Ethiopian Red Cross Society
6.26K subscribers
3.68K photos
82 videos
486 links
This is Ethiopian Red Cross Society Headquarters' Telegram channel, which was set up to discuss humanitarian issues and the organization's humanitarian assistance efforts.
Download Telegram
ማኅበሩ በሠራተኞቹ እና በአምቡላንሶቹ ላይ በተፈፀመ ዘግናኝ ጥቃት እጅግ ማዘኑን ይገልፃል፡፡

የማኅበሩ አምቡላንሶች በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ሲሬ ወረዳ እና በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ ለህይወት አድን ተግባር በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ባልታወቁ ኃይሎች በተተኮሰባቸው ጥይት የሁለቱም አምቡላንስ አሽከርካሪዎች ለከፍተኛ ጉዳት የተዳረጉ ሲሆን አምቡላንስ ተሽከርካሪዎቹም ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

ማኅበሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሠራተኞቹን ጨምሮ በበጎፈቃደኞቹ እና ተሽከርካሪዎቹ ላይ በሚፈፀሙ ጥቃቶች አማካኝነት ሰብዓዊ አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ወገኖች ለማድረስ ፈተና እየሆነበት ነው፡፡ በመሆኑም ጥቃት የሚፈፅሙ የትኛውም ተፋላሚ ኃይሎች ድርጊቱ ኢትዮጵያ የፈረመችውን ዓለም አቀፍ የጄኔቫ ሥምምነቶችን የሚፃረርና ከማኅበሩ ዓላማ ውጪ መሆኑን ተረድተው የማኅበሩ ሠራተኞች፣ በጎፈቃደኞችም ሆኑ ተሽከርካሪዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው ሰብዓዊ ተግባራቸውን ማከናወን እንዲችሉ፣ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፣ ከመሰል ድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ማኅበረሰቡም ድርጊቶቹን እንዲያወግዝ የተለመደ ተማፅኗችንን እናቀርባለን፡፡

በመጨረሻም ማኅበሩ የወገኖቻቸውን ህይወት ለመታደግ ሲንቀሳቀሱ የጥቃት ሰለባ በመሆን መተኪያ የሌላት ውድ ህይወታቸውን ላጡ ሠራተኞች እና በጎፈቃደኞች ቤተሰቦች መፅናናትን እንዲሁም ለተጎዱት በቶሎ ማገገምን ይመኝላቸዋል፡፡
👍22😱5😨41
ማኅበሩ ከ316 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከጀርመን ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች በተመረጡ ወረዳዎች ድርቅን ለመቋቋም እና እሱን ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳቶችን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። እነዚህ ተግባራት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ባሌ ዞን ሰዌና፣ ራይቱ እና ለገሂዳ ወረዳዎች እንዲሁም በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን አባ ኮሮ፣ በራኖ፣ ዳናን እና ምስራቅ ኢሜይ ወረዳዎች የሚተገበሩ ናቸው።

በዚህም መሰረት ማኅበሩ በተጠቀሱት ሁለቱም ክልል ወረዳዎች ለሚገኙ 25 ሺህ አባወራዎች በድምሩ 261.25 ሚሊዮን ብር የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም ከ55 ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን ወጪ የእንስሳት መኖን ለ1,500 አባወራዎች በማከፋፈል፣ ከ50 ሺህ በላይ የቤት እንስሳትን በመከተብ እና በፀሃይ ሃይል የሚሰሩ የውሃ ተቋማትን በመገንባትና በመጠገን ላይ ይገኛል።

ማኅበሩ አደጋ ከተከሰተ በኋላ ከሚያደርገው ምላሽ በተጨማሪ አደጋን አስቀድሞ ለመከላከልና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚያስችሉ ተግባራትን በተለያዩ አካባቢዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡
👏13👍92
የማኅበሩ በጎፈቃደኞች እያከናወኑ በሚገኙት የበጎፈቃድ አገልግሎት ዙሪያ ቪኦኤ የሠራውን ዘገባ ይመልከቱ👇
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👏15👍2
ማኅበሩ ከዴንማርክ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን ለሚገኙ በድርቅ እና በጦርነት ለጉዳት ለተጋለጡ 1,600 አባዎራዎች የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርጓል። ይህንንና ሌሎች ማኅበሩ በክልሉ እያከናወናቸው በሚገኙ ሰብዓዊ ተግባራት ዙሪያ ትግራይ ቴሌቪዥን የሰራውን ዘገባ ይመልከቱ👇
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👍6👏2
👍123
የኢትዮጲያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከብሪታንያ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር ምቹና ከፆታዊ ጥቃት ነጻ የሆነ የሥራ-ቦታ መፍጠር (Safeguarding/PSEA) እና ጠቀሜታዎቹን በተመለከተ የማኅበሩ የሥራ ኃላፊዎችን፣ የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎችን እና የፕሮግራም አስተባባሪዎችን ያሳተፈ ውይይት አካሄደ፡፡

በዕለቱ በአመራር አካላት ድርሻ እንዲሁም ምቹና ከፆታዊ ጥቃት ነጻ የሆነ የሥራ-ቦታ የመፍጠር ድርጅታዊ-ባህል ግንባታ ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡ የውይይቱ ተሳታፊዎች ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ ማኅበሩ በአሁኑ ወቅት የሚገኝበትን ደረጃ የገመገሙ ሲሆን፣ በውይይቱ የተለዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ያስችላሉ ያሏቸውን ተግባራት ለማከናወን የድርጊት መርሃ ግብር አዘጋጅተዋል።

ERCS, in collaboration with the British Red Cross (BRC), held a Safeguarding/PSEA Sensitization Workshop for its Senior Management Team, Regional Branch Heads, and Program Coordinators.

The discussion centered on the crucial role of leadership in shaping an inclusive organizational culture that fosters a conducive and gender-neutral workplace. Participants evaluated the Society’s current status on the matter, identified key gaps, and proposed targeted activities to address them. The session concluded with the development of a concrete action plan to drive meaningful change.
👍211
Norwegian Red Cross Delegates Visit ERCS, Reaffirm Strong Partnership and Priority to Ethiopia.
A delegation from the Norwegian Red Cross, led by its President Siri Hatlen, paid a courtesy visit to the Ethiopian Red Cross Society (ERCS). They were warmly welcomed by ERCS President Abera Tola and Acting Secretary General Abera Lulessa, along with senior management members, who provided an extensive briefing on the humanitarian situation in Ethiopia and ERCS's response efforts.
ERCS higher officials expressed their heartfelt gratitude to the Norwegian Red Cross for its long-standing partnership and collaboration in addressing critical humanitarian challenges. The Norwegian delegation acknowledged the vital role of this collaboration and emphasized that Ethiopia remains a top priority in their humanitarian support agenda.
👍10