Ethiopian Red Cross Society
6.27K subscribers
3.68K photos
82 videos
486 links
This is Ethiopian Red Cross Society Headquarters' Telegram channel, which was set up to discuss humanitarian issues and the organization's humanitarian assistance efforts.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከኦስትሪያ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር በደቡብ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች በመተግበር ላይ የሚገኘውን የህይወት አድንና አደጋን መቋቋም የሚያስችል ዘርፈ ብዙ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ፕሮጀክት አፈፃፀም ግምገማ እና ተጨማሪ ድጋፍ ማስጀመሪያ አካሄደ፡፡

ፕሮጀክቱ በመጀመሪያ ዙር ለ18 ወራት (እ.አ.አ ከታህሳስ 01 ቀን 2023 - ግንቦት 31 ቀን 2025) ታቅዶ ሲተገበር የነበረና አሁን ወደ 36 ወራት (እ.አ.አ እስከ ህዳር 2026) እንዲራዘም የተደረገ ሲሆን፣ የሚተገበርባቸውንም አካባቢዎች በማስፋት ከደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ/ሀርቡ ወረዳ፣ ከሰሜን ወሎ ዞን ደግሞ ራያ ቆቦ እና ግዳን ወረዳዎች እንዲጨመሩ ተደርገዋል፡፡ አጠቃላይ በጀቱም ከ150 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ 176 ሚሊዮን ብር በመመደብ ከ326 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

በመጀመሪያው ምዕራፍ እየተከናወኑ ከሚገኙ ተግባራት ባሻገር፣ በፕሮጀክቱ ተጨማሪ የድጋፍ ሂደት 1,610 አባወራዎችን/እማወራዎችን በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ፣ 100 ሴቶችን በራስ አገዝ ቡድን ድጋፍ፣ 100 አካል ጉዳተኞችን በኑሮ ሁኔታ ማሻሻያ ድጋፍ እንዲሁም 1,000 ሴቶች እና ልጃገረዶችን በወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተጠቃሚ ለማድረግ የታለመ ሲሆን፣ አምስት የውሃ ተቋማትን በማደስ/በመገንባት አካታች የውሃና ሥነ-ንፅህና መዋቅሮችን ማሻሻልም የዕቅዱ አካል ነው፡፡

በፕሮጀክቱ ግምገማ ላይ ከተለያዩ የመንግስት ቢሮዎች የመጡ የሥራ ኃላፊዎች፣ የማኅበረሰብ ተወካዮች፣ በኢትዮጵያ የኦስትሪያ ቀይ መስቀል ቢሮ ኃላፊና ሠራተኞች፣ የማኅበሩ ዋና መስሪያ ቤትን ጨምሮ የአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን፣ ተሳታፊዎቹም ኘሮጀክቱ በግጭት እና በድርቅ የተጎዱ ቤተሰቦችን በተለይም ሴቶችን እና ልጃገረዶችን የኑሮ ሁኔታ በማሻሻልና አደጋ የመቋቋም አቅማቸውን በማጎልበት እንዲሁም በንፁህ ውሃ አቅርቦት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
6👍1
👍31
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰብዓዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል ለ30 የማኅበሩ ድንገተኛ አደጋ ሕክምና ምላሽ ሰጪ በጎ ፈቃደኞች ሥልጠና ሰጠ፡፡
ሥልጠናው በእንግሊዝ መንግስት የውጪ የጋራ ልማት ቢሮ (FCDO) ድጋፍ ከሰብዓዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ CPD ማዕከል እና ጠብታ አምቡላንስ ጋር በመተባበር የተሰጠ ሲሆን፣ ተሳታፊዎቹም ከአምስት የማኅበሩ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተወጣጡ ናቸው፡፡
ሥልጠናው የማኅበሩ ድንገተኛ አደጋ ሕክምና ምላሽ ሰጪ በጎ ፈቃደኞቹ በተለያዩ አደጋዎች ለጉዳት የተጋለጡ ወገኖችን ህይወት ለመታደግ የሚያስችሉ ክህሎቶችን እንዲያገኙ ታልሞ የተዘጋጀ ነው፡፡
The Ethiopian Red Cross Society’s Center for Capacity Development for Humanitarian Services (ERCS-CCDHS) has trained 30 Emergency Medical Responder volunteers to enhance their life-saving skills.
The training was conducted with the support of the Foreign, Commonwealth & Development Office (FCDO) in collaboration with ERCS-CCDHS, Addis Ababa University College of Health Sciences CPD Center, and Tebita Ambulance. Participants were drawn from five regional branches of the Society.
The training was designed to equip the Society’s volunteer Emergency Medical Responders with the skills necessary to save the lives of individuals affected by disasters.
👍91