"ዘ-smart short histories"
142 subscribers
51 photos
1 video
3 files
51 links
የሚመስጡ ታሪክ ከፈለጉ እየውሎት

https://t.me/DMAFS14 ይቀላቀሉን
Download Telegram
የእሁድ ፎ..ቀሽ ያለ ግጥም👇👇

"አይጥ ጠላ
ጠጥታ ጠጥታ
ዱላ ስጡኝ አለች
🐱ድመትን ለትመታ"

*ከሰው p.p የተወሰደ😁
😁4👎1
መተኪያ የሌለውን ኩላሊቷን  ለአለቃዋ የለገሰችው ሰራተኛ ከህመምሽ ለማገገም ቆየሽ በማለት ኩላሊቷን በለገሰቻት አለቃዋ ከስራ ተባረረች😭😭😭

Debbile Steven የተባለችዋ ተቀጣሪ Jackie Brucia የተባለች አሰሪዎ ኩላሊቷ ፌል ያደርጋል። Steven ኩላሊቷን ለመስጠት እና አለቃዋን ለማዳን ሳታመነታ ብትወስንም ማች አላደርግ አለ። አሁንም አለቃየን የግድ ማዳን አለብኝ ብላ በቅያር  የሷን ኩላሊት ለሌላ ሰጣ ያኛው አካል ለአለቃዋ እንዲሰጥ አድርጋ አለቃዋን አዳነቻት። አለቃዋ ቶሎ ስትድን እንዳለመታደል ሁኖ እሷ ግን የነርቭና የምግብ አለመፈጨት እክል ገጥሟት ለማገገም አንድ ወር ፈጅቶባት ወደ ስራ ስትመለስ ለምን ይህን ያህል ጊዜ ቆየሽ ብላ ከስራ አባራታለች😭😭😭

::::::::ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ ማለት አሁን ነው:::::::
😢4👎1🤯1
"መልካምነት ዋጋው ስንት ነው?"
  በቅርብ በውድ ዋጋ የገዛሁት እና ብዙ መረጃዎቼን የያዘ ስልኬ መጥፋቱን ያረጋገጥኩት ገና ከታክሲ እንደወረድኩ ነበር፤በፍጥነት በሰው አስደወልኩ፤ስልኩ እንደጠራ ወዲያው ተነሳ፤እባክህ ስልክ ጥዬ ነበር ከማለቴ...የአንድ ወጣት ድምፅ ፤አዎ! ታክሲ ውስጥ ጥለህ ነው እኔ ጋር ነው አለኝና ያለበትን ቦታ ነገረኝ፤ወደ ቦታው ሰደርስ አለባበሱ እጅግ የሚያሳዝን ወጣት የተቃጠርንበት ቦታ ቆሞ አገኘሁት፤ሞባይሌን ከነክብሯ መለሰልኝ እና ምስጋና እንኳን ሳይፈለግ ወደ መጣበት ለመሔድ ሲያማትር፤ ምሳ ልጋበዝህ ብለው አሻፈረኝ አለ፤እሺ እቺን የሻይ ያዛት ብዬ ትንሽ ብር ብሰጠውም ሞቼ እገኛለሁ ብሎ የዘረጋሁትን እጄን መለሰው፤ከሁሉ የገረመኝ እና ልቤን የነካው ግን ...ለክፉም ለደጉም ሰልክ ቁጥርህን ልያዘው ብለው፤ስልክ እንደሌለው ሲነግረኝ ነው።
https://t.me/DMAFS14
👍4👎1
አስተማሪ ታሪክ!

አንደ ሰውዬ ቤቱን ሽጦ የተሻለ ቤት ለመግዛት ያስብና ።
በንግድ ማስታወቂያ ስራው በጣም ወደሚታወቀው ጋ
ጓደኛው ጋር በመሄድ ቤቱን ሽጦ የተሻለ ቤት ለመግዛት እንዳሰበ ይነግረዋል።
ቤቱን ለመሸጥ ጥሩ አድርጎ የሽያጭ ማስታወቂያውን በመስራት እንዲረዳው ይለምነው።

ጓደኛውም ለጥያቄው ፍቃደኛ በመሆን ቤቱን በደንብ ያውቀው ስለነበረ አንድ በአንድ ቤቱን ዘርዝሮ መፃፍ ጀመረ።
የቤቱን ውበት የጊቢውን ስፋት ዲዛይኑን እና መሰረቱን በተገቢው ሁኔታ በመግለፅ ዉብ ወደሆነው መናፈሻው እና የመታጠቢያ ቤቶቹ በስፋት ገለፆ የሽያጭ ማስታወቂያውን ፅፎ ጨረሰ።

ከዚያም የፃፈውን ማስታወቂያ ለቤቱ ባለቤት ቤቱ አነበበለት።

የቤቱ ባለቤትም በመገረም «ደግመህ አንብብልኝ» በማለት ጠየቀው።

ፀሀፊውም ደግሞ እንዳነበበለት የቤቱ ባለቤት ጮክ በማለት «እንዴት ያለ ያማረ ቤት ነው»

«በእርግጥም እድሜ ልኬን ይሄን የመሰለ ቤት እየተመኘሁ ኖሪያለሁ ነገር ግን አንድም ቀን እኔ እኖርኩበት መሆኑን አስቤው አላውቅም ። አሁን ገና ስታነብልኝ ነው ይህ ሁሌ የምመኘው ቤት ውስጥ እየኖርኩ መሆኑን የተረዳሁት ። »

ፈገግ በማለት ለፃሀፊው « እባክህ ይህን ማስታወቂያ ይፋ እንዳታርገው» በማለት ተማፀነው።

ቤቱም ሳይሸጥ ሰውየው በቤቱ መኖር ጀመረ።

እዚህ ታሪክ ላይ በርካታ አስተማሪ በጥቦች አሉበት ሼር ያድርጉት።

☞ ፈጣሪ ለአንተ የሰጠህ በርካታ በረከቶች አሉ እሱን ተመልከት።

☞ ፈጣሪ ለኛ የሰጠን ፀጋዎችን ረስተን የሰውን ስንመለከት ደስታችንን እና በረከታችንን እናጣለን።
https://t.me/DMAFS14
🥰5👎1
///አለም እንደዚህ ናት///
ይህቺ ከንቱ አለም ዛሬ ያልህባት፣
ውሽት ያነገሰች እውነት የሞተባት፤
ምስኪኖቹ በሰሩት በሌሎች ልፋት፣
አፈኛ በወሬው የሚሸለምባት፣
የተገፍው ትቶ ገፊ የሚከስባት፣
በሀሰት መስክሮ ፍርድ የሚሰጥባት፣
ቃላት ያንሱብኛል ብቻ እንዴት ልግለፆት?
ካለወክ እወቃት አለም እንደዚህ ናት።
👍3👎1
⚡️አስገራሚ ሳይኮሎጂካል እዉነታዎች!

🔥1.ስለ አንድ ሰዉ በጣም እያሰባችሁ ከሆነ ፤ ያ የምታስቡት ሰዉ ቀድሞ እያሰባችሁ ነበር!

🔥2.ከአለም የህዝብ ብዛት ዉስጥ 1% ህዝብ ብቻ በዉስጡ የሚሠማዉን ስሜት በተሳካ ሁኔታ ይደብቃል!

🔥3.ጠንክሮ መስራት ከስኬቱ በላይ ደስታን ያጎናፅፋል!

🔥4. ስለ አንድ ሰዉ በተደጋጋሚ  በህልማችን ማለም  ፤ ያ ሰዉ እኛን በጣም እንደናፈቀን እና  ስለኛ እያሰበ እንደሆነ ያመላክታል!
7
🔥5. 90% ሰዉ ፊት ለፊት ማለት የማይችለዉን ነገር በፅሑፍ መልእክት ይልካል!

🔥6.ለነገሮች ግድ የለሽ እንደሆነ የሚያስመስል ሰዉ ለነገሮች በይበልጥ ግድ የሚሠጠዉ ሠዉ ነዉ!

🔥7.በተደረጉት ጥናቶች መሠረት ፤ አንድን ሰዉ እንዳልናፈቀን የምናስመስል እና ስሜቶቻችንን የምንደብቅ ከሆነ ከበፊቱ በበለጠ ያን ሰዉ እንድንናፍቅ ያደርገናል!

🔥8.ብዙ አይነት ከለሮችን መጠቀም የፈጠራ አቅምን ከፍ ያደርጋል!

🔥9.በማታ እንቅልፍ መተኛት አለመቻል በሌላ ሰዉ ህልም ዉስጥ እየታለምን እንደሆነ ያመላክታል!

መልካም ምሽት 🙌🔥
 
🔥5👎1
አባት የመጀመርያም የመጨረሻም የሆነ ብቸኛ ልጁን ሊድር ድል ያለ ሰርግ ደግሶ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆቹን ጠርቶ የምሳ ግብዣውን እየተዟዟረ ይመለከታል።

‹‹ማን ቀረ ማን መጣ›› የሚለውን በትኩረት እየተመለከተ ሳለ የቅርብ የግድግዳ ጎረቤቱን ከእይታው ያጣዋል። ግራ በመጋባት እየተዟዟረ ቢመለከትም ጎረቤቱንም ሆነ የጎረቤቱን ልጆች ሊያይ አልቻለም።

‹‹የልብ ወዳጄ በዛሬ ቀን እንዴት ከጎኔ ይጠፋል›› እያለ በንዴት ስሜት በመብሰልሰል ላይ ሳለ ድንገት የጎረቤቱ ልጅ ብቅ አለ ና በፍጥነት ትንሽ ምግብ ቀማምሶ ትቶ ወጣ።

ይህን ትዕይንት የተመለከተው ደጋሽ በንዴት ተብከነከነ።የአባቱ በደስታው ግዜ አለመገኘት ሳያንሰው ልጁ መጥቶ በምግቡ አላግጦ መውጣቱ አበሳጨው።

በዚህ መሀል የሙሽራው አጃቢዎች ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት ጉዞ ሊጀምሩ መኪናቸውን ማንቀሳቀስ ሲጀምሩ ምግቡን ቀማምሶ በፍጥነት የወጣው የጎረቤቱ ልጅ ሙሽራውን ለማጀብ ከግቢ መኪናውን ይዞ ይወጣል።

አባት ተበሳጨ፣ ንዴቱን መቆጣጠር ቢያቅተው በቁጣ መንፈስ ተሞልቶ ወደ ጎረቤቱ ልጅ በመሄድ፦‹‹አባትህ ጎረቤቴ ሁኖ ደስታዬ ላይ አልተገኘም፣ ታላላቅ ወንድሞችህም እንደዝያው፤:ታድያ አንተ ምን አስበህ ነው በምግብ አላግጠህ ትተህ የወጣኸው? አሁን ተመለስ ያንተን አጃቢነት አንፈልግም›› ብሎ መለሰው። ልጁም እቤቱ ገባ፤ ሰርገኛዎችም ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት አቀኑ።

በመጨረሻም አጃቢዎች ሙሽሮችን ይዘው ወደ ቤት በመግባት የደስታቸው ተካፋይ ከሆኑ በኋላ ቀኑ ሲጨልም ሁሉም ተበታትኖ ሰርግ ቤቱ በሙሽሪት እና በሙሽራው ጭር አለ።

አባት አሁንም በጎረቤቶቹ ንዴት እየተብሰለሰለ ነው። ድንገት ከመሸ ያለ ወትሮው የጎረቤቱ ጊቢ ተከፈተ። የሙሽራው አባት እየተመለከተ ነው።

የጎረቤቱ ልጆች በትከሻቸው አስክሬን ተሸክመው ከቤታቸው ሲወጡም ተመለከተ። ፍፁም ዝግታ እና እርጋታም በሚስተዋልበት እርምጃ ልጆቹም ይራመዱ ጀመር።

የሙሽራው አባት ጠጋ አለ። ፦‹‹ምንድነው? የማንን አስክሬን ነው የተሸከማችሁት ›› ሲልም ጠየቃቸው።

‹‹አባታችን ጠዋት ሙቶ ነው፤ ሲሞትም በሱ ለቅሶ ምክንያት ያንተ ደስታ እንዳይጓደል መሞቱን ከሰርግህ በፊት ለማንም እንዳንናገር እና ድምፅ አውጥተን እንዳናለቅስ ተናዞልን ነበር። ለዝያ ነው ድግሱ ላይ መገኘት ያልቻልነው። ›› በማለት ጀናዛ የተሸከሙ ልጆች ጉዳያቸውን አስረዱ።

ደጋሽ ተፀፀተ፦‹‹ እኔ በሱ ቦታ ብሆን ይህን የማድረግ አቅም አይኖረኝም ነበር›› ሲልም የፀፀት እንባ ያነባ ጀመር።

የሚመስጡ ታሪክ ከፈለጉ እየውሎት

https://t.me/DMAFS14 ይቀላቀሉን
😢5👎1
Audio
ያየህ ሰዉ በሙሉ ብርቱ ነዉ ይልሀል
ስትደክም አያዉቁህም በደጉ ያሙሀል

ታለቅሳለህ አይደል ትደክማለህ አይደል
ይርብሀል ይጠማሀል አይደል?

አንተም እንደሰዉ ተሰብረህ ተከፍተህ ታዉቃለህ አይደለ?

እንዴት አወክበት ........
እያነቡ እስክስታ
ማነዉ ያስተማረህ......
ስቆ ማለፍ
አይቶ መተዉ
ተማሮ ማመስገን
ተዳክሞ መጀገን

ማን😊

💕ትዝታ ወልዴ(@Tizita21)

@getem
@getem
5👎1
በማላዊ አገር ሚስትዎን በ30 ቀናት ውስጥ እንዴት መለወጥ እንደሚቻል" (HOW TO CHANGE YOUR WIFE IN 30 DAYS) በሚል ርዕስ የወጣ መጽሐፍ  ርዕሱ ላይ የፊደል ስህተት እንዳለ ከመታወቁ በፊት በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁለት ሚሊዮን (2,000,000) ቅጂዎች ተሽጦ ነበረ ።

ትክክለኛው ርዕስ ግን "ሕይወትዎን በ30 ቀናት ውስጥ እንዴት መለወጥ እንደሚቻል" (HOW TO CHANGE YOUR LIFE IN 30 DAYS) የሚል ነበር። የፊደል እርማቱ ከተደረገ በኋላ  በዚያ ሙሉ ወር ውስጥ የተሸጠው 3 ቅጂ ብቻ ነበር።
https://t.me/DMAFS14
😁4👎2
በጃፓን ጦርነት ወቅት የወንድሙን ሬሳ (አስክሬን) በጀርባው አዝሎ በጥልቅ ስሜት ሊቀብር ይሄድ የነበረውን ታዳጊ ሕጻን ያስተዋለ አንድ ወታደር!

"ለምን እራስህን ታደክማለህ የሕጻኑን እሬሳ ጥለኸው ብትሄድ እኮ ድካምህ ይቀንስልህ አልነበር?" ሲል ጠየቀው::

ሕጻኑም :- "ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም" አለው::

ያን ጊዜ ጥያቄውን ያቀረበው ወታደር ራሱን መቆጣጠር አልቻለም ... ስሜቱ በጣም ተነካ ... ዓይኖቹ በዕንባ ታጠቡ::

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጃፓን ይህ ፎቶ የወንድማማችነት፣ የአንድነት ተምሳሌት ሆነ::

እናም ... የሕይወት መርሃችን እንዲህ ቢሆንስ:-
ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም !
እህቴ ናት እኔን አትከብደኝም !
ወንድምህ ቢወድቅ አንሳው !
እህትህ ብትደክም ከጉኗ ቁም !
ወንድምህ ቢስት በየውሃት መንፈስ አቅናው !
እህትህ ስህተት ብትሰራ ይቅርታህን አትንፈጋት ።
3👎1
አንድ ገበሬ ነበር ለማዳበሪያ መግዢያ መቶ ብር ቸገረውና ለአምላኩ ደብዳቤ ጽፎ ፖስታ ቤት አስገባ።
የፖስታ ቤቱ ሠራተኛ የሁሉንም ደብዳቤ በየአድራሻው አስገብቶ የአምላክ አድራሻ ቢጠፋው ፖስታውን ከፍቶ ማንበብ ጀመረ። አንብቦም ከት ብሎ ሳቀ። በአጭሩ እንዲህ ይላል
አምላኬ ሆይ የማዳበሪያ ምንም የለኝም
ክረምቱ መጥቷል እና ያረብ እስከዛሬ ወር መቶ ብር ላክልኝ።
የማዳበሪያ ካላገኘሁ አላርስም ካላረስኩ አልዘራም ካልዘራሁ እኔም ቤተሰቤም በረሃብ እንሞትብሃለን ይህን ደግሞ አንተ አትፈልገውም።……………
የፖስታ ቤቱ ሠራተኛ ደብዳቤውን አንብቦ ካበቃ በኋላ እስኪ የዚህን የዋህ ገበሬ ጉድ ልይ ብሎ ከኪሱ 99 ብር አወጣና በፖስታ አሽጎ ገበሬው ሳጥን ውስጥ አስገባ።
በወሩ ገበሬው አምላኩ እንደላከለት እርግጠኛ ሆኖ መጣ፣ ፖስተኛው ከሩቁ ተደብቆ ይከታተለው ጀመር ገበሬው ፖስታውን ሲከፍት 99 ብር ሆነበት። መልሶ ሌላ ደብዳቤ ጻፈ።
አምላኬ ሆይ የላክልኝ ብር ደርሶኛል። አንተ የላከው መቶ ብር ነበር„ የፖስታ ቤት ሠራተኞች ግን አንድ ብር ቆርጠዋል።
ስለዚህ ለወደፊት በነርሱ አትላክልኝ ይቆርጡብኛል አለ ይባላል😁
በአምላካክህ እርግጠኛ ከሆንክ ጥያቄህን በምን መንገድ እንደሚመልሰው አታቅምና እርሱን በደንብ እመን

https://t.me/DMAFS14
Share ይደረግ🙄🙄
👎1😁1
100 ብር ቦነስ ልኬልሃለሁ!
In this channel you can get many essential questions and shortnote that would help you in your exam specifically in your national exam
https://t.me/ethioexam12th
እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በቻናላችን ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

መልካም በዓል ተመኘን
!🙏🏾
🙏31
ዜና - ዕረፍት !!

ብዙዎቻችን የምናውቀው ተወዳጁ የኪነ ጥበብ ባለሙያ ነፃነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም ድካም በሞት ተለይቷል !!

ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ በሙሉ ከልብ መፅናናትን እንመኛለን !!

Rest In Peace 🕊
😢3
👉 በአንድ ገዳም የሚኖር ጀማሪ መነኩሴ የሥጋ ፈቃዱን መግታት ያቅተውና በዕለተ ረቡዕ በጾም ቀን ማለት ነው እንቁላል ጠብሶ ለመብላት ያስባል፡፡ ያቺን እንቁላል ሰብሮ ጠብሶ እንዳይበላት ሽታዋ ብዙ መዘዝ ሊያመጣበት ሆነና ተጨንቆ አንድ መላ አመጣ፡፡ ጥሬዋን እንቁላል በግራ እጁ ከፍ አድርጎ ይዞ በቀኝ አጁ የሚንቀለቀል ጧፍ ይዞ ከእንቁላሉ ሥር እያበራ እንቁላሉን በቅርፊቱ ውስጥ እያለ ለመጥበስ ይሞክራል፡፡ በዚህ ጊዜ የገዳሙ አበምት (አስተዳዳሪ) ደረሱበትና ምነው ልጄ ምን እያረክ ነው? ብለው በማስተዛዘን ቢጠይቁት አባቴ ሰይጣን አስቶኝ እኮ ነው አለና አረፈው:: ሰይጣኑ ድርጊቱን በቅርብ ርቀት ይከታተል ነበርና ተገልጦ "ኧረ! እኔ የለሁበትም እንዲያውም እንዲህ ዐይነቷን የእንቁላል አጠባበስ ዘዴ ያለዛሬም ዐላየኋትም " አለ ይባላል።
😁5