E͜͡t͜͡h͜͡i͜͡o͜͡ M͜͡. A͜͡l͜͡l͜͡e͜͡g͜͡a͜͡t͜͡i͜͡o͜͡n͜͡ H͜͡u͜͡n͜͡t͜͡e͜͡r͜͡s͜͡
376 subscribers
50 photos
12 videos
18 files
96 links
Download Telegram
ይህ በሰሜን ምዕራብ ቻይና ኪንኻይ ግዛት ውስጥ የሚገኘው ከ12 ክፍለዘመን በፊት የነበረ (ከ1100 ዓመት በላይ እድሜ ያለው) የቁርዓን እደ-ክታብ ነው። ሙሉ የቁርዓንን ጹሑፍ "text" የያዘ ሲሆን ወደ 867 ገፆች አሉት። እስካሁን ካየኁዋቸው የቁርኣን እጅ-ጹሑፎች ይህኛው በጣም ያምራል :)

(🌐CGTN:- China's oldest Koran manuscript 09-Feb-2019)

https://t.me/mahircomp123
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ፣ በጣም አዛኝ በሆነው።

{إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ}

“እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡”
[📖 አል-ሒጅር ፣ 17÷9]

Kaፊሮች ስለ ቅዱስ ቁርአን አጠባበቅ ለማጉደፍ ሲሞክሩ አንዳንድ የአንቀፅ፣ የቃላትና ፊደላት አቆጣጠር ልዩነቶችን ከሙስሊም ትውፊቶች እየመዘዙ አሉታዊ ትርጓሜያቸውን በመጫን ወደ እውር ድምዳሜያቸው ሲሻገሩ ይስተዋላሉ!

◉ ‹አል-ኢትቃን፣ ፊ ኡሉም አል-ቁርአን ቅጽ 1፣ ገጽ 88› ላይ ዑመር(ረ.ዐ) ሲናግር ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፤- ቁርአን 1,027,000 ፊደላትን የያዘ ነው፡፡

◉ ‹ተፍሲር ኢብን ከሲር ቅጽ 1፣ ገጽ 36› ላይ
ዓታ ቢን የሳር ➪ ቁርአን 77,439 ቃላትን ይዟል
ሙጃህዲን ➪ ቁርአን 321,180 ፊደላትን ይዟል
ዓላ ቢን የሳር ➪ ቁርኣን 323,015 ፊደላትን ይዟል
አል-ሐጃጅ ➪ የቁርአኑን ሓፊዞችን ጠይቆ 340,740 ፊደሎች ነው አሉት፡፡

◉ ‹አል-ኩላይኒ አል-ካፊ ቅጽ 2፣ 14 ፡ 28› ላይ አቡ አብደላ /አል-ሳዲቅ ሲናገር፡- ገብርኤል ወደ ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ያመጣው ቁርአን 17,000 አንቀጾች ነበሩት፡፡


❐ ከዚህ ተንተርሰውም ቁርኣን ቆጠራ ላይ ልዩነቶች ስላሉት ከብርዛት አልተጠበቀም ይላሉ። በመጀመርያ ደረጃ በቁርኣን ኣያት(አንቀፆች) ፣ ከሊማት(ቃላት) እና ሑሩፍ(ፊደላት) የቆጥራ ልዩነቶች የታዩት

❶, አንዳንድ ትርክቶች ሰነዳቸው ዷዒፍ ስለሆነ
❷, ቁርኣን በሰባት አይነት አሕሩፍ ስለወረደ
❸, በስመላን(ቢስሚላህ አር-ረሕማን አር-ረሒማ) በፈቃደኝነት ጨምረው የደመሩ እንዲሁም ያልደመሩም ስለነበሩ
❹, ሁለት ቃላትን አጣምረው እንደ አንድ የቆጠሩ እንዲሁም ሌሎች ለየቅል እንደ ሁለት አርገው የቆጠሩም ስለነበሩ
(ለምሳሌ - ‘فِی ٱلسَّمَاۤءِ’ ፊ አስ-ሰማኢ /ፊስ-ሰማኢ)
❺, ተሽዲድ ያላቸው ፊደላትን እንደሁለት ለየቅል ፊደላት አርገው የቆጠሩ እንዲሁም ሌሎች ያልቆጠሩም ስለነበሩ
(ለምሳሌ - ‘عَلَّمۡنَـٰه’ ዐልለምናሁ /ዐለምናሁ)
❻, አንዳንድ ትውፊቶች የሺዓ መዛግብት ናቸው
(ለምሳሌ - አል-ኩላይኒ አል-ካፊ መጽሐፍ)
❼, በመጨረሻም እነዚያ ቁርኣንን የቆጠሩት ሑፋዞች መነሻቸው ከየት እንደሆነ ማወቁ ተገቢ ነው
(ለምሳሌ - አንድ ሰው ከአዲስ አበባ እስከ ባህርዳር 321 km ነው ብሎ ሌላ ሰው 490 km ነው ቢል ሁለቱም ሲለኩ መነሻቸው ከየት እንደሆነ ማወቁ ሰናይ ነው።)


🎯 “የቁርአን ፊደላት 1,027,000 ነው” የሚለውን በተመለከተ ዘጋቢው ሙሐመድ ኢብኑ ዑበይድ ሲሆን ትርክቱ

አዝ-ዘሀቢይ ➪ «ባጢል ትርክት» ነው ብሏል። ¹
አስ-ሱዩጢይ ➪ «ዷዒፍ» ነው ብሏል። ²
አል-አልባኒይ ➪ «መውዱዕ» ነው ብሏል። ³ በተጨማሪም «ባጢል» ነው ብሏል። ⁴

🎯 “እንዲሁም ቆጠራ ላይ ልዩነቶች የታዩበት ምክንያትን በተመለከተ አዝ-ዘርከሺይ በቡርሃን መጽሐፉ ላይ እንዲህ ሲል ያትታል :- «ሊቃውንቶች በአንቀፅ ፣ ቃላት እና ፊደላት ቆጠራ ላይ የመለያየታቸዉ ምክንያት የሆነው ፣ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሲያነቡ በአያ(አንቀፅ) መጨረሻ ላይ ይቆሙ ነበር ፣ ሰሚው ግን እንደ አንቀፅ ማጠናቀቂያ አርጎ አይቆጥረውም ፣ እንዲሁም ደግሞ በስመላህ በአንዳንድ ከሰባቱ አሕሩፍ(ፊደላት) አቀራር ውስጥ ከምዕራፉ ጋር ወርዳለች ፣ በዛ ሐርፍ ያነበበ ሰውም (በስመላውን) ይቆጥረዋል ፣ ከዚያ ውጭ የሚያነብም ሰው አይቆጥርም።»” ⁵

فَإِذَا عُلِمَ مَحَلُّهَا وَصَلَ لِلتَّمَامِ فَيَحْسَبُ السَّامِعُ أَنَّهَا لَيْسَتْ فَاصِلَةً، وَأَيْضًا الْبَسْمَلَةُ نَزَلَتْ مَعَ السُّورَةِ فِي بَعْضِ الْأَحْرُفِ السَّبْعَةِ فَمَنْ قَرَأَ بِحَرْفٍ, نَزَلَتْ فِيهِ عَدَّهَا، وَمَنْ قَرَأَ بِغَيْرِ ذَلِكَ لَمْ يَعُدَّهَا. انتهى.
https://quranpedia.net/ar/book/240/1/252


🎯 “መጅድ አድ-ዲን አል-ፈይሩዘባዲ እንዲህ ብሏል:- «የቁርአን ሱራዎች ብዛት - በስምምነት - አንድ መቶ አስራ አራት መሆናቸውን እወቁ። ስለ ጥቅሶች ብዛት - አብዛኛው የአገሪቱ ሕዝብ እና የቀደሙት ኢማሞች ከሊቃውንት እና ከአንባቢዎች መካከል በቁርአን እና በእውቀቱ መስክ በጣም ጠንቃቃ ነበሩ ፣ ምንም ቃል እና ትርጉም አልቀረም በውስጡ ቢፈለጉ እንጂ ፤ አንቀፆችን ፣ ቃላቱን እና ፊደሎችን እንኳን ሳይቀር ቆጥረዋል ፣ ቢሆንም በአንባቢዎች መካከል ልዩነት አለ፡፡ ግን ልዩነቱ በቃል ደረጃ እንጂ በእውነቱ አይደለም ፣ ለምሳሌ የኩፋ አንባቢዎች "የክብር ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ(38:1)" የሚለውን ነጥለው ለብቻ እንደ አንድ አያ(አንቀፅ) አርገው ቆጥረዋል። ሌሎቹ ግን ነጥለው እንደ አንድ ኣያ(አንቀፅ) አርገው አልቆጠሩትም።

የኩፈህ አንባቢያን “قَالَ فَالْحَقُّ وَالْحَقَّ أَقُولُ.(38:84)” የምትለዋን ነጥለው እንደ አንድ ኣያ(አንቀፅ) ቆጥረዋታል ፣ ሌሎችም ያልቆጠሯት አሉ። ሌሎችም የኣያዋ መጨረሻ “بَلِ الَّذِينَ كَفَرُوا فِي عِزَّةٍ وَشِقَاقٍ.(38:2)” የምትለዋን አደረጉ። ሌሎችም لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنكَ وَمِمَّن تَبِعَكَ مِنْهُمْ“ أَجْمَعِينَ(38:85)” የሚለውን የኣያዋ ማጠናቀቂያ አርገው ቆጥረዋል።

የመካ ፣ መዲና ፣ ኩፈህ እና ሻም ሰዎችም በዚሁ መንገድ የአያዋ ማጠናቀቂያ ”وَالشَّيَاطِينَ كُلَّ بَنَّاءٍ وَغَوَّاصٍ.(38:37)“ አድርገው ቆጥረዋል።

የበስረህ ሰዎችም የአያዋ መጨረሻ
”وَآخَرِينَ مُقَرَّنِينَ فِي الْأَصْفَادِ.(38:38)“አድርገው ቆጥረዋል።
ያለ ምንም ጥርጥር ፣ ይህ መንገድ አቆጣጠር ልዩነት እንጂ የቁርአን ልዩነት አይደለም ፣ እናም ከዚህ የተነሳ በአንዳንዶቹ ዘንድ የቁርአን አንቀጾች በቁጥር በለጡ ፣ በአንዳንዶቹም ዘንድ ደግሞ ያነሱ ነበሩ፡፡ እንጂ ከፊሎች እየጨመሩበት ከፊሎቹም እየቀነሱበት ነው ማለት አይደለም። በቁርአን ላይ መጨመርም ሆነ መቀነስ ኩFርና ግብዝነት ነው። እንዳሁም የማይቻል ነውም አላህ(ሱ.ወ) - "እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡" ብሏልና።

በአንቀፆቹ ውስጥ ይህንን ደንብ ካወቅን፡፡ በቃላት እና በፊደላት ላይም የነበራቸው ልዩነት ተመሳሳይ ነው ፣
አንዳንድ አንባቢዎች “فِی ٱلسَّمَاۤءِ(በ ሰማይ)" እና “فِی ٱلۡأَرۡضِ(በ ምድር)” እና “فِی ٱلۡخَلۡقِۚ(በ ፍጥረት)” የመሳሰሉትም ነጣጥለው እንደ ሁለት ለየ ቅል ቃላት አድርገው ቆጥረዋ ፣ “ፊ(በ)” አንድ ቃል ፣ “ሰማኢ(ሰማይ)” እንደዛው አንድ ቃል ነው እያሉ። ሌሎች ግን "በ" እና "ሰማይ" የሚሉትን በአንድ ላይ አጣምረው "ፊ አስ-ሰማኢ" እንደ አንድ ቃል አድርገው ቆጥረዋል ከዚም የተነሳ ነው "ፊ አስ-ሰማኢ" እንደ ሁለት ቃል አድርገው የቆጠሩት በነሱ ዘንድ የቁርአኑ ቃላት በቁጥር በልጦ የተገኘው ልዩነትም የመጣው።

ስለ ፊደሎቹ በተመለከተም አንዳንድ አንባቢዎች ተሽዲድ(ሸዳ) የነበራቸውን ፊደላት እንደ ሁለት ለየ ቅል ፊደላት አድርገው ቆጥረዋል ፣ ለዛም ነው በነሱ ዘንድ የቁርአን ፊደሎቹ በቁጥር በልጠው የተገኙት፡፡»” ⁶
ማጣቀሻ 📌 -

¹ ‹ሚዛን አል-ኢዕቲዳል፣ 3/939›
² ‹አል-ጃሚዕ አስ-ሰጊር፣ 4/536›
³ ‹ዷዒፍ አል-ጃሚዕ አስ-ሰጊር፣ ቁ.4133›
⁴ ‹አስ-ሲልሲለህ አድ-ዷዒፈህ 9/70›
⁵ ‹አል-ቡርሃን ፊ ዑሉም አል-ቁርኣን 1/252›
⁶ ‹በሳኢር ዘዊ አት-ተምዪዝ ፊ ለጣኢፍ አል-ኪታብ አል-ዐዚዝ ፣ ቅጽ 1 ፣ ገፅ 558-559

በመጨረሻም ክርስትያኖችዬ መጽሐፋችሁ መበረዙን አረጋግጣችሁ በኛ ላይ የእከክልኝ ልከክልህ ስሑት አካሄዳችሁን ትታችሁ እውነትን ብታሰላስሉ ይሻላቹኃል አላህ ሂዳያውን(መመራት) ይስጣችሁ ለኛም ጽናቱን! አሚን...✍︎

የቴሌግራም ቻናላችን

https://t.me/EAAAresponse

የቴሌግራም ግሩፕ

https://t.me/A3E1response

የፌስቡክ ፔጅ

https://www.facebook.com/Ethiomuslimallegationhunters/
◉ ለውሸት ለሁሉ ቅጥፈት የተሰጠ መልስ

የአቡበከር ብልጠትና የቁርኣን ሐሰተኛነት??
                                      

➛ አቡበከር አስ-ሲዲቅ(ረዐ) የመጀመርያው የሙስሊሞቹ ኸሊፋ ሲሆን ነብዩ (ሰዐወ) እንደ ማንኛውም ነብይ በሞት ይችን ምድር ሲለዩ በሰሓቦች ስምምነት ስልጣኑን ተረከበ። በወቅቱም በርካታ አዕራቦች እስልምናን መልቀቅ ጀመሩ ከነሱ መካከልም ሐሰተኛ ነብያትን እነ ሙሰይለማ, ጡለይሓን, አል-አሥወድ እና ሰጃሕን የተከተሉ ሲሆኑ ሌሎችም ፣ ግብዝና መናፍቃን የነበሩ ሰዎች ፣ በነብዩ ሞት እስልምና ያበቃለት የመሰላቸው ሰዎች ፣ ለስጦታ ሲሉ ሙስሊም የነበሩ ጥቅመኞች እና ዘካን ላለመክፈል የሰሰቱ ሰዎች ነበሩ።

➛ አቡበክርም(ረዐ) እነዚህ ሙርተዶች የእስልምና ሀይማኖት ማእከላዊ መሰረት የሆነችዋን መዲና ለማጥቃት መነሳሳታቸውን የሚገልጹ እንቅስቃሴዎችና አማፂያን ዘካን ከሰላት እንደለያዩ ሲደርሰው ለመጋፈጥ ጥምር ኃይል አዘጋጀ በአጋጣሚም 1,200 ሰዎች ከነሱ መካከልም በየማማ ጦርነት ላይ 70 የቁርአን ሓፊዞች ሸሂድ ሆኑ ከዚህ ተነስቶም በመዲና የቀሩት በቁርአን ሃፊዞች አማካኝነት ቁርኣን በጊዜ አንድ ላይ እንዲሰበሰብ ተወሰነ። በአጭሩ አቡበከር(ረዐ) «ቁርኣንን በቃላቸው ያጠኑት ወገኖች ከሞቱ ቁርኣን ስለሚጠፋ አላህ ለቁርኣኑ ጥበቃ ሲል ቁርኣንን በቃላቸው የሸመደዱ ወገኖችን ከሞት ይታደጋል።» ለተባለው ነገር ከዕውቀት እጥረትና ዕውር ጥላቻ የመነጨ መረጃ አልባ ክስ ስለሆነ መልስ አያስፈልገውም [إِنَّ الظَّنَّ لَا يُغْنِي مِنَ الْحَقِّ شَيْئًا' ጥርጣሬ ከእውነት ምንም አያብቃቃም፡፡] (Qur'an 53÷28) ባይሆን ቁርኣን አልተጠበቀም ተብሎ የተለጠፉት ሁለቱን ሐዲሳት እንመልከት።


🎯 በመጀመርያ ደረጃ ማንኛውም ሐዲስ በኛ ሙስሊሞች ላይ መረጃ ሊሆን የሚችለው በ ‹ሥነ-ሐዲስ ጥናት› መሰረት አምስቱን መስፈርቶች ያሟላ ሲሆን ነው።


1️⃣ ➟ በ Ibn Abi Dawud, Kitab Al-Masahif, መጽሐፍ ላይ የተዘገበው ሐዲስ የተላለፈልን ከዙህሪይ (ረላ) ሲሆን ትውልዱ በ40 ዓመተ-ሂጅሪ ሆኖ ሳለ የየማማ ጦርነት ደግሞ በ12ኛው ዓመተ-ሂጅሪ ነበር ማለትም 28 ዓመት ያህል ከሱ ቀድሞ የታወጀ ዘመቻ ነው። አዝ-ዙህሪም ታሪኩን ማን እንዳስተላለፈለት በግልጹ ስላላሳወቀና የተራኪዎቹ ሰንሰለትም ላይ ክፍተት ስለተፈጠረ ሐዲሱ ‹ሙንቀጢዕ› ማለትም የተቋረጠ ነው። የተቋረጠ ሐዲስ ደግሞ ተቀባይነት ከሌላቸው ዷዒፍ(ደካማ)ሐዲሶች ሥር ይመደባል።

☞ ቢን ዐብድ አል-ሃዲ ❝ዷዒፍ❞ ነው ብሏል ¹ እንዲሁም አሽ-ሻፊዒይ ፣ ቢን ረጀብ አል-ሐንበሊይ ፣ የሕያ ቢን ሰዒድ አል-ቀጣን እና አዝ-ዘሀቢይም የዙህሪ የተቋረጡ ትረካዎችን(በላጋት) አስተባብለዋል። ²


2️⃣ ➟ በ Kanz Ul Ummal, መጽሐፍ ላይ የተዘገበው ሐዲስ ደግሞ የተላለፈልን ከሐሰን አል-በስሪይ(ረላ) ሲሆን ትውልዱ በ21 ዓመተ-ሂጅሪ ሆኖ ሳለ የየማማ ጦርነት ደግሞ በ12ኛው ዓመተ-ሂጅሪ ነበር ማለትም 9 ዓመታት ያህል ከሱ ቀድሞ የታወጀ ዘመቻ ነው። ታሪኩም ማን እንዳስተላለፈለት በግልጹ ስላላሳወቀና የተራኪዎቹ ሰንሰለትም ላይ ክፍተት ስለተፈጠረ ይሄኛው ሐዲስም ‹ሙንቀጢዕ› ማለትም የተቋረጠ ነው።

☞ አል ኢማም ኢብኑ ሐጀር ❝ሙንቀጢዕ❞ ነው ብሏል። ³
☞ ኢማም አስ-ሱዩጢይ ❝ሙንቀጢዕ❞ መሆኑን ገልጿል።⁴
☞ ሙሒብ አድ-ዲን ዋዒዝ ❝ሙንቀጢዕ❞ ነው ብሏል። ⁵
☞ 4ኛው ተራኪ «ዐብደላህ ቢን ሙሐመድ ቢን ኸላድ»
በጀርህ ወት-ተዕዲል ጥናት ላይ ማንነቱ አይታወቅም። ⁶
☞ 2ኛው ተራኪ «ሙባረክ ቢን ፈዳለህ» በተመለከተ
አቡ ዘርዐህ አር-ራዚ :- ❝ብዙ ይቀጣጥፋል።❞ ብሏል። ⁷


❐ በመጨረሻም ክርስትያኖችዬ ቁርኣን ላይ ምታዋክቡት ጸለምተኛ ክሳችሁን ትታችሁ ሁለት ተመሳሳይ(identical) የእጅ ጽሑፍ(እደ ክታብ) የሌለው መጽሐፍ ቅዱሳችሁ ላይ አትኩራችሁ ለብርዛቱ ፈውስ ብትፈልጉ ይሻላቹኃል።
❝No two of the 5340-plus Greek manuscripts of the NT are exactly alike. In fact the closest relationships between any two manuscripts in existence even among the majority average from six to ten variants per chapter. It is obvious therefore that #no_manuscript_has_escaped_corruption.❞ ⁸


لَّا يَأْتِيهِ الْبَاطِلُ مِن بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِ ۖ تَنزِيلٌ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍ
ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፡፡ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ነው፡፡
— ፉሲለት 41÷42 📖


📓📙ዋቢ መጽሐፍ 📌
━━━━━━━━━━

1 – ተንቂሕ አት-ተሕቂቅ 4/585.
2 – ሲየር አዕላም አን-ኑበላእ ሊዝ-ዘሀቢይ 5/338.
3 – ፈትሕ አል-ባሪ ሊሸርሕ ሰሒሕ አል-ቡኻሪይ 9/15.
4 – አል ኢትቃን ፊ ዑሉም አል-ቁርኣን 1/204
5 – ኪታብ አል መሳሒፍ (በህዳግ) 1/181
6 – ታሪኽ ዋሲጥ ሊ አስለም ቢን ሰህል ገጽ 65 & 108
7 – https://islamic-content.com/rawi/6706
8 – Gordon D. Fee, “Modern Textual Criticism and the Revival of the Textus Receptus," in Journal of the Evangelical Theological Society 21:1, March 1978, p.23.



ወሠላሙ ዐለይኩም...✍︎

የፌስቡክ ገጻችን ~› https://www.facebook.com/Ethiomuslimallegationhunters/

የቴሌግራም ገጻችን ~› https://t.me/A3E1response

የቴሌግራም ቻናላችን ~› https://t.me/EAAAresponse
👍2
╔─────────◎ - ◎──────────╗
 ዒልም አር-ሪጃል (Science Of Narrators)
╚─────────◎ - ◎──────────╝

➛ “ዒልም/عِلْم” ማለት ‘ዕውቀት’ ወይም ‘ጥናት’ ማለት ሲሆን ”ዒልም አር-ሪጃል/ عِلْمُ الرِّجال‎/ Science of Narrators” በኛ ሙስሊሞች ዘንድ የሆነ ሐዲስ ተቀባይነት ለማግኘት ቅድሚያ የተረኩልን ግለሰቦች የሚገመገሙበት እንዲሁም ታማኝነታቸውና የማስታወስ ብቃታቸው የሚጣራበት በጥቅሉ የሕይወት ዳራቸው (Biographical Eavaluation) በጥልቀትና በምጥቀት የሚያጠነጥን ሰፊ ጥናት ነው።


يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا أَن تُصِيبُوا قَوْمًا بِجَهَالَةٍ فَتُصْبِحُوا عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَادِمِينَ
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጸቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ፡፡
— አል-ሑጁራት 49÷6 📖
‏
➛ የዚህ መስክ እሴትም ከጊዜ በኃላ መንገዱን ስተው መገነጣጠል ለጀመሩት ኑፋቄዎች እንደነ ራፊዳ(ሺዐ) ፣ ኸዋሪጅ ፣ ሙዕተዚላ እና ሌሎችም የቢድዓ ሰዎች «ነቢዩ(ሰዐወ) እንዲህ ብሏል...» በማለት ከልብ ወለድ ያለ ኢስናድ በሺህ የሚቆጠሩ ሐዲሳትን ለሚቀጣጠፉት መስመር አስያዥ ነው። ¹

➛ በፊትናው ወቅት ታቢዒይ ኢማሞች እንደነ ኢብን ሲሪን(ረላ) ፣ አሕመድ ቢን ሐንበል(ረላ)፣ ሹዕበህ(ረላ)...ወዘተ በዚህ ረገድ ላይ እውነትን ከውሸት ሥጋውን ከአጥንት ለይተው ከሐሰተኞች ዘንድ ማንኛውም ሐዲስ በተላለፈላቸው ቁጥር ‘ሰነዱን (የተራኪዎቹን ስም ዝርዝር) ጥቀሱልን?’ እያሉ በማፋጠጥ ተከታትለው አጋልጠዋል ከነሱ በኃላም ሌሎች ዓሊሞች መጥተው ሰነዱን ፣ የተራኪዎች ታእማኒነት ፣ የማስታወስ ብቃታቸውን እና ዳራቸውን በሰፊው አሰላስለው በርካታ መጽሐፋትን ጽፈው በዚህ ዙርያም ትልቅ ሚና ተጫወተዋል። ²

➛ እዚህ ድረስ ከተግባባን ዘንዳ ብዙ የሙስሊም ምሑራኖች እና ሙፈሲሮች በሐዲስም ሆነ የተፍሲር መጽሐፍቶቻቸው ውስጥ ተቀባይነት ያሏቸው (ሰሒሕ እና ሐሰን) እንዲሁም ተቀባይነት የሌሏቸው (ዷዒፋ ፣ መዉዱዕ ፣ ኢስራኢሊያት... ወዘተ) ዘገባዎችን አንድ ላይ እንዳጠቃለሉ ማወቁ ሰናይ ነው። ³

🎯 ታድያስ “ይህ ሥራ(ዷዒፍ ምንጮችን ማጣቀስ) ለምሑራን ከታማኝነታቸው አይቀንስምን?” ከተባለ መልሱ አዎ አይቀንስም ነው ምክንያቱም —

❶ ከፊሎቹ ምሑራን ሰሒሕ ምንጮችን ብቻ እናቀርባለን በማለት መጽሐፍቶቻቸውን አልገደቡም፤
❷ ከፊሎቹም መግብያው ላይ ደካማ ምንጮችን እንደሚያካትቱ ቀድመው አስጠንቅቀዋል፤ ⁴
❸ ከፊሎቹም በገጹ በህዳግ ዳርቻ ላይ ምንጩን አስቀምጠው በታማኝነት አሳውቀዋል፤
❹ ከፊሎቹም ትርክቱን አጣቅሰው ሐዲሱ ችግር እንዳለበት እዛው በዛው አብራርተዋል፤
❺ ከፊሎቹም ትርክቱን ሰሒሕ ነው ብለው ሳያፀድቁ ሐዲሱ እንደደረሳቸውኑ በልብ ቅንነት አስተላልፈዋል።


🎯 በተረፈ “እንኪያስ ዑለሞች ዷዒፍ ሐዲሳትን መጽሐፍቶቻቸው ውስጥ ለምን መጥቀስ አስፈለጋቸው?” ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል መልሱንም በከፊሉ ስንመለከት —

❶ ዷዒፍ ሐዲስ የተረከውን ግለሰብ ድክመቱን ለይተው ሌሎች ዘገባዎቹንም አጋልጠው ለማስተባበል እንደ አንድ ማስረጃ ስለሚሆናቸው።

❷ ሰነዳቸው ላይ ጥቃቅን ችግሮች ያሉባቸው ሐዲሳት ሌሎች በዚህ ረገድ ላይ በዕውቀት የጠለቁ ዑለሞች እንደገና እንዲያጤኑት ሲባል።

❸ ሰነዳቸው ላይ ጥቃቅን ችግሮች ያሉባቸው ሐዲሳት ከበርካታ መንገዶች ሲመነጩ እርስ በእርሳቸው ተደጋግፈው አልፎ አልፎ ተቀባይነት ስለሚኖሯቸው።
ለምሳሌ – «ሐሰን ሊገይሪሂ»

❹ በዷዒፍ ሐዲስ ኢስናድ ላይ ያለ አንድ ሐሰተኛ ግለሰብ በሌላ ታማኝ ሰው ተተክቶ የማጭበርበር ሥራ እንዳይኖር።

ለምሳሌ – “የሆነ ጊዜ ያሕያ ቢን መዒን(ረላ) ከዐብዱረዛቅ ፣ ከሚዕመር ፣ ከዐባን ቢን ዐያሽ የተላለፈ ደካማ ሐዲስ ፅፎ ሳለ አሕመድ ቢን ሐንበል(ረላ) ይህን አይቶ :- «ዐባን ቢን ዐያሽ ሐዲስ ላይ የሚቀጣጥፍ ውሸታም ሰው መሆኑን እያወቅክ ከሱ የተላለፈን ነገር ትዘግባለህን?» ብሎ ጠየቀው
ያሕያ ቢን መዒንም :- «የፃፍኩበት ምክንያት ለወደፊት ሐሰተኛ ሰው መጥቶ ሐዲሱን ከሙዐመር፣ ከሳቢት፣ ከአነስ አድርጎ(ቀያይሮ) ከዘገበ፤ ዋሽተሃል! ይህ ሐዲስ ከሳቢት ሳይሆን ከዐባን የተላለፈልን(ደካማ ሐዲስ) ነው ብዬ አስተባብልበታለሁ።» አለው!” ⁵


بَلِّغُوا عَنِّي وَلَوْ آيَةً، وَحَدِّثُوا عَنْ بَنِي إِسْرَائِيلَ وَلاَ حَرَجَ، وَمَنْ كَذَبَ عَلَىَّ مُتَعَمِّدًا فَلْيَتَبَوَّأْ مَقْعَدَهُ مِنَi النَّارِ
ነቢዩ (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል:- «ስለኔ አንዲትም ዓረፍተ ነገርም ብትሆን ለሰዎች አሳውቁ፤ ከበኒ እስራኢል ተጓዳኝ ነገር ተናገሩ ፤ ይህን ማድረጉም ኃጢአት አይደለምና። በኔ ላይም (ሆን ብሎ) ውሸትን የተናገረ መቀመጫው ገሃነም መሆኑን (ይገንዘብ)።»
— ሰሒሕ አል-ቡኻሪ 3461, መጽ 60, ሐዲስ 128.📚


❐ በመጨረሻም ክርስትያኖችዬ ባይብላችሁ በአጠባበቁ ዙርያ ሰነድ የሌለው እና የአንዳንድ መጻሕፍት ደራስያን ትክክለኛ ማንነታቸው የማይታወቁ ሆነው ሳለ ‘ሙስሊሞች ለምን ዷዒፍ ሐዲሶቻችሁን አታቃጥሉም’ ብላችሁ ለመተቸት ሞራሉም ብቃቱም የላችሁም። ዝንጀሮ የራሷ መላጣ አይታያትም የናንተ ባይብል በዒልም አር-ሪጃል ጥናት ሥር ቢውል ሙሉ ሰነዱ እና ደብጡን በትክክል ጠብቆ በጥሩ ሁኔታ የሚወጣ አንድ መጽሐፍ መኖሩ አጠራጣሪ ነው። “All the Gospels originally circulated anonymously. Authoritative names were later assigned to them by unknown figures in the early church.” ⁶



📓📙ዋቢ መጽሐፍ 📌
━━━━━━━━━━


1 – አስ-ሲልሲለህ አድ-ዷዒፈህ ወል መውዱዐ 1/476.
2 – እነ አል-ጀርሕ ወት-ተዕዲል ሊ ኢብን አቢ ሓቲም ፣ ተህዚብ አት-ተህዚብ ሊ ኢብን ሐጀር ፣ ተህዚብ አል-ከማል ሊል መዚይ ፣ ሚዛን አል-ኢዕቲዳል ሊ ዘሀቢይ ፣ አት-ታሪኽ አል-ከቢር ወስ-ሰጊር ሊል ቡኻሪ ፣ ኪታብ አል-ዒለል ወ መዕሪፈቱር ሪጃል ፣ አል-መጅሩሒን ሊ አቢን ሒባን ፣ ሲየር አዕላም አን-ኑበላእ...ወዘተ
3 – ፈይድ አል-ቀዲር ሸርሕ አል-ጃሚዕ አስ-ሰጊር 1/17 ፣ አን-ኑከት ዐላ ኢብን ሰላሕ 1/147.
4 – መውሱዐህ አል-አሓዲስ ወል ኣሳር አድ-ደዒፈህ ወል መውዱዐህ 1/173.
5 – ተድሪብ አር-ራዊ ፊ ሸርሕ ተቅሪብ አን-ነወዊይ 1/246
6 – Robert W. Funk, The Jesus Seminar, The Five Gospels: What Did Jesus Really Say? The Search for the Authentic Words of Jesus, Harper One, 1996, p.20.


ወሠላሙ ዐለይኩም...✍︎

የፌስቡክ ገጻችን ~› https://www.facebook.com/Ethiomuslimallegationhunters/

የቴሌግራም ገጻችን ~› https://t.me/A3E1response

የቴሌግራም ቻናላችን ~› https://t.me/EAAAresponse
ሴቶች በቁርአን ክፍል 3
Convert To Voice
—የኛ መልስ—

ሴቶች በቁርአን ክፍል 3

《Amir & Triple-ኤ Respond》

(Ewnetlehulu Refuted)
⚪️ ❝ቁርኣን ዘላለማዊው ተዓምር❞ [𝟏]

በቅሪተ አካላት(Fossils) አጠባበቅ ዙርያ አጥንት ተቀብሮ ረጅም ዘመናትን ሲቆጥር ከድንጋይ ወይም ብረት ጋር የሚቆራኝበት ሁኔታዎች እንዳሉ ጥናቶች አትተዋል...

➛ አጥንት በቂ ከከርስ ምድር ወኃ የሚፈጠሩ ማዕድናትን (ሲሊካ/Silica) ሲያገኝ ፣ ቀዳዳዎቹ ተደፍነው በቀስታ አጥንቱ ድንጋይ መሆን ይጀምራል።
[🔗 https://www.digitalatlasofancientlife.org/learn/nature-fossil-record/types-of-fossil-preservation/]

➛ አጥንት በቂ በብረት መጠን በተሞላ ደለል ውስጥ ቆይቶ ለከፍተኛ እርጥበት ሁኔታ ሲጋለጥ ፣ በቀስታ ብረቱ ተከማችቶ አጥንቱ የሚያብለጨልጭ ፒራይት(Pyrite) ወይም ብረት ሞኖሰልፋይድ(Iron Monosulphide) መፍጠር ይጀምራል።
[🔗 https://www.rockhoundtimes.com/pyritized-fossils.html]


🎯 አላህﷻ በቅዱስ ቃሉ ትንሣኤን ላስተባበሉ ሰዎች ከ1,400 ዓመታት በፊት ይህን አስደናቂ እውነታ ቀድሞ በመጠቆም መልስ ሰጥቷል —

۞ {አሉም «እንዴት አጥንቶችና ብስብሶች በኾን ጊዜ እኛ አዲስ ፍጥረት ኾነን በእርግጥ ተቀስቃሾች ነን»}

۞ {በላቸው «ድንጋዮችን ወይም ብረትን ሁኑ»...«ወይም በልቦቻችሁ ውስጥ የሚተልቅን ፍጥረት (ኹኑ መቀስቀሳችሁ አይቀርም)፡፡»...}
  — አል-ኢሥራእ 17÷50-51


“እርሱም (ቁርኣን) እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው ድረስ በአጽናፎቹ ውስጥና በነፍሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን፡፡” (Qur’an 41÷53)


ሰደቀሏሁል ዐዚም...✍︎

https://t.me/EAAAresponse
❤1👍1
⚪️ ❝ቁርኣን ዘላለማዊው ተዓምር❞ [𝟐]

በሥነ ሕይወት(Biology) ዙርያ “Argyroneta aquatica” በመባል የምትታወቅ የውኃ ሸረሪት በኩሬዎች ፣ ጅረቶች እና ሌሎች ጥልቀት በሌላቸው የንፁህ ውኃ አካላት ውስጥ ሙሉ ሕይወቷን የምታሳልፍ ብቸኛው ሸረሪት ስትሆን መኖርያዋን በተመለከተ —


➛ የውኃ ሸረሪት በውኃ ውስጥ ባሉ እፅዋቶች ወይንም ሌሎች ነገሮች ላይ ድሯን ትጠቀልላለች ፣ ቀጥሎ በሆዷ እና እግሮቿ ላይ የሚገኙ ጥቃቅን ፀጉሮቿን በመጠቀም ወደ ወኃው ወለል ወጥታ የአየርን አረፋ በመያዝ እንደገና ወደ ታች በመጥለቅ አረፋውን አንድ ላይ አጠራቅማ መኖርያዋን ትሰራለች።

➛ ቀስ በቀስም በአየር የተነፋው ድሯ ይፈርሳል በየቀኑም አንድ ጊዜ ቤቷን በአየር ለማሳደስ ወደ ውኃው ወለል መውጣት ይኖርባታል።
[🔗 https://www.britannica.com/animal/water-spider]


🎯 አላህ ﷻ ከ1,400 ዓመታት በፊት እነዛን የካህዳይን ረዳቶችን ስንኩልነት ለመግለፅ ይህን የመሰለ ደካማ ቤት ከሚሰሩ ሸረሪቶች ጋር አነፃፅሮ ወደዚህ አስደናቂ እውነታ ጠቁሟል —

۞ {የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን (ጣዖታትን) የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ (አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር)፡፡}
  — አል-ዐንከቡት 29÷41


“እርሱም (ቁርኣን) እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው ድረስ በአጽናፎቹ ውስጥና በነፍሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን፡፡” (Qur’an 41÷53)


ሰደቀሏሁል ዐዚም...✍︎

https://t.me/EAAAresponse
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚪️ ❝ቁርኣን ዘላለማዊው ተዓምር❞ [𝟑]

በሥነ ከዋክብት (Planetology) ዙርያ “Pulsar star” የሚባል ኮከብ በ1967 ዓም ሁለት ተመራማሪዎች ከሬዲዮ ቴሌስኮፕ ያልተለመደ ድምፁን አስተውለው በ1968 ላይ ሙሉ መረጃውን ይፋ አረጉት። 

➛ “Pulsar star” በሁለት ተቃራኒ ጎኖቹ ኃይለኛ ጨረር አመንጪና በእንጨት ላይ እንደማንኳኳት ይመስል ድምጽ አሰሚ ከ ‹nutron star› ክዋክብቶች የሚመደብ ደማቅ ኮከብ ነው።
[🔗 https://imagine.gsfc.nasa.gov/science/objects/neutron_stars1.html#:~:text=Pulsars%20are%20rotating%20neutron%20stars,very%20powerful%20beams%20of%20light.]


🎯 አላህ ﷻ በቅዱስ ቃሉ ከሺህ አራት መቶ ዓመት በፊት «በሰማዩ *በጧሪቅም(በአንኳኪው)* እምላለሁ፡፡» ብሎ ቀጥሎ «ጨለማን ቀዳጁ #ኮከብ ነው፡፡» (Qur’an 86÷1-3) በማለት ስለዚህ ግሩም ኮከብ አስቀድሞ ነግሮናል።

➛ "አጥ-ጣሪቅ/ الطّارق/ At-Tariq" የሚለው ቃል ‘ጠረቀ’ ወይንም ‘አንኳኳ/ he knocked’ ከሚል ግስ የረባ ሲሆን ትርጉሙ «አንኳኪ, knocker, striker» ማለት ነው።
[🔗 https://m.name-doctor.com/tarik/]


“እርሱም (ቁርኣን) እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው ድረስ በአጽናፎቹ ውስጥና በነፍሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን፡፡” (Qur’an 41÷53)


ሰደቀሏሁል ዐዚም...✍︎

https://t.me/EAAAresponse
👍1
⚪️ ❝ቁርኣን ዘላለማዊው ተዓምር❞ [𝟒]

በሥነ ጠፈር(Spaceology) ዙርያ አስትሮኖመሮች ወደ ጠፈር ጉዞ ሲያደርጉ (space blindness or VIIP) የሚባል ቅምረ ህመም በእይታቸው ላይ የዓይን እክልነትን/ስውርነትን አስከተሏል። እዛ ስበተ ቁስ(gravity) ስለሌለ በአንጎል እና በአይን ጀርባቸዉ ላይ ጫና ተፈጥሮ ነው ተብሎም ይታሰባል።


➛ ‘Julie Robinson’ እንዳለችው :- ‹ባለፉት 10 አመታት ውስጥ ከደረስንባቸው ነገራቶች አንዱ የተወሰኑ ጠፈርተኞች ወደ ህዋ ሲሄዱ ዓይናቸው ጠፋ...ጥቂቶቹ ወደ ምድር ሲመለሱ የማይቀለበስ ቋሚ የእይታ እጦት ደረሰባቸው።”›
[🔗 https://m.lasvegassun.com/news/2017/dec/02/space-blindness-must-be-solved-before-mission-to-m/]

➛ አንዳንዶችም እንደ ‘Scott Kelly’ እና ‘John Phillips’ ከጠፈር ጉዞ ከተመለሱ በኃላ በአጭር ጊዜ ውስጥ እይታቸው ላይ ችግር እንደተፈጠረ ታውጇል።
[🔗 https://www.sciencealert.com/we-finally-know-why-astronauts-lose-their-vision-in-space-and-it-s-bad-news-for-mars-missions]


🎯 አላህ ﷻ በቅዱስ ቃሉ ቁርአንን ያስተባበሉ ከሃድያን የሰማይን ደጃፍ (ozone layer) ከፍቶላቸው ወደ ላይ ቢያርጉ ኖሮ ‘space blindness’ ያጋጥማቸው እንደነበር ወደዚህ አስደናቂ ክስተት አስቀደሞ ጠቁሞናል—

۞ «በእነርሱም ላይ ከሰማይ ደጃፍን በከፈትንላቸውና በእርሱ ሲወጡ በዋሉ ኖሮ»

۞ «#የተዘጉት_ዓይኖቻችን_ናቸው፡፡ እንዲያውም እኛ የተደገመብን ሰዎች ነን» ባሉ ነበር፡፡»
  — አል-ሒጅር 15÷14-15


ሰደቀሏሁል ዐዚም...✍︎

https://t.me/EAAAresponse
👍3
AEMerge1641706886795
Convert To Voice
📚 Sahih Al-Bukhari⁵⁷⁷ & Muslim¹⁸²

❍ በዚህ ላይ ለሚነሱ አንዳንድ ሹብሃዎች ማብራሪያ

➊▸ አላህﷻ በተለየ ገጽታ ይገለጣል ሲባል?
➋▸ ሁለቴ በመገለጡስ ያለው ጥበብ ምንድ ነው?
➌▸ በተለየ ገጽታ መገለጥስ መቀያየርን ያመላክታልን?


🔊 በወንድም ‘𝖒𝖆𝖍𝖉𝖎 مهدي’ 🪔
https://t.me/A3E1response
Audio
አላህ ስለ ራሱ ሲናገር ለምን "እሱ" የሚለውን ተውላጠ ስም ተጠቀመ?
t.me/religionandphylosophy
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
◉ በረመዳን ወር ልናውቃቸው የሚገቡን ነገራቶች🪔

➀, “የጾም ትሩፍቶች” ➟ (00:27)
➁, “ጾምን የሚያበላሹ” ➟ (01:53)
➂, “ልንሰራቸው የሚገቡ” ➟ (02:36)


🎤 ▹ ወንድም እስሚዝ
⌛️ ▹ 03:42 min
💾 ▹ 91.9 MB

───────────────
📎 https://t.me/EAAAresponse

📎 https://vm.tiktok.com/ZMLHbX18X/
👍1