TIKVAH-ETHIO
702 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
#NEBE

ነገ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጪውን ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ እንደሚያደርግ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በድረገፁ ዘግቧል።

ምርጫ ቦርድ በምርጫ የጊዜ ሰሌዳው ላይ ከ47 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ለመምከር ነገ በአዲስ አበባ ስብሰባ ጠርቷል።

በነገው ምክክር መድረክ ላይ ዝርዝር የምርጫ ክንውኖችን የያዘ የጊዜ ሰሌዳ ለፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚቀርብ የቦርዱ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሶልያና ሽመልስ ተናግረዋል።

Via Ethiopia Insider
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#WoalitaSodo

በዎላይታ ሶዶ ከተማ በተከሰተዉ የእሳት አደጋ ለተጎዱ ነጋዴዎች ጊዜያዊ አማራጭ የገበያ ቦታ እየተዘጋጀ ነዉ፡፡

በተለምዶ መናፈሻ ተብሎ የሚጠራዉ የቀድሞ የዎላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ምድረ ግቢ ነዉ በአማራጭ ገበያ ቦታነት እየተዘጋጀ የሚገኘዉ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ እና የዞኑ መንግስት ከተጎጂዎቹ ጋር ተወያይተው በተስማሙት መሰረት ነው ስራው የተጀመረው።

ነጋዴዎቹ በሚዘጋጅላቸዉ ጊዜያዊ ቦታ እየሠሩ ጎን ለጎን ነባሩ መርካቶ ገበያ ተገንብቶ የሚጠናቀቅ ይሆናል ብሏል ከተማ አሰተዳደሩ።

ነባሩ የመርካቶ ገበያ ግንባታ በዘመናዊ መልኩ ሳይቆይ የሚጀምር እንደሚሆን ተገልጿል።

Via Wolaita City Administration
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#PASSPORT

የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በቴክኒክ ችግር ምክንያት አቋርጦት የነበረውን የፓስፖርት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ኤጀንሲው ደንበኞች አገልግሎቱን ከዛሬ ታህሳስ 16 ቀን 2013 ጀምሮ ማግኘት እንደሚችሉ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት አሳውቋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛ አገራዊ ምርጫን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱ ምክክሮች በኋላ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን እንዲሁም መደረግ ስላለባቸው ተጨማሪ ጉዳዮች እና የጊዜ ሰሌዳን አስመልክቶ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያየ ይገኛል።

ዛሬ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ይደረጋል።

አሁን ላይ የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱኳን ሚደቅሳ የቀድሞ ምክክሮችን በማስከተል የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ለፓርቲ አመራሮችና ተወካዮች በማቅረብ ላይ ናቸው።

#TikvahFamilyAA

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#UPDATE

በወላይታ ሶዶ ከተማ 'መርካቶ ገበያ' ደርሶ በነበረው የእሳት አደጋ 1.5 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ተገለፀ።

42 ሺ የሚሆኑ ዜጎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ በአደጋው ለቀውስ መጋለጣቸው ተነግሯል።

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከተጎጅዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በአደጋው ሀብት ንብረታቸውን ያጡ ነጋዴዎች አደጋው በመከሰቱ ለከፍተኛ የስነ ልቦና ቀውስ መዳረጋቸውን በማንሳት ሀብታቸውን በማጣታቸው ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ በርካቶች ለከፋ ችግር ተጋላጭ በመሆናቸው ስጋት ገብቶናል ብለዋል።

የክልሉ መንግስትና ሁሉም ዜጋ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የደቡብ ከልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው ከእለታዊ ድጋፍ ጀምሮ እስከ መልሶ ማቋቋል ድረስ የክልሉ መንግስት የድርሻውን እንደሚወጣ አረጋግጠዋል።

ተጊጂዎቹ ወደ ቀደመ ስራቸው እንዲመለሱ የማይክሮ ፋይናንስና የባንክ ብድር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ይመቻቻል ብለዋል።

የመርካቶ ገበያ ማእከል ለተመሣሣይ አደጋ ተጋላጭ እንዳይሆን በዘመናዊ መንገድ እንዲገነባ ድጋፍ የክልሉ መንግስት ያደርጋል ብለዋል።

ለመነሻ እንዲሆን የደቡብ ክልል መንግስት የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

Via Wolaita Zone Communication
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#BREAKING

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28 እንዲሆን ሃሳብ አቅርቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ እና የድሬደዋ ከተማ መስተዳድር የድምጽ መስጫ ቀን ሰኔ 5 መሆኑን አስታውቋል።

ቦርዱ ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳውን ይፋ አድርጓል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተሰጠ ማሳሰቢያ !

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የጥገና ሥራ ስለሚያከናውን እሁድ ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከጥዋቱ 12፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ፦
- በድሬዳዋ፣
- በሐረር፣
- በጭሮ፣
- በጅግጅጋ፣
- በፊቅ ፣
- በደገሃቡር፣
- በአዋሽ ሰባት ኪሎ፣
- በአዲጋላ፣
- በሁርሶ፣
- በአሰላ፣
- አዳማ፣
- አዳሚ ቱሉ እና ሻሸመኔ እንዲሁም በምስራቅ ኢንዱስትሪ ዞን በኖሪያ፣ ቢሾፍቱ፣ በኢላላገዳ፣ በጆርጅ ጫማ ፋብሪካ፣ በሞጆ፣ በራም፣ በጎዴ፣ በኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር እና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡

ይህን በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደረጉ መልዕክት ተላልፏል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#BulenWoreda

ኢሰመኮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፣ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ታኅሣሥ 13 በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 207 መድረሱን ገልጿል።

የሟቾችን ማንነት የማጣራቱ ስራ በመታወቂያ እና ከጥቃቱ በተረፉ ሰዎች ምስክርነት አማካኝነት መጀመሩ ታውቋል።

በዚህም መሰረት፣ በጥቃቱ ሕይወታቸው ካለፉ አዋቂዎች መካከል 133ቱ ወንዶች ሲሆኑ 35ቱ ሴቶች ናቸው።

አንድ የስድስት ወር ሕጻንን ጨምሮ በጥቃቱ አስራ ሰባት ሕጻናት ተገድለዋል። ቀሪ ሃያዎቹ አዛውንቶች መሆናቸው ተረጋግጧል።

ከሟቾች መካከል ሁለቱ በቡለን ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እያለ ታኅሣሥ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. የሞቱ መሆናቸውን፣ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

በቡለን ከሚገኙ አራት ቀበሌዎች (ጭላንቆ ፣ በኩጂ ፣ ዲሽባኮ እና ባር) የተፈናቀሉና ቁጥራቸው ከ500 የሚበልጡ ሰዎች በጋሌሳ ቀበሌ በሚገኝ የአውቶቡስ መናኃሪያ እንዲሁም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቀበሌውን ጥለው ከ40 ኪ.ሜ. በላይ በእግራቸው በመጓዝ ወደ ቡለን ከተማ በመግባት ላይ ይገኛሉ ሲል ገልጿል።

የቡለን ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተፈናቃዮችን እየመገቡ ነው።

ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እስከሚመለሱ ድረስ የሚቆይ አፋጣኝ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ኢሰመኮ ያስታወቀ ሲሆን ተፈናቃዮች እና ተጎጂዎች በሰብአዊ እርዳታ እጥረት ምክንያት ለተጨማሪ አደጋ እንዳይጋለጡ ለመከላከል የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ አሳስቧል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#BONGA

ትላንት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ህዝበ ዉሳኔ መስጫ ቀን መግለጹን ተከትሎ ምሽቱን በቦንጋ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች እንዲሁም የከተማይቱ ነዋሪዎች ደስታቸውን አደባባይ ወጥተው ሲገልፁ አምሽተዋል።

የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ ድምፅ መስጫ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ/ም እንዲሆነ የምርጫ ቦርድ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ይጠቁማል።

Via Kafa Zone Communication
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
* የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ !

የትምህርት ቤቶችን ድጎማ በጀት (school grant) ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ የትምህርት ር/መምህራን፣ መምህራንና በጽ/ቤት ባለሙያዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለፀ፡፡

በባስኬቶ ልዩ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በዳብፃ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ር/መምህር፣ ሁለት መምህራን፣ የወረዳው ት/ጽ/ቤት ልማት ዕቅድ አስተባበሪያ፣ የአንድ መምህር ባለቤትን ጨምሮ 5 አምስት ግለሰቦች ምናባዊ ትምህርት ቤት በመፍጠርና የሌለ ተማሪ በመመዝገብ ህገ-ወጥ የባንክ አካውንት በመክፈት 237,680.00 ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን ከወረዳው ፀረ-ሙስና በደረሰን ጥቆማ መሰረት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ግለሰቦቹን ለህግ እንዲቀርቡ አድርጓል፡፡

በተደረገው የህግ ማጣራት ሥራ የባስከቶ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀለኛ ሆነው በተገኙ ግለሰቦች ላይ በ25/03/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት በእያንዳንዳቸው ላይ ከአንድ ዓመት ተኩል እስከ አራት አመት ጽኑ እስራትና የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡና የወሰዱትን ገንዘብ ለመንግስት ተመላሽ እንዲያደርጉ መወሰኑን የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
በከፋ ችግር ውስጥ ያሉ የቡለን ወረዳ ተፈናቃዮች !

በቡለን ወረዳ "በኩጂ ቀበሌ" በተፈፀመው ጥቃት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎቻችን የከፋ ችግር ውስጥ እንዳሉ እየተናገሩ ነው።

የቡለን ወረዳ አስተዳደር ለዜጎቻችን አስቸኳይ የምግብ እና የመጠለያ ድጋፍ በማድረግ ወገንን እንታደግ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

እስካሁን ለተፈናቃዮች ከመንግስትም ሆነ ከረጂ ድርጅቶች ምንም የተላከ የምግብ ድጋፍ የለም።

መንግስትም አስፈልጊውን ድጋፍ እንዲያድርግ ጥሪ ቀርቧል።

ችግሩ ግን በመንግስት ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ ለተፈናቀሉ ወገኖች እኔንም ይመለከተኛል የሚል ለወገኖቹ የሚቆረቆር ሁሉ ከሀገር ውስጥ ሆነ ከውጭ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Tigray

• የኮሪያ ሪፐብሊክ ምስራቅ ሱዳን ውስጥ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞች የ300 ሺ ዶላር ድጋፍ ማድረጓን የሱዳን ዜና አገልግሎት በድረገፁ አስነብቧል።

የኮሪያ ሪፐብሊክ መንግስት የሱዳን ህዝብ እና የሱደን መንግስት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ተቀብሎ ስላስተናገደ ምስጋናውን አቅርቧል።

• የስዊድን መንግስት በትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 6 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አሳውቋል።

ድጋፉ በIOM ፣ WFP፣ ICRC አማካኝነት ለተጎጂዎች እንደሚደርስ እንደሆነ የስዊድን ኤምባሲ ገልጿል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#AddisAbabaUniversity

ዛሬ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀን እና በማታ ያሰለጠናቸውን 4,087 ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።

ከተመራቂዎቹ መሀከል ፦

• 48ቱ በ3ኛ ዲግሪ በቀን የሰለጠኑ
• 809 በመጀመሪያ ዲግሪ በማታ ፕሮግራም
• 3,039 በቀን
• 18 በርቀት የሰለጠኑ ናቸው።

ዛሬ ከሚመሩቁ መካከል በህክምና ስፔሻሊቲ 26 ተማሪዎች ይገኙበታል።

የዛሬዎቹ ተመራቂዎች 2,635 ወንዶች ሲሆኑ 1452 ሴቶች ናቸው፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#FDREDfeneseForce

መከላከያ በወሰደው እርምጃ የተደመሰሱ ከፍተኛ የሕወሓት አመራሮች መኖራቸውን ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ፡፡

ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የሞቱ አመራሮች መኖራቸውን ተናግረው ይህም ወደፊት ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

በመተከል ዞን ውስጥ በተደጋጋሚ እያጋጠመ ያለውን የዜጎች ጭፍጨፋ ለማስቆም የመከላከያ በሽፍታዎች ላይ ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ጄኔራል ብርሃኑ ገለጻ ሌ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮም ወደ መተከል የሄዱት ለዚሁ ተግባር ነው፡፡

እስካሁንም ሀገር መከላከየ በርካታ ጸረ ሰላም ኃይሎች ላይ እርምጃ እንደወሰደ ጄኔራሉ ገልጸዋል፡፡ ይሁንና ይህ ሥራ በጸጥታ ኃይል ብቻ የሚሰራ እንዳልሆነና የፖለቲካ ስራ እንደሚጠይቅ ነው ያብራሩት፡፡

በአመራሮች መካከል ያለው የፖለቲካ ሽኩቻ፣መሬትህ ሊነጠቅ ነው በማለት ሽፍቶችን ማደራጀት እንዲሁም የውጭ ኃይሎች ተሳትፎ ለአካባቢው ቀውስ ዋነኛ ምክንያቶች እንደሆኑም አንስተዋል፡፡

ይህም ነገሮችን እንዳወሳሰበ ነው ጄኔራሉ ያነሱት፡፡ ሽፍቶቹ እርምጃ ሲወሰድባቸው ጎረቤት ሀገር ጭምር እየሄዱ እንደሚሸሸጉም ጄኔራል ብርሃኑ ተናግረዋል፡፡

ነባሩ (Indigenous) ማሕበረሰብ እንዲሁም ‘ደገኛው’ የየራሳቸው ችግር እንዳለባቸውም የተናገሩ ሲሆን ‘ደገኛው’ መተከል የኛ ነው የሚል ፖለቲካ የማራመድ ከነባር ብሔረሰቦች ደግሞ የጉሙዝ ሽፍቶች ንጹኃንን የመግደል ተግባሮች እንደሚፈጸሙ ገልጸዋል፡፡

ዋናው የፖለቲካው መበላሸት ስለሆነ ለዘላቂ መፍትሔ ፖለቲካዊ ሥራ መስራት እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (አል ዓይን ኒውስ)
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
CAR ውስጥ የUN ሰላም አስከባሪዎች ተገደሉ።

ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ 2 የቡሩብዲ ዜጎች የሆኑ የተመድ ሰላም አስከባሪዎች መገደላቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

ሌሎች ሁለት ሰላም አስከባሪዎች ቆስለዋል።

ጥቃቱን ያደረሱት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ናቸው ተብሏል።

የአንቶኒዮ ጉተሬዝ ቃል አቀባይ የሆኑት ስቴፈን ዱጃሪች በሰላም አስከባሪዎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት በጦር ወንጀል ሊያስጠይቅ የሚችል ነው ብለዋል።

የCAR ባለስልጣናት በአስቸኳይ ጉዳዩን መርምረው ተጠያቂዎችን ህግ ፊት እንዲያቀርቡ ጉተሬዝ ማሳሰባቸውን ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

ዛሬ በሀገሪቱ ሀገር አቅፍ ምርጫ ይደረጋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#SNNPRS

በደቡብ ክልል እስካሁን ወደ ትምህርት ቤት ያልሄዱ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች አሉ።

እነዚህን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ የመመለስ ንቅናቄ እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

ከ9 ወራት በኋላ የገፅ ለገፅ ትምህርት ቢጀመርም ተማሪዎች የሚጠበቀውን ያህል በትምህርት ገበታቸው ላይ አልተገኙም ብሏል ቢሮው።

አሁን እየተካሄደ ያለው ንቅናቄ ቤት ለቤት በመንቀሳቀስ ተማሪዎች ከሰኞ ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማድረግ ያለመ ነው።

* በደቡብ ክልል በዘንድሮው የትምህርት ዘመን 4 ሚሊዮን 200 ሺህ ተማሪዎችን ለመቀበል ከታቀደው ውስጥ 77 ነጥብ 3 በመቶ ተፈፅሟል። ቀሪውን በንቅናቄው ለማሳካት እየተሰራ ነው ተብሏል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Metekel

በኩጅ ቀበሌ ከተከሰተው ጭፍጨፋ ተርፈው በቡለን ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ ዜጎች የተለያዩ ለዕለታዊ ፍጆታ የሚሆኑ የምግብ ገብዓቶችን እየቀረበ ነው።

• ስንዴ 875 ኩንታል፣
• ዱቄት 1751 ኩንታል ፣
• ፓስታ እና የህጻናት አልሚ ምግብ ደግሞ 440 ኩንታል በአጠቃላይ 3 ሺህ 66 ኩንታል በቡለን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች መቅረቡን በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በዚህ መሰረት 7 የሚደርሱ መኪናዎች ድጋፉን ጭነው ወደ ቦታው አቅንተዋል።

ከሰሞኑ በቡለን ወረዳ በተፈፀመው የንፁሃን ጥቃት 35 ሺህ ዜጎቻችን ከቀያቸው ተፈናቅለው በቡለን ከተማ ተጠልለው ይገኛሉ።

በአጠቃላይ በመተከል ዞን 56ሺ የሚደርሱ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለው በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ።

[በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን]
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#የእርቀ_ሰላም_ኮንፈረንስ

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳደር እንዲሁም ኧሌ ልዩ ወረዳ አስተዳደር በአንድ ላይ ተባብረው የተፈጠረውን ግጭት በእርቅ ለመፍታት የእርቀ ሰላም ኮንፈረንስ አዘጋጅተዋል።

ይኸው ኮንፈረንስ ዛሬ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ትላንት ለዚሁ የእርቀ ሰላም ኮንፈረንስ ዝግጅት የክልሉ ማርሽ ባንድ በካራት ከተማ ትዕይንት አቅርቧል።

በእርቀ ሰላም ኮንፈረንሱ ላይ ከሁለቱም መዋቅሮች ከሁሉም ቀበሌዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ፣ ከአጎራባች ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች የተጋበዙ እንግዶች፣ የክልል እና የፌዴራል ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ይሳተፉበታል ተብሏል።

መረጃው የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
የፈረንጆች 2020 በቁጥሮች ፦

(በAddis Admas)

• 4 ሚሊዮን - በዓመቱ ለረጅም ጊዜ ስራ አጥ የሆኑ አሜሪካውያን ቁጥር

• 115 ሚሊዮን - በዓመቱ በመላው ዓለም ወደ ከፋ ድህነት የገቡ ሰዎች ቁጥር

• 3.2 ሚሊዮን - በዓመቱ በተለያዩ ምክንያቶች ለሞት የተዳረጉ አሜሪካውያን ቁጥር

• 30 - በዓመቱ በመላው ዓለም በስራ ላይ እያሉ የተገደሉ ጋዜጠኞች ቁጥር

• 79.5 ሚሊዮን - በዓመቱ በመላው ዓለም ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር

• 1.5 ቢሊዮን - በዓመቱ በዓለማችን በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ ህፃናት እና ወጣቶች ቁጥር

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#UPDATE

በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ላይኛ በደኔ ቀበሌ በደረሰው አደጋ ቤት ለተቃጠለባቸው እና ንብረት ለወደመባቸው አካላት ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የአደጋው መንስኤም የተለያዩ እህሎች በተከመሩበት ቦታ በሶላር ባትሪ ቻርጅ የተሰካ የሞይባል ስልክ ፈንድቶ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የዚህ አይነት አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በተለያዩ አጋጣሚዎች ግንዛቤ የመፍጠር ስራ የተሰራ ቢሆንም በህብረተሰቡ ዘንድ አሁንም የጥንቃቄ ጉድለቶች እንደሚስተዋሉ ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም በጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት መሰል የእሳት አደጋ እንዳይከሰት አስቀድሞ ለመከላከል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበትም የወረዳው አስተዳደር አሳስቧል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
* ቀይ መስቀል

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሃላባ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዌራ ወረዳ እሳት አደጋ ቤት ንብረታቸው ለተቃጠለባቸው ወገኖች የአልባሳትና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ቀይ መስቀል ለተጎጂ ቤተሰቦች ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ብርድ ልብስ ፥ ከሰፍ ፥ ሸራ እና ሳሙና ነው ድጋፍ ያደረገው።

ማህበሩ እገዛ ለሚያስገልጋቸው ዜጎች የሚደረገውን ድጋፍ እንደሚያጠናክር አሳውቋል።

(ሀላባ ዞን ኮሚኒኬሽን)
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA