Ethiopian Red Cross Society
6.26K subscribers
3.68K photos
81 videos
485 links
This is Ethiopian Red Cross Society Headquarters' Telegram channel, which was set up to discuss humanitarian issues and the organization's humanitarian assistance efforts.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከኔዘርላንድስ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር ከአውሮፓ ህብረት የሰብአዊ እርዳታ (ECHO) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በሶማሌ ክልል፣ ሸበሌ ዞን፣ ጎዴ እና ኤሌሌ ወረዳዎች ለሚገኙ ለድርቅ አደጋ ተጋላጭ አባወራዎች ሁለገብ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡

በአካባቢው ካለፈው ጥቅምት እስከ ታህሣሥ ወር ይጠበቅ የነበረው ዝናብ ባለመጣሉ ሊከሰት የሚችልን የድርቅ አደጋ ለመከላከል በአጠቃላይ በሁለቱ ወረዳዎች 1,800 አባወራዎች የገንዘብ ድጋፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡

በኤሌሌ ወረዳ ቦቅ ቢላል ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ፈርዶሳ ኡስማን ድጋፉን አስመልክቶ እንደተናገሩት፣ "ቀይ መስቀል 11,300 ብር የሰጠን ሲሆን፣ ይህም ያለብንን የምግብና ውሃ ችግር ለመፍታት ይጠቅመናል፡፡ ከብቶቻችንም የሞቱብን በመሆኑ ድጋፉ ለኑሮአችን የሚያስፈልገንን ወጪ ለመሸፈን ይጠቅመናል፡፡ ለተደረገልን ድጋፍም እናመሰግናለን" ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በድርቅ እና በሌሎች አደጋዎች ለጉዳት የተጋለጡ ወገኖቻችንን ህይወት ለመታደግ ድጋፍ በማድረግ ላይ ሲሆን፣ በእነዚህ ሁለት ወረዳዎች ለሰጠው ምላሽ ድጋፍ ላደረጉለት ለአውሮፓ ህብረት የሰብአዊ እርዳታ እና ለኔዘርላንድ ቀይ መስቀል ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
👍14
ERCS, Austrian Red Cross, and IFRC Hold PGI Capacity Building Workshop

The Ethiopian Red Cross Society (ERCS), in collaboration with the Austrian Red Cross and the International Federation of Red Cross and Red Crescent Societies (IFRC), has launched a two-day workshop to validate the Protection, Gender, and Inclusion (PGI) Organizational Capacity Assessment Report. This initiative is part of the Skybird Project, which aims to enhance inclusive humanitarian action.

The workshop, attended by ERCS senior management, representatives of Partner National Societies, and IFRC representatives, focuses on addressing violence, discrimination, and exclusion based on gender.

In his opening remarks, ERCS Secretary General Abera Lullessa emphasized the importance of the project, reaffirming ERCS’s commitment to ensuring equal and inclusive humanitarian services for all vulnerable communities. He also highlighted the Society’s ongoing efforts to integrate PGI principles into all its humanitarian programs.

By the end of the workshop, participants will develop a one-year strategic action plan to strengthen PGI implementation within ERCS operations.
👍81
ማኅበሩ የስድስት ወር አፈፃፀሙን በመገምገም ላይ ይገኛል

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት አፈጻጸሙን እየገመገመ ነው። በግምገማው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የማኅበሩ ዋና ፀሀፊ አቶ አበራ ሉሌሳ፣ በበጀት ዓመቱ በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት ከፍተኛ ሆኖ መቀጠሉን በማንሳት፣ ድርቅ እና ግጭት ለቀጠለው ሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ማኅበሩ ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር ምላሽ እየሰጠ መሆኑን የገለፁት አቶ አበራ፣ ለአብነትም ከእንግሊዝ መንግስት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በአራት ክልሎች የጤና እና የውሃ አገልግሎትን ለማሻሻል በርካታ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሀገራችን ያለው ሰብዓዊ ፍላጎት የቀጠለ ቢሆንም ከውጪ የሚገኘው የገንዘብ ድጋፍ እየቀነሰ መሆኑን ዋና ፀሀፊው የተናገሩ ሲሆን፣ በቅርቡም የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት የሚያደርገውን ድጋፍ ማቋረጡን ተከትሎ ማኅበሩ ከሁለት አጋር ድርጅቶች ጋር ይተገብራቸው የነበሩ ፕሮጀክቶቹን ለማቋረጥ መገደዱን ገልፀዋል፡፡

ማኅበሩ በዚህ ረገድ የገጠመውን ተግዳሮት ለመቅረፍ መሰረታዊ ስትራቴጂክ ለውጦቸችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ያስታወቁት አቶ አበራ፣ ይህም ተቋማዊ መዋቅራዊ ለውጥን ጨምሮ የሃብት አሰባሰብ ዘዴዎችን በአዲስ መልክ ማዋቀርና ማጎልበት እንደሚያካትት ተናግረዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ማኅበሩ በግማሽ ዓመት አፈፃፀሙ፣ 122,869 ሰዎችን በምግብ እና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ፣ 313,572 የህብረተሰብ ክፍሎችን በውሃና ሥነ ንፅህና ድጋፍ፣ 25,918 ሰዎችን በድንገተኛ ህክምና አገልግሎት፣ 25,473 ተጠቃሚዎችን በአየር ንብረት ለውጥ መላመድ እና በኑሮ ሁኔታ ማሻሻያ ደጋፍ እንዲሁም፣ የተጠፋፉ ቤተሰቦች በማገናኘት፣ ማኅበራዊ ትስስር በማጠናከር እና የስደት ተመላሾች ድጋፍ 772,748 ሰዎችን መድረስ የቻለ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በግማሽ ዓመት ውስጥ ወደ 1.12 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል፡፡

ማኅበሩ እያካሄደ ባለው ግምገማ ቀጣይ የሚኖሩ ስትራቴጂክ አቅጣጫዎች ምን መሆን እንዳለባቸው እና የገጠሙ ፈተናዎች በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ ተወያይቶ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል፡፡
👏62👍1