Debre markos preparatory school
1.07K subscribers
316 photos
5 videos
295 files
52 links
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE

ዩኒቨርሲቲዎች ስለተማሪዎቻቸው ትክክለኛ መረጃ ካላቀረቡ ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ ሀላፊዎቻቸው ከስራ ይባረራሉ ተባለ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በቀጣይ 6 ወራት ዩኒቨርሲቲዎች ስለተማሪዎቻቸውና ሌሎችም ጉዳዮች መረጃ በትክክል ለትምህርት ሚኒስቴር ማቅረብ አለባቸው ብለዋል።

ይህንን ያላደረገ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በስራው አይቀጥልም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" ይህንን ስራ እኔ በቀጥታ እከታተለዋለሁ " ማለታቸውን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

ከወራት በፊት ሚኒስትሩ " ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ከነፎቶ እንዲሁም ስለሚሠሩት ሥራ ትክክለኛ መረጃ ስጡን ብለን ከጠየቅን ሦስት ዓመት አልፎናል፡፡ ሆኖም እስካሁን የተሟላ መረጃ ለማግኘት ችግር ሆኖብናል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች ዘንድ እውነተኛ መረጃ መስጠት አልተለመደም " ማለታቸው ይታወሳል።

ዩኒቨርስቲዎች ከተማሪዎች ምገባ ጋር ተያይዞ የውሸት ሪፖርት ያቀርቡ እንደነበር ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪ ቁጥር በውሸት በመጨመር በጀት እንዲጨመርላቸው ያደርጉም እንደበር ተናግረው ነበር።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
Forwarded from ድብዛ ጉድኝት ማዕከል
Forwarded from Yetsedaw Tesfaye
#MoE

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም  ድረስ ማስተካከል እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የሪሚዲያል ፕሮግራም #የማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች ፦
1.  አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
2.  አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
3.  አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
4.  ሲቪል ሰርቪርስ ዩኒቨርሲቲ
5.  ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
6.  ጅማ ዩኒቨርሲቲ
7.  ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ናቸው።

ተማሪዎች የሞሉትን ምርጫ በ student.ethernet.edu.et በኩል ማረጋገጥ የሚችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

Via @tikvahuniversity
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ9-12ኛ ክፍል ይሸፍናል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከት ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች እንዲሁም ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ትናንት ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ደብዳቤ ልኳል፡፡

የደብዳቤውን ትክክለኝነት ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

በሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ሥራ አስፈጻማ ቴዎድሮስ ሽዋርገጥ (ዶ/ር) የተፈረመው ደብዳቤው፤ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ9-12ኛ ክፍል እንደሚሸፍንና ተማሪዎች የተማሩትን ይዘቶች የሚፈተኑ መሆኑን ይገልጻል፡፡

ብሔራዊ ፈተናው ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍሎች የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይዘቶችን መሠረት ያደረገ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡

በ2015 ዓ.ም የሙከራ ትምህርት ቤቶች 9ኛ ክፍልን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት፤ ሌሎቹ ደግሞ በቀድሞው ስርዓተ ትምህርት የተማሩ በመሆኑ ፈተናው ከሁለቱ ስርዓተ ትምህርቶች የጋራ የሆኑ ይዘቶች ተጣጥሞ የሚወጣ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ ትምህርት ሪፎርም መሠረት የሁለተኛ ደረጃ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በ2015 ዓ.ም የሙከራ ትግበራ በማካሔድ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ መገባቱ ይታወቃል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

Via @tikvahuniversity
Forwarded from M
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#National_ID

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ላይ ለመቀመጥ ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ቅድመ ሁኔታ ተደረገ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት " ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ለፈተና ለመቀመጥ ቅድመ ሁኔታ ነው " ብሏል።

" ማንኛውም የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ከፈተና ምዝገባ ቀድሞ ማውጣትና በእጁ መያዝ ይገባዋል " ሲል አሳውቋል።

" ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) የሌለው ተማሪ ለፈተና መመዝገብ ሆነ በማንኛውም ሁኔታ መፈተን አይችልም " ሲል አስገንዝቧል።

ተማሪዎች የብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ይዘው እንዲገኙ ፦
- የተማሪ ቤተሰብ
- መምህራን
- የትምህርት አመራሮች
- የሚዲያ አካላት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#National_ID

@tikvahethiopia
Forwarded from Yamral Tadesse
❗️❗️አስቸኳይ መልዕክት❗️❗️

🗯 ቅዳሜና እሁድ ማለትም ጥቅምት 15&16/2018 ዓ፣ም በሃገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም አካባቢዎች የፋይዳ መታወቂያ ማውጣት መርሃ ግብር ይካሄዳል።

🗯በዚህ ፕሮግራም ተማሪዎችን ጨምሮ የፋይዳ መታወቂያ ያላወጡ መርሱዎችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች እንዲያወጡ መልዕክቱን ለሁሉም እንዲደርስ አድርጉ።

🗯ሁሉም ተማሪዎች የፋይዳ መታወቂያ ለማውጣትና ለመመዝገብ የሚያስፈልጋቸው ……

@……የልደት ሰርተፊኬት
@……የሁለተኛ ደረጃ ትቤት ተማሪዎች የትቤት መታወቂያ፣ወይም የባንክ ደብተር፣ይዘው መመዝገብና የፋይዳ መታወቂያ ማውጣት ይችላሉ።

🗯 የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ የሚከናወንባቸው ቦታዎች……

1……አብማ ክፍለ ከተማ……ክፍለ ከተማው ቢሮ ላይ፣ከ/መ/ል/መምሪያ ቢሮ ጎን፣

2……ንጉስ ተክለ ሃይማኖት ክፍለ ከተማ………ቀበሌ 04 አስ/ፅ/ቤት ግቢ ውስጥ፣

3……መንቆረር ክፍለ ከተማ ………ክፍለ ከተማው ቢሮ ውስጥ፣ሆስፒታል ከፍ ብሎ፣

4……ተድላ ጓሉ ክፍለ ከተማ……ቀበሌ 02 አስ/ፅ/ቤት፣ሲኒማ በታች።

👉ነገ 2:30 ሰዓት ጀምሮ ከላይ በጠቀስናቸው ቦታዎች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ስለሚጀመር ለሁሉም ተማሪዎች፣መርሱዎችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች መልዕክቱን አድርሳችሁ እንዲመዘገቡ አድርጉ።

ለተግባሩ ልዩ ትኩረት ይሰጠው።

ተማሪዎችን በየክፍሉ በመዞር እንዲሁም በሰልፍ ላይ ጥብቅ መልዕክት አስተላልፉ።
Forwarded from Yamral Tadesse
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ነገ እሁድ ልዩ በሆነ መልኩ እንዳለ ሰምተዋል?

ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ አስበው ጊዜ እና ሰዓት አልመቻች ብሎዎታል? ተማሪዎችስ ከትምህርት ሰዓት ውጭ ለመመዝገብ? እንግዲያው ነገ ጥቅምት 16 በልዩ ሁኔታ በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች አገልግሎት ስለምንሰጥ በአቅራቢያዎ በሚገኝ የምዝገባ ጣቢያ በመሔድ ይመዝገቡ።

ለተጨማሪ መረጃ id.gov.et ይጎብኙ ወይም 9779 ይደውሉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳለሁሉም #ፋይዳምዝገባ
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" በስልጠና ማጠናቀቂያ ወቅት ያገኙት ሰርተፍኬት በዩኒቨርሲቲው ለመማር በሚወዳደሩበት ወቅት 10 በመቶ ውጤት እንዲኖረው እናደርጋለን "- የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ2017 ዓ/ም የክረምት መርሃ ግብር በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 629 ታዳጊ ወጣቶችን በዛሬው ዕለት አስመረቋል።

ታዳጊዎቹ በክረምት መርሃ ግብር የሰለጠኑት ፦
- በሳይበር ደህንነት፣
- በቴክኖሎጂ ልማት፣
- በኢምቤድድ ሲስተም፣ እና በኤሮስፔስ ዘርፎች ነው።

ላለፉት ሦስት አመታት አዲስ አበባ ላይ ብቻ ሲካሄድ የቆየው የስልጠና መርሃ ግብር፤ በ2017 ዓ/ም ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለመጀመሪያ ጊዜ 76 ልጆች ሰልጥነው መመረቅ መቻላቸው ተገልጿል።

ስልጠናውን የተከታተሉት ታዳጊዎች ከኢለመንተሪ፣ ሃይስኩል እና ዩኒቨርሲቲ የተወጣጡ ናቸው ።

ታዳጊዎቹ ስልጠናቸውን ከኢንሳ በተጨማሪ  በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በማጠናቀቂያው ወቅት የተሰጣቸው ሰርተፍኬት በዩኒቨርሲቲው ትምህርት ለመከታተል በሚወዳደሩበት ወቅት የመቁረጫው ነጥብ ዝቅ እንደሚያደረግላቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ በዝርዝር ምን አሉ ?

" ግቢ ውስጥ በቆዩበት ጊዜ በተለያዩ ዘርፎች ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል ስልጠናውን ኮርስ በመስጠት ብቻ ሳይሆን ችግሮቻችንን በመንገር ችግሮችን መፍታት ከመቻላቸውም በላይ ፕሮዳክቶችን ይዘው መጥተዋል።

የራሳቸው የሆነ የተለያዩ ችግሮችን መፍታት እና መሸጥ የሚችሉ ፕሮዳክቶችን ይዘው ወጥተዋል።

እኛ ፈተና ፈትነን ተማሪዎችን የምንቀበል መሆኑ ይታወቃል ፈተና ፈትነን ስንቀበል የ 12 ውጤት እና የመግቢያ ፈተና ውጤት ነው የምናየው።

በእዚህ ስልጠና ከመላው የኢትዮጵያ አካባቢዎች መጥተው በግቢያችን ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች የወሰዱት ሰርተፍኬት በግቢያችን ለመማር በሚያመለክቱበት ወቅት ቫልዩ ይኖረዋል።

ከእዚህ ቀደም ስናወዳድር 50 በመቶ 12 ክፍል ውጤት 50 በመቶ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት እንመለከት ነበር አሁን 10 በመቶ በስልጠና ማጠናቀቂያው ወቅት ያገኙትን ሰርተፍኬት እንዲይዝ  እናደርጋለን።

አንድ ላይ ተደምሮ ከመቶ ሲያዝ የመቁረጫ ነጥብ ላይ ባመጡት ቁጥር ዝቅ ያደረግላቸዋል ፣ ልዩ ኮታ ይሰጣቸዋል ማለት ነው ።

ይህንን እድል አምናም ሰጥተናል ዘንድሮ ከገቡ መካከልም ይህንን እድል ያገኙ አሉ በሚቀጥለው አመትም ይህ ይቀጥላል።

ሁለተኛ እዚህ ስልጠናቸውን የተከታተሉ ተማሪዎች የተለያዩ ፕሮዳክቶችን አውጥተዋል እኛ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የኢንዱስትሪያል ኢኖቬሽን እና ኢንኩቤሽን ሃብ ሰርተናል ይህ ሃብ ወደ 189 ስታርታፖችን መቀበል ይችላል።

እነዚህ ስታርታፖች ከተለያዩ ቦታ እና ዩንቨርሲቲዎች የተወጣጡ ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን ሜድ ኢን ኢትዮጵያ ምርቶች ያላቸው እና መሸጫ ቦታ ያጡ ሰዎችን የምናሰባስብበት ቦታ ነው።

ይህንን ስፔስ (ቦታ) ስልጠናውን ለተከታተሉ ሰዎች ለሰሯቸው ምርቶች (ፕሮዳክቶች) እናቀርባለን።

የምናቀርበው በሁለት አይነት መንገድ ነው አቅሙ ኖሯቸው በራሳችን እንቀጥል ካሉ የተወሰነ ኪራይ እናስከፍላለን ፣ምንም አቅም የለንም የሚሉ ካሉ ከተለያዩ ባለሃብቶች እና ከዩኒቨርሲቲውም አንድ ላይ አድርገን ድጋፍ በማድረግ ምርታቸው ወደ ገበያ እንዲወጣ እና ስራ ፈጣሪ እንዲሆን ድጋፍ እናደርጋለን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Forwarded from Getachew Biazen
Grade 12 physics unit 2 horizontal projectile motion https://youtu.be/o1jBMcjeZYM?si=7PO-dAgle7KyQZDb
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" ተማሪዎች ምደባቸውን በድረ-ገፅ፦ https://student.ethernet.edu.et እና
በቴሌግራም ቦት፦
@moestudentbot መመልከት ይችላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ምደባ ተለቋል፡፡

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ብሔራዊ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባቸው ዛሬ ይፋ ተደርጓል።

ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ተማሪዎች ምደባቸውን ማየት የሚችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በድረ-ገፅ፦ https://student.ethernet.edu.et
በቴሌግራም ቦት፦ @moestudentbot

Via @tikvahuniversity