17 ሰዎች ሞት እና ለ17 ሰዎች የአካል ጉዳት እንዲሁም 7 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ተፈፅሟል።
በሁለቱም ክልሎች በሰላማዊ ዜጎች ንብረት ላይ በመንግስት እና በግል ተቋማት ላይ ዘረፋና ውድመት በስፋት መድረሱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በአጠቃላይ ምርመራው በሂደት ላይ ያለ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
እስከ አሁን በተደረሰበት ግን ሁለቱም ክልሎች በተፈጸሙት የወንጀል ድርጊቶች 482 ሞት፣ 165 የአካል ጉዳት እና 109 የአስገድዶ መድፈር ኢሰብዓዊ ድርጊቶች መፈጸማቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል። #አልዓይን

#AddisAbaba : የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ ክልከላ ወደ ነበረበት መመለሱ ተገለፀ፡፡
በመዲናዋ የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለሱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት በከተማው ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ አየተስተዋለ በመሆኑ የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለስ እንዳስፈለገ ተገልጿል።
በመሆኑም ከጥቅምት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በመመሪያው መሰረት ማንኛውም የጭነት፣ የማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካራች ከማለዳ 12፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት እንዲሁም ከቀኑ 10፡00 እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ እንዲሁም ጭነት መጫንና ማራገፍ እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

#WHO : ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገብረእየሱስ ለዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዋና ዳሬክተርነት ብቸኛ እጩ ሆነው መቅረባቸውን የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ሲጂቲኤን አፍሪካ በሰበር ዜናው ዘግቧል።
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
" ተማሪዎች የምግብ መመረዝ አጋጠማቸው ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው " - የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች የምግብ መመረዝ አጋጥሟቸዋል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብሏል።
ክስተቱ ''ከተማሪዎቹ መካከል ሁለት ተማሪዎች አጥወለወለን ብለው ከወደቁ በኃላ ሌሎችም ተማሪዎች ልጆቹን በማየታቸው የህመም ስሜት ተሰምቷቸዋል" ሲል ከተማ አስተዳደሩ ሁኔታውን አስረድቷል።
የወደቁትንና ሌሎች ተማሪዎችን ጨምሮ ወደ ህክምና በመውሰድ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ተማሪዎቹ የምግብ መመረዝም ሆነ ሌላ ምንም አይነት ህመም ስላልተገኘባቸው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል ሲል ከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።
ከምግብ መመረዝ ጋር የተያያዘ ምንም አይነት ችግር የሌለ በመሆኑ የተማሪ ወላጆች እንዲረጋጉ እና በሀሰተኛ መረጃዎች እንዳይታለሉ ከተማ አስተዳደሩ መልዕክት አስተላልፏል።

#ተጨማሪ
" ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል " ለህክምና 98 ተማሪዎች የመጡ ሲሆን ምርመራ ከተደረገላቸዉ ሴት 47 እና 51 ወንድ በአጠቃላይ 98 ተማሪዎች የመደንገጥና ከመጠነኛ ማስታወክ ስሜት ዉጭ የከፋ ኬዝ አለመኖሩን ነገር ግን ሁለት ተማሪዎች ብቻ መጠነኛ ህመም እንዳጋጠማቸው ሆስፒታሉ አሳውቋል።
ሆስፒታሉ ይህን ያሳወቀው ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ነው።
የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዶክተር ሳምሶን ጉታ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል የዛሬው ክስተት ለከፋ ጉዳት የሚዳርግ አለመሆኑን እና የሞተ ተማሪ አለመኖሩን ገልፀዋል።
ዶ/ር ሳምሶን ወደ ሆስፒታሉ የገቡ ተማሪዎች ምርመራ እየተደረገላቸዉ መሆኑን ሁሉም ተማሪዎች ጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
በምግቡ ላይ የተከሰተዉን ሁኔታ በባለሙያ ጥናት ተደርጎ ይረጋገጣል ፤ ለህብረተሰቡም ይፋ ይደረጋል ያሉ ሲሆን ወላጆች እንዲረጋጉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
በሌላ በኩል ፦
ዶ/ር ሙልጌታ እንዳለ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ፤ 714 ተማሪዎች ወደ ህክምና ማዕከላት ሄደው በተደረገላቸው ምርመራ 7 ተማሪዎች ላይ ከታየ የማስመለስ ምልክት በስተቀር በሌሎቹ ላይ ምንም አይነት ከምግብ መመረዝ ጋር የተገናኘ ችግር አላጋጠመም ብለዋል።
የሰባቱ ተማሪዎች የድምና ሰገራ ናሙና ተወስዶ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንና ውጤቱም እንደታወቀ ለህብረተሰቡ ይገለፃል ሲሉ አሳውቀዋል።

#Update
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊነት ዶ/ር ቴድሮስ ብቸኛ እጩ መሆናቸውን አረጋገጠ።
ከሰዓታት በፊት CGTN Africa ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ብቸኛ እጩ ሆነው መቅረባቸውን ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ መዘገቡ ይታወሳል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፥ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊው ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ለቀጣይ ዙር ብቸኛ ተወዳዳሪ መሆናቸውን አረጋግጧል።
ዶ/ር ቴድሮስ በማመልከቻ ጽሑፋቸው ላይ ኮቪድ-19 ወረርሺኝ ዓለምን ማንኮታኮቱን ገልፀው በሁለተኛ ዙር የሥልጣን ዘመናቸው ዓለማችንን ለመሰል ወረርሺኝ "የምር ዝግጁ" መሆኗን ማረጋገጥ ፍላጎታቸው መሆኑን ገልፀዋል።

ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 9 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,753 የላብራቶሪ ምርመራ 478 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 435 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

#EMA
ከዛሬ ጀምሮ በአገር ውስጥ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የውጭ አገር ፕሮግራሞችን ሊንክ አድርጎ ማስተላለፍ ከዛሬ ጀምሮ መከልከሉን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ እድሪስ አሳውቀዋል።
አቶ መሃመድ ይህ ያሳወቁት ለኢዜአ በሰጡት ቃል ነው።
አቶ መሃመድ ፥ በውጭ አገራት የሚሰሩ የሬዲዮ ጣቢያዎች የሚተላለፉ ፕሮግራሞች የአገር ውስጥ ህግና ስርዓትን ተከትለው አይካሄዱም ብለዋል።
በተጨማሪ የአገሪቷን ፖለቲካዊ ነበራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያላስገቡ ፕሮግራሞችም ሲተላላፉ እንደነበርም አስታውሰዋል።
እነዚህ አካላት በአገር ውስጥ ፈቃድ ያላገኙ በመሆናቸው የሚተላለፉ መርሃ ግብሮችን በመከታተል ግብረ መልስና የማስተካከያ ሃሳብ ለመስጠት የሚቻልበት ሁኔታ አለመኖሩን ገልጸዋል፡፡
በአገር ውስጥ የሚያስተላልፉ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች ፕሮግራሞቹ ላይ የሚያደርጉት ቁጥጥር አነስተኛ መሆኑን አቶ መሃመድ ተናግረዋል።
"በፕሮግራሞቹ የአንዳንድ አገራት አቋም መግለጫ ሲተለለፍ የሚታይበት እና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ግምት ውስጥ ያላስገ ሲሆን ተስተውሏል" ሲሉም አስረድተዋል።
የተጠቀሱትን ሃሳቦች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ባለስልጣኑ ከዛሬ ጀምሮ ከውጭ ሚዲያዎች ወደ አገር ውስጥ የኤፍ ኤም ጣቢያዎች ሊንክ አድርጎ ማስተላለፍን ከልክሏል ሲሉ አሳውቀዋል።
በአገር ውስጥ ፈቃድ ያልተሰጣቸው የውጭ አገር የሬዲዮ ጣቢያዎች ፈቃድ ባላቸው የአገር ውስጥ የኤፍ ኤም ማሰራጫ ጣቢያዎች አማካኝነት ፕሮግራሞቻቸውን ሲያስተላልፉ ቆይተዋል።
Credit : ENA

አቶ ተወልደ ገ/ማርያም የለውጥ አስመዝጋቢ የእውቅና ሽልማትን አሸነፉ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረማርያም፣ የለውጥ አስመዝጋቢ የእውቅና ሽልማትን እንዳሸነፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።
በጥቅምት 17 ቀን 2014 ዓ/ም በአቪየሽን አመራር ስራ አስፈጻሚዎች መድረክ/በአቪየተርስ አፍሪካ ታወር በተዘጋጀው መድረክ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተቋማዊ አመራር ሽልማት ዘርፍ 2021ን የእውቅና ሽልማትንም መቀዳጀታቸውን አየር መንገዱ ገልጿል።

#Somali : የሶማሊ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ የመሩት የሶማሊ ክልል የፀጥታ ኮሚቴ ሳምንታዊውን ስብሰባ ዛሬ አካሂዷል።
በፀጥታ ኮሚቴ ስብሰባው ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የፀጥታ አካላት የተገኙ ሲሆን፣ በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉ ተገልጿል።
ስብሰባው አራት ነጥቦችን በማውጣት የተጠናቀቀ ሲሆን እነዚህም ፦
1ኛ. ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን ትኩረት መስጠት፤
2ኛ. የክልሉን ውስጣዊ ሰላምና ፀጥታ ማጠናከር፤
3ኛ. ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ድንበር በንቃት መጠበቅና ሽብርተኛ ቡድኖች ወደ ክልሉ እንዳይገቡ መከላከል፤
4ኛ. የብሄር ግጭቶችን የሚያነሱ አካላት መከላከል የሚሉት ናቸው።
Credit : SMMA

#Ethiopia : የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ማብራሪያ መስጠታቸውን ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ማምሻውን ዘግቧል።
በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) የከፈተውን ጦርነት እና ጦርነቱን እየመራበት ያለው ህዝባዊ አካሄድ አስመልክቶ ማብራሪያ መስጠታቸውን የገለፀው ቴሌቪዥን ጣቢያው ህዝብ ለመከላከያ ሠራዊቱ ያሳየው ድጋፍ የሚበረታታ እንደነበር አስታውሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ በቅስቀሳ የመጣውን የህዝብ ኃይል ለማስተናገድ በመንግስት በኩል በቂ ዝግጅት እንዳልነበር በዛሬው መድረክ የተናገሩ ሲሆን አሁን ላይ ከዛ ሁኔታ እርምት ተወስዶ ስትራቴጂካዊ በሆነ መልኩ እየተሰራበት እንደሆነ መግለፃቸውን የቴሌቪዥን ጣቢያው ዘገባ ያስረዳል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በወሎ ግንባር በነበረ ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ተሳትፈዋል አሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።
" በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ከአሸባሪው ቡድን ጋር ተሳትፈዋል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጦርነቱ የተሳተፉት እንነዚህ አካላት ኢትዮጵያውያን ያልሆኑና የኢትዮጵያውያን ዝርያ የሌላቸው #ነጮች እና #ጥቁሮች ናቸው ብለዋል ፤ በጦርነቱ ላይ ተሳትፈውም መስዋትነት መክፈላቸውን ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የገጠመችው ጦርነት ከአንድ ወገን ጋር ብቻ እንዳልሆነ በመረዳት ህዝቡ ዋጋ ለመክፈል ያለውን ፍቅር በተግባር ሊገልጽ እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

#US #EU #USEmbassyAA
አሜሪካ በድጋሚ ተኩስ እንዲቆምና ድርድር እንዲጀመር ጠየቀች (ይህን ስትል በዚህ ሳምንት ብቻ ሁለተኛዋ ነው)
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን በሰሜን ኢትዮጵያ የቀጠለው ጦርነት አሜሪካን እጅግ እንዳሳሰባት አሳውቀዋል።
ብሊንከን ጦርነቱ በስፋት መዛመቱ ሰብዓዊ ቀውሱን እንደሚያከፋው ጠቁመዋል።
ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በድርድር ላይ የተመሠረተ ተኩስ አቁም እንዲያደርጉም በመግለጫቸው ላይ አሳስበዋል።
ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተጨማሪ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነር ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ሁሉም ወገኖች ያለ ቅድመ ሁኔታ ተኩስ እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።
ሁሉም ወገኖች የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቱን እንዲያቀላጥፉ እና የጥላቻ ንግግሮችን እንዲያቆሙም አሳስበዋል።
የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ኅብረት ልዩ ልዑክ ኦሌሴጎን ኦባሳንጆ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉ ህብረቱ እምነቱን ገልጿል።
በሌላ መረጃ ፦
አዲስ አበባ ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ በሰሜን ኢትዬጵያ ያለውን ሁኔታ እየተከታተለ እንደሚገኝ ገልጿል።
በአማራ ክልል፤ ደሴና ኮምቦልቻን ጨምሮ ግጭት ተባብሷል ብሏል። በሚፈጠርባቸው አካባቢዎች ካሉም ለመጠለል መዘጋጀት እንዳለባቸውና እነዚህን አካባቢዎች መልቀቅ ሊያስቡበት እንደሚገባ አብቆ አሳስቧል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 8 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,296 የላብራቶሪ ምርመራ 205 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 414 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

ደሴ እና ኮምቦልቻ ?
የራሷን ነዋሪዎች ጨምራ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የጦርነት ሰለባ የሆኑ ተፈናቃዮችን አቅፋ በያዘችው ደሴ የስልክ ግንኙነት ከተቋረጠ ቀናት ተቆጥሯል፤ ይህም በአካባቢው ስላለው ውቅታዊ ሁኔታ ለመረዳት አዳጋች አድርጎታል።
ከአካባቢ ለቀው የወጡ አባላት መጠነኛ መረጃን ያካፈሉ ሲሆን በከተማው ወንጀል በከፍተኛ ደረጃ መበራከቱን፣ ኃይለኛ የንብረት ዘረፋም እንዳለ ጠቁመዋል።
የከተማው ነዋሪዎች ሁኔታ እጅጉን እንዳሳሰባቸው የገለፁ ሲሆን በተለይ ደግሞ ከፍተኛ ተፈናቃዮች በመጠለላቸው በፊትም እጥረት የነበረበት የመሰረታዊ አቅርቦት ችግር አሁን ላይ ተባብሶ የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ሊፈጥር እንደሚችል በብርቱ አሳስበዋል።
ደሴ በጦርነት የተፈናቀሉ ወላዶች፣ ህፃትናት፣ ነፍሰጡሮችን፣ አቅመ ደካሞችን አቅፋ አስጠልላላች።
በተጨማሪ በርካቶች በኔትዎርክ መቋረጥ የቤተሰቦቻቸውን ደህንነት ለማወቅ አልቻሉም።
በኮምቦልቻ በተመሳሳይ ዝርፊያ እየተፈፀመ መሆን ለመረዳት ተችሏል፤ ሁለቱ ከተሞች ያሉበት ቀጠና አሁንም በግጭት ውስጥ መሆኑን ለማውቅ ተችሏል፤ እንደከዚህ ቀደሞቹ አካባቢዎች በግንኙነት መቋረጥ ምክንያት መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ አሁንም ለመረዳት አስቸጋሪ እንደሆነ ቀጥሏል።
በጦርነት ቀጠና ውስጥ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ግን ለበርካታ ወራት እጅግ የከፋ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለት 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ይካሄዳል።
ምክር ቤቱ በስብሰባው ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ያፀድቃል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላት ለመሰየም የሚቀርበውን የውሳኔ ሃሳብ በመመርመር ያፀድቃል።

" ... ከ5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስገልገዋል " - የአማራ ክልል መንግስት
የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስታና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ፥ በክልሉ ህወሓት ወረራ በፈፀመባቸው ዞኖች ማለትም ፦
- ሰሜን ወሎ
- ደቡብ ወሎ
- ከፊል ደቡብ ጎንደር
- ዋግኽምራ ውስጥ የሚኖሩ እና ተፈናቅለው ያሉትን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል አሳውቋል።
ህወሓት በከፈተው ጦርነት ከ991 ሺ በላይ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን በወረራ በተያዙ አካባቢዎች ደግሞ ከ5 ሚሊዮን ህዝብ በላይ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፤ እነዚህ ነዋሪዎች ለምግብ እጦት ፣ የመጠጥ ውሃ እና የመድሃኒት እጦት ችግር ተጋልጠዋል።
በሰሜን ወሎ ሜቄት አካባቢ ብቻ በህክምና እጦት 90 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ በተመሳሳይ የወለሊድ አገልግሎት ባለመኖሩ ምክንያት 13 እናቶች ሞተዋል።
በጋዝጊብላና በዝቋላ አካባቢ በመድሃኒት እጥረት ፣ በምግብ እጦት 13 ሰዎች ሞተዋል።
በአጠቃላይ በወረራ ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች ቤታቸውን እንደዘጉ በምግብ እና በመድሃኒት እጦት ሞተው የሚገኙበት ሁኔታ ነው እየተፈጠረ ያለው።
ከላይ የተገለፀው ቁጥር ሙሉ አይደለም ፤ ከዚህ በጣም ሊጨምር ይችላል፤ በየአካባቢው የመንግስት መዋቅር በመፍረሱ በምግብ እና በህክምና እጦት የሞቱ አጠቃላይ ሰዎችን ቁጥር ማወቅ አልተቻለም።