EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
134K subscribers
42.1K photos
483 videos
80 files
13.5K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
**************

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰው ልጆች እና በአምላክ መካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ አፍርሶ በምህረት፣ በይቅርታ እና በታላቅ ፍቅር ወደ ምድር መምጣቱ ሰላምን እና ፍቅርን ለምድር እንዲሁም አብሮነት እንዲጎለብት ምሳሌ ለመሆን ነው ብለዋል::

ስለዚህ በዓሉን ስናከብር የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌነትን በመከተል የሰላም እሴቶችን እየገነባን፣ ፍቅራችንን ይበልጥ እያጎለበትን እንዲሁም አብሮነታችንን እያጠናከርን ሊሆን ይገባል ሲሉም አስፍረዋል::

በዓሉን ስናከብር ያላቸው ለሌላቸው ማዕድ በማጋራት ፍቅር፣ መተሳሰብና አብሮነት በሚገለጽበት መልክ እንዲሆን ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከንቲባዋ በዓሉ የሰላም እና የደስታ በዓል እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡
17👍6👎2
ከንቲባ ከድር ጁሀር ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
********************

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከንቲባው በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት የሚከበረው የገና በዓል የስጦታ እና የልግስና በዓል መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም በዓሉን ስናከብር በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ ወገኖችን በተለይም ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው አቅመ ደካማ አረጋውያንን ፣ ወላጆቻቸውን በተለያዩ ምክንያቶች ያጡ ህጻናትን ፣ ታምመው አልጋ ላይ የዋሉ ሕሙማንን በማሰብና የበዓሉ ደስታ የእነሱም እንዲሆን በማድረግ ልናሳልፍ ይገባል ብለዋል።

ከንቲባው በዓሉ የሰላም የፍቅር ፣ የጤና ፣ የብልጽግና የመደጋገፍና የመተጋገዝ ይሁንልን ሲሉም መልካም ምኞታቸውን መግለጻቸውን የአስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመልክታል።
👍228👏5
የገና በዓል ገበያ ድባብ በአዲስ አበባ
*************

በአዲስ አበባ በጉለሌ እና ሾላ ገበያ አካባቢዎች የቁም እንስሳትና የተለያዩ የምግብ ፍጆታዎች ግብይት በፎቶ፡-

📷 ኢቢሲ ዶትስትሪም
👍132
የአቶ ቡልቻ ደመቅሳ የአደራ መልእክት

"ከዚህ ምርጫ በኋላ ለአገሬ የምመኘው ሰላም፣ አንድነት እና ብልፅግና ነው፡፡ እኔም በ91 ዓመቴ በምርጫው የተሳተፍኩኝ ሲሆን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የማስተላልፈው መልእክት የአገሪቱን ሰላምና አንድነት እንድትጠብቁ አደራ እላለሁ፡፡ አገር ከፖለቲካ ፓርቲዎች በላይ ናት፡፡"

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስተላለፉት መልእክት
41👍24👎4
6ተኛው የሕዋ ኢንተርንሺፕ ፕሮግራም በይፋ ተጀመረ
*****************

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ 6ተኛው የሕዋ ኢንተርንሺፕ ፕሮግራም በይፋ ተጀምሯል፡፡

የፕሮግራሙን መጀመር የሶሳይቲው የበላይ ጠባቂ አቶ ደመቀ መኮንን እና የቀድሞ የበላይ ጠባቂ አቶ ተፈራ ዋልዋ ይፋ አድርገዋል፡፡

ፕሮግራሙ ወጣቶች ያላቸውን ዕምቅ ችሎታ በሕዋው ዘርፍ ላይ ማፍሰስ እንዲችሉ ምቹ መድረክ እንደሚፈጥር አቶ ደመቀ መኮንን ተናግረዋል፡፡

አቶ ተፈራ ዋልዋ በበኩላቸው ፤ አዳዲሶቹ ኢንተርኖች የወጣትነት ጊዜያቸውን ለሀገራቸው በዘርፉ የተሻለ ነገር ለማበርከት ማዋል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ ስለ ኢንተርንሺፕ ፕሮግራሙ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን አዳዲሶቹ ኢንተርኖችም ከቀድሞ የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ጋር የልምድ ለውውጥ አካሂደዋል፡፡

ወጣቶች በህዋው ዘርፍ ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ታልሞ በተዘጋጀው በዚህ ፕሮግራም ላይ 50 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና አዲስ ምሩቃን እንደሚሳተፉ ተመላክቷል፡፡
5👍3
በዓሉን የሰላም እሴቶችን በማጉላት ማክበር ይገባል - አቶ መሐመድ እድሪስ
***********************

የገና በዓልን በመረዳዳት እና የሰላም እሴቶችን በማጉላት ማክበር እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዓሉን በመከባበር፣ በመረዳዳት እና በመተሳሰብ ማሳለፍ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
12👍5