The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus - EECMY
3.48K subscribers
7.52K photos
32 videos
9 files
141 links
The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus (EECMY) is a national Lutheran church with more than 10 million members.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ እስቲዋርድሽፕ እና ቸርች ኤኮኖሚ ቦርድ ለ22ኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ ካውንስል፤ ከባንኮች የመበደር መመሪያ ማሻሻያ በቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ዬሴፍ ብርሀኑ አቅርቧል።

ካውንስሉም በቀረበው ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ከተወያየ በኋላ በሙሉ ድምጽ ተቀብሎ አጽድቋል።

ቀጣይ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዘገባዎች ለመከታተል የሚከተሉትን አካውንቶች ፎሎ በማድረግ ይከታተሉ:-

Facebook - https://www.facebook.com/share/1GDpuFoseh/
Telegram - https://t.me/EECMYeth
YouTube News- https://youtube.com/@mekaneyesusofficial?si=cPuWOIVvHYDI01nd
YouTube Education - https://youtube.com/@mekaneyesus1959?si=0XKpyBECeLaTIZFg
በአባታችን ቄስ ተስፋ ጅሬን ዜና እረፍተ የተሰማንን ሀዘን እንገልጻለን።
* * ***
ቄስ ተስፋ ጅሬን ከልጅነታቸው አንስቶ በቤተ ክርስቲያኒያኒቱ ውስጥ ያደጉ፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርታቸውን የተከታተሉ እና ከዚያም በመምህርነት ህብረተሰባቸውን ያገለገሉ አባት ነበሩ።

ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሙሉ ጊዜ ሰጥተው እንዲያገለግሉ በቀረበላቸው ጥሪ መሠረት፤ ከወንጌላዊነት አንስቶ በበርካታ እርከኖች እና ሃላፊነቶች ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል። ቄስ ተስፋ የቅስና ሀላፊነት ተቀብለው ሙሉ የእረኝነት አገልግሎት መስጠት የጀመሩት በ1968 ዓ.ም በቦጂ ድርመጂ እናት ማህበረ ምዕመናን ነበር።

እስከ 1991 ዓ.ም በኖሌና ዴጌሮ ሰበካዎች የእግዚአብሔር ቃል በማስተማር እና ሰበካዎቹን በመምራት አገልግለዋል። ቀጥለውም 1991-1994 የምዕራብ ሲኖዶስ የወንጌል እና ቲኦሎጂ መምሪያ ዳይሬክተር፤ የቀድሞ የምዕራብ ሲኖዶስ ወደ አራት ሲኖዶስ ከተከፋፈለ በኋላ እንደ አዲስ በተዋቀረው የምዕራብ ሲኖዶስ ከ1994-2002 የመጀመሪያው ጠቅላይ ጸሐፊ ሆነው በትጋት እና በታማኝነት ቤተክርስቲያንን አገልግለዋል። በአገልግሎት ዘማናቸውም በሲኖዶሱም የሥነ መለኮት ኮሌጅ አስተምረዋል።

አባታችን ቄስ ተስፋ በጡረታ ከተገለሉም በኋላ በቤተ ክርስቲያኒቱ ህይወት እና አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራቸው አባት ሲሆኑ የእረፍት ጊዜያቸውን በመጠቀም በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ <<BOOJJI KARKARROO IDDOO BARNOOTA AMMAYYAA FI WANGEELLI CAAFFATA AFAAN OROMOO ITTI JALQABE >> የተሰኘን ታሪካዊ መጽሐፍ በመጻፍ ለትውልድ አሻራ ጥለው አልፈዋል።

የቤተሰባቸውም ሁኔታ ባለ ትዳር እና የአራት ልጆች አባት ነበሩ።

ቄስ ተስፋ ጅሬን በተወለዱ በ80 ዓመታቸው ከዚህ አለም ድካም ያረፉ ሲሆን፤ የሽኝታቸውም ሥነ ሥርዓት በትውድ ሥፍራቸው ቦጂ ድርመጂ ቤተሰቦቻቸው፤ ወዳጅ ዘመዶች እና ከፍተኛ የሲኖዶሱ መሪዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

የቤተ ክርስቲያኒቱም 22ኛ ካውንስል በዘመናቸው ስለ ሰጡት አገልግሎት ጌታን አመስግኖ ለቤተሰባቸውም መጽናናት ጸልዮአል።
👍2
ኑሮአቸውን በአሜሪካ ያደረጉት የቀድሞ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የክብር ፕሬዚዳንት ቄስ ያደሳ ዳባ በስኬት የተጠናቀቀውን 22ኛ የቤተ ክርስቲያኒቱን ካውንስል ስብሰባ አስመልክቶ የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን ልከዋል።

አስቀድመው ቤተ ክርስቲያኒቱ ያካሄደችው 22ኛ የካውንስል ስብሰባ በተለያዩ ሀላፊነቶች አዳዲስ መሪዎችን በመምረጥ በስኬት ስለመጠናቀቁ መልካም ዜና መስማታቸውን ገልጸዋል።

ለዚህም ውጤት አንድ ላይ በመቆም ወደዚህ ስኬት ለደረሱና የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች ለሆኑት፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ፤ ምክትል ፕሬዚዳንት፤ አቃቤ ንዋይ፤ ጠቅላይ ጸሐፊ፤ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ እና መላውን የካውንስሉን አባላት፤ እንኳን ለዚህ አበቃችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን እና አድናቆታቸውን አስተላልፋዋል።

የክብር ፕሬዚዳንቱ በላኩት አባታዊ መልዕክት፤ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በአንድ መንፈስ አንድ ላይ በመቆም አስፋላጊ ውሳኔዎችን ሲወስኑ ማየት አስደሳችና አበረታች መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ከዚህ ቀደም ስለ ሰራው እና አሁንም በመስራት ላይ ስላለው ነገር ሁሉ ክብርና ምስጋና ለእግዚአብሔር አቅርበዋል።

እግዚአብሔር እቺን ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ እና በመላው አለም ምስክር እንዳደረጋት እምነታቸው መሆኑን በመልዕክታቸው አስፍረዋል። እናም እግዚአብሔር ታላቅ ያደረገውን የትኛውም ፍጥረታዊ ሰው ዝቅ እንዳያደርግ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር በአገልጋዮቹና በህዝቡ በዚች ቤተ ክርስቲያን የሰራውን እና እየሰራ ያለውን ታላቅ ነገር በሰዎች ድካም እንዳይመዘን አሳስበዋል።

በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያኒቱ በአንድነት መንፈስ፤ በአካታችነት፤ በታማኝነት፤ በትዕግሥት፤ በፍትህ፤ በሰላምና በመግባባት ሁለንተናዊ አገልግሎቷን እንድትቀጥል ፀሎታቸው እና መልካም ምኞታቸው መሆኑን ገልጸዋል።
7🕊2
በደቡብ አፍሪካ የተካሄደው የመላው አፍሪካ ሉተራዊያን አብያተ ክርስቲያናት የ2026 የመሪዎች ምክክር ስብሰባ በስኬት ተጠናቋል።
** **
ከመላው አፍሪካ የሉተራን አብያተ ክርስቲያናት ተወክለው የመጡ 72 መሪዎች የተሳተፉበት የመሪዎች የምክክር ስብሰባ በደቡብ አፍሪካዋ የጆሀንስበርግ ከተማ ተካሂዷል።

በደቡባዊ አፍሪካ የሚገኙ ወንጌላዊያን ሉተራዊያን አብያተ ክርስቲያናት አዘጋጅነት ከነሐሴ 18-22 / 2018 ዓ.ም በተካሄደው ምክክር፤ መሪዎቹ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን በውይይታቸው ዳሰዋል። በዋነኛነትም የወንጌል አገልግሎትና ማዳረስ፤ የሰላም ግንባታ እና በአህጉረ አፍሪካ በአብያተ ክርስቲያናቱ በትብብር መሠራት የሚችሉ ጉዳዮች በምክክሩ ተነስተዋል።

በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያን አለምአቀፋዊነቷን ተከትሎ፤ አጥባቂ የአፍሪካ ሉተራን አብያተ ክርስቲያናት በጋራ በተቀረው አለም ላይ ያላቸውን የትብብር ግንኙነቶች በመጠቀም ተጽዕኖ መፍጠር እንደሚገባቸው በመድረኩ የተነሳ ሲሆን ጉዳዩንም በሚመለከት መሪዎቹ በሰፊው መክረዋል።

በዚህም የምክክር ስብሰባ የመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ፕሬዚዳንትዋን ጨምሮ በአምስት ልኡካን የተወከለች ሲሆን የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ መሪዎችና ልኡካኑ በሰላም ወደ ሀገር ተመልሰዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በሀገራችን፤ በአፍሪካ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ቀደምት እና ግዙፍ ከሆኑ ሉተራዊ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ተጠቃሽ ነች። ይህንንም ተከትሎ ቤተ ክርስቲያኒቱ በተለያዩ አለም አቀፍ የትብብር ግንኙነቶች ዙሪያ ታሪካዊት እና የበርካታ ዘመናት ልምዶች ባለቤት ሆናለች። በአሁኑም ሰዓት በተሰጣት እድል ቤተ ክርስቲያኒቱ በፕሬዚዳንትዋ በኩል የአፍሪካ ሉተራዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትን እየመራች ትገኛለች።
4👍4