Forwarded from Yamral Tadesse
❗️❗️አስቸኳይ መልዕክት❗️❗️
🗯 ቅዳሜና እሁድ ማለትም ጥቅምት 15&16/2018 ዓ፣ም በሃገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም አካባቢዎች የፋይዳ መታወቂያ ማውጣት መርሃ ግብር ይካሄዳል።
🗯በዚህ ፕሮግራም ተማሪዎችን ጨምሮ የፋይዳ መታወቂያ ያላወጡ መርሱዎችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች እንዲያወጡ መልዕክቱን ለሁሉም እንዲደርስ አድርጉ።
🗯ሁሉም ተማሪዎች የፋይዳ መታወቂያ ለማውጣትና ለመመዝገብ የሚያስፈልጋቸው ……
@……የልደት ሰርተፊኬት
@……የሁለተኛ ደረጃ ትቤት ተማሪዎች የትቤት መታወቂያ፣ወይም የባንክ ደብተር፣ይዘው መመዝገብና የፋይዳ መታወቂያ ማውጣት ይችላሉ።
🗯 የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ የሚከናወንባቸው ቦታዎች……
1……አብማ ክፍለ ከተማ……ክፍለ ከተማው ቢሮ ላይ፣ከ/መ/ል/መምሪያ ቢሮ ጎን፣
2……ንጉስ ተክለ ሃይማኖት ክፍለ ከተማ………ቀበሌ 04 አስ/ፅ/ቤት ግቢ ውስጥ፣
3……መንቆረር ክፍለ ከተማ ………ክፍለ ከተማው ቢሮ ውስጥ፣ሆስፒታል ከፍ ብሎ፣
4……ተድላ ጓሉ ክፍለ ከተማ……ቀበሌ 02 አስ/ፅ/ቤት፣ሲኒማ በታች።
👉ነገ 2:30 ሰዓት ጀምሮ ከላይ በጠቀስናቸው ቦታዎች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ስለሚጀመር ለሁሉም ተማሪዎች፣መርሱዎችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች መልዕክቱን አድርሳችሁ እንዲመዘገቡ አድርጉ።
ለተግባሩ ልዩ ትኩረት ይሰጠው።
ተማሪዎችን በየክፍሉ በመዞር እንዲሁም በሰልፍ ላይ ጥብቅ መልዕክት አስተላልፉ።

Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ነገ እሁድ ልዩ በሆነ መልኩ እንዳለ ሰምተዋል?
ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ አስበው ጊዜ እና ሰዓት አልመቻች ብሎዎታል? ተማሪዎችስ ከትምህርት ሰዓት ውጭ ለመመዝገብ? እንግዲያው ነገ ጥቅምት 16 በልዩ ሁኔታ በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች አገልግሎት ስለምንሰጥ በአቅራቢያዎ በሚገኝ የምዝገባ ጣቢያ በመሔድ ይመዝገቡ።
ለተጨማሪ መረጃ id.gov.et ይጎብኙ ወይም 9779 ይደውሉ።
#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳለሁሉም #ፋይዳምዝገባ
ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ አስበው ጊዜ እና ሰዓት አልመቻች ብሎዎታል? ተማሪዎችስ ከትምህርት ሰዓት ውጭ ለመመዝገብ? እንግዲያው ነገ ጥቅምት 16 በልዩ ሁኔታ በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች አገልግሎት ስለምንሰጥ በአቅራቢያዎ በሚገኝ የምዝገባ ጣቢያ በመሔድ ይመዝገቡ።
ለተጨማሪ መረጃ id.gov.et ይጎብኙ ወይም 9779 ይደውሉ።
#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳለሁሉም #ፋይዳምዝገባ
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" በስልጠና ማጠናቀቂያ ወቅት ያገኙት ሰርተፍኬት በዩኒቨርሲቲው ለመማር በሚወዳደሩበት ወቅት 10 በመቶ ውጤት እንዲኖረው እናደርጋለን "- የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ2017 ዓ/ም የክረምት መርሃ ግብር በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 629 ታዳጊ ወጣቶችን በዛሬው ዕለት አስመረቋል።
ታዳጊዎቹ በክረምት መርሃ ግብር የሰለጠኑት ፦
- በሳይበር ደህንነት፣
- በቴክኖሎጂ ልማት፣
- በኢምቤድድ ሲስተም፣ እና በኤሮስፔስ ዘርፎች ነው።
ላለፉት ሦስት አመታት አዲስ አበባ ላይ ብቻ ሲካሄድ የቆየው የስልጠና መርሃ ግብር፤ በ2017 ዓ/ም ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለመጀመሪያ ጊዜ 76 ልጆች ሰልጥነው መመረቅ መቻላቸው ተገልጿል።
ስልጠናውን የተከታተሉት ታዳጊዎች ከኢለመንተሪ፣ ሃይስኩል እና ዩኒቨርሲቲ የተወጣጡ ናቸው ።
ታዳጊዎቹ ስልጠናቸውን ከኢንሳ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በማጠናቀቂያው ወቅት የተሰጣቸው ሰርተፍኬት በዩኒቨርሲቲው ትምህርት ለመከታተል በሚወዳደሩበት ወቅት የመቁረጫው ነጥብ ዝቅ እንደሚያደረግላቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ በዝርዝር ምን አሉ ?
" ግቢ ውስጥ በቆዩበት ጊዜ በተለያዩ ዘርፎች ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል ስልጠናውን ኮርስ በመስጠት ብቻ ሳይሆን ችግሮቻችንን በመንገር ችግሮችን መፍታት ከመቻላቸውም በላይ ፕሮዳክቶችን ይዘው መጥተዋል።
የራሳቸው የሆነ የተለያዩ ችግሮችን መፍታት እና መሸጥ የሚችሉ ፕሮዳክቶችን ይዘው ወጥተዋል።
እኛ ፈተና ፈትነን ተማሪዎችን የምንቀበል መሆኑ ይታወቃል ፈተና ፈትነን ስንቀበል የ 12 ውጤት እና የመግቢያ ፈተና ውጤት ነው የምናየው።
በእዚህ ስልጠና ከመላው የኢትዮጵያ አካባቢዎች መጥተው በግቢያችን ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች የወሰዱት ሰርተፍኬት በግቢያችን ለመማር በሚያመለክቱበት ወቅት ቫልዩ ይኖረዋል።
ከእዚህ ቀደም ስናወዳድር 50 በመቶ 12 ክፍል ውጤት 50 በመቶ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት እንመለከት ነበር አሁን 10 በመቶ በስልጠና ማጠናቀቂያው ወቅት ያገኙትን ሰርተፍኬት እንዲይዝ እናደርጋለን።
አንድ ላይ ተደምሮ ከመቶ ሲያዝ የመቁረጫ ነጥብ ላይ ባመጡት ቁጥር ዝቅ ያደረግላቸዋል ፣ ልዩ ኮታ ይሰጣቸዋል ማለት ነው ።
ይህንን እድል አምናም ሰጥተናል ዘንድሮ ከገቡ መካከልም ይህንን እድል ያገኙ አሉ በሚቀጥለው አመትም ይህ ይቀጥላል።
ሁለተኛ እዚህ ስልጠናቸውን የተከታተሉ ተማሪዎች የተለያዩ ፕሮዳክቶችን አውጥተዋል እኛ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የኢንዱስትሪያል ኢኖቬሽን እና ኢንኩቤሽን ሃብ ሰርተናል ይህ ሃብ ወደ 189 ስታርታፖችን መቀበል ይችላል።
እነዚህ ስታርታፖች ከተለያዩ ቦታ እና ዩንቨርሲቲዎች የተወጣጡ ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን ሜድ ኢን ኢትዮጵያ ምርቶች ያላቸው እና መሸጫ ቦታ ያጡ ሰዎችን የምናሰባስብበት ቦታ ነው።
ይህንን ስፔስ (ቦታ) ስልጠናውን ለተከታተሉ ሰዎች ለሰሯቸው ምርቶች (ፕሮዳክቶች) እናቀርባለን።
የምናቀርበው በሁለት አይነት መንገድ ነው አቅሙ ኖሯቸው በራሳችን እንቀጥል ካሉ የተወሰነ ኪራይ እናስከፍላለን ፣ምንም አቅም የለንም የሚሉ ካሉ ከተለያዩ ባለሃብቶች እና ከዩኒቨርሲቲውም አንድ ላይ አድርገን ድጋፍ በማድረግ ምርታቸው ወደ ገበያ እንዲወጣ እና ስራ ፈጣሪ እንዲሆን ድጋፍ እናደርጋለን " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

Grade 12 physics unit 2 horizontal projectile motion https://youtu.be/o1jBMcjeZYM?si=7PO-dAgle7KyQZDb
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" ተማሪዎች ምደባቸውን በድረ-ገፅ፦ https://student.ethernet.edu.et እና
በቴሌግራም ቦት፦ @moestudentbot መመልከት ይችላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር
የ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ምደባ ተለቋል፡፡
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ብሔራዊ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባቸው ዛሬ ይፋ ተደርጓል።
ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ተማሪዎች ምደባቸውን ማየት የሚችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
በድረ-ገፅ፦ https://student.ethernet.edu.et
በቴሌግራም ቦት፦ @moestudentbot
Via @tikvahuniversity

#Hemorrhagic_Fever ምንድን ነው❓
ይህ በሽታ በቫይረስ የሚከሰት ከባድ የበሽታ ቡድን ነው ። በሽታው በመሰረቱ የደም መፍሰስን ወይም የደም መርጋትን በሰውነት ውስጥ የሚያመጣ ነው ። በርካታ የሰውነት አካላትን በማጥቃት እና በሰውነት ውስጥ ያሉ የደም ሥሮችን የሚጎዳ ፣ በተለያዩ ቫይረሶች የሚመጣ በሽታ ነው።
#የበሺታው_መንስኤ እና የቫይረስ ዓይነት
. Ebola and ,Rift Valley Fever (RVF) & Yellow Fever ተብሎ የሚከፈል ሲሆን እንደ #ኢቦላቫይረስ ፣#ደንጉ እና #የለውፊቨር የተባሉ ቫይርሶች የበሺታው መንስኤ ሲሆኑ #በትንኝ ንክሻም የሚመጡ ናቸው ።
በሽታው ስሙ እንደሚያመለክተው በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ደም እንዲፈስ በማድረግ ለሞት የሚዳርግ ህክምና አልባ አደገኛ በሺታ ነው።
በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ደም መድማት እና መፍስሥ ከተከሰተ የበሽታው ከባድ ደረጃ ምልክት ነው።
በሽታው እንዴት ይተላለፋል?
1· ከተያዙ እንስሳት ጋር በመነካካት፡ በእንስሳት (ለምሳሌ አይጥ) ፣ ሽንት፣ ምራቅ ፣ ወይም ሌሎች ከሰውነት የሚለቀቁ ፈሳሾች በሚነካኩበት ጊዜ።
2· በነፍሳት ንክሻ፡
3· ከሰው ወደ ሰው፡ ከተያዘ ሰው የሚገኘው ደም፣ ምራቅ፣ የሰውነት ፈሳሾች ወይም ሌሎች ክምችቶች በቀጥታ በሚነካኩበት ጊዜ። ይህ ለበሽታው ከባዱ እና ዋነኛው ዓይነት የመተላለፊያ መንገድ ነው።
#የበሽታው_ምልክቶች
ምልክቶቹ በድንገት ሊታዩ እና በፍጥነት ሊባባሱ ይችላሉ። አንድ ሰው በቫይረሱ በተጠቃ ከ 2-21 ቀናት ውስጥ ምልክቶቹ መታየት ይጀምራሉ
መጀመሪያ ላይ የሚታዩ ምልክቶች
ምልክቶቹን በሁለት ከፍሎ ማየት የሚቻል ሲሆን
የመጀመሪው ቀለል ያሉ ምልክቶች እና የመጨረሻው አደገኛ //አስጊ ደረጃ ላይ ሲደርስ የሚታዩ ናቸው
#የመጀመሪያ_ምልክቶች
· ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት (ትኩሳት)
· ድካም እና የመዛል ስሜት
· የጡንቻ፣ የአጥንት ህመም እና ቁርጥማት
· ራስ ምታት
· የጉሮሮ ህመም
#ከባድ_ምልክቶች (በሽታው እየተባባሰ ሲሄድ)፡
· በቆዳ ስር ደም መውጣት
. ከአፍ፣ አፍንጫ፣ ከዓይን ወይም ከጆሮ ደም መፍሰስ።
· የጭንቅላት አዕምሮ መናጋት ፣ መደንገጥ፣
. ራስን መሳት ኮማ ውስጥ መግባት)
· የኩላሊት እና የጉበት መጎዳት እና ስራ ማቆም
· ከፍተኛ ድካም እና ሾክ/Shock
· የበርካታ አካላት አለመሥራት
እንዴት መከላከል ይቻላል ?
በሽታው በትንኝ ንክሻ አማካኝነት የሚተላለፍ በመሆኑ #የአልጋ_አጎበርን ነፍሶን ከሞት መታደግ ስለሆነ በአግባቡ ይጠቀሙት ። ከታማሚ ሰው ጋር ያልዎትን ንክክ መከላከል እና
አፋጣኝ አስፈላጊ የህክምና እርዳታ ማግኘት አስፈላጉ ሆኖ ፣በሺታውን ሙሉበሙሉ ማዳን የሚችል ህክምና የለም ፣
መከላከል ብቸኛው ቁልፍ መንገድ ነው !
የሚከተሉትን ማድረግ ያስፈልግዎታል !!
1. እጆችዎን በንፅህና ይታጠቡ፡ በሳሙና እና በንጹህ ውሃ ዘወትር ማጠብ አስፈላጊ ነው።
2. ከሌሎች ሰዎች (ክምችቶች) ራስዎን ይጠብቁ፡ ከሰዎች ደም፣ ምራቅ ወይም ሌሎች ከሰውነት የሚለቀቁ ፈሳሾች ንክኪዎች ራስዎን ይጠብቁ። ይህ ለቤተሰብ አባላት እና በተለይም ለህክምና ባለሙያዎች እጂግ አስፈላጊ ነው።
ብዙ የህክምና/ጤ ና ባለሙያዎች ህይወታቸውን የሚያጡበት ወረርሺኝ ነው።
3. ከእንስሳት ይራቁ፣ አይጦችን እና ሌሎች እንስሳት ከቤትዎ አርቀው ያቆዩ። የሚታወቁ የእንስሳት ክምችቶች ባሉበት ስፍራ ጥንቃቄ አይለይዎት
4.ከ ነፍሳት ይጠበቁ ፣ አጎበር መጠቀም፡
ይህን በሽታ ለመግታት እና ለመቆጣጠር መከላከያ መንገዶቹ ላይ ማተኮሩ ይመከራል።

Forwarded from Ethiopian Digital Library
የተማሪዎች_ስነ_ምግባር_መመሪያ_2018_@Ethiopian_Digital_Library.pdf
312.4 KB
የተማሪዎች ስነ ምግባር መመሪያ 2018
ሁሉም ተማሪዎች ሊያነቧቸው ይገባል::
@Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library

አዲሱ የክፍል መሸጋገሪያ መመሪያ ምን ይላል?
በአዲሱ የትምህርት ሥርዓት (6-2-4) መሠረት፣ ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል ለመሸጋገር "ዝም ብሎ አማካይ ውጤት" ማምጣት ብቻ በቂ አይደለም።
መመሪያው የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አካቷል፦
1. የማለፊያ ነጥብ (Pass Mark):
👉ማንኛውም ተማሪ ከክፍል ወደ ክፍል ለመሸጋገር በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ቢያንስ 50% እና ከዚያ በላይ ማምጣት አለበት።
👉ከአንድ በላይ የትምህርት ዓይነት ላይ ከ50% በታች (Fail) ያመጣ ተማሪ እንደ ድሮው "በአማካይ" ማለፍ አይችልም፤ ክፍሉን እንዲደግም ይገደዳል።
2. የ50/50 የውጤት አሰጣጥ ሥርዓት:
👉50% ተከታታይ ምዘና (Formative Assessment): ይህ በክፍል ውስጥ የሚሰሩ ስራዎች፣ ፕሮጀክቶች፣ ተግባራዊ ሙከራዎችና አጫጭር ፈተናዎችን ያካትታል።
👉50% የማጠቃለያ ፈተና (Summative Assessment): በሴሚስተር መጨረሻ የሚሰጥ አንድ ወጥ ፈተና።
👉ትኩረት፦ ተማሪው በክፍል ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ካላደረገ የማጠቃለያ ፈተናው ብቻውን አያሳልፈውም።
3. የብሔራዊ ፈተናዎች ለውጥ:
👉6ኛ ክፍል: ተማሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ መካከለኛ ደረጃ (Middle School) ለመሸጋገር የክልል አቀፍ ፈተና ወስደው ማለፍ አለባቸው።
👉8ኛ ክፍል: ወደ ሁለተኛ ደረጃ (High School) ለመግባት ክልላዊ ፈተና የግድ ነው።
👉12ኛ ክፍል: ወደ ከፍተኛ ትምህርት ለመግባት የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በ10ኛ ክፍልም የመውጫ ፈተና ሊኖር ይችላል።
4. የስነ-ምግባር እና የመገኘት መስፈርት:
👉አንድ ተማሪ በዓመቱ ውስጥ ከ 80% በላይ በክፍል ውስጥ ካልተገኘ፣ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ወደ ቀጣዩ ክፍል አይሸጋገርም።
5. ተግባር ተኮር ትምህርት:
👉በአዲሱ ካሪኩለም፣ ተማሪዎች በንድፈ-ሀሳብ (Theory) ብቻ ሳይሆን በተግባር (Practical) ብቁ መሆናቸው ይገመገማል። በተለይ በሳይንስ ትምህርቶች የላብራቶሪ ስራዎች ውጤት ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አላቸው።
💡 ወላጆች ምን ማድረግ ይኖርባቸዋል?
👉ልጅዎ በፈተና ሰሞን ብቻ እንዲያጠና ከመጠበቅ ይልቅ፣ በየቀኑ የሚሰጡ የቤት ስራዎችን እና የክፍል ስራዎችን (Portfolio) በትክክል መስራቱን መከታተል አለብዎት። ምክንያቱም 50% ውጤቱ የሚመዘገበው በየቀኑ ከሚሰራው ስራ ነው።
#New_Curriculum#ትምህርት #አዲሱ_ካሪኩለም_የተማሪዎች_ውጤት!!
#Follow_Like_sher!!

ደ/ማ/አጠ/2ኛ/ደረጃ ትቤት የመጀመሪያው ወሰነ ትምህርት የማጠቃለያ ፈተና በአንድ ወንበር አንድ ተማሪ