እንዴት ልብ ውስጥ የሚቀር መዝሙር ነው?! የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ፍቅር በልቡናችን ይሳልብን። ይህን መዝሙር ሰምቶ ቀንን መጀመር መታደል ነው።
ለነፍሴ ነፍሷ ነሽ ለመንገዴ ፋና
እንዳልጠፋ አምናለሁ የአንቺው ልጅ ነኝና
https://youtu.be/5eFAilxF0WY
ለነፍሴ ነፍሷ ነሽ ለመንገዴ ፋና
እንዳልጠፋ አምናለሁ የአንቺው ልጅ ነኝና
https://youtu.be/5eFAilxF0WY
YouTube
ለነፍሴ ነፍሷ ነሽ
ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
"ነፍሳችን ከዚህ ዓለም ሕይወት በተለየች ጊዜ ፤ ክስ የሚቀርብብን ተአምራት ስላላደረግን ወይም የነገረ መለኮት ሊቅ ስላልሆንን ወይም ደግሞ ራእያትን ስላላየን አይደለም። ነገር ግን ስለ ኃጢአታችን ሳናቋርጥ ባለ ማልቀሳችን ምክንያት በዚህ በእርግጠኝነት በእግዚአብሔር ፊት እንጠየቃለን።"
ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው
(St. John Climacus, Author of the Divine Ladder)
+++ፍጽምት በሆነች የንስሓ እንባ ጎርፍ እንደ በረሃ የደረቀች ነፍሳችንን በጽድቅ እናለምልም!!!+++

🌟🌟🌟በገና አባት የተሸፈነ ቅዱስ አባት🌟🌟🌟
+++ቅዱስ ኒቆላዎስ ገባሬ መንክራት (St.Nicholas the wonder worker)+++
ቅዱስ ኒቆላዎስ (St.Nicholas-Santa Claus) በሮማ መንግስት ዘመን በኤዥያ ውስጥ በምትገኝ ሜራ በምትባል ሃገር (የአሁኗ ቱርክ) ግሪካዊ ከሆኑ ክርስቲያን ቤተሰቦቹ ተወለደ፡፡ የዚህም ቅዱስ እናቱ ጦና (Tona) አባቱ ኤጲፋንዮስ ይባላሉ፡፡ እኒህም እግዚአብሔርን የሚፈሩና ባለጠጎችም ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከሞቱ በኋላ ንብረታቸውን የሚያወርሱት፣ ለልባቸውም ደስታን የሚመግብ ልጅ አልነበራቸውም፡፡ ዕድሜያቸውም እየገፋ በመምጣቱም ምክንያት በተስፋ መቁረጥ ተከበው ይኖሩ ነበር፡፡ በልብ መታሰቡ በቃል መነገሩ ከፍ ከፍ ያለ አምላክ በእርጅና ዘመናቸው በቸርነቱ ጎበኛው፡፡ ቅዱስ የሆነም ልጅን ሰጣቸው፡፡ ይህም ልጅ ገና ታናሽ ሳለ መንፈሰ እግዚአብሔር የሞላበት ነበር፡፡ ዕድሜውም ለትምህርት በደረሰ ጊዜ ዕውቀትና ጥበብን ይቀስም ዘንድ ወደ መምህራን የተላከ ቢሆንም ፤ ከመምህሩ ከተማረው ይልቅ ከመንፈስ ቅዱስ የተረዳው ይበልጥ ነበር፡፡
መሠረታዊ የሆኑትን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርቶች በልጅነቱ ተምሮ በማጠናቀቁ በዲቁና መዓርግ ተሾመ፡፡ በኋላም የአጎቱ ልጅ አበምኔት በሆነበት በአንዱ ገዳም አርዑተ ምንኩስናን (የምንኩስናን ቆብ) ጭኖ የቅድስና እና የትሕርምት ሕይወትን ኖሯል፡፡ በአሥራ ዘጠኝ ዓመቱም የቆሞስነትን መዓርግ አግኝቷል፡፡
ለዚህም ቅዱስ አባት እግዚአብሔር ተአምር እና ድንቅን የማድረግ ፤ሕሙማንንም የመፈወስ ታላቅ ጸጋ ሰጥቶታል፡፡
#ለጋስ (የስጦታ) አባት
በሜራ ከተማ የሚኖር ቀድሞ ባለጠጋ የነበረ በኋላ ግን ሃብት ንብረቱን ያጣ አንድ ሰው ነበረ፡፡ በድህነቱ ምክንያት ሊድራቸው ያልቻለ ሦስት ዕድሜያቸው ለጋብቻ የደረሱ ሴቶች ልጆች ነበሩት፡፡ ሰይጣንም እነዚህን ልጆቹን በዝሙት ሥራ ገንዘብ እየሰበሰቡ ሕይወታቸውን እንዲመሩ ያደርጋቸው ዘንድ ክፉ ሐሳብን በሕሊናው አመጣበት፡፡ እግዚአብሔርም በዚህ ሰው ልቡና ውስጥ ሰይጣን የተከለበትን ክፉ ሐሳብ እና ምን ሊያደርግ እንደተነሣሣ ለቅዱስ ኒቆላዎስ ገለጠለት፡፡
ቅዱስ ኒቆላዎስም የእናት የአባቱ ገንዘብ ከሆነው ላይ መቶ ዲናር ወስዶ በስልቻ (sack) ጠቅልሎ ማንም ሳያየው በምሽት ወደዚያ ደሃ ሰው ቤት በመሄድ በመስኮት በኩል ወረወረለት፡፡ ያም ደሃ ከየት እንደመጣ ያላወቀውን 100 ዲናር በቤቱ ባገኘ ጊዜ ተደነቀ አምላኩንም አመሰገነ፡፡ ያሰበውንም ክፉ ሐሳብ ተወ። በገንዘብ እጦት ምክንያትም ከትዳር የዘገየችውን የመጀመሪያ ልጁን ዳረ፡፡ በሌላም ቀን ቅዱስ ኒቆላዎስ ሁለተኛ ልጁን መዳር ይችል ዘንድ ፤ አሁንም ተጨማሪ መቶ ዲናር ገንዘብ በጥቅል ስልቻ አድርጎ በመስኮቱ በኩል ወረወረለት፡፡ ይህንም ገንዘብ ዳግመኛ በቤቱ ያገኘው ያም ደሃ ሰው ፤ እንዲህ ያለውን ቸርነት በስውር የሚያደርገው ምን ዓይነት ሰው እንደሆነ አይቶ ያውቅ ዘንድ ጉጉት አደረበት፡፡ ቤቱንም በንቃት መከታተል ጀመረ፡፡
ቅዱስ ኒቆላዎስም እንደ ለመደው ለሦስተኛ ጊዜ መቶውን ዲናር የያዘውን ስልቻ በመስኮት ሲወረውር ወዲያው ተዘጋጅቶ ይጠብቀው የነበረው ሰው ፈጥኖ በሩጫ ከቤቱ ወጣ። ሊያየው ይመኘው የነበረ ያንንም ቸር ሰው ሊቀ ጳጳሱ ኒቆላዎስ ሆኖ አገኘው፡፡ ከእግሩ ስርም ተደፍቶ ልጆቹን ከድህነት እና ከኃጢአት ሕይወት ስለታደገለት ሊያመሰግነው ቢሞክርም ፤ ቅዱስ ኒቆላዎስ ግን ምስጋናውን እምቢ አለ፡፡ ይህን ሐሳብ በልቡ ያኖረ እግዚአብሔርንም ያመሰግን ዘንድ ለመነው፡፡
ከዚህ ታሪክ በተጨማሪም ለሕፃናት እና ለተቸገሩ ሰዎች ያደረገው ልግስና የብዙ ብዙ ነው። ለዚህም ይመስላል በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት መታሰቢያውን በልግስና የሚያከብሩት።
በአጠቃላይ ይህ ቅዱስ አባት በዘመነ ዲዮቅልጥያኖስ ስለ እምነቱ ብዙ ስቃይ እና እስራት ደርሶበታል፡፡ ፋታ በማይሰጥ መከራ እና ግርፋት ውስጥ እያለ የራሱን ሕመም ከማዳመጥ ይልቅ በውጪ ላሉ ለልጆቹ ምዕመናን የሚያበረታታ እና በእምነታቸው እንዲጸኑ የሚያደርግ መልእክትን ይጽፍላቸው ነበር፡፡ በ325 ዓ.ም ለአውግዞተ አርዮስ ከተበሰቡት 318ቱ ሊቃውንት መካከል አንዱ የነበረ የዚህች ኦርቶዶክሳዊት እምነት ባለውለታ ነው፡፡ ከአርባ ዓመታት በላይ በሊቀ ጵጵስና መንበር በጎቹን ከነጣቂ ተኩላ እየጠበቀ ቤተ ክርስቲያንን ካገለገለ በኋላ በሰማንያ ዓመቱ አርፏል፡፡
(ይህም አባት በእኛ (በኢትዮጽያ) የስንክሳር መጽሐፍ ላይ የእረፍቱ መታሰቢያ የጥር ወር በገባ በአስራ ስምንተኛው ቀን እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ኒቆላዎስም ማለት ‹መዋኤ ሕዝብ - ሕዝብን የሚያሸንፍ› ማለት እንደሆነ ስሙን ይተረጉምልናል።)
የልደት በዓል እግዚአብሔር አብ ልጁን ለዓለም የሰጠበት በመሆኑ ‹የሥጦታ በዓል› በመባል ይጠራል፡፡ ይህንንም በማሰብ ለድሆች በመራራት ለተቸገሩት ቸርነት በማድረግ እናከብረው ዘንድ ምሳሌ እንዲሆነን ቅዱስ ኒቆላዎስን እናስባለን፡፡ ምንም ዓለም አፈ ታሪክ አድርጋ ብታወራውም የዚህንም ቅዱስ ማንነት እንዳይታወቅ በፈጠረቻቸው ተረቶች ብታጠለሸውም እኛ ግን የ‹ገና አባት› ብላ ከሰየመቻቸው የፈጠራ ሰው ጀርባ እውነተኛ የሆነውን ይህን ቅዱስ አባት እናስበዋለን፡፡
+++++ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን! እኛ ኃጢአተኞቹንም በዚህ ጻድቅ ሰው ጸሎት ይማረን!!!+++
ምንጭ:– -መጽሐፈ ስንክሳር
-Coptic synaxarium
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com

"መላእክት" በተሻለ የኅትመት ጥራት ለ3ኛ ጊዜ ታትማ ከፊታችን ቅዳሜ (ታኅሣሥ 18) ጀምሮ በሁሉም መጻሕፍት መደብር ውስጥ ያገኝዋታል። የመልአኩን በዓል ስለ መላእክት በማንበብ ያሳልፉ።
"መላእክት" መጽሐፍ አሁን ገበያ ላይ ትገኛለች!
የመጽሐፏ አከፋፋይ ብራና የመጽሐፍት መደብር
መልካም በዓል ከንባብ ጋር ይሁንልዎ!
የመጽሐፏ አከፋፋይ ብራና የመጽሐፍት መደብር
መልካም በዓል ከንባብ ጋር ይሁንልዎ!
+++የሕጻናት ጥምቀት+++
አዳምና ሔዋን ሕግ አፍርሰው ከተከለከሉት ዛፍ ፍሬ ከበሉባት ሰዓት ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔርን ተገፈው እርቃናቸውን ቀርተዋል፡፡ በወቅቱም የተሰማቸውን እንግዳ የሐፍረት ስሜት መቆጣጠር ስለተሳናቸው ዕርቃናቸውን የሚሸፍኑበትን ቅጠል በገነት ካሉት ዛፎች ቆርጠው በሰውነታቸው ላይ አገለደሙ፡፡ እግዚአብሔርም ከገነት ባስወጣቸው ጊዜ ያገለደሙት የቅጠል ስፌት የዚህን ዓለም ብርድ እንደማይቋቋምላቸው ስላወቀ ከእንስሳት ለምድ የተዘጋጀ የሚሞቅ የቁርበትን ልብስ አለበሳቸው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የሰው ልጅ ሁሉ ልብስ ያስፈልገው ጀመር፡፡ የዕድሜ ክልል ገደብ ሳይኖረው አረጋዊውም ፣ዛሬ የተወለደውም ሕጻን በጨርቅ የሚጠቀለል ሆነ፡፡
ማንኛውም ሕፃናት ልጆች ያሉት ጤናማ ወላጅ ልጆቹ የልብስን ጠቀሜታ ስላልተረዱ ‹አድገው እስኪረዱት ድረስ እርቃናቸውን ይቆዩ› በማለት እንደማይተዋቸው የታወቀ ነው፡፡ ምንም ክፉና ደጉን ባይለዩ፣ ራቁት የመሆን የሐፍረት ስሜት ባያሸንፋቸውም ፤ ከጤናቸው አንጻር በብርድ እንዳይታመሙበት ሲል ለልጆቹ በማሰብ ልብስ ያለብሷቸዋል፡፡
የሰው ልጅ ሥጋዊ ወይም ቁሳዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊም ፍጥረት ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ለግዙፍ ሥጋው መጎናጸፊያ ልብስ እንደሚያስፈልገው ፤ ለረቂቅ ነፍሱም ልብስ ያስፈልጋታል፡፡ በልብስ ያልተሸፈነ ሰውነት ለብርድና ለተለያዩ በሽታ አምጪ ሕዋሳት እንደሚጋለጥ ፣እንዲሁ በልብስ ያልተሸፈነች ነፍስም በኃጢአት ከሚመርዟት አጋንንት ማምለጥ አትችልም፡፡ ታዲያ ይህ የነፍሳችን ልብስ ምንድር ነው? እንዴትስ ነው የምትለብሰው?
ድንኳን ሰፊ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነፍሳችን ስለምትለብሰው ረቂቅ በፍታና ስለምትለብስበትም መንገድ ምንነት ለገላትያ ሰዎች በላከው መልእክቱ ‹የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋል› ሲል ይናገራል (ገላ 3፡27)፡፡ ከዚህም የሐዋርያው ትምህርት በመነሣት የነፍስ ልብስ የተባለው ‹ክርስቶስ› ሲሆን ፤ እርሱን የምንለብስበት መንገድ ደግሞ ‹ጥምቀት› መሆኑን እንረዳለን፡፡
በዛሬ ጽሑፋችን ምሥጢራትን በመመገብ የእናትነት ድርሻዋን የምትወጣው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ለምን በሕፃንነት ዕድሜያችን እንድንጠመቅ እንደምታደርገን በጥቂቱ እንመለከታለን፡፡ ብዙ ጊዜ ይህ ርዕሰ ጉዳይ ሲነሣ በተቃራኒ የትምህርት ጎራ ውስጥ ያሉ ወንድሞቻችን ከሚያቀርቧቸው የተቃውሞ አሳቦች መካከል ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡ አንደኛው ‹ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ› የሚለውን የቅዱስ ጴጥሮስን የስብከት ቃል ይዘው ‹እነዚህ የምታጠምቋቸው ሕጻናት ምን ኃጢአት አለባቸው?› ሲሉ የሚጠይቁት ሲሆን ፣ሁለተኛው ደግሞ ‹ገና ሕጻናት ሲሆኑ ምን አውቀው ነው ያለ ፈቃዳቸው የምታጠምቋቸው?› የሚል ከማወቅ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ነው (ሐዋ 2፡38)፡፡
የመጀመሪያው ጥያቄ የጥምቀትን ጥቅሞች ካለመረዳት የመጣ ጥያቄ ይመስላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ጥምቀት ከሚፈጸምባቸው ምክንያቶች አንዱ ለኃጢአት ስርየት እንደሆነ ቢናገርም ‹ለኃጢአት ሥርየት ብቻ› ግን አይልም፡፡ ከሁሉም በላይ በጥምቀት የምናገኘው ትልቁ ጸጋ ‹ልጅነት›ን ነው፡፡ ስለዚህም ታላቅ ጸጋ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአይሁድ አለቃ ለኒቆዲሞስ ‹ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ… › በማለት በጥምቀት ስለሚገኘው የእግዚአብሔር ልጅነት አስተምሮታል (ዮሐ 3፡5)፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም እንደሚናገረው ቤተ ክርስቲያን ሕጻናትን የምታጠምቀው ኃጢአት ፣በደል አለባቸው ብላ ሳይሆን ፤ ከለጋነት ዕድሜያቸው ጀምረው ፍቅሩን እያጣጣሙ እንዲያድጉ የሚያስችላቸውን የእግዚአብሔር ልጅ የመሆንን ጸጋ ልትሰጣቸው ነው፡፡
ወደ ሁለተኛው ጥያቄ ስንመጣ በራሱ በጥያቄው መነሻ አሳብ ላይ የምንመለከተው እንደ ገደል የሰፋ ክፍተት አለ፡፡ ይህም ክፍተት ጥያቄውን የሚጠይቁ ሰዎች የተነሡበት ‹ሕጻናት አያውቁም› የሚለው ጭፍን መንደርደሪያ ነው፡፡ እነርሱ ‹ሕጻናት እንደማያውቁ በምን አወቁ? አንድ ሕጻን ስላልተናገረና አሳቡን በቃላት ስላልገለጸ ብቻ አያውቅም ሊባል ይችላል? ፡፡ እንዲህ ካሉ ደግሞ የጌታ እናት እመቤታችን ወደ እርሱ እንደቀረበች አውቆ በስግደት የደስታውን ስሜት ስለገለጸው የስድስት ወር ፅንስ ምን ይላሉ? ሳያውቅ ነው የዘለለው ሊሉን ይሆን? ቢቀበሉ ደግሞ ይህን የመሳሰሉ ድንቅ ማስረጃዎችን ከቅዱሳን አበው ገድላት እናቀርብላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን እንኳን የአዋልዱን ይቅርና የአሥራው መጻሕፍቱንም ምስክር ለማመን ስለሚቸገሩ ማስረጃ አናባክንም፡፡
ታዲያ እነዚህን ጥያቄዎች ስንጠይቅ እኛ ደግሞ በተቃራኒው ሕጻናት ያውቃሉ ወደሚል ሌላ ጽንፍ እያመራን አይደለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሕጻናትን የምታጠምቀው ያውቃሉ ወይም አያውቁም ብላ አይደለም፡፡ የቤተሰቦቻቸውን እምነት ምስክር በማድረግ ነው እንጂ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በልጅነታቸው ጥምቀተ ክርስትና የተፈጸመላቸው እንዳሉ የሚያሳዩ ልዩ ልዩ የንባብ ክፍሎች አሉ፡፡ ለአብነትም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በተመሳሳይ ምዕራፍ ላይ የምናገኛቸውን ሐር ሸጯ ልድያንና የወኅኒ ቤተ ጠባቂውን ማቅረብ እንችላለን፡፡ መጽሐፉ ሁለቱም ሰዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንደተጠመቁ ይናገራል (ሐዋ 16፡15 ፣34)፡፡ ታዲያ ከቤተሰቦቻቸው መካከል ሕጻናት ሊኖሩ አይችሉምን?
ሌላው በበዓለ ሃምሳ ከተሰጠው የቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት ውስጥም ስለ ሕጻናት ጥምቀት የሚናገር ግልጽ ማብራሪያ እናገኛለን፡፡ ይኸውም ‹ኃጢአታችሁ ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ… የተስፋው ቃል (ተጠምቆ መንፈስ ቅዱስን መቀበል) ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ነውና› የሚለው ሲሆን በዚህ አረፍተ ነገር ውስጥ ‹ለልጆቻችሁ› የሚለው ቃል ያለ ማብራሪያ ጥምቀት ለሕጻናት እንደሚፈጸም የሚያሳይ ነው (ሐዋ 2፡38-39)፡፡ ጌታችንም በወንጌል ‹ሕፃናትን ተዉአቸው ፤ ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው› ሲል የተናገረውን ቃል እንዴት እንረዳዋለን? ሕፃናት ወደ እግዚአብሔር እንዴት ይቀርባሉ? ሕፃናት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የሚችሉት በምሥጢራት (Sacraments) ነው፡፡ ታዲያ ከምሥጢረ ጥምቀት የበለጠ ሕፃናት እና አምላክን በአባትና ልጅነት የሚያቀራርብ ምን አለ? ሕጻናት እንዳይጠመቁ ከመከልከል የበለጠስ እነርሱን ከፈጣሪ የማራቅ ሥራ ምን አለ? (ማቴ 19፡14)፡፡
እነ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮትም ቅዱስ ጳውሎስ ለጥምቀት ምሳሌ አድርጎ ያነሣውን የግዝረት ሥርዓት ለሕጻናት ጥምቀት ማስረጃ አድርገው አስተምረውበታል፡፡ በአብርሃም ዘመን ግዝረት የእግዚአብሔር ሕዝብ ወይም ወገን ለመሆን ምልክት ነበር፡፡ ስለዚህም በአብርሃም ቤት የሚወለዱ ሕፃናት ስምንት ቀን ሲሆናቸው እንዲገረዙ ሕግ ወጥቷል (ዘፍ 17፡10-14)፡፡ ሕፃኑም በዚያ የቀናት ዕድሜ ላይ እያለ ይገረዛል እንጂ ቆይ ይደግና ጠይቀነው አይባልም፡፡ ልክ እንደ ግዝረቱ በሐዲስ ኪዳንም ጥምቀት ከእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ጋር በሕዋስነት የምንቆጠርበት ምሥጢር ነው፡፡ ግዝረት በሕጻንነት ይፈጸም እንደነበር ፤ ጥምቀትም በሕፃንነት ይፈጸማል፡፡ እንደ ቅዱስ ጎርጎርዮስም አባባል ‹የጣቶቻቸው ጥፍር ሳይጸና› በጨቅላነት ዕድሜያቸው ይጠመቃሉ፡፡ ይኸው ሊቅ ሌላው የጥምቀት ምሳሌ የሆነውን የእ

ስራኤላውያንን ቀይ ባሕር መሻገር በማንሣት ፤ ባሕሩን የተሻገሩት ሕፃናትም ጭምር እንደሆኑ ፣ጥምቀተ ክርስትናም ለሕፃናት ይፈጸማል ሲል ይናገራል (1ኛ ቆሮ 10፡1-2)፡፡
ጥምቀተ ክርስትና ሁል ጊዜ ተጠማቂው ተጠይቆ ላይፈጸም ይችላል፡፡ ለምሳሌ የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረው የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አዳምን ከፈጠረው በኋላ በአፍንጫው የሕይወት እስትንፋስን እፍ ብሎበታል፡፡ ይህም እፍታ ለአዳም የልጅነትን ጸጋ ያገኘበት ጥምቀቱ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን ታሪክ በያዘው የኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ እግዚአብሔር ለአዳም የልጅነት ጸጋውን ከመስጠቱ በፊት እንደ ጠየቀው አይናገርም፡፡ ታዲያ እንዴት የሠላሳ ዓመቱ ጎልማሳ አዳም ያልተጠየቀውን ጥያቄ የአርባን ቀን ልጅ ጠይቁ ይሉናል? ፡፡ እግዚአብሔር አዳምን አልጠየቀውም ማለት አስገደደው ማለት አይደለም፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ሕጻናትን በቀጥታ እነርሱን አልጠየቀችም ማለት አስገድዳቸዋለች ማለት አይደለም፡፡ አዳም የኋላ ኋላ በፈቃዱ ፈጣሪውን ክዶ ልጅነቱን እንዳጣ እንዲሁ የእግዚአብሔርን አባትነት ያልፈለጉትም አድገውም ቢሆን የመካድ መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡
ሌላው አንዳንድ ጊዜ ከማመን (ከትምህርት) ጥምቀት ሊቀድም የሚችልባቸውም ሁኔታዎች እንዳሉ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ነው አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያቱን ወደ ዓለም ሲልካቸው ‹ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ፤ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው› ሲል ያዘዛቸው (ማቴ 28፡19)፡፡ ልብ በሉ በዚህ የጌታችን ትዕዛዝ ውስጥ በቀዳሚነት የተነገረው ‹አስተምሩ› የሚለው ሳይሆን አጥምቁ የሚለው ነው፡፡ ስለዚህ አድገው ወደ ቤተ ክርስቲያን ለሚገቡ ካልሆነ በቀር ለሕፃናት ጥምቀት ሊቀድም ይችላል፡፡ ደቀ መዝሙርነት የሚገኘው ከጥምቀት በኋላ ነው፡፡ ሳይጠመቁ ደቀ መዝሙርነት የለም፡፡
በአጠቃላይ ከላይ ያቀረብናቸው ነጥቦች የሕፃናትን ጥምቀት ተገቢነት የሚያሳዩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ሲሆኑ በተቃራኒው ግን የሕፃናትን ጥምቀት የሚከለክል ምንም አይነት ትምህርት ወይም ማስረጃ በመጽሐፍ ቅዱስ አናገኝም። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተግባሯ ብትመሰገን እንጂ የምትነቀፍ አይደለችም።
ዲ/ን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
Repost

በጉልምስናው ወቅት በብርሃን ተምትቶ ወደ ፈጣሪው የቀረበው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከዚህ ዓለም ሕይወት ይልቅ ከክርስቶስ ጋር መኖር ከተሻለው ፤ ከልጅነቷ ጀምሮ በመቅደስ ከእርሱ ያልተለየች በኋላም ራሷ ሕያው መቅደስ ሆኗ በማሕጸኗ የተሸከመችው የብርሃን እናቱ እመቤታችን ወደ ልጇ ወደ አምላኳ መሄድ እንዴት አብልጦ አይሻላትም?! ። የጳውሎስ ድንካኑ የተባለች እመቤታችን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ዓለም ለተሸጋገረችበት ዕለተ እረፍቷ እንኳን በሰላም አደረሰን። እኛንም ባሮቿን ከክፉው ወደ መልካም ነገር ታሻግረን!!!