"ዘ-smart short histories"
142 subscribers
51 photos
1 video
3 files
51 links
የሚመስጡ ታሪክ ከፈለጉ እየውሎት

https://t.me/DMAFS14 ይቀላቀሉን
Download Telegram
ባንድ ቅርብ ዘመን ባንድ ራቅ ያለ ቦታ ሁለት የሚዋደዱ ፍቅረኛምች ነበሩ፡፡
ልጁ ልጀቷን በጣም ነው የሚወዳት፡፡ የፍቅሩን
መግለጫ ደግሞ
ስጦታዎች! ፍቅር በሚመራቸው ጣቶቹ
የከሸናቸውን ከአንድ ሺ
በላይ የተለያዩ የወረቀት ቅርፃ ቅርፆች (Paper cranes)
አበርክቶላታል፡፡
ሁለቱም ተፋቃሪዎች በፍቅራቸው ደስተኞች ነበሩ። እሱ በአንድ
ድርጅት ውስጥ አነስተኛ ኃላፊነት ያለው ባለሙያ ነው:: ሆኖም
ግን ለወደፊት ያን ያህልም ተስፋ ያለውና ትልቅ ቦታ የመድረስ
ዕድል ያለው አይመስልም፡፡ ለዚህም ይሆናል በሞቀ ፍቅራቸው
መሃል ድንገት አንድ ቀን ሊሸከመው የማይችለውን
መርዶ
ያረዳችው። ወደ ፓሪስ እሄዳለሁ...' አለችው። ብንዋደድም
ካንተጋ የትም የምንደርስ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ
እስቲ
ሁለታችንም የየራሳችንን የህይወት መንገድ እንምራ ብላው
ተሰናበተችው:: ሄደች:: ጥላው ነጎደች፡፡ ልቡ ተሰበረ፡፡ ግን ልቡ
ተሰብሮ አልቀረም፡፡
ከስብራቱ ሲያገግም በሙሉ ጉልበቱ መስራት ጀመረ። በልፋቱ
የራሱን የንግድ ኢምፓየር ገነባ። እና አሁን ሀብታም ሆኗል፡፡
ተሳክቶለታል፡፡ ቤተ-መንግስት የሚያስንቅ ቪላ፣ ሺዎችን በስሩ
የሚያስተዳድር ትልቅ ኩባንያ ባለቤት፡፡ ሌላም... ሌላም፡፡
ከዕለታት ባንድ ዝናባማ ቀን ዘመናዊ መኪናውን እያሽከረከረ ሳለ
ሁለት አዛውንት ባልና ሚስት አንድ ዣንጥላ ተጋርተው ሲሄዱ
ተመለከተ፡፡ የተጋሩት ዣንጥላ ሁለቱንም በበቂ አላስጠልል ብሎ
የዝናቡ ወጨፎ አበስብሷቸዋል፡፡ እየቀረበ ሲመጣ
ማን እንደሆኑ
ለመለየት ቻለ፡፡ የዛች ልቡን ሰብራው የሄደችው ፍቅረኛው
ወላጆች ናቸው፡፡
አሃ....አለ፡፡ አሁን ነው ማሳየት ሲል አሰበ::.
🤔1
Part፪
....... ሲል አሰበ:: አሁን ያ የድሮው
መናጢ አይደለም። ስለዚህ እንዲለዩት በማሰብ መኪናውን
በቀስታ እያሽከረከረ ወደ እግረኛው መንገድ ሲያስጠጋ
አረጋውያኑ ጥንዶች ወደ ጎን ሲታጠፉ ተመለከተ፡፡ ሳያዩት
በመሄዳቸው በሽቆ ወደ ሄዱበት አቅጣጫ ገልመጥ ሲል
እያመሩ ያሉት ወደ ከተማው የቀብር ቦታ ነው። መኪናውን
አቁሞ ተከተላቸው፡፡ ያየውን ነገር ማመን አልቻለም፡፡ የዛች
ከድታው የሄደችው ፍቅረኛው ሳቂታ ፎቶ ከመቃብሩ ሀውልት
ላይ... ከመቃብሩ አጠገብ ደግሞ እነዛ በስጦታ መልክ
ያበረክትላት የነበሩት የወረቀት ቅረፃ ቅርፆች በሚያምር
የመስታወት ማስቀመጫ ውስጥ! ነገሮች ተደበላለቁበት፡፡
ወደ ወላጆቿ ቀረብ አለና ምንድነው የሆነው ሲል ጠየቀ፡፡
ሁሉንም ነገሩት። ፍቅረኛው ወደየትም አልሄደችም ነበር። ይልቅ
ካንሰር ነበር የያዛት። በበሸታዋ ሳቢያ ሸክምና የሙያ ህይወቱ
እንቅፋት ልትሆንበት አልፈለገችም፡፡ ስለዚህ ላልመለስ
እሄዳለሁ ብላ ተለየችው፡፡ እናም እንያን ውድ ስጦታዎቹን
በህመሟ ጊዜ ሁሉ ራስ
ራስጌዋ አድርጋ ፍቅራቸውንእያሰበች
እንዳልተፅናናችባቸው
ሁሉ....እነሆ....አሁንም መቃብሯን አድምቀውታል፡፡
🔥3
እንዲ አይነትም ዳኛ አለ?😌😱

አንድ ሰው በአንድ ወቅት ለጓደኛው የተወሰነ ገንዘብ አበደረው፤ ጓደኛው ግን በኋላ ገንዘቡን እንዳልተቀበለ ካደ። ስለዚህም ሰውየው ጓደኛውን ከሰሰውና ፍርድ ቤት አቆመው።

ዳኛውም "ምስክር አለህ?" ሲሉ ጠየቁት። ሰውየውም "የለኝም፤ ገንዘቡን በድብቅ ነው የሰጠሁት።" ሲል መለሰ። ዳኛውም "እንግዲያውስ ገንዘቡን ወደሰጠህበት ቦታ ሄደህ፣ እጠይቀው ዘንድ፣ ከዚያ ቦታ አንድ እፍኝ አፈር ይዘህልኝ ና።" አሉት።

ሰውየው በዚህ ጥያቄ ቢገረምም በታዘዘው መሰረት ከዚያ ቦታ አንድ እፍኝ አፈር ሊያመጣ ሄደ።

እሱ ሄዶ ሳለ ዳኛው ወደ ተበዳሪው ዞረው፦ "አሁን ቦታው የሚደርስ ይመስልሃል?" ብለው ጠየቁት። ሰውየውም በፍጥነት "አይ፤ ቦታው ከዚህ በጣም የራቀ ነው።" ሲል መለሰ። ዳኛውም እየሳቁ "ቦታው ሩቅ መሆኑን እንዴት አወቅክ... እዛ ሄደህ ገንዘቡን ካልተቀበልክ በቀር?" አሉት።

በመሆኑም ዳኛው ሰውየው እዳውን እንዲከፍል ወሰኑ፤ በዋሸውም ሃያ ግርፋት እንዲገረፍ አዘዙ።
Be like 🥰
🥰3😁3🤬1
Good Morning everyone
🔥3
ሰላም ቤተሰብ
እሁድ እንዴት ነው?
👍4🙏1
Audio
ብትስቅ ምን አለበት ??

@getem
@getem
@getem
🥰3🤩2
#ሁለት በሬዎች ጋጣ ላይ እያሉ አንዱ ሰነፍ በሬ ለጓደኛው ዛሬ ገበሬው ሊጠምደን ሲመጣ አመመኝ ብዬ ዝርር እላለሁ ይለዋይ

ይገርማል....
ኤጭ አሁንስ መጠመድ ሰለቸኝ ቀንበር እላዬ ላይ ተሸክሜ እስከመቼ...ዛሬ ገበሬው ሊጠምደን ሲመጣ አመመኝ ብዬ ዝርርእላለሁ ይለዋል። ጓደኛውም ቀንዱን አዘቅዝቆ በሹክሹክታ ተው ግዴለክም እንረስ በኋላ መተኛት መዘዙ ብዙ ነው አትለግም ተነስ…ይለዋል።አንደኛው በሬ ግን በሀሳቡ ፀንቶ ልክ ገበሬው ሲመጣ መሬት ላይ ፍንግል ብሎ አልነሳም አለ።በበሬው ሁኔታ የደነገጠው ገበሬ ታድያ የቀዬውን ሰወች ጮኾ "ድረሱልኝ"ሲል መጣራት ጀመረ....ይሄኔ አጅሬው በሬ ገበሬው አዘነልኝ ብሎ በውስጡ ደስ መሰኘት ጀመረ...ከደቂቃወች በኋላ ግን የተጠሩት ሰወች ሲደርሱ ሁሉም በእጃቸው ካራ(ቢላ )እንደያዙ
በሉ ቶሎ እንባርከው... ከሞተ ጥንብ ይሆናል...በሉ እግሩን እሰሩት...ያዙ ያዙ እያሉ መጯጯህ ጀመሩ
የገዛ አሳዳጊው እግሩን ለመያዝ ሲተባበር አየ።ሊያድኑት የተጠሩ የመሰለው ጭንቅላቱን በሀይል እያቃኑ አንገቱን ሊቆርጡት መሆኑን አወቀ።ይሄኔ ውሸታሙ በሬ ቢፈራገጥ ቢጮህ ቢያለቅስ መታረዱ ግድ ሆነና በራሱ እጅ ሞቱን አፈጠነ። ይሄኔ ጓደኛው በሬ ቆሞ እያየ
ሞኙ በሬ ሆይ ሞኙ በሬ ሆይ
"ከካራ"መጠመድ አይሻልም ወይ ....አለው
ወንድሜ....እንግዲህ ስንፍና ሚያስከትለው ሞት መሆኑን አይተካል።አለም ደከመው አመመው ደበረው ብላ አትረዳንም!! የውሸት ስትተኛ የእውነት መሞቻ ቀንህን እያቀረብክ መሆኑን አትርሳ!!ካልታመምክ በቀር በቻልካት በአቂሚቲ ተነስተህ የሆነች ነገር አድርገህ ዋል፡፡ባትሰራ ቤተክርስትያን ሄደህ ፀልየህ ተመለስ።ተኝተህ ከቆየህ ጎረቤቶቹን እንደጠራው ገበሬ ሰይጣንም ድህነት፤ ድባቴ፤ ጭንቀት፤ስንፍና፤ የበታችነት፤ሲልም ደሞ ሞትን ጠርቶ እጅህ እና እግርህን አስሮ ያሰናብትሐል....
🤝3
ትረካ "ዝጎራ" መፀሀፍ ሊጀምር ነው👏👏 ክፍል ፩ ይሆንሎት👇👇👇
ትረካ ዝጎራ ክፍል 1
◄▻◄▻◄▻◄▻◄▻▻◄▻◄▻
ትረካ ዝጓራ
ክፍል = 1◄▻◄
ምርጥ መፅሐፍ
👍3
ትረካ ዝጎራ ክፍል 2
◄▻◄▻◄▻◄▻◄▻◄▻◄▻◄▻◄▻
ትረካ ዝጓራ
ክፍል = 2
🔥1
አራተኛ ክፍል ይሆንሎት💫💫
ትረካ ዝጎራ
ክፍል 8
ከ 23 ክፍል ውሰጥ እስከ ክፍል 8 ያዳመጠ
be like 👍
👍1
ትረካው ይቀጥል ወይስ ይቅር?
Anonymous Poll
73%
ይቀጥል
27%
ይቅር
እውነት ክፋል 20 በጣም ደስ ይላል፤
ማዳመጣችሁን ቀጥሉ!