ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 15 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,341 የላብራቶሪ ምርመራ 327 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 420 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily
@ETHIO_TIKVHA

#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ተጨማሪ አዳዲስ የደንብ ልብሶችን ስራ ላይ ማዋሉን ዛሬ አሳውቋል።
ነባሩን የደንብ ልብስ መጠቀም ማቆሙን ተቋሙ ገልጿል፡፡
ከዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ አዳዲሶቹ የደንብ አልባሳትን ብቻ መጠቀም እንደሚገባ እና ነባሩ የደንብ ልብስ ሙሉ በሙሉ መቀየሩ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ አሮጌውን የደንብ ልብስ ለብሶ የተገኘ አመራር እና አባል ላይ ጠንከር ያለ የዲስፕሊን እርምጃ ይወሰድበታል ተብሏል።
ህብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካላት አሮጌው የደንብ ልብስ ሙሉ በሙሉ በአዳዲሶቹ መቀየሩን ተገንዝበው አሮጌውን የደንብ ልብስ የለበሰ የፖሊስ አባል ሲያጋጥማቸው መረጃ በመስጠት እንዲተባበሩ ጥሪ ቀርቧል።
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ፖሊስ ስራ ላይ ካዋላቸው አዳዲስ የደንብ አልባሳት ጋር ወይም ከሌሎች የፀጥታ አካላት የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ዩኒፎርም መጠቀም ክልክል መሆኑ በህግ የተደገገ ስለሆነ ከአ/አ ፖሊስ የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ዩኒፎርም የሚጠቀሙ አካላት ማስተካከያ እንዲያደርጉ ተቋሙ መልዕክቱን አስተላልፏል።
#AddisAbabaPolice
#Share #ሼር

#ETHIOPIA
ማንኛውም የፀጥታ ችግር እንቅስቃሴ ሲመለከቱ ወይም ደግሞ ጥቆማ ለመስጠት ከፈለጉ ከላይ በተቀመጡት የስልክ መስመሮች ፈጥነው እንዲደውሉ የፌዴራል ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።
#ሼር #Share

በእጃቹ ያለውን መሳሪያ እስከ ጥቅምት 27 / 2014 ደረስ ማስመዝገብ ትችላላችሁ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ በተለያዩ ምክንያቶች የጦር መሳሪያ ምዝገባው እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2014 ዓ/ም በድጋሚ መራዘሙን አሳውቋል።
የጦር መሳሪያ በእጁ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ በአስራ አንዱ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያዎችና በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች በግንባር በመገኘት እንዲያስመዘግብ መልዕክት መተላለፉን ተከትሎ በርካታ ግለሰቦች በእጃቸው ላይ የሚገኝን የጦር መሳሪያ ለተከታታይ 3 ቀናት ማስመዝገባቸው ተገልጿል።
መሳሪያ በእጃቸው ላይ ያለ ሰዎች የማስመዝገብ ፍላጎቱ እያላቸው የምዝገባ ቀኑ በማጠሩ ፣ ያላቸውን የጦር መሳሪያ ሌላ ቦታ በማስቀመጣቸው እና ማስመዝገብ እንደሚቻል በቂ መረጃ ያልሰሙ ግለሰቦች በመኖራቸው ምክንያት ምዝገባው እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2014 ዓ/ም መራዘሙ ተገልጿል።
በእጁ ላይ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ያላስመዘገበ ማንኛውም ግለሰብ የተጨመረውን ቀን ተጠቅሞ እንዲያስመዘግብ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።

#SNNPRS
በደቡብ ክልል መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በ5 ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግብ ጥሪ ቀረበ።
ይህ ጥሪ የተላለፈው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ትናንት ያካሔዱትን ውይይት መድረክ ተከትሎ ነው።
በዚህም መሰረት ማንኛውም የጦር መሳሪያ የታጠቀ አካል ከዛሬ ከጥቅምት 26 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በአካባቢው በሚገኙ የፖሊስ ጣቢያዎች ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪ ማንኛውም #መታወቂያ የሚሰጥ አካል አዲስ መታወቂያ መስጠት አልያም የመታወቂያ እድሳት ማካሔድ ክልክል መሆኑ ተገልጿል።
አስቸጋሪ ሁኔታ ቢፈጠር እና መታወቂያ ማግኘት ግዴታ ሆኖ ከተገኘ ግን የክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ እዝ አውቆት ውሳኔ ሊሰጥበት ይችላል ተብሏል።
መረጃው ከደቡብ ክልል ኮሚኒኬሽን ያገኘነው ነው።

የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 ጀምሮ ይሰጣል።
የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል የአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቅያ ፈተና (የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና) ከጥቅምት 29 - ህዳር 2/2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ገልጿል።
የብሄራዊ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናው በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ የሚሰጥ መሆኑን በማወቅ በተረጋጋ ስነ-ልቦና ቅድመ-ዝግጅታቸውን እንዲያደርጉ ኤጀንሲው አሳስቧል።
በሌላ በኩል ፥ አጠቃላይ የፈተናውን ቅድመ ዝግጅት እና አጠቃላይ ሁኔታ በተመለከተ ነገ ቅዳሜ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በኤጀንሲው ተወካይ ዋና ዳይሬክተር በኩል መግለጫ ይሰጣል።

የቀድሞ ሰራዊት አባላት ጥሪ ተደረገላቸው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ፥ ለቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ሰራዊቱን እንዲቀላቀሉ በዛሬው ዕለት ጥሪ አቀረበ።
የመከላከያ ሰራዊት ባወጣው ጥሪ ፥ " በሀገራችን እየተደረገ ያለውን ሃገርን የማፍረስ ሴራን በማክሸፍ አገርን የማዳን ዘመቻ ላይ ባላቸው እውቀት ልምድ እና አቅም ከአገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ ይህ አፍራሽ ሃይል እስኪደመሰስ ድረስ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ባላቸው ተነሳሽነት ከሀገር መከላከያ ጎን በመቆም አቅማቸውና እውቀታቸው የፈቀደውን አስዋፅኦ ለማበርከት ጥያቄ አቅርበዋል " ብሏል።
በዚሁ መሠረት ይህን ተልዕኮ መወጣት የሚያስችል አካላዊ ሁኔታ ፣ የጤና ፣ የስነ - አእምሮ ዝግጁነት ፣ እውቀትና ልምድ ያላቸውን አባላት የወጣውን መስፈርት የሚያሟሉ የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ሰራዊቱን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት የሀገር መከላከያን እንዲቀላቀሉ ለቀረበው ጥሪ ሊያሟሉ ይገባቸዋል የተባሉት አጠቃላይ መስፈርቶች ዝርዝር ከላይ በምስሉ ተያይዟል።