Doctor Alle 8809/ዶክተር አለ 8809
57.6K subscribers
5K photos
18 videos
1.58K links
ጤናዎን ያብዛሎ
8809 ዶክተር አለ
መተኪያ ስለሌለው ጤናዎ የሀኪም መፍትሄ የሚያገኙበት የጥሪ ማዕከል 8809 ዶክተር አለ
- አካላዎ ህመም -
- የውስጥ ደዌ
- የስነልቦና ችግር
- እንዲሁም የሚያስፈልግዎ ህክምና የት ሆስፒታል እንደሚሰጥ እንጠቁምዎታለን፡፡
- የውጪ ሀገር ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ባለን ዓለምአቀፍ ኔትዎርክ ሁሉን ያሟላ
Download Telegram
✍️ #ቡና #በጽንስ #ላይ #ችግር #ይፈጥራል? (ምላሽ)
#ውድ #የዶክተር #አለ #ተከታታዮች #ትላንት #ቃል #በገባንላቹ #መሰረት #ቡና #በጽንስ #ላይ #ችግር #ይፈጥራል? #ለሚለው #ጥያቄ #ምላሽ #ልንሰጣቹ #ቀርበናል #ተከታተሉን፡፡
ሴቶች ከየትኛውም ጊዜ በላይ በእርግዝና ወቅት የተመጣጠነ ምግብ መመገብ አለባቸው፡፡ ለጽንስ ጤንነት እንዲሁም ልጅ ሲያድግ ጤንነቱ ተጠብቆ እንዲያድግ በጽንስ ጊዜ እናት የምትመገበው ምግብ ወሳኝ ነው፡፡

የተለያዩ ቫይታሚኖች ለጽንስ ጤንነት እንደሚጠቅሙ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ ቫይታሚኖች አንዱ የሆነው ፎሊክ አሲድ ሲሆን በጽንስ ላይ የሚፈጠረውን የአከርካሪ አጥንት ሙሉ ለሙሉ ሳይሸፈን መወለድ(spainal pefida) በሽታ እንዳይመጣ ይከላከላል፡፡ ነገር ግን በእርግዝና ወቅት እናት የምትመገበው ነገር ሁሉ ይጠቅማል ማለት አይደለም፡፡

ካፌን እንደ ኦክስጅን እና አንዳንድ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች የማህጸን ግድግዳን አልፎ የመግባት አቅም ያለው ንጥረ ነገር ነው ጽንስ ግን ካፌንን ለመዋሃድ የሚያውል እጢ ገና አላዳበረም፡፡

👉 ቡና እና ካፌንነት ያላቸውን ምግብ እና መጠጦችን ጨምሮ ጽንስ እና እናቶች ላይ ምን ችግር ይፈጥራል?

📌 የጽንስ ክብደት መቀነስ
📌 የእርግዝና ጊዜን ያረዝማል
📌 ከተወለዱ በኋላ ለተለያዩ የጤና ችግሮች ያጋልጣል
📌 እናት ላይ የደም ግፊት እና የልብ ምት እንዲጨምር ያደርጋል
📌 የሰውነት ፈሳሽ መጠን ይቀንሳል
📌 ውርጃ
📌 የጽንስ እድገት መዘግየት እንዲኖር ያደርጋል

👌👌 #ከእርግዝና #ጋር #በተያያዘ #እንዲሁም #በሌሎች #የጤና #ችግሮች #ላይ #ማንኛውም #ጥያቄ #ካሎት #ወደ #ዶክተር #አለ #8809 #ላይ #በመደወል #በቂ #ምክር #እና #አገልግሎት #ለመስጠት #ባለሞያዎቹ #ዝግጁ #ናቸው፡፡

#መልካም #የጤና #ጊዜን #ተመኘን!!!

**********************

(#በጤና #ባለሙያ #ርብቃ)
የአረንጓዴ ተክል ምግቦች ለጤና ያላቸው ፋይዳ
********************************
📌 ጥቅል ጎመን
የተለያዩ አይነት የጎመን ዝርያዎች ያሉ ሲሆን ሁሉም በቫይታሚን ኤ፤ ሲ፤ካልሲየም እና ሌሎች ንጥረ ነገሮች የበለጸጉ ናቸዉ፡፡በአዉስትራሊያ የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተዉ እነዚህን አረንዴ ተክሎች መመገብ ለካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡
📌 የጀርመን ሰላጣ
የጀርመን ሰላጣ ሠዉነታችንን ካንሰር እንዲዋጋ አቅም የሚሠጥ ሲሆን ከዛም ባለፈ ለብጉር፤የፀጉር መነቀል እና ሌሎችንም ይከላከላል፡፡
📌 ቆስጣ
ቆስጣን መመገብ የጉበት፣ የአንጀት፣ የማህፀን እና የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ጥናቶች የሚያሳዩ ሲሆን ከነዚህም በተጨማሪ ለጡንቻ መዳበር ጠቃሚነት አለዉ፡፡
📌 የሾርባ ቅጠል
ምግብን ለማጣፈጥ የምንጠቀምበት የሾርባ ቅጠል በዉስጡ ፎሊክ አሲድ፣ቫይታሚን ኤ፣ቢ፣ኬ እና ሌሎች ንጥረ ነገሮችን የያዘ ሲሆን የአጥንት መሳሳትንና የልብ ህመም ተጋላጭነትን እንደሚቀንስም ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
📌 ሠላጣ
ሠላጣን መመገብ ለደም ግፊት ህመምተኞች ና ከፍተኛ የሠዉነት ክብደት ላላቸዉ ሠዎች የሚመከር ሲሆን የደም ዉስጥ ስብ መጠንንም ይቀንሳል፡፡ ሠላጣ በዉስጡ የያዘዉ ካልሲየምና ፎስፈረስ ለአጥንት ጤናማነት ጠቃሚ ሲሆን ሴሊኒየም የሚባለዉ ንጥረ ነገር ደግሞ የሠዉነታችን ቆዳ ቶሎ እንዳረጅና የአንጀት ካንሠርን የመከላከል አቅም እንዲኖረዉ ያደርጋል፡፡

********************

(#በጤና# ባለሙያ# ሄርለም#)
✍️ #ህጻናትና #ምግባቸው

*********************

👉 👉 ልጅሽ ከ6 እስክ 24 ወራት (2 ዓመት) ያለው የአመጋገብ ሥርዓት የጤንነታቸው የአካልና የአእምሮ ዕድገታቸው ዋነኛ መሠረት ነው፡፡

👉 👉 በአብዛኛው የሕፃናቱ የምግብ መጎዳትና መታመም የሚጀምረው ከ6ወር በኋላ ለዕድገት በቂ ወዳልሆነ የአመጋገብ ሁኔታ ሲገቡ በመሆኑ ከ0 እስከ 2 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ትክክለኛ ካልሆነ አመጋገብ የተነሳ የሕፃናት መቀጨጭ እና የእእምሮ ለትምህርት ብቁ ያለመሆን ሁኔታ ከተከሰተ በኋላ ለመመለሰ አአስቸጋረሪ ይሆናል፡፡

👉 👉 ታዲያ ተጨማሪ ምግብን አስቀድሞም ሆነ ዘግይቶም መጀመር ችግር ሊያመጣ ይችላል።ተጨማሪ ምግብን ሕፃናት ስድስት ወር ሳይሆናቸዉ ቀደም ብሎ መጀመር ጉዳትን ያስከትላል፡-

📌 ሕፃናት የጡት ወተትን በደምብ እንዳይጠቡ ያደርጋል፤

📌 ተጨማሪ ምግቡ እንደጡት ወተት ንጹህ ስለማይሆን በተቅማጥ በሽታ የመያዝ እድልን ይጨምራል፤

👉 👉 ተጨማሪ ምግብን ሕፃናት ስድስት ወር ካለፋቸው በኋላ ዘግይቶ መጀመር ጉዳት ያስከትላል፡-

📌 ሕፃናት የሚያስፈልጋቸዉን ኃይል እና ንጥረ ነገር ለሟሟላት መመገብ ያለባቸውን ተጨማሪ ምግብ አያገኙም፤

📌 የሕፃናት በምግብ እጥረት እና የንጥረ ነገሮችን አለመመጣጠን ችግር የመከሰት ዕድልን ይጨምራል፤

📌 እንዲሁም እድገታቸውን ይቀንሳል ወይም ያቆማል፡፡

#ለሕጻናት #የበለፀገ #ምግብ #አዘገጃጀት

📌 ለገንፎ ዱቄት ዝግጅት: ሦስት እጅ እህል (በቆሎ፣ማሽላ፣ጤፍ፣ገብስ ወይም ማንኛውም በአካባቢዉ የሚገኝ እህል)/ስራስር ( ቡላ ) እና አንድ እጅ ጥራጥሬ (አተር፤ ሽንብራ፣ ባቄላ እና ምስር) በማደባለቅ የተዘጋጀ ዱቄት ማምጣት፤

📌 ከላይ የተጠቀሰውን የእህል ዝግጅት በመጠቀም ለስለስ እና ወፈር ያለ ገንፎ ማዘጋጀት፤

📌 የተዘጋጀውን ገንፎ የበለጠ ጠቃሚ ለማድረግ ከዚህ የሚከተሉትን የምግብ ዓይነቶች በተገኘ ጊዜ ሁሉ አንድ ወይም ሁለት ዓይነት ምግቦችን መጨመር፤

📌 አንድ የሻይ ማንኪያ የቋንጣ ዱቄት፣ ልሞ የተከተፈ አትክልት ጎመን ፣ካሮት፣ ዕንቁላል፣ በወተት ማገንፋት
በተዘጋጀው ገንፎ ውስጥ ትንሽ የአትክልት/ የወይራ ዘይት እና አዮዲን ያለው ጨው መጨመር፤

📌ለመመገብ ዝግጁ አድርጎ ማብላት ፡፡

👉 👉 ውድ የዶክተር አለ ቤተሰቦች ለልጆ ጤና የሚጨነቁ ከሆነ ጤናማ አመጋገብን ይምረጡ!! ታዲያ ጤናማ አመጋገብ ለልጆ መማከር ሲሹ ዶክተር አለ 8809 ይደውሉ በባለሙያ ይማከራሉ !!

(#በጤና #ባለሙያ #ከድጃ)
አንዳንድ የጤና እውነታዎች
**********
ውድ የዶክተር አለ ተከታታዮች እንደምን ቆያችሁ ዛሬም እንደተለመደው ለናንተ ይጠቅማል ብለን ይዘንላችሁ የቀረብነው ጥናቶች ካረጋገጡት አንዳንድ እውነታዎች መሃከል መርጠን አዘጋጅተንላችኃል ተከታተሉን፡፡

o መሳቅ ልብን ጤንነት ይጠብቃል
o ከ35 አመት በፊት ሲጋራ ማጨስ ማቆም ከሞት ይታደጋል
o በአሁን ሰአት ከልክ ያለፈ ውፍረት ለካንሰር በሽታ እንደሚያጋልጥ ጥናቶች ጠቁመዋል
o ስኳር ያላቸውን መብሎች በብዛት መጠቀም ለከፋ የጤና ጉዳት ይዳርጋል
o ቀና አስተሰሳሰብ ረጅም እድሜ ለመኖር ይጠቅማል
o በየቀኑ ለ10 ደቂቃ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ለሙሉ ጤንነት ይጠቅማል
o በስራ መጨናነቅ ለሁለተኛው የስኳር ህመም አይነት ይዳርጋል
o መመሰጥ ለአእምሮ ጤንነት ይጠቅማል
o ከ30 አመት በላይ ያሉ ሰዎች የጡንቻቸውን 40% እያጡ ነው የሚሄደውት
o በቂ እንቅልፍ አለማግኘት ክብደት ክብደትን አንዲጨምሩ ያደርጎታል
o ረጅም ሰአት ከመቀመጥ ይልቅ ረጅም ሰአት መቆም ለጤና ተቃሚ መሆኑን ጥናቶች ጠቁመዋል
o በድብርት ጊዜ የማነቃቂያ መድሃኒቶችን ከመጠቀም ይልቅ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ጠቃሚ ነው
o በብዛት ፍራፍሬ መመገብ የጉበትን ጤንነት ይጠብቃል
o 70% አካባቢ የሚሆኑ መሃከለኛ እድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሴቶች ከታይሮይድ ሆርሞን ጋር በተያያዘ ችግር ላይ ይወድቃሉ
o ጥልቅ የሆነ አተነፋፈስ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል

👌👌👌 ዶክተር # አለ # 8809 # በእያንዳንዳችንን # የጤና ችግር # ላይ አስቀድሞ # ምክሮችን የሚለግስ # የሚያስተምር # ተቀዳሚ # የጤናዎ # አጋር !! ይምረጡት # ይጠቀሙበታል !!!

👌👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦
የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፣
👉👉 http://tiny.cc/gf606y
የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ
👉👉👉 T.ME/DOCTORALLE8809
#የፕሮስቴት #እጢ #ማበጥ(ማደግ)#(BPH)
**********
የፕሮስቴት እጢ ማበጥ(ማደግ) ማለት ማደግ እጢው ከመጠን በላይ ማበጥ ማለት ነው፡፡ ወንዶች እድሜያቸዉ እየገፋ በመጣ ቁጥር የፕሮስቴት እጢ መጠኑ እየጨመረ ይመጣል፡፡ ይህ ደግሞ በሽንት መተላለፊያ ቱቦ ላይ ችግር ስለሚያመጣ ወንዶችን ሊያስጨንቅ ይችላል፡፡
👉 #ምልክቶች
የፕሮስቴት ችግር ያለባቸዉ ሰዎች የህመማቸዉ ምልክት ደረጃዉ የሚለያይ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን ህመሙ እየተባባሰ ይመጣል፡፡ ከሚታዩት ምልክቶች ዉስጥ፡-
• ሽንት ሲሸኑ ማጣደፍ/ ቶሎ ቶሎ መሽናት
• ማታ ማታ ሽንት መብዛት
• ሽንት ለመሽናት ሲጀምሩ መቸገር
• ሽንት በደንብ ያለመዉጣት/መቆራረጥ መከሰት
• ሽንት ሲሸኑ ወደ መጨረሻዉ ላይ መንጠባጠብ
• ሲሸኑ ማማጥ
• ሽንት ከፊኛዎ ዉስጥ ሙሉ በሙሉ ወጥቶ ያለማለቅ/ ሽንት ከሸኑ በኃላ ፊኛዎ ዉስጥ መቅረት
• የሽንት ቧንቧ እንፌክሽን መከሰት
• መሽናት ያለመቻል
• ከሽንትዎ ጋር ደም መታየት
የፕሮስቴት ዕጢ መጠን ትልቅ መሆን ህመሙን ያባብሰዋል ማለት አይደለም፡፡ አንዳንዶች መጠኑ ትንሽ ዕጢ እያላቸዉም የህመማቸዉ ምልክት ከፍ ያለ ሲሆን በተቃራኒዉ ደግሞ መጠኑ ትልቅ የሆነ ዕጢ እያላቸዉ የሚያሳዩት ህመም መጠነኛ ሲሆን ይችላል፡፡ አንዳንዶች ላይ ደግሞ ህመሙ ከመጣ በኃላ ተመልሶ ሊጠፋ ይችላል፡፡
👉 #አጋላጭ #ሁኔታዎች
• የእድሜ መጨመር
• በቤተሰብዎ ዉስጥ መሰል ችግር መኖር
• የስኳርና የልብ ችግር

👉 #ሊደረግ #የሚችል #ህክምና
ለችግሩ ብዙ አይነት የህክምና ዘዴዎች ያሉ ሲሆን እነርሱም መድሃኒቶችንና ቀዶ ጥገናን ያጠቃልላል፡፡ ሊደረግልዎ የሚችለዉ የህክምና ዘዴ እንደ
• የፕሮስቴት ዕጢዉ መጠን
• እድሜዎ
• አጠቃላይ የጤናዎ ሁኔታና
• እንደ ሚያሳዩት የህመም ደረጃ/አሳሳቢነት ይወሰናል፡፡
የፕሮስቴት ችግር እንዳለ ካወቁ አስፈላጊውን ህክምና ማግኘት ያስፈልጋል እንዲሁም ስለበሽታው በቂ ማብራሪያ እና ትንታኔ ሲሹ ዶክተር አለ 8809 ላይ መደወል ይችላሉ!!!

መልካም የጤና ጊዜ ተመኘንልዎ!!!

****************************

(#በጤና #ባለሞያ #ራሔል)
#ይነበብ!! #ይነበብ!! #ሼር #ይደረግ !! #አሁንም #ጥንቃቄ #ያስፈልጋል !!

#በኢትዮጵያ #ከፍተኛ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዋች ቁጥር እና የከፋ ጉዳት ሊደርስ የሚችለው #ሰኔ መጨረሻና #ሐምሌ መጀመርያ ቀናት ላይ መሆኑን ጤና ጥበቃ ሚንስቴር አስታወቀ

መንግስት የኮሮና መከላከያ እርምጃዎችን ባይወስድ ኖሮ #ከ27 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ ይጠቁ እንደነበርም ተገልጿል።

ጤና ሚኒስቴር ወረርሽኙ ሊያደርስ የሚችለው የከፋ ውጤት ገና አላለፍነውም፤ እንደ ኮሮና ወረርሽኝ አንድ ሀገር ገብቶ የሚብስበት ጊዜ ገና የሚመጣ ነውና መዘናጋት አደገኛ ነው ብሏል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የጤና ነክ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር ያዕቆብ ሰማን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ፤ አንድ ወረርሽኝ የስርጭት ጣርያው ላይ ለመድርስ በአማካይ አስር ሳምንት ወይንም 3 ወር ይፈልጋል፤ እኛ አንድ ወር ከ ሁለት ሳምንታችን ስለሆነ አስከፊው ነገር ገና ከፊታችን ነው ብለዋል ፡፡

ጥናታችን እንደሚያሳየው በሀገር አቀፍ ደረጃ አሁን የምናደርገውን ጥንቃቄ ባናደርግ ከ 27 ሚሊዬን በላይ ህዝብ ኮሮና ያጠቃብን ነበር የሚሉት ዶ/ር ያዕቆብ በደንብ ከተጠነቀቅን ደግሞ የዚህን ቁጥር 60 በመቶ ወይንም 13 ሚሊዮን መቀነስ ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እንደ ዶ/ር ያዕቆብ ኮሮና ቫይረስ በሀገራችን ሊያደርስ የሚችለው ከፍተኛውን ጉዳት የሚያደርስበት ወቅት ሰኔ መጨረሻና ሀምሌ መጀመርያ ላይ ነው፡፡

በታሪክ የተከሰቱ ወረርሽኞችም ለምሳሌ የህዳር በሽታ የዝናብና የብርድ ወቅት መውጣትን ተከትሎ ነው የስርጭታቸው ከፍታ ላይ የደረሱት ያሉ ሲሆን ከቅርብ አመታት ወዲህ ዝናብ ቀደም ብሎ ሚያዚያ፣ግንቦት ላይ እየጀመረ ስለሆነ የሰኔ የመጨረሻ ሳምንትና የሀምሌ የመጀመርያ ሳምንት ሊከፋ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

እኛም እየሰራን ያለነው ከዚያ አንፃር ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ኮሮና ሀገራችን ገባ ሲባል ድንጋጤው ህዝቡም ላይ ብቻ ሳይሆን ፌደራል መንግስትም ክልል መንግስታትም ላይ እንደነበር የምታውቀው የተወሰዱት እርምጃዎችን ስታስታውስ ነው የሚሉት ዶ/ር ያዕቆብ አሁን በኮሮና የሚያዘው ቁጥር ሲያድግ ህዝቡ ብቻ ሳይሆን መንግስትም በቁጥጥር ላላ እያለ እንደሆነ ነው የምታስተውለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አንዳንድ መፍትሄዎች ቀድመህ በማድረግህ ብቻ ላይሰሩልህ ይችላሉ፤ የወረርሽኙ የከፍታ ወቅት ላይ (እንደ ግምታችን ሰኔ መጨረሻና ሀምሌ መጀርመያ ላይ) ፤ ህዝቡ በጣም እንዲጠነቀቅ ብትፈልግ፤ ሊዳከምና ሊሰላችብህ ይችላል፣ ስለሆነም መቼ በምን ያህል መጠን ነው እንቅስቃሴ የምገድበው፣ እርምጃዎቼን የማጠብቀው የሚለውን ሲወስን መንግስት ባለሙያዎችን ሁሌም ማማከር አለበት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

©️ኢትዮ Fm107.8
*******
#COVID19

የኢትዮጵያና የአጎራባች ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,112፣ ሞት 2፣ ያገገሙ 686

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 435፣ ሞት 22፣ ያገገሙ 152

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 671፣ ሞት 31፣ ያገገሙ 34

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 533፣ ሞት 36፣ ያገገሙ 46

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 133፣ ሞት 3፣ ያገገሙ 69

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 45፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 0

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 26
✍️ #የምጥ #ጊዜ #እንዲረዝም#የሚያደርጉ #ምክንያቶች


#ሰላም #ጤና #ይስጥልን #ውድ #የዶክተር #አለ #ቤተሰቦች #ከኮሮና #ቫይረስ #እራሶትንም #ቤተሰቦትንም #ለመጠበቅ #ከጤና #ባለሞያዎች #የሚሰጡትን #ምክሮች #በማክበር #ይተግብሩ #እያልን #ዶክተር #አለ #መልእክቱን #ያስተላልፋል፡፡

📌 ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት መጨመር

📌 የሰውነት ክብደት መቀነስ

📌 የጡንቻ አለመዳበር

📌 የተወሰነ የሰውነት እንቅስቃሴዎችን አለማድረግ

📌 የእናት እድሜ ከ15 አመት በታች ወይም ከ35 አመት በላይ መሆን

📌 የዳሌ አጥንት መጥበብ

📌 የጽንስ ክብደት ከፍተኛ መሆነ

📌 አነስተኛ ቁርጠት(contraction) መኖር

📌 የማህጸን በር ማበጥ

📌 መንታ መጸነስ

📌 ጭንቀት ወይም አላስፈላጊ ፍራቻ መኖር


👌👌👌 #ከእርግዝና #ጋር #፣ከምጥ #ጋር #በተገናኘ #እንዲሁም #በሌሎች #ተጓዳኝ #የጤና #ችግሮች #ላይ #ማንኛውም #ጥያቄ #ካሎት #ወደ #ዶክተር #አለ #8809 #ላይ #በመደወል #በቂ #ምክር #እና #አገልግሎት #ለመስጠት #ባለሞያዎቹ #ዝግጁ #ናቸው፡፡
#መልካም #የጤና #ጊዜን #ተመኘን!!!
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
(#በጤና #ባለሙያ #ርብቃ)
✍️ #የኮሮና #ስርጭት 25/08/2012 #ከጠዋቱ 2:59

********************

📌 #በኢትዮጲያ

👉 ምርመራ

• በ 24ሰዓታት የተሰራው ላቦራቶሪ =2016
• አጠቃላይ ላቦራቶሪ ምርመራ =20,770

👉 አጠቃላይ የተያዙ ሰዎች ቁጥር፡- 133
👉 ባለፉት 24 ሰአት የተያዙ ሰዎች ቁጥር፡- 0
👉 አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር፡- 3
👉 ባለፉት 24 ሰአት የሞቱ ሰዎች ቁጥር፡- 0
👉 አጣቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር፡- 69
👉 በፅኑ የታመመ=0
👉 አሁን ለይቶ ማከሚያ ያሉ=59
👉 ወደ ሃገራቸው የተመለሱ =2

📌 #በአፍሪካ

👉 አጠቃላይ የተያዙ ሰዎች ቁጥር፡- 43,734
👉 ባለፉት 24 ሰአት የተያዙ ሰዎች ቁጥር፡- 2,294
👉 አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር፡- 1,763
👉 ባለፉት 24 ሰአት የሞቱ ሰዎች ቁጥር፡- 72
👉 አጣቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር፡- 14,664
👉 በፅኑ የታመሙ ሰዎች =130

📌 #በአለም #አቀፍ

👉አጠቃላይ የተያዙ ቁጥር፡- 3,484,567
👉 ባለፉት 24 ሰአት የተያዙ ሰዎች ቁጥር፡- 83,255
👉 አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር፡- 244,787
👉 ባለፉት 24 ሰአት የሟቾች ቁጥር፡- 5,215
👉 አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር፡- 1,121,612
👉 በፅኑ የታመሙ ሰዎች = 50,861



(#በጤና #ባለሙያ #ከድጃ)
#ንጹህ #ማር #በውሃ #በጥብጦ #በባዶ #ሆድ #መጠጣት #ያለው #አስገራሚ #ጥቅሞች

************************

#አዘገጃጀት ፡-

አንድ ብርጭቆ ለብ ያለ ውሃ እና አንድ የሾርባ ማንኪያ ንጹህ ማር ማዘጋጀት። በመቀጠልም ማሩን ውሃው ውስጥ በመጨመር ሁለቱ ተዋህደው የሚያስገኙት የቀለም አይነት እስኪመጣ ድረስ በደንብ ማማሰል እና በአግባቡ መቀላቀል፤ በጣም ያልቀላ የቀለም አይነትእስኪያመጣ ድረስ። ከዛም ያዘጋጁትን የማር እና የውሃ ቅልቅል ምንም አይነት ምግብ ሳይቀምሱ በባዶ ሆድ ከቁርስ በፊት መጠጣት፥ ከቻሉም ይህን ውህድ ማታ ላይ ከእራት በፊት ቢደግሙት እና ቢጠጡት መልካም ነው።

#ውህድ #በመጠጣት #ጥቅም ፡-

📌 ሳንባ ላይ የሚከማችን አክታ ያስወግዳል

📌 የጉሮሮ ቁስለትንና አደገኛ ጉንፋንን በመከላከል እና በማስወገድ
📌 የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን ያዳብራል፤

📌 የሆድ እቃ እና የውስጥ ቁስለትን በማስወገድ ለበሽታ የሚያጋልጡ

📌 ጥገኛ ህዋሳት እንዳይራቡ ያደርጋል፤

📌 የሆድ ድርቀትን በመከላከልና በማለስለስ ለተስተካከለ የሰውነት ሽግግር ይረዳል። ከዚህ መፀዳጃ አካባቢ የሚፈጠር ድርቀትንም መከላከል ያስችላል፤

📌 አጠቃላይ ሰውነትንና አንጀትን ንጹህ እና ፅዱ በማድረግ መርዘኛ ነገሮችን ከሰውነት ለማስወገድ ይረዳል፤
ፈንገስን ፣ ባክቴሪያን እና ቫይረስ በሰውነት ውስጥ እንዳይከሰትና እንዳይከማች ያደርጋል፤

📌 የሚከሰትን የሽንት አለመቆጣጠር ስርአትን ማስተካከልም የዚሁ ውህድ ሌላው ጠቀሜታ ነው።

📌 ማር የኩላሊትን የማጣራት ተግባር በእጅጉ በማገዝ እና ስራውን ቀልጣፋ በማድረግ የሚፈጠረውን የጤና ጠንቅ የማስወገድ አቅም አለው።

📌 ማራኪና ፅዱ የቆዳ ገጽታንም ያላብስዎታል።

*****************************
(#በጤና #ባለሙያ #ሄርለም)
📌 #በኢትዮጵያ #ተጨማሪ 2 #ሰዎች #በኮሮና #ቫይረስ #መያዛቸው #ተረጋግጧል!

ባለፉት24 ሰዓት በተደረገው 1,560 ላቦራቶሪ ምርመራ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 135 ደርሷል።