EEP Communication
15.6K subscribers
10.9K photos
33 videos
32 files
2.03K links
EEP Communication
Download Telegram
የገናሌ ዳዋ 3 የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ዓለምአቀፍ ትኩረት ስቧል
……………/////………..
የኤሌክትሪክ ዘርፍ ተሸላሚው የገናሌ ዳዋ 3 ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክን ለሁሉም ለማዳረስ እገዛ እያደረገ መሆኑን ፓወር የተሰኘው በኃይል ላይ በማተኮር የሚዘጋጀው ዓለምአቀፍ መጽሔት ዘግቧል፡፡
ከህዝቦቿ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ኤሌክትሪክ የማያገኙባት ኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ አቅርቦት እየተሻሻለች መምጣቷን መጽሔቱ በዝርዝር አትቷል፡፡
መፅሔቱ ይፋ እንዳደረገው የገናሌ ዳዋ 3 ፕሮጀክት መንግስት እ.ኤ.አ እስከ 2025 በመላው ሀገሪቱ ኤሌክትሪክ ለማስፋፋት የሚደረገውን የያዘውን ዕቅድ ለማሳካት እገዛ ማድረግ ጀምሯል፡፡
በ3 ተርባይኖች 254 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የገናሌ ዳዋ 3 የኃይል ማመንጫ ተመርቆ ስራ የጀመረው በተያዘው ዓመት አጋማሽ ላይ ነበር፡፡
ይህን ሊንክ በመጫን ዝርዝር ዘገባውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
https://www.powermag.com/award-winning-hydropower-project-helps-electrify-ethiopia/
የታላቁ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሰራተኞች የ የበጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆኑ
*****************//////*****************
የታላቁ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሰራተኞች የ2012 ዓ.ም የበጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆኑ።
ሽልማቱ የተበረከተው የግድቡ መሰረት ድንጋይ ከተጣለበት ከመጋቢት 24/2004 ዓ.ም ጀምሮ በጉባ በሥራ ላይ ለሚገኙ የግድቡ ሰራተኞችና ጸጥታውን ለሚቆጣጠሩ የመከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፓሊስ አባላት ነው።
በጉባ የሚገኙ ሰራተኞችን ወክለው የታላቁ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ሽልማቱን ተረክበዋል፡፡
በአባይ ፖለቲካ ላይ የተለያዩ ጥንቶችን ያደረጉት ዶ/ር ያዕቆብ አርሳኖ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የጤና ባለሙያዎችና የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች እንዲሁም የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአረብኛ የኢትዮጵያን አቋም በተለያዩ መድረኮች በማንፀባረቅ የሚታወቀው መሀመድ አል አሩሲ የ8ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/?modal=admin_todo_tour
ጳጉሜ 02 ቀን 2012 ዓ.ም
አዋሽ II የኃይል ማመንጫ ጣቢያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
…………./////………..
በእንቦጭ አረም በመዘጋቱ አገልግሎት ለጊዜው አቋርጦ የነበረው የአዋሽ II የውኃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

የእንቦጭ አረሙ የውሃ መቀየሻ ግድብ ላይ በመተኛቱ የተነሳ የውሃ መቀበያው (water intake) አገልግሎቱ ተቋርጦ ቆይቷል፡፡

አረሙን ከወንጂ ስኳር ፋብሪካ በተገኘ ኤክስካቫተር የማንሳት ሥራ ሲከናወን ቆይቶ የውሃ መቀበያው በመከፈቱ የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ከአርብ ነሐሴ 29 ጀምሮ ዳግም ኃይል ማምረት ጀምሯል፡፡

32 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው አዋሽ II የኃይል ማመንጫ ጣቢያ አገልግሎት መስጠት የጀመረው እ.ኤ.አ. በ1966 ዓ.ም ነበር፡፡

የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/?modal=admin_todo_tour
ጳጉሜ 02 ቀን 2012 ዓ.ም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስመ ጥር ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የሀገራችንን አቋም የሚያሳይ ቪድዮ ተለቀቀ።
EEP new year 2013.mpg
384.2 MB
እንኳን ለ2013 ዓ.ም. በሰላም አደረሳችሁ!!
አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የጤናና የብልፅግና እንዲሆንላችሁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይመኛል!!
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
🌻🌻 መልካም 🌻🌻
🌻🌻 አዲስ 🌻🌻
🌻🌻 ዓመት 🌻🌻
🌻🌹🌾🌻💐🌷🌻
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
እንኳን ለ2013 ዓ.ም. በሰላም አደረሳችሁ!!
አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የጤናና የብልፅግና እንዲሆንልን ከልቤ እመኛለሁ!!
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
🌻🌻 መልካም 🌻🌻
🌻🌻 አዲስ 🌻🌻
🌻🌻 ዓመት 🌻🌻
🌻🌹🌾🌻💐🌷🌻
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
25 ጊጋ ዋት ኃይል ለማመንጨት ፍላጎት ካለው ድርጅት ጋር ውይይት ተካሄደ
...................////............
ፎርቲስኪው የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት በ10 ቢሊዮን ዶላር 15 ጊጋ ዋት ከውሃና 10 ጊጋ ዋት ከጂኦ ተርማል ኃይል ለማመንጨት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ፡፡

የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ በሸራተን አዲስ ሆቴል ከድርጅቱ ተወካዮች ጋር በተካሄደው ውይይት ላይ እንደገለፁት መንግስት 45 በመቶ ብቻ የሆነውን የኃይል ተደራሽነት ለማሻሻል የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች ማከናወኑን ገልፀዋል።

በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የኃይል ተደራሽነት ለማሳደግ ንፁህና ታዳሽ ኃይል በማልማት ፣ ዘርፉንም ፋይናንስ በማድረግና የግሉን ባለሃብት በማሳተፍ እንዲሁም ጠንካራ ተቋማትን የመገንባት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ለልዑካኑ አብራርተውላቸዋል፡፡

እ.አ.አ. በ2030 ኢትዮጵያ ለዜጎቿ መቶ በመቶ ኃይል ለማቅረብ የያዘችውን ዕቅድ ለማሳካት ድርጅቱ ያሳየው ተነሳሽነት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ኃይል እያቀረበች እንደሆነና 350 ሜጋ ዋት የደረሰው የኃይል ሽያጭ በጥቂት ዓመታት ወደ 700 ለማሳደግ መታቀዱንም ገልጸውላቸዋል፡፡

በተለይ በከተሞች አካባቢ እየጨመረ የመጣው የኢንዱስትሪዎች መስፋፋትና የኃይል ፍላጎት መጨመር ለግል ባለሀብቱ ትልቅ ዕድል እንደሆነም ጠቅሰውላቸዋል፡፡

ሚኒስትሩ ንጹህና ታዳሽ ኃይል ማልማት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች ኢትዮጵያ ምቹ እንደሆነችና ሰፊ አማራጮችም እንዳሏት ነግረዋቸዋል፡፡

በተለያዩ ዓለም ሀገራት ንጹህና ታዳሽ ኃይል በማመንጨት ግንባር ቀደም የሆነው ፎርቲስኪው የተሰኘው ዓለም አቀፍ ድርጅት ልዑካን ድርጅታቸው በኢትዮጵያ በ10 ቢሊዮን ዶላር 15 ጊጋ ዋት ከውሃና 10 ጊጋ ዋት ከጂኦ ተርማል ኃይል ለማመንጨት ፍላጎት እንዳለው ለሚኒስትሩ ገልፀውላቸዋል።

ውይይቱም በኢትዮጵያ የኃይል ልማቱን ለመጀመር ያለንን ተነሳሽነት ለማሳየት ሲሆን ይህን ድርጅቱ በአውስትራሊያ በጊኒና በሌሎችም ሃገራት ተመሳሳይ ሥራ በመሥራት ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል።

የሚሠሩትም የልማት ሥራ በርካታ ሥራ አጥ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግና በተለይም ሴቶችን ያሳተፈ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

ሚኒስትሩም የድርጅቱ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋዩን ማፍሰስ ዘርፈ ብዙ ትልቅ እድል ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ፎርቲስኪው በማዕድን ፣ በማዳበሪያ፣ በኃይል ማመንጨት፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና በሌሎችም ሥራዎች ላይ የተሰማራ ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው፡፡

መስከረም 07 ቀን 2013 ዓ/ም
ፎርቲስኪው በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የመሰማራት ፍላጎት አለው
……………../////………………..
በማዕድን ፣ በማዳበሪያ፣ በኃይል ማመንጨት፣ በሃይድሮጂን ምርት እና በሌሎችም ሥራዎች ላይ የተሰማራው ፎርቲስኪው በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ በማዕድን ልማት፣ በማዳበሪያ አቅርቦትና በሃይድሮጂን ምርት ሲሰማራ የሚያስፈልገውን ኃይል በራሱ ከማሟላት ባሻገር የሚያመርተውን ኃይል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችና የኃይል ቋት በመጠቀም እስከ 25 ጊጋ ዋት ኃይል ለማመንጨት ፍላጎት አለው፡፡
የፎርቲስኪው እንቅስቃሴ የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ በማሻሻል ኤሌክትሪክ ለሁሉም ለማዳረስ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡
ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ጋር በመሆን በሀገሪቱ የተጀመረውን የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ በማሳካት በአህጉሪቱ በቀዳሚነት ለመሰለፍ ማለሙን ይፋ አድርጓል፡፡
መስከረም 08 ቀን 2013 ዓ/ም
ከ25 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የቢሾፍቱ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ
………………..///………………
ከአዲስ አበባ በ45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በቢሾፍቱ ከተማ የተገነባው ባለ 400/230/15 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑን የፕሮጀክቱ ማናጀር አቶ ዳዊት ገብረ እግዚአብሄር ገለጹ፡፡
አቶ ዳዊት እንደገለፁት የማከፋፈያ ጣቢያው የግንባታ፣ የፍተሻ እና የሙከራ ስራ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል፡፡
ከነባሩ አቃቂ - ገላን ባለ 400/230 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ተነስቶ እስከ ቢሾፍቱ ማከፋፈያ ድረስ 46 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ጥንድ ባለ 400 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታም ተከናውኗል፡፡
የፕሮጀከቱ የሳይት ተቆጣጣሪ መሃንዲስ አቶ ዘውዱ ለገሰ እንደገለፁት ማከፋፈያ ጣቢያ ሁለት ባለ 600 ሜጋ ቮልት አምፒር እና ሁለት ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር ትንስፎርመሮች ተተክለውለታል፡፡
ጣቢያው ጥንድ ባለ 400 ኪሎ ቮልት ገቢ መስመር እና ሁለት ጥንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት እንዲሁም 10 ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች አሉት፡፡
የማከፋፋያ ጣቢያውን የገነባው ላርሰን ኤንድ ቱብሮ የተባለ የህንድ ኩባንያ ሲሆን ግንባታው ለመጨረስ ከ25 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ወጪ ተደርጎበታል፡፡
የማከፋፈያ ጣቢያው መገንባት በቢሾፍቱ ከተማ እና በዙሪዋ ለሚገኙ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎችና የልማት እንቅስቃሴዎች እንዲሁም ለህብረተሰቡ የኃይል ፍላጎት ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይታመናል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/?modal=admin_todo_tour
መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም.
ፓርቲው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ
...............//////................
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ( ኢዜማ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የግማሽ ሚሊዮን ብር ስጦታ አበረከተ።
በድጋፍ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በልዩነት ብቻ የተመሰረተውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ በማሻሻል በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ፓርቲው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያደረገው ድጋፍም የትብብሩ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ እንዳሉት ስጦታው በሀገር ውስጥና በሀገር ውጭ ከሚኖሩ የፓርቲው አባላት ለዚሁ ዓላማ የተሰበሰበ ነው፡፡
ኢትዮጵያውያን ባለፈው ታሪካችው በሀገራዊ የጋራ አጀንዳዎች ላይ የማይደራደሩ መሆናቸውን አስታውሰው ሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በልዩነት ምክንያት ሀገራዊ ጥቅማቸውን ለአፍታም ቢሆን አሳልፈው መስጠት እንደሌለባቸው አሳስበዋል፡፡
ኢዜማ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የማያወላውል አቋም እንዳለውና ወደፊትም ድጋፉን እንደሚቀጥል ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አረጋግጠዋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ብራሄራዊ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ታገል ቀኑብህ በበኩላቸው ኢዜማ ያደረገው ድጋፍ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አንድ መሆን እንዳለባቸው ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ከአሁን በፊት ፓርቲዎች በእንደዚህ ዓይነት ሀገራዊ ልማት ላይ የሚያሳዩት ተሳትፎ ብዙም እንዳልነበር አቶ ታገል ጠቁመዋል፡፡
ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነገ መንግሥት ሆነው ቢመረጡ የሚያስተዳድሩት አሁን በልዩነት ሁነው የሚሰሩትን መልካም ሥራ በመሆኑ በጋራ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ የጋራ ኃላፊነት እንዳለባቸው ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/?modal=admin_todo_tour
መስከረም 12 ቀን 2013ዓ/ም
የጊንጪ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ
…………………../////……………..
ላርሰን ኤንድ ቱብሮ በተባለ የህንድ ኩባንያ የተገነባው የጊንጪ ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ፡፡
የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ገ/እግዝአብሔር እንዳስታወቁት የማከፋፈያ ጣቢያው መጠናቀቅ በጊንጭና በዙሪያው የሚገኙ ከተሞችን የኃይል መቆራረጥ ከማስቀረቱም በተጨማሪ ወደ ፊት አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ያስችላል፡፡
የማከፋፈያ ጣቢያው ኃይል የሚያገኘው ከገፈርሳ - ጌዲዮን ከተዘረጋው ባለ 230 ኪ.ቮ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ሲሆን ሁለት ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመሮች ተተክለውለታል፡፡
ጣቢያው ሁለት ጥንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ገቢ እና 10 ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች አሉት፡፡
በ2008 ዓ.ም የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪው 67 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ነው፡፡

የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric
መስከረም 13 ቀን 2013 ዓ.ም.
የኃይል ሽያጭ ስምምነት ተደረገ
………………..////…………………
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኃይል ሽያጭ ስምምነት አደረጉ፡፡
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ እና የኢትየጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈረው ተሊላ ተፈራርመዋል፡፡
ትናንት በተካሄደው የፊርማ ሥነ-ስርዐት ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ እንደተናገሩት ስምምነቱ ተቋማቱ በተሻለ መንገድ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡና የጋራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡
ተቋማቱ በኃይል ኔትወርክ የተገናኙ እንደመሆናቸው ስምምነቱ ያላቸውን ቅንጅትና ትብብር የበለጠ ለማጠናከር እና የስራ አፈጻጸማቸውን ለማሻሻል የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈረው ተሊላ በበኩላቸው መስሪያ ቤቶቹ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በህግ በተወሰነው አግባብና በስምምነታቸው መሰረት እንዲወጡ እንደሚያስችላቸው ነው ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማርኬቲንግ እና ገበያ ልማት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ታምራት እንደተናገሩት ስምምነቱ የሁለቱ ተቋማትን የኤሌክትሪክ ግብይት በህግ አግባብ ለማከናወን ያስችላቸዋል፡፡
በተቋማቱ መካከል ቀደም ሲል የነበረው የኤሌክትሪክ ግብይት በ40/60 ሽያጭ ስምምነት ላይ የተመሰረተ ሲሆን የአሁኑ ስምምነት ግን የቀድሞውን አሰራር በመለወጥ በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች በሚገጠም ቆጣሪ ንባብ ላይ ተመስርቶ የሚከናወን ይሆናል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric
መስከረም 13 ቀን 2013 ዓ.ም.