ISLAMIC-QUOTES
2.26K subscribers
1.01K photos
280 videos
39 files
981 links
ለአስተያየት @Tefekurbot



ቆይ ቆይ ምን ጎደለብን ልንል ነው?? የምናመልከው ጌታ እያለን፣የምንከተለው ዲን እያለን፣ተውሂድና ቁርአንን የመሰለ ሀብት እያለን !!!ምንው ማስተዋሉ ከበደን ?ከልሀምዱሊላህ ለሙላልን ኒዕማ
Download Telegram
#የቢደዓ_አስከፊነት
~~~
ኢማም ማሊክ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ

"በእስልምና ላይ አዲስ ፈጠራን የፈጠረ  (ይህችን ፈጠራ ወይንም ቢደዓ ) ጥሩ እንደሆነች አድርጎ የተመለከተ በእርግጥም ረሱል ﷺ መልእክታቸውን እንዳጓደሉ(በትክክል) አላደረሱም ብሎ ሞግቷል!!
............
#ምንጭ አልኢእቲሷም ሊሻጢቢ 64/1
በታሪኽ #አጭሯ የጁመዓ #ኹጥባ
አሽሸይኽ ሙሐመድ አል-ጣሂር ቢን አሹር - አላህ ይዘንላቸው ሚንበር ላይ ወጡ ፡-

" እነዚህ በገበያ ላይ ያሉ ሴቶች እነማን ናቸው? !" ብለው ጠየቁ ። ሰጋጆቹም አልመለሱለትም ። ከዚያም ያንኑ ጥያቄ በድጋሚ ጠየቋቸው ። ምንም ምላሽ አላገኙም ። ተቀምጠው እንደገና ተነሱና

" ሴቶቻችሁ ራቁታቸውን እየሄዱ በሰላታችሁ ምንም ደግ ነገር የለም። !" አሉ ።
ኢቃም አድርገው ሰላቱን አሰገዱ ።

#አጂብ አጭር ግን መልዕክቱ ከባድ የሆነ ኹጥባ
እያንዳንዱ የምትጎዳኘው ባልደረባ ፣ የምትሄድበት ቦታ ፣የምታነበው መፅሀፍ እና የምትሰማቸው አመለካከቶች በነፍስህ ላይ አሻራ እንደሚያስቀሩ እወቅ። በርግጥ ላይታወቅህ ይችላል ነገር ግን በምድር ላይ ያለች ልክ እንደ ትንሽ የወይራ ፍሬ አስበው***** ማንም ዞር ብሎ ሳያስተውላት ቀኗ ይደርስና በዙሪያዋ ያለ የሚያስተውላት ትልቅ ዛፍ ትሆናለች።

አሊ አጠንጣዊ |•🧡

----------------------
----------------------
🗓ሸዋል -7

⇛ረመዷንን ጨርሰው ሸዋልን ላስከተሉ ዛሬ የመጨረሻ ቀናቸው ነው። -እንኳን ደስ አላቸው!!

☞መጀመር ትልቅ ዉሳኔ ነው ። የጀመረ ነው የሚጨርሰው እንደ «መጀመር» ከባድ ነገር የለም። ዛሬ ነገ እያሉ እንደ መቅጠርም ስንፍና የለም።ሳይታወቅ ቀኑ ይሮጣል፣ሳይታሰብ ወሩ ያልቃል፤ እንደዋዛ አጅሩም ያመልጣል። የዓመት ፆም ምንዳ ማለት ቀላል ነገር አይደለም።

⇛ባለፉት ስድት ቀናት ያልፆምን በተቀሩት ቀናት ዉስጥ ሸዋልን እንፁም። አላህ የሠጠንን ዕድሎች በደስታ እንጠቀም።

አላህ ሆይ ስላስጀመርከንም ስላስጨረስከንም አብዝተን እናመሰግንሃለን።ሥራ ከኛ ነው፤ ምንዳ ካንተ ነው።
~
🟢የሚዲያ ተጠቃሚዎች ሆይ:

በተለያዩ ብዙሃን መገናኛዎች (ሚዲያዎች) ላይ የምትንቀሳቀሱና ዲናዊ ትምህርቶችን የምታሰራጩ ሁሉ የሚከተሉትን ነጥቦች ተጠንቀቁ⤵️

1⃣ ያለ እውቀት መዳፈር

አላህ በጥብቅ የከለከለው ጉዳይ ነው:
قال الله سبحانه
وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۚ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا》  الإسراء:(36)
"እውቀት በሌለህ በሆነ ነገር አትከተል ።መስሚያ ፣ መመልከቻም ፣ ልብም በእነዚህ ሁሉ (ተግባር) ባለቤታቸው እኮ ተጠያቂ ነው።"

ከዚህ ውስጥ ያላዳመጡትን ድምፅ ፣ ያላነበቡትን ፅሁፍ፣ ያልተረዱቱና ያለመኑበትን መልእክት ማስተላለፍ አይገባም። ጉዳዩ የስግብግቦች የጅምላ ንግድ ሳይሆን ትልቁን የነቢያትን ውረስ የማስተላለፍ ሀላፊነት ነው።

2⃣ ተከታዮችን አለማገናዘብ

መልእክቱ በቀጥታ የሚደርሳቸውን ተከታታዮች ከግምት ያለስገባ ስርጭት አደጋው ብዙ ነው። ከመምራቱ ይልቅ ማጥመሙ ሊያዘነብል ይችላልና። ከጥቅሙም ጉዳቱ። በተቻለ መጠን በአስተላለፊው ደረጃ ሳሆን ተከታታዮችን ያገናዘበ ጉዳይ ነው መተላለፍ ያለበት።
ዲኑ የምር ጉዳይ ነውና ዛዛታና የሀሰት ወሬ ይፃረረዋል። ከሚከተተሉን ውስጥ ብዙ የተከበሩ ሰዎች እንዳሉም እናተውል።
አላህ እንዳዘዘው:
﴿…وَقُولُوا لِلنَّاسِ حُسْنًا…﴾[البقرة: ٨٣]

3⃣ ቀደም ቀደም ማለት

አዲስ አጀንዳ ከማሰራጨት በፊት በጉዳዩ ላይ የተሻለ እውቀት ያላቸው ሰዎች ሊናገሩ ወይም ሊፅፉ እየቻሉ የደፋሮች ቀዳም ቀደም ማለት በርካታ መዘዞች አንዳሉት በመረጃም በታሪክም የታወቀ ነው።
በተለይም ኡማውን የሚመለከቱ አዳዲስ ክስተቶችን አስመልክቶ ሰለፊይ ዑለማዎች የሚሉቱን በትዕግስት መጠበቅና መጠየቅ በራሱ አዋቂነትና ሰለፊይነት ነው። ተቃራኒውም በተቃራኒ።
አላሁ ተዓላ እንዳለው:
《…وَإِذَا جَاۤءَهُمۡ أَمۡرࣱ مِّنَ ٱلۡأَمۡنِ أَوِ ٱلۡخَوۡفِ أَذَاعُوا۟ بِهِۦۖ وَلَوۡ رَدُّوهُ إِلَى ٱلرَّسُولِ وَإِلَىٰۤ أُو۟لِی ٱلۡأَمۡرِ مِنۡهُمۡ لَعَلِمَهُ ٱلَّذِینَ یَسۡتَنۢبِطُونَهُۥ مِنۡهُمۡۗ…》[النساء :٨٣]

4⃣ አመፅን ማሰራጨት

ለምሳሌ: ሱረህ (ፎቶና ቪዲዮ) ፣ የዘፈን ድምፅ፣ የአጥማሚዎችን ጣቢያ (ቻናል) ፣ ከአመፅ ሚዲያዎች (ለምሳሌ ቲክቶክ) የመጡ ነገሮች ፣ ውሸት እና የመሳሰሉትን ማስተላለፍ አለማው ጥሩ ቢመስልም በራሱ አመፅና ፈሳድን መባባስ (ማስተዋወቅ) ነው።
👌መርዝና ማር ከተቀላቀሉ መርዙ ገዳይ ነው ተብሎ አይፈራምን?!
አላህ ፀያፍ ነገሮች እንዲሰራጩ የሚፈልጉትን አሳማሚ ቅጣት እንደሚቀጣ አስጠንቅቋል።
﴿إِنَّ ٱلَّذِینَ یُحِبُّونَ أَن تَشِیعَ ٱلۡفَـٰحِشَةُ فِی ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِیمࣱ فِی ٱلدُّنۡیَا وَٱلۡـَٔاخِرَةِۚ وَٱللَّهُ یَعۡلَمُ وَأَنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ﴾ [النور: ١٩]

5⃣ ስህተትን አለመቀበል

ያሰራጩት ጉዳይ ጥፋት ሆኖ  ሲነገራቸው ከማስተካከልና ወደ ሀቁ ከመመለስ ይልቅ የሚብስባቸው ቀልበደረቆችና ኩራተኞች ናቸው።
ሚዲያ ላይ ከወጡ መካሪ ብቻ ሳይሆን ምክር ተቀባይ ለመሆንም መዘጋጀት ያስፈልጋል። ሀቅን አይቶ የማይረታ ድርቀቱ የከፋ ሰለመሆኑ አላህ ነግሮናል።

﴿ثُمَّ قَسَتۡ قُلُوبُكُم مِّنۢ بَعۡدِ ذَ ٰ⁠لِكَ فَهِیَ كَٱلۡحِجَارَةِ أَوۡ أَشَدُّ قَسۡوَةࣰۚ وَإِنَّ مِنَ ٱلۡحِجَارَةِ لَمَا یَتَفَجَّرُ مِنۡهُ ٱلۡأَنۡهَـٰرُۚ وَإِنَّ مِنۡهَا لَمَا یَشَّقَّقُ فَیَخۡرُجُ مِنۡهُ ٱلۡمَاۤءُۚ وَإِنَّ مِنۡهَا لَمَا یَهۡبِطُ مِنۡ خَشۡیَةِ ٱللَّهِۗ وَمَا ٱللَّهُ بِغَـٰفِلٍ عَمَّا تَعۡمَلُونَ﴾ [البقرة :٧٤]
🤲አላህ ይጠብቀን

አቡ ሀመዊየህ
"اقرَؤُوا القُرآنَ فإنَّه يَأْتي يَومَ القِيامَةِ
شَفِيعاً لأَصحابِهِ"
Forwarded from Abu Taymiyyah Amir Mohammed (أبو تيمية عامر بن محمد الولقطي الأثري)
إنا لله وإنا اليه راجعون لله ما أخذ وله ما أبقى وكل شيء عنده لأجل مسمى توفي الشيخ العلامة صالح الحديثي
اسأل الله أن يغفر له ويرحمه ويسكنه الجنة ويقيه فتنة القبر وعذاب  ويجعل المرض كفارة له عظم الله أجركم يا أهل السنة
💎 ጌጥሽ ነው ኒቃቡ !!!!
🌹🌹🌹🌹🌹
በፍቅር ልበሺው ፈፅሞ አታውልቂው፡
ያምርብሻል ወሏህ ውበትሽን እወቂው፡
ኒቃብን ልበሺ ከብርሽን ጠብቂው።
ስቃይ ጎርፍ ሆኖ ቢጥልም ዝናቡ፡
በዱንያዊ ሕይወት ቢበዛም ኢቂቡ፡
ከቶ እንደታወልቂው ጌጥሽ ነው ኒቃቡ።
ይሄን መልክት አድርሱልኝ ለእነዝያ መገላለጥ አረደነት ለሚመስለቸው
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Amine
💦:::::::ውዱ ወንድሜ ሆይ!:::::::::::💦

❥መልካም ሚስት በፍለጋ አትገኝም ስልህ ከዓላህ የምትሠጥ ውድ ሥጦታ ብትሆን እንጂ ማለቴ ነዉ።

ስለዚህ እሷንም በሱጅድህ ውሥጥ ፈልጋት።☜

🍃ወንድሜ ሆይ ያየሃትን ሴት ሁሉ ☞☞ሚስት ለማደድረግ አትሞክር ።

☞የምታያት ሴት ሁሉ ያንተ ሚስት አይደለችም!።

☞የኔ የምትላትን ከእግርህ ሥር ባታገኛትም
በሱጅድ ውሥጥ ፈልጋት ታገኛታለህ። ስልህ መልካም ትዳር የዱአ ውጤት ነው√ ።

☞ላየሃት ሴት ሁሉ ቴክሥት አትፃፍ ማለቴ አስር ያባረረ አንድ አይዝም √☜

🌱ሚሥት አጣሁ አትበል እኔ ባል ነኝ ወይ ብለህ እራሥህ ፈትሽ☜

☞ዓንተ የምትፈላጋትንና የምትወዳትን ሚሥት ለማግኘት በመጀመሪያ አንተ (ዓሏህ) እንደሚፈልገው እንደሚወደው ሆነህ ተገኝ !!

ምክንያቱም አላህ ትዕዛዙን ያሟላ ባሪያውን አያሳፍርም ሊፈትነው ካልሆነ በስተቀር።
~ኒቃብ ላሠራችሁ ሁሉ… ይህችን እሥር በጭንቅላታችሁ ላይ ከማሠራችሁ በፊት በልባችሁ ላይ እሠሩ።የዛኔ በሱ ምክኒያት የሚመጣባችሁ ፈተና ሁሉ ይቀላቹኃል!
Ⅱ~t.me/S1U2M3E4YA
አተኩሮ ላየ ዱንያና ፀሐይ ይመሳሰላሉ። ፀሐይ እንደምትጠልቀው ሁሉ ዱንያም ትጠልቃለች።
ዓለም ላይ የማያልፍ ነገር የለም፤ ላያልፍ የመጣ ነገርም የለም።
كل من عليها فان ويبقى وجه ربك ذوالجلال
t.me/S1U2M3E4YA والإكرام

የጀነት የሆነች ሴት ላሳይህን
🫵ያቻትና በሒጃብዋ የነገሰች የጥቁሮች ተምሳሌት……

ይህ የሆነው በነብዩﷺ ዘመን ነው።
ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ ለተማሪው ዓጣእ ቢን አቢ ረባሕ ጠየቀው… …
"ከጀነት የሆነች ሴት ላሳይህን?"
ሲለው
"እንዴታ! አዎን አሳየኝ" አለው።

"የውህ እቺ ጥቁሯ ሴት ናት; ወደ የአላህ መልእክተኛﷺ ዘንድ መጥታ
“እኔ ራሴን ስቼ እወድቃለሁ: በምወድቅ ጊዜ ሰውነቴን ይገለጣል። ዱዓ ያድርጉልኝ” አለቻቸው።
ነብዩﷺ «ከፈለግሽ ሰብር ታደርጊና ጀነት ትገቢያለሽ; ከፈለግሽ ደግሞ አላህ ዓፊያ እንዲያደርግሽ ዱዓ አደርግልሻለሁ።» አሏት

“የአላህ መልእክተኛ ሆይ!
ሰብር አደርጋለሁ! ግን በምወድቅ ጊዜ ሰውነቴ ይገለጥብኛል: እንዳይገለጥ ዱዓ ያድርጉልኝ።”
አለቻቸው። ዱዓ አደረጉላት።"

እነዚህ ናቸው የሙስሊም ሴቶች!!
ከጤናቸውም ከዱንያቸውም ከምናቸውም በላይ ሂጃባቸው የሚያስጨንቃቸው!! በሂጃባቸው ድርድር የማያውቁ።።

እቺ ሴት ምንም እንኳ መልኳ አላዋቂዎች ዘንድ ቦታ የማያሰጣት ቢሆንም እሷ ግን ለሂጃብዋ ባላት ደረጃና ለጌታዋ ውሳኔ ባላት ታጋሽነት ምክንያት አላህ አዝኖላት
👇
👉በምድር እየተንቀሳቀሰች ጀነት ተመስክሮላታል!!
"በምድር የምትሄድ የጀነት እንስት!!" ተብላ ተሰየመች።

👌ሙስሊም ሴት አስፈላጊ ከሆነ ውድ ሕይወቷን መስዕዋት ታደርጋለች እንጂ በተኣምር ለአንድ ፅንፈኛ ባንዳ ብላ ለትዳር ብላ ወይም ለስራ ለዱኒያዊ ጥቅም ስትል ሂጃብዋን አትጥልም‼️
እስከ መጨረሻ እስትንፋስዋ በሒጃብዋ ትፀናለች።

#ኒቃቧንም_ትለብሳለች
#ትምህርቷንም_ትማራለች

t.me/HijabNewWebta
ኢብኑል ቀይም  رحمـه اللـه تعالـﮯ :-
              እንዲህ አሉ፦


🔹አንዳንድ ሴቶች የለሊት ሰላትን አብዝተው
ይሰግዱ ነበር።ለምን የለሊት ሰላትን እንደምታበዛ
    
   ስትጠየቅ እንዲህ ብላ መለሰች

እሷ (የለሊት ሰላት) ፊት ታሳምራለች እኔ
      
#ፊቴ_እንዲያምር_እፈልጋለሁ

💎وقـد ڪـان بعـض النسـاء تڪثـر صـلاة
                الليـل فقيـل لهـا فـﮯ ذلـك،

🔸 فقالـت :- إنهـا تحسِّـن الوجـه وأنـا أحـب
                   أن يحسـن وجهـي.


📙 روضـة المحبيـن ( صـ321
‎)
﴿مَن كَانَ يُرِيدُ الْعَاجِلَةَ عَجَّلْنَا لَهُ فِيهَا مَا نَشَاءُ لِمَن نُّرِيدُ ثُمَّ جَعَلْنَا لَهُ جَهَنَّمَ يَصْلَاهَا مَذْمُومًا مَّدْحُورًا﴾

«اللَّهُمَّ إنَّا نَعُوذُ بِكَ مِنْ حُبِّ الدُّنْيَا وَطُولِ الأمَلِ»
Forwarded from 🌴ለወጣቶች ምክር🌴 (Mãhämmi Sëiď)
አላህ ዘንድ የቀለለ ሰው የሰዎች ውዳሴ አይጠቅመውም
~
በሰው እጅ እሳትም ሆነ ጀነት የለም። ስለሆነም የሰዎች ጭብጨባና አድናቆት ግብ ሊሆን አይገባም። አላህ ከፍ ያደረገውን የምቀኞች ክፋት አያወርደውም። አላህ ዝቅ ያደረገውን ጭብጨባና ከንቱ ውዳሴ አይሰቅለውም። ስለሆነም የሰዎች ውግዘት ጭንቀትህ፣ ውዳሴያቸው ደግሞ መሻትህ አይሁን። ይልቁንም ለትእዛዙ በማደር ጌታህ ዘንድ ከፍ ለማለት ጣር። ኢማሙል አውዛዒይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
ﺇﻥّ من الناس مَن يُحِبُّ الثّناء عليه، ﻭﻣﺎ يُساوي عند الله جناح بعوضة
"ከሰዎች ውስጥ መወደስን የሚወድ አለ። አላህ ዘንድ ግን የትንኝ ክንፍ አያክልም።" [ሒልየቱል አውሊያእ፡ 8/255]

#ከደጋጎቹ_ቀዬ

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️🀄️ሉን!
👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir
መስጅድ ሁሉም ቦታ መስጅድ ነው። ጉዳቱም ያው ነው። መስጅድን በማታ ጨፍረው ሲያፈርሱት ቢቆጭም ሳይጨፍሩም 11 አመት የተሰገደበትን  በቀን ጠራራ ሲያፈርሱት ሊላህ ከሆነ ጥቃትና ንቄቱ በላጭ ነው።
KH Abate እስካሁን ድረስ በሸገር ሲቲ የፈረሱ መስጅዶች ብዛት ቢደመር ከአማራ ክልሉ አይተናነስም። በዚህ ጉዳይ ላይ የኦሮሚያ መጅሊስና የፌዴራል መጅሊስ ከአቻዎቻቸው የመንግስት መዋቅሮች ጋር በመነጋገር ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲያገኝ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

ምክንያቱም የሸገር ሲቲ አስተዳደር ተብዬዎቹ የቡራዩንም የሆነ የሰበታ መጅሊሶችን ሃሳብ እየሰሙ ስላልሆነ!

ሰበታ አካባቢ መስጂድ፣ የጴንጤ ቸርች፣ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና የባዕድ አምላኪዎች ማምለኪያ ቤት አለ። 4ቱም ተቀራራቢ ቦታ ላይ ናቸው። ነገር ግን ያፈረሱት መስጂዱን ብቻ ነው።
የራሳቸው የእምነት ተቋም ሲሆን ህገ ወጥ ቢሆን እንኳ ከማፍረስ ይልቅ ህጋዊ የሚሆንበትን መንገድ ያመቻቻሉ። የሙስሊሙ መስጅድ ሲሆን ግን እንኳን ህገ ወጥ ነው የሚል ሰበብ አግኝተው ህጋዊ ሆኖ ራሱ የሚያፈርሱበትን ሌላ ስልት ይፈልጋሉ።