TIKVAH-ETHIO
702 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
ብ/ጄኔራል ኃይሌ መለሰ ተሰማ ፦

- በድሮው አስተዳደራዊ አወቃቀር በደብረ ታቦር አውራጃ በፋርጣ ወረዳ ጥር 28 /1933 ዓ/ም ነበር የተወለዱት።

- እስከ ጄነራልነይ ማዕረግ ያደረሳቸውን ህይወታቸውን በውትድርና የጀመሩት በ1960 ዓ/ም ነበር።

- በሶማሊያ ወረራ ወቅት የ69ኛውን ሚሊሻ ብርጌድ በማሰልጠን በግንባርም አዋጊ ሆነው በመምራት ታላላቅ ጀብዶችን ለሀገራቸው የፈፀሙ ነበሩ።

- መስከረም 1970 ዓ/ም ላይ በድሬዳዋ ግንባር ወደውጊያ የገቡ ሲሆን ካራማራ፣ ጅግጅጋ፣ ደጋሀቡር እና ቀብሪደሃር (መጋቢት 1/1970) ከሶማሊያ ጦር ወረራ ነፃ አውጥተው በመቆጣጠር የምስራቁን ግንባር ጦርነት በድል እንዲጠናቀቅ ያደረገውን ብርጌድ መርተዋል።

- ከወታደራዊ ስራቸው ተጨማሪ የተለያዩ የኢትዮጵያ ክ/ሀገሮችን አስተዳድረዋል።

- የፌዴራል መንግስት ተቋማትን መርተዋል።

- ለሀገራዊ አገልግሎታቸው የህበረተሰባዊ ኢትዮጵያ ታላቅ የክብር ኮከብ ኒሻን እና የየካቲት 66 አብዮት ኒሻን እና ሌሎች ሽልማቶችን አግኝተዋል።

- ባለትዳር እና የ7 ልጆች አባት ነበሩ።

#አሚኮ

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ዙሪያ እየመከረ ነው።

በመድረኩ ላይ ትላንት የተጠናቀቀውን የመራጮች ምዝገባ በተመለከተ ጊዜያዊ መረጃ ተሰጥቷል።

በዚህ መሰረት ፦

- እስከ ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ያ36 ሚሊዮን 245 ሺህ 444 ሰዎች የምርጫ ካርድ ወስደዋል።

- ምርጫ ካርድ ከወሰዱት ውስጥ 16.6 ሚሊዮኑ ሴት ፤ 19.5 ሚሊዮኑ ወንድ ናቸው፡፡

- 50 ሚሊዬን ዜጎች ካርድ ሊወስዱ እንደሚችሉ ተገምቶ ነበር፡፡ አሁን ያለው ካርድ የወሰዱ ዜጎች ቁጥሩ የግምቱን 78 በመቶ ይሸፍናል።

- ጋምቤላ፣ አዲስ አበባ፣ ሶማሌ እና አፋር ክልሎች ከተገመተው በላይ የመራጮች ካርድ የተወሰደባቸው ናቸው።

- በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአንጻራዊነት ዝቅተኛ የመራጮች ምዝገባ የተከናወነበት ክልል ነው።

በዝርዝር ስንመለከተው ፦

• በአዲስ አበባ ከ1.4 ሚሊዬን፣
• በአፋር ከ1.7 ሚሊዬን፣
• በአማራ ከ5.9 ሚሊዬን፣
• በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ174 ሺ፣
• በጋምቤላ ከ326 ሺ፣
• በኦሮሚያ ከ15.9 ሚሊዬን፣
• በሃረር ከ135 ሺ፣
• በድሬዳዋ ከ177 ሺ፣
• በደቡብ ብ/ብ/ህ ከ4.8 ሚሊዬን፣
• በሲዳማ ከ1.5 ሚሊዬን እና በሶማሌ ከ3.9 ሚሊዬን በላይ መራጮች ካርድ መውሰዳቸውን ምርጫ ቦርድ አሳውቋል። (አል ዓይን)

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#BREAKING

6ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በተያዘለት ቀን እንደማይካሄድ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ ይህ ያሳወቀው ዛሬ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየመከረ ባለበት መድረክ ላይ ነው።

ምርጫው ግንቦት 28 ይካሄዳል ተብሎ ነበር።

የምርጫ ካርድ ምዝገባውና ሌሎች ስራዎች በተያዘላቸው ቀናት ባለመጠናቀቃቸው ምርጫው በተያዘለት ቀን አይካሄድም ተብሏል።

ምርጫ ቦርድ ድምጽ መስጫው ቀን በ3 ሳምንት እንዲራዘም ፓርቲዎችን መጠየቁን አል ዓይን ዘግቧል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
የሙያ ብቃት ምዘና የተፈተኑ የጤና ሳይንስ ምሩቃኖች ጉዳይ ፦

በ2013 ዓ.ም. ከተለያዩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጤና ሳይንስ ተመርቀው የሙያ ብቃት ምዘና የወሰዱ ምሩቃኖች የትምህርት ማስረጃቸው ትክክለኛነት እንዲረጋገጥ ዝርዝራቸው ከጤና ሚኒስቴር ወደ ከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ተልኳል፡፡

ይህ የተደረገበት ምክንያት የትምህርት ማስረጃቸው ህጋዊነትና ትክክለኛነት በኤጀንሲው ሳይረጋገጡ የሙያ ብቃት ምዘና የወሰዱ ምሩቃኖች በመኖራቸው የማጣራትና የማረጋገጥ ስራን ለማከናወን መሆኑ ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የብቃት ምዘና የወሰዱ በርካታ የጤና ባለሙያዎች በኦንላይን(በኢንተርኔት) ውጤታቸውን ለማየት ጥረት እያደረጉ ሲሆን የሙያ ብቃት ምዘና ውጤታቸውን ሊያዩ የሚችሉት የትምህርት ማስረጃቸው ትክክለኛነት ከተረጋገጠ በኋላ መሆኑን ተገልጿል።

* ተጨማሪ ከላይ የተያያዘው ደብዳቤ ያንብቡ !

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
የድምፅ መስጫ ቀን ማራዘም ያስፈለገው ለምንድነው ?

ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተካሄደ በሚገኘው የምክክር መድረክ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቀን ሊራዘም እንደሚችል አስታውቋል።

ቦርዱ የምርጫው ጊዜ ቀድም ብሎ ከተያዘለት ጊዜ እስከ 3 ሳምንት በሚደርስ ጊዜ ነው እንደሚራዘም የገለፀው።

ምክንያት ብሎ ያቀረበው ፦

- የድምፅ መስጫ ወረቀት ህትመት የወሰደው ጊዜ በመኖሩ ፤ ውጭ ሀገር የሚታተመው ወረቀት የሚገባበት ጊዜ ሂደቱን ሊያጓትት ስለሚችል (በመጪው 15 ቀን መጨረሻ ነው ይገባል ተብሎ የሚጠበቀው)

- የመራጮች ምዝገባ የወሰደው ተጨማሪ ጊዜ በመኖሩ

- ለቁሳቁስ ማጓጓዣ በቂ ጊዜ ስለሚያስፈልግ

- በአንድ ምርጫ ጣቢያ 3 የነበሩትን የምርጫ አስፈፃሚዎች መጨመር ስለሚያስፈልግ ለነሱ ስልጠና መስጠት ጊዜ ስለሚወስድ ይህን ለማስተካከል ነው የምርጫው ጊዜ እንዲራዘም ያለው።

ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚያደርገው ምክክር አሁንም የቀጠለ ሲሆን የሚደረስበትን ድምዳሜ ተከታትለን እናሳውቃለን።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
"...ድምጽ አሰጣጡ በተመሳሳይ ቀን እንዲሆን የተወሰነው ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤትና ከፓርቲዎች በቀረበ ጥያቄ ነው" - ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ

የ6ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ በሁሉም አካባቢዎች በአንድ ቀን እንዲካሄድ መወሰኑን በተመለከተ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በዛሬው መድረክ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ቀደም ሲል የአገራዊ ምርጫው የድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 ቀን 2013 እንደሚሆን የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለት እንደነበር አስታውሰዋል።

ነገግ ግን ቦርዱ የድምጽ መስጫው ቀን በመላ አገሪቱ በተመሳሳይ ቀን እንዲካሄድ መወሰኑን በይፋ አሳውቀዋል።

ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ፥ የድምጽ አሰጣጡ በተመሳሳይ ቀን እንዲሆን ከውሳኔ የተደረሰው ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትና ከፓርቲዎች በቀረበው ጥያቄ መሰረት መሆኑን አስረድተዋል።

#ENA
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ለተሰንበት_ግደይ

ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ሄንግሎ ላይ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ አትሌቶቿን ለይታለች።

የሄንግሎ የዕለቱ መርሐ ግብር የመጨረሻ ውድድር የነበረው ደግሞ የሴቶች 10,000 ሜትር ውድድር ነበር።

በሴቶች 10 ሺህ ሜትር በተካሄደ ውድድር ለተሰንበት ግደይ ድንቅ ብቃቷን በማሳየት ውድድሯን 29:01.03 በሆነ ደቂቃ በመግባት በበላይነት አጠናቃለች።

ለተሰንበት ግደይ ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ እንደምትወክል ከማረጋገጡ ባለፈ ሪከርዱን የግሏ ማድረግ ችላለች ።

በውድድሩ ከቀናት በፊት በሲፋን ሀሰን የተሰበረውን የ 10,000 ሜትር ሪከርድ ቀናቶች ሳይቆጠሩ ሪከርዱ በኢትዮጵያ ስር እንዲሆን አድርጋለች።

ቲክቫህ ስፖርት t.me/joinchat/VvwzStMNcNHmhK0x

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#LetesenbetGidey

የዓለም የ10,000 ሜትር የሴቶች ሪከርድ ወደ ሀገሩ ተመልሷል - ለተሰንበት ግደይ 29:01.03

#ETHIOPIA

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#LetesenbetGidey

ከ 249 ቀናት በፊት የ 5,000 ሜትር ሪከርድን የግሏ ማድረግ የቻለችው ለተሰንበት ግደይ ዛሬ ከስምንት ወራት ቆይታ በኋላ ሌላ ደማቅ ታሪክን ፅፋለች።

የሳምንታት እድሜ በቀረው የቶኪዮ ኦሎምፒክ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ከሲፋን ሀሰን ጋር የምታደርገው ውድድር ከወዲሁ በጉጉት ይጠበቃል።

ቲክቫህ ስፖርት : t.me/joinchat/VvwzStMNcNHmhK0x

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#ምርጫ2013

የቁሳቁስ ስርጭትን በተመለከተ በተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ላይ ሰማያዊ ሳጥኖች ተከፍተው መገኘታቸውን ምርጫ ቦርድ አሳወቀ።

ሳጥኖቹን ከፍተው የተገኙበት ምርጫ ክልሎች ላይ አንዳንዶቹ ወደወንጀል ምርመራ ሲላኩ አንዳንዶቹ #ምርጫ_እንዳይካሄድ ተወስኖባቸዋል።

- ደንቢያ የምርጫ ክልል ሰማያዊ ሳጥኖቹ ተከፍተው ፤ ውስጣቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን የሚያሳየው የቡክሌት ተከፍቶ ውስጡ ያለውን ነገር አይተው ተገኝቷል፤ በዚህ ምክንያት 3 አስፈፃሚዎች ላይ ምርመራ እንዲደረግ ለፌዴራል ፖሊስ ደብዳቤ ተፅፏል።

ደምቢያ ምርጫ ክልል የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶችን መነካካት ፣ መክፈት በጥብቅ የተከለከለ የወንጀል ተግባር በመሆኑን አስፈፃሚዎች ምርመራ እንዲደረግባቸው ተልኳል።

በደምቢያ ምርጫ ክልል ምርጫው #አይካሄድም

- ተውለደሬ 1 እና 2 ሰማያዊ ሳጥን ተከፍቶ ውስጡ ያሉእጩዎች እነማን እንደሆኑ ፣ የድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ ያሉትን እጩዎች የማየት (ፓርቲዎች ቅሬታ አለን ስላሉ ነው እዩ ተብለን ነው) በሚል ተክፍቶ ታይቷል።

በዚህ ምክንያት ተውለደሬ 1 እና 2 ነገ ድምፅ አይሰጥም፤ ታግዷል።

- ግንደበረት (ኦሮሚያ) ነገ ድምፅ #አይሰጥም ፦ ድምፅ የማይሰጥበት ምክንያት የድምፅ መስጫ ወረቀት እና ቁሳቁስ ስለተከፈተ ሳይሆን የአስፈፃሚዎች እጥረት ነበር። ከዚህ ውጭ ግን ወረዳው አስፈፃሚዎችን አሰልጥኖ ለማስፈፀም ለማሰማራት ሲል በመገኘቱ ገንደበረት ላይ ድምፅ አይሰጥም።

- ነገሌ ምርጫ ክልል (ጉጂ-ኦሮሚያ) ፦ በምርጫ ክልሉ የሚወዳደር የግል ተወዳዳሪ በምርጫ መስጫ ወረቀቱ ላይ ዝርዝሩ ባለመካተቱ ባቀረበው ቅሬታ መሰረት ቦርዱ ምርጫውን ወደ ጳጉሜ 1 አዛውሮታል።

#TikvahEthiopia #SolianaShimeles

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ ሳጥን ተከፍቶ ውስጡ ያለው የድምጽ መስጫ ወረቀት ማሸጊያው ባለመከፈቱ ምክንያት የምርጫ ሂደቱ እንዲቀጥል የተወሰነባቸው የምርጫ ክልሎች ስለመኖራቸው አሳውቋል።

እነዚህም ፦

• ስንቄ 1 እና 2 የምርጫ ቁሳቁስ ሳጥኑ (ሰማያዊ ሳጥን) ወድቆ በመሰበሩ የተወዳዳሪ ፖርቲዎች ወኪል ባሉበት ቃለጉባኤ ተይዞ የድምፅ መስጫ ወረቀቱ የታሸገው ባለመከፈቱ ምርጫው እንዲካሄድ ተወስኗል።

ይህ ምርጫ ጣቢያ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሚወዳደሩበት ነው።

• መተማ ላይ የምርጫ ቁሳቁስ መያዣ ሳጥኑ (ሰማያዊ ሳጥኑ) ቢነካካም የድምጽ መስጫ ወረቀቶቹ ማሸጊያ ባለመከፈቱ ምርጫው እንዲቀጥል ቦርዱ ወስኗል።

#SolianShimeles #TikvahEthiopia #TikvahFamily

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#ማስጠንቀቂያ

የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ታሽጎ የሚሄድበትን ሳጥን ፦
- መክፈት
- ማንቀሳቀስ
- መቁረጥ
- ውስጡን ማየት ከፍተኛ የሆነ #ወንጀል ነው።

ምርጫ ቦርድ ለሁሉም ምርጫ አስፈፃሚዎች፣ ወረዳ ላይ ያሉ ዝቅተኛ እርከን ላይ የሚሰሩ የመንግስት አካላት (ይከፈት እንየው የሚሉ) በሙሉ ከፍተኛ #ማስጠንቀቂያ ሠጥቷል።

በማንኛውም ሁኔታ በምርጫ ክልሎች ላይ ችግር ተፈጥሮ ከተገኘ ወደድጋሚ ምርጫ እንደሚሄድ መታወቅ አለበት ብሏል ቦርዱ ፤ አክሎም የድጋሚ ምርጫ ለሀገር ሃብት ጠቃሚ ስላልሆነ፣ ቦርዱም ብዙ ገንዘብ ስለሚያባክን ከድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ጋር በተገናኘ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል።

#TikvahEthiopia #TikvahFamily

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
Audio
AudioLab
#ሀሰተኛ_መረጃ_እና_ምርጫ2013

"የምርጫ ወቅት ላይ ስለሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እና እንዴት እነዚህን ሀሰተኛ መረጃዎችን መከላከል እንችላለን" በሚለው ጉዳይ ዛሬ በቀጥታ Voice Chat ለቲክቫህ ቤተሰቦች ገለፃ ተደርጓል/ለጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቷል።

ገለፃና ለጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ከCARD በፍቃዱ ኃይሉ ፤ ከኢትዮጵያ ቼክ ደግሞ ኤልያስ መሰረት ነበሩ።

ምናልባት በቀጥታ በVoice Chat ገለፃውን ማዳመጥ ሳትችሉ የቀራችሁ ቤተሰቦቻችን ከላይ የድምፅ ቅጂው ተያይዟል፤ አዳምጡት።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
የነገ ምርጫ/የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን በተመለከተ ያሉት ሂደቶች ፦

- አንድ መራጭ የመራጮች ምዝገባ ካርዱና ለመራጮች ምዝገባ ያካሄደበትን መታወቂያ መያዝ አለበት።

- መራጩ ምርጫ ጣቢያ በደረሰበት ወቅት ሰልፍ ካለ መሰለፍ ይኖርበታል።

- በሰልፉ ላይ ምንም አይነት ቅደም ተከተል (በስም ፣ በፊደል ወይም በምርጫ ካርድ...) የለም።

- የሰልፍ ርቀት የሚያስጠብቁ፣ ሰልፉን ሁኔታ የሚያስተካከሉ አካላት የሚሉትን ማዳመጥ ይኖርበታል።

- መራጩ ተሰልፎ ተራው ሲደርስ ወደውስጥ ገብቶ መዝገቡ ላይ ስሙ መኖሩ ተረጋግጦ የድምፅ መስጫ ወረቀት ይሰጠዋል።

- የድምፅ መስጫ ወረቀት ሲሰጠው እጁ ላይ የቀለም ምልክት ይደረግበታል።

- በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚመርጠውን እጩ የሚመርጥበት የተሸፈነ ወይም ደግሞ የተከለለ (የድምፅ አሰጣጥ መከለያ) አለ እዛ ገብቶ ድምፁን ይሰጣል፤ መራጩ ተመልሶ ሲወጣ ባሉት ሳጥኖች ወስጥ ድምፁን ይከታል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Attention

በድምጽ መስጫ ቀን የተከለከሉ ተግባራት ምን ምን ናቸው ?

• ማንኛውም ሰው ከምርጫ ጣቢያው 200 ሜትር ዙሪያ መለስ ርቀት ውስጥ በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ፣ የጦር መሣሪያ ይዞ ወይም በሌላ በማናቸውም ፀጥታን በሚያደፈርስ ሁኔታ ውስጥ መገኘት የለበትም

• መራጭ ያልሆኑና ድምፅ የሰጡ ሰዎች በምርጫ ጣቢያው ውስጥ መገኘት የለባቸውም

• ማንኛውም ሰው ያለፈቃድ ወደምርጫ ጣቢያው በመግባት / በምርጫ ጣቢያው ግቢ ውስጥም ሆነ ውጭ የምርጫውን እንቅስቃሴ ማወክ ወይም ማደናቀፍ ወይም ምንም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ እንቅስቃሴ ማድረግ የለበትም

ወደ ምርጫ ጣቢያ የማይገቡ ነገሮች ምንድናቸው?

• ማንኛውም ሰው እንደ በራሪ ወረቀት፣ ፖስተር እና በሌሎች አጭር ጽሁፍ መልክ የተዘጋጁ የምርጫ ቅስቀሳ ሰነዶችን ይዞ ወደ ምርጫ ጣቢያው መግባት አይችልም፡፡

• ማንኛውም ሰው የጦር መሳሪያ ወይም እንደጩቤ እንደ ሴንጢ የመሳሰሉ ስለትነት ያላቸውን ወይም እንደየአካባቢው ሁኔታ ለሀይል መጠቀሚያነት የሚውሉ እንደዱላ ፣ አለንጋ ፣ ቁራጭ እንጨት ወይም ብረት ወይም ሌላ ማንኛውንም ተቀጣጣይ ወይም የሚፈነዳ ጠጣር ወይም ፈሳሽ ነገር ይዞ ወደ ምርጫ ጣቢያ መግባት የለበትም።

• ከላይ የተዘረዘሩትን የተከለከሉ ነገሮች ወደምርጫ ጣቢያ ይዞ የመጣ መራጭ የምርጫ ጣቢያው የሰልፍ አስከባሪ በሚሰጠው መመሪያ መሰረት በአደራ አስቀምጦ መግባት አለበት።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#ምርጫ2013

ኢትዮጵያ 6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ማካሄድ ጀመረች።

ዛሬ ምርጫ በሚካሄድባቸውን የምርጫ ጣቢያዎች ከማለዳው 12:00 ጀምሮ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ጀምሯል።

ከተለያዩ ከተሞች የወጡ ፎቶዎችን መመልከት እንደቻልነው ፥ ህዝቡ በለሊት ተነስቶ ድምፁን ለመስጠት ሰልፍ ይዟል።

ወደ በኃላ ምርጫውን ተንቀሳቅሰው ለመመልከት ፍቃድ ያገኙ የቲክቫህ አባላት በየምርጫ ጣብያው በመገኘት ያለውን ሁኔታ በቀጥታ በVoice Chat በቀጥታ ያሳውቃሉ።

Photo Credit : AAPS

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#ምርጫ2013

ኢትዮጵያ 6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ማካሄድ ጀመረች።

ዛሬ ምርጫ በሚካሄድባቸውን የምርጫ ጣቢያዎች ከማለዳው 12:00 ጀምሮ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ጀምሯል።

ከተለያዩ ከተሞች የወጡ ፎቶዎችን መመልከት እንደቻልነው ፥ ህዝቡ በለሊት ተነስቶ ድምፁን ለመስጠት ሰልፍ ይዟል።

ወደ በኃላ ምርጫውን ተንቀሳቅሰው ለመመልከት ፍቃድ ያገኙ የቲክቫህ አባላት በየምርጫ ጣብያው በመገኘት ያለውን ሁኔታ በቀጥታ በVoice Chat በቀጥታ ያሳውቃሉ።

Photo Credit : AAPS

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
የፖሊስ ሪፖርት :

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በአገር አቀፍ ደረጃ እስከአሁን ባሰባሰበው መረጃ መራጩ ህዝብ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላማዊና በተረጋጋ መንገድ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል።

በቀጣይ ተመሳሳይ መረጃ ከፌዴራል ፣ ከክልልና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እያሰባሰበ ተአማኒነት ያለው መረጃ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ፎቶ : ይህ አ/አ አያት ዞን ሁለት የሚገኝ ምርጫ ጣቢያ ነው። መራጩ ዜጋ ከጥዋት ጀምሮ ተሰልፏል፤ ሰልፉ ግን የሚጠበቀውን ያህል ንቅንቅ አላለም።

ሌሎችም ጣቢያዎች ላይ ቀደም ብለን እንዳሳወቅነው ተመሳሳይ ሁኔታ ይታያል፤ ይህ ሁናቴ መራጩን ዜጋ እያሰላቸ ነው #መፍትሄ ይፈልጋል።

(የቲክቫህ አባላት)

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#ምርጫ2013

(ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ/ም)

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከደቂቃዎች በኃላ በዛሬው ቀን ስላለው የምርጫ እንቅስቃሴ የመጀመሪያ ዙር መግለጫ ይሰጣል።

መግለጫውን የሚከታተሉ የቤተሰባችን አባላት በቦታው ተገኝተዋል።

ውድ አባላት በመግለጫው ላይ የሚነሱትን ዋና ዋና ጉዳዮችን የምንልክላችሁ ይሆናል።

ከዚህ ባለፈ በቀጥታ መግለጫውን በ Voice Chat መከታተል እንደምትችሉ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
መግለጫ
TIKVAH-ETHIOPIA
#መግለጫ1

ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከደቂቃዎች በፊት የሰጡትን መግለጫ በቀጥታ በVoice Chat ላይ ማዳመጥ ላልቻላችሁ እና ላመለጣችሁ የድምፅ ቅጂው ከላይ ተያይዟል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA