Ethiopian Red Cross Society
6.26K subscribers
3.68K photos
82 videos
486 links
This is Ethiopian Red Cross Society Headquarters' Telegram channel, which was set up to discuss humanitarian issues and the organization's humanitarian assistance efforts.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከኦስትሪያ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ እና ደሴ ዙሪያ ወረዳዎች እንዲሁም በሰሜን ወሎ ዞን ጃራ የተፈናቃዮች ካምፕ ላይ የህይወት አድንና አደጋን መቋቋም የሚያስችል ዘርፈ ብዙ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በግጭት እና ድርቅ አደጋዎች ምክንያት ለጉዳት የተጋለጡ በተለይም ሴቶችና ልጃገረዶች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ነው፡፡

ፕሮጀክቱ እ.አ.አ ታህሳስ 01 ቀን 2023 የተጀመረና ለ18 ወራት የሚቆይ ሲሆን በእስካሁን አፈፃፀሙ ለ2,560 አባወራዎች/እማወራዎች ለእያንዳንዳቸው 21,000 ብር የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም 120 ሴቶች በራስ አገዝ ቡድኖች እንዲሁም 120 አባወራዎች/እማወራዎች በእንስሳት እርባታ ድጋፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ በፕሮጀክቱ ለ1,200 ሴቶችና ልጃገረዶች የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በማሰራጨት፣ ሰባት የውሃ ተቋማትን በማደስ/በመገንባት እንዲሁም ከ37,000 በላይ ሰዎችን ተደራሽ ያደረገ የአምቡላንስ አገልግሎት እና የሥነ-ንፅህና አጠባበቅ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ተሰርቷል፡፡

ፕሮጀክቱ ወደ 150 ሚሊዮን ብር በሚሆን በጀት የማኅበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል አደጋን የመቋቋም አቅማቸውን ለማጎልበት ታልሞ እየተተገበረ የሚገኝ ሲሆን፣ የውሃ አቅርቦትን በማሻሻል፣ የማኅበረሰብ ትስስርን በማጠናከር እንዲሁም ተጠቃሚዎች ዘላቂ የገቢ ማስገኛ ሥራ ዘርፍ እንዲኖራቸው በማድረግ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡

The Ethiopian Red Cross Society, in partnership with the Austrian Red Cross, has successfully implemented the Multisector Emergency Support for Lifesaving and Leading to Resilience (MESELAL) project in Tenta and Dessie Zuria woredas of South Wollo and Jara IDP Camp in North Wollo. This project focuses on providing critical support to vulnerable households affected by conflict and drought, with a focus on women and girls.

This 18-month project, launched on December 01, 2023, has provided cash assistance of 21,000 Birr each to 2,560 households. Additionally, 120 women have been supported through Self-Help Groups, and 120 households have received livestock assistance. The project has also distributed menstrual hygiene management (MHM) products to 1,200 women and girls, rehabilitated seven water points, and reached over 37,000 people with ambulance services and hygiene & sanitation awareness initiatives.

The project, with a budget of about 150 million Birr, aims to help communities restore and sustain their livelihoods and build long-term resilience. The efforts have greatly improved water access, strengthened community bonds, and helped build sustainable businesses for the future.
👍3👏3
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከኦስትሪያ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር በደቡብ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች በመተግበር ላይ የሚገኘውን የህይወት አድንና አደጋን መቋቋም የሚያስችል ዘርፈ ብዙ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ፕሮጀክት አፈፃፀም ግምገማ እና ተጨማሪ ድጋፍ ማስጀመሪያ አካሄደ፡፡

ፕሮጀክቱ በመጀመሪያ ዙር ለ18 ወራት (እ.አ.አ ከታህሳስ 01 ቀን 2023 - ግንቦት 31 ቀን 2025) ታቅዶ ሲተገበር የነበረና አሁን ወደ 36 ወራት (እ.አ.አ እስከ ህዳር 2026) እንዲራዘም የተደረገ ሲሆን፣ የሚተገበርባቸውንም አካባቢዎች በማስፋት ከደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ/ሀርቡ ወረዳ፣ ከሰሜን ወሎ ዞን ደግሞ ራያ ቆቦ እና ግዳን ወረዳዎች እንዲጨመሩ ተደርገዋል፡፡ አጠቃላይ በጀቱም ከ150 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ 176 ሚሊዮን ብር በመመደብ ከ326 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

በመጀመሪያው ምዕራፍ እየተከናወኑ ከሚገኙ ተግባራት ባሻገር፣ በፕሮጀክቱ ተጨማሪ የድጋፍ ሂደት 1,610 አባወራዎችን/እማወራዎችን በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ፣ 100 ሴቶችን በራስ አገዝ ቡድን ድጋፍ፣ 100 አካል ጉዳተኞችን በኑሮ ሁኔታ ማሻሻያ ድጋፍ እንዲሁም 1,000 ሴቶች እና ልጃገረዶችን በወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተጠቃሚ ለማድረግ የታለመ ሲሆን፣ አምስት የውሃ ተቋማትን በማደስ/በመገንባት አካታች የውሃና ሥነ-ንፅህና መዋቅሮችን ማሻሻልም የዕቅዱ አካል ነው፡፡

በፕሮጀክቱ ግምገማ ላይ ከተለያዩ የመንግስት ቢሮዎች የመጡ የሥራ ኃላፊዎች፣ የማኅበረሰብ ተወካዮች፣ በኢትዮጵያ የኦስትሪያ ቀይ መስቀል ቢሮ ኃላፊና ሠራተኞች፣ የማኅበሩ ዋና መስሪያ ቤትን ጨምሮ የአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን፣ ተሳታፊዎቹም ኘሮጀክቱ በግጭት እና በድርቅ የተጎዱ ቤተሰቦችን በተለይም ሴቶችን እና ልጃገረዶችን የኑሮ ሁኔታ በማሻሻልና አደጋ የመቋቋም አቅማቸውን በማጎልበት እንዲሁም በንፁህ ውሃ አቅርቦት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
6👍1
👍31
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰብዓዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል ለ30 የማኅበሩ ድንገተኛ አደጋ ሕክምና ምላሽ ሰጪ በጎ ፈቃደኞች ሥልጠና ሰጠ፡፡
ሥልጠናው በእንግሊዝ መንግስት የውጪ የጋራ ልማት ቢሮ (FCDO) ድጋፍ ከሰብዓዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ CPD ማዕከል እና ጠብታ አምቡላንስ ጋር በመተባበር የተሰጠ ሲሆን፣ ተሳታፊዎቹም ከአምስት የማኅበሩ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተወጣጡ ናቸው፡፡
ሥልጠናው የማኅበሩ ድንገተኛ አደጋ ሕክምና ምላሽ ሰጪ በጎ ፈቃደኞቹ በተለያዩ አደጋዎች ለጉዳት የተጋለጡ ወገኖችን ህይወት ለመታደግ የሚያስችሉ ክህሎቶችን እንዲያገኙ ታልሞ የተዘጋጀ ነው፡፡
The Ethiopian Red Cross Society’s Center for Capacity Development for Humanitarian Services (ERCS-CCDHS) has trained 30 Emergency Medical Responder volunteers to enhance their life-saving skills.
The training was conducted with the support of the Foreign, Commonwealth & Development Office (FCDO) in collaboration with ERCS-CCDHS, Addis Ababa University College of Health Sciences CPD Center, and Tebita Ambulance. Participants were drawn from five regional branches of the Society.
The training was designed to equip the Society’s volunteer Emergency Medical Responders with the skills necessary to save the lives of individuals affected by disasters.
👍91