EEP Communication
15.6K subscribers
10.9K photos
33 videos
32 files
2.03K links
EEP Communication
Download Telegram
በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደርና አካባቢው ኃይል ተቋርጧል
................///////..................
ትናንት ማምሻውን የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደር በወንዝ አቅራቢያ የሚገኝ አንድ የባለ 132 ኪሎ ቮልት ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ በጎርፍ በመውደቁ ዛሬ ከእኩለ ቀን ጀምሮ በአካባቢው ኃይል ተቋርጧል፡፡
የወደቀውን የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ በሌላ ለመተካት እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡
የወደቀውን ምሰሶ ሙሉ በሙሉ ለማቆም ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም ከኮተቤ ከሚወጣ መስመር ጋር በጊዜያዊነት በማገናኘት አካባቢው ነገ ኃይል እንዲያገኝ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡
በኢንደስትሪ መንደሩና ከዚህ ጋር በተገናኘ ኃይል በተቋረጠባቸው አካባቢዎች ያላችሁ ነዋሪዎች ችግሩን ለመፍታት የጀመርነውን ጥረት በመገንዘብ በትዕግስት እንድትጠብቁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጥሪውን ያቀርባል፡፡
አሁን ችግር በደረሰበት አካባቢ ሰኔ ወር አጋማሽ ላይ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶ በዘራፊዎች ተፈቶና ተቆርጦ በመውደቁ የቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደርና አካባቢው ኃይል ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/?modal=admin_todo_tour
ነሐሴ 21 ቀን 2012 ዓ.ም.
በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደርና አካባቢው የተቋረጠውን ኃይል ለመቀጠል ርብርብ እየተደረገ ነው
................///////..................
በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደር በወንዝ አቅራቢያ የሚገኝ አንድ የባለ 132 ኪሎ ቮልት ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ በጎርፍ በመውደቁ ምክንያት ከትናንት እኩለ ቀን ጀምሮ የተቋረጠውን ኃይል ለመቀጠል ርብርብ እየተደረገ ነው።
የአካባቢው መስመር ከኮተቤ ከሚወጣ መስመር ጋር በጊዜያዊነት በማገናኘት እስከ ማምሻው ድረስ ኃይል እንዲያገኝ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/?modal=admin_todo_tour
ነሐሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም.
የተቋረጠውን ኃይል ለመቀጠል የተጀመረው ርብርብ በከባድ ዝናብ ውስጥም ቀጥሏል
................///////..................
በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደርና በአካባቢው የተቋረጠውን ኃይል ለመቀጠል እየተደረገ ያለውን ርብርብ በአካባቢው እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብና መብረቅ እያስተጓጎለው ቢሆንም ርብርቡ ቀጥሏል።

አካባቢው ኃይል ያገኝ የነበረበትን የቀድሞ መስመር ከኮተቤ ከሚወጣ መስመር ጋር በጊዜያዊነት በማገናኘት እስከ ማምሻው ድረስ ኃይል እንዲያገኝ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

ይሁንና እየጣለ ያለው ዝናብ እና የመብረቅ ብልጭታ በመስመሩ ውስጥ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ንዝረት በመፍጠር የጥገና ባለሙያዎች ስራቸውን በተገቢው እንዳያጠናቅቁ እንቅፋት እየሆነ ነው፡፡

መስመሩን ለማገናኘት አሁንም ጥረት የቀጠለ መሆኑን በመገንዘብ ክቡራን ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ነሐሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም.
የቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደርና አካባቢው ኃይል አግኝቷል
................///////..................
በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደር በወንዝ አቅራቢያ የሚገኝ አንድ የባለ 132 ኪሎ ቮልት ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ በጎርፍ በመውደቁ ምክንያት የተቋረጠውን ኃይል ለመቀጠል ሲደረግ የነበረው ርብርብ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
በምሰሶው መውደቅ ምክንያት በአካባቢው ላለፉት ሁለት ቀናት ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል።
በእነዚህ ቀናት ከነበረው ከባድ ዝናብና የመብረቅ ብልጭታ ከሚፈጥረው ከባድ ንዝረት ጋር በመታገል መስመሩን ላገናኙ የጥገና ባለሙያዎቻችን ላቀ ያለ ምስጋናችንን እያቀረብን የአካባቢው ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞችም በትዕግስት ስለጠበቃችሁን ከልብ እናመሰግናለን።
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/?modal=admin_todo_tour
ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም.
አዋሽ III የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለጊዜው አገልግሎቱን አቋረጠ
…………./////………..
በአዋሽ III የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ በማጋጠሙ ከቅዳሜ ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ጣቢያው ለጊዜው አገልግሎት ማቋረጡን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአዋሽ II እና III ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዲሳሳ ገልሜሳ አስታውቀዋል፡፡
ላለፉት 49 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየውና 32 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የአዋሽ III የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በውሃ መጥለቅለቅ አደጋ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት መስጠት አቁሟል፡፡
ከተርባይን ወለል እስከ ተርባይን ሮተር ማገናኛ ዘንግ (Turbine Rotor Coupling Shaft) ድረስ ያሉት የኤሌክትሮ-መካኒካል እቃዎች በውሃ በመዋጣቸው የጉዳቱን መጠን ለማወቅ እንዳልተቻለ አቶ ዲሳሳ ተናግረዋል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/?modal=admin_todo_tour
ነሐሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም.
ተንሳፋፊ ሳርና የመለዋወጫ አቅርቦት እጥረት የጣቢያው ስጋት እየሆኑ ነው ተባለ
--------------/////////----------------
የበለስ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ተንሳፋፊ ሳርና የመለዋወጫ አቅርቦት ስራውን እያስተጓጎለበት መሆኑን የጣቢያው ኃላፊ ገለፁ፡፡
ኃላፊው አቶ ፍቃዱ ደምሴ እንደገለፁት ወደ ጣቢያው የውሃ መቀበያ እየተገመሰ የሚመጣው ተንሳፋፊ ሳር ለኃይል ማመንጫው የኦፕሬሽን ሥራ ከፍተኛ ስጋት እየሆነ ነው፡፡
ተንሳፋፊ ሳሩ ከሐምሌ 9-11 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ የኃይል ማመንጫ ጣቢያውን እስከማስቆም ደርሶ እንደነበረ የገለፁት ኃላፊው ባለፈው ዓመትም በተንሳፋፊ ሳሩ ምክንያት ከ10 ቀን በላይ ጣቢያው መቆሙን አስታውሰዋል፡፡
ጣቢያውን መልሶ ሥራ ለማስጀመር ኤክስካቬተር በመከራየትና ዋና በሚችሉ የጣቢያው ሠራተኞችን በመጠቀም የኃይል ማመንጫውን ውሃ መቀበያ የዘጋውን ተንሳፋፊው ሣር ለጊዜውም ቢሆን በማስወገድ ሥራ ማስጀመር መቻሉን አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል፡፡
ጣቢያውን ከተንሳፋፊ ሳር ለመጠበቅ የሚያግዝ መከላከያ (Taff Boom) ያለው ቢሆንም በዘንድሮ ዓመት ከሃይቁ ዳር እየተገመሰ የሚመጣው የሳር ደሴት መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ ቀደም ሲል የተገጠመው መከላለያ ሊመልሰው አልቻለም፡፡
በመሆኑም በየጊዜው ወደ ኃይል ማመንጫው ለሚመጣው ተንሳፋፊ ሳር ዘላቂ መፍትሄ ካልተሰጠው በቀር ጣቢያውን እስከ መዘጋት ሊያደርሰው እንደሚችል አብራርተዋል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/?modal=admin_todo_tour
ነሐሴ 27 ቀን 2012 ዓ.ም.
የገናሌ ዳዋ 3 የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ዓለምአቀፍ ትኩረት ስቧል
……………/////………..
የኤሌክትሪክ ዘርፍ ተሸላሚው የገናሌ ዳዋ 3 ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክን ለሁሉም ለማዳረስ እገዛ እያደረገ መሆኑን ፓወር የተሰኘው በኃይል ላይ በማተኮር የሚዘጋጀው ዓለምአቀፍ መጽሔት ዘግቧል፡፡
ከህዝቦቿ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ኤሌክትሪክ የማያገኙባት ኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ አቅርቦት እየተሻሻለች መምጣቷን መጽሔቱ በዝርዝር አትቷል፡፡
መፅሔቱ ይፋ እንዳደረገው የገናሌ ዳዋ 3 ፕሮጀክት መንግስት እ.ኤ.አ እስከ 2025 በመላው ሀገሪቱ ኤሌክትሪክ ለማስፋፋት የሚደረገውን የያዘውን ዕቅድ ለማሳካት እገዛ ማድረግ ጀምሯል፡፡
በ3 ተርባይኖች 254 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የገናሌ ዳዋ 3 የኃይል ማመንጫ ተመርቆ ስራ የጀመረው በተያዘው ዓመት አጋማሽ ላይ ነበር፡፡
ይህን ሊንክ በመጫን ዝርዝር ዘገባውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
https://www.powermag.com/award-winning-hydropower-project-helps-electrify-ethiopia/
የታላቁ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሰራተኞች የ የበጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆኑ
*****************//////*****************
የታላቁ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሰራተኞች የ2012 ዓ.ም የበጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆኑ።
ሽልማቱ የተበረከተው የግድቡ መሰረት ድንጋይ ከተጣለበት ከመጋቢት 24/2004 ዓ.ም ጀምሮ በጉባ በሥራ ላይ ለሚገኙ የግድቡ ሰራተኞችና ጸጥታውን ለሚቆጣጠሩ የመከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፓሊስ አባላት ነው።
በጉባ የሚገኙ ሰራተኞችን ወክለው የታላቁ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ሽልማቱን ተረክበዋል፡፡
በአባይ ፖለቲካ ላይ የተለያዩ ጥንቶችን ያደረጉት ዶ/ር ያዕቆብ አርሳኖ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የጤና ባለሙያዎችና የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች እንዲሁም የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአረብኛ የኢትዮጵያን አቋም በተለያዩ መድረኮች በማንፀባረቅ የሚታወቀው መሀመድ አል አሩሲ የ8ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/?modal=admin_todo_tour
ጳጉሜ 02 ቀን 2012 ዓ.ም
አዋሽ II የኃይል ማመንጫ ጣቢያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
…………./////………..
በእንቦጭ አረም በመዘጋቱ አገልግሎት ለጊዜው አቋርጦ የነበረው የአዋሽ II የውኃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

የእንቦጭ አረሙ የውሃ መቀየሻ ግድብ ላይ በመተኛቱ የተነሳ የውሃ መቀበያው (water intake) አገልግሎቱ ተቋርጦ ቆይቷል፡፡

አረሙን ከወንጂ ስኳር ፋብሪካ በተገኘ ኤክስካቫተር የማንሳት ሥራ ሲከናወን ቆይቶ የውሃ መቀበያው በመከፈቱ የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ከአርብ ነሐሴ 29 ጀምሮ ዳግም ኃይል ማምረት ጀምሯል፡፡

32 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው አዋሽ II የኃይል ማመንጫ ጣቢያ አገልግሎት መስጠት የጀመረው እ.ኤ.አ. በ1966 ዓ.ም ነበር፡፡

የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/?modal=admin_todo_tour
ጳጉሜ 02 ቀን 2012 ዓ.ም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስመ ጥር ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የሀገራችንን አቋም የሚያሳይ ቪድዮ ተለቀቀ።
EEP new year 2013.mpg
384.2 MB
እንኳን ለ2013 ዓ.ም. በሰላም አደረሳችሁ!!
አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የጤናና የብልፅግና እንዲሆንላችሁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይመኛል!!
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
🌻🌻 መልካም 🌻🌻
🌻🌻 አዲስ 🌻🌻
🌻🌻 ዓመት 🌻🌻
🌻🌹🌾🌻💐🌷🌻
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊