Computeck
49 subscribers
6 photos
6 links
Download Telegram
#አሪፍ_አፕሊኬሽን_ልጠቁማችሁ

ይህ አፕሊኬሽን PDF Cam Scanner ይባላል፡፡
ይህ አፕሊኬሽን በሞባይል ስልካችሁ ካሜራ አማካኝነት የተለያዩ በጣም ጠቃሚ ዶክመንቶቻችሁን ስካን አድርጎ ሶፍት ኮፒ ወደ PDF ፎርማት ለውጦ ያስቀምጥላችኋል፡፡

PDF Cam Scanner አፕሊኬሽን ተጠቃሚ ከሆናችሁ የተለያዩ ጠቃሚ ዶክመንቶቻችሁን በPDF ፎርማት ስልካችሁ ላይ በማስቀመጥ ቤትኛውም ቦታና ሰዓት ዶክመንቶቻችሁን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

የተለያዩ ከስራ ጋር የተያያዘ ወይም የግል ጠቃሚ ዶክመንቶች ይኖራችኋል፡፡
ለምሳሌ፡-

ተማሪዎች፡-
· ሲቪ
· የትምህርት ማስረጃዎች ይኖራችኋል

ሌሎቻችሁ ደሞ፡-
· መንጃ ፍቃድ
· ፓስፖርትና የቀበሌ መታወቂያ
· ንግድ ፍቃድ
· ግብር የከፈላቸችሁበት ደረሰኞች
· ውሎች
· የፍርድ ቤት ዶክመንቶች….ወዘተ ይኖራችኋል

እነዚህ በጣም ጠቃሚ ዶክመንቶች በወረቀት መልክ ቤታችን እናስቀምጣለን፡፡

ጉዳያችንን ለማስፈፀም የተለያዩ መ/ቤቶች ስንሄድ የነዚህ ዶክመንቶች ፎቶ ኮፒ እንጠየቃለን፡፡ስለዚህ ምንድ ነው የምናደርገው- እነዚህን በጣም ጠቃሚ ዶክመንቶች በፎልደር ይዘን እንዞራለን ማት ነው፡፡

ነገር ግን ይህ ሁኔታ ብዙ ችግሮችን ይፈጥራል፡፡

ለምሳሌ እነዚህ ዶክመንቶች ይዘን ስንዞር ዶክመንቶቹ ቢጠፉስ፤ከነ ፋይል መያዣው ቢጠፋስ፤፤፤፤ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው የምንገባወ፡፡

ነገር ግን በPDF Cam Scanner አፕሊኬሽን ዶክመንቶቻችሁን በሙሉ ስካን እያደረጋችሁ ሞባይል ስልካችሁ ላይ ብታስቀምጡ፡-

1ኛ፡- ዶክመንታችሁ በፎልደር ይዞ ከመዞር ትገላገላላችሁ

2ኛ፡- ዶክመንቶቹ ቢጠፉ ስልካችሁ ላይ ስለተቀመጡ ከመጨነቅ ትድናላችሁ

3ኛ፡- አንድ ቢሮ ሄዳችሁ ድንገት አንድ ዶክመንት ብትጠየቁ…አይ አልያዝኩትም ወይም ረስቼው መጣሁ…ነገ አመጣለሁ አትሉም፡፡ እዚያው ሞባይላችሁ ላይ ገብታችሁ የተፈለገው ዶክመንት ፕሪንት አድርጋችሁ መስጠት ትችላላችሁ፡፡ ግዜ ይቆጥባል፡፡

ለምሳሌ፡- ስራ ፈላጊ አዲስ ተመራቂዎች መንገድ ላይ ስትሄዱ ድንገት ለናንተ የሚሆን ስራ ማስታወቂያ ብታገኙ እና የማመልከቻው የመጨረሻ ቀን ዛሬ ቢሆን አመለጣችሁ ማለት ነው፡፡

ምክንያቱም ሲቪያችሁ ቤት ኮምፒውተር ላይ ፤ወይም ፍላሽዲስክ ላይ ነው ያለው፡፡ እና ኮምፒውተራችሁም፤ፍላሽ ዲሰካችሁንም አልያዛችሁም፤ ቤታችሁ ሄዳችሁ ለማምጣት ደሞ ግዜ አይበቃችሁም፡፡ ስለዚህ ቀለጣችሁ ማለት ነው፡፡

ነገር ግን ቀደም ብላችሁ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን፤ሲቪያችሁን በ PDF Cam Scanner ስካን አድርጋችሁ ሞባይላችሁ ላይ ካስቀመጣችሁ እንዲህ ዓይነት አጋጣሚ ስታገኙ ከሞባይል ስልካችሁ ላይ የተፈለገውን ዶክመንት ዳውንሎድ አድርጎ ፕሪንት በማድረግ መጠቀም ትችላላችሁ፡፡

PDF Cam Scanner አፕሊኬሽን ዶክመንቶቻችሁን ብትፈልጉ በከለር ብትፈልጉ በነጭና በጥቁር በPDF ፎረማት ስካን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

ተጠቀሙበት፡፡ትውዱታላችሁ፡፡

አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ላማድረግ ይህንን ሊነክ መጠቀም ትችላላችሁ፡-
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.cutestudio.pdf.camera.scanner

@Computersalesjava
@Computersalesjava
@Computersalesjava
ላፕቶፓችን_ያለኛ_ፍቃድ_ፍላሽ_ዲሰክ_እንዳይቀበል_ማድረግ_እንዴት_እንደ_ሚቻል_ላሳያችሁ

ፍላሽ ዲሰክ ፋይሎችን የምናስቀምጥበትና በቀላሉ ይዘነው የምንቀሳቀሰውማሽን ነው፡፡ በስራ ምክንያትም ይሁን በሌላ ፋይሎችን ላማስተላለፍና ኮፒ ለማድረግ ሰዎች የሚጠቀሙበት ፍላሽ ዲሰኮች ላፕቶፓችን ላይ እንሰካል፡፡

ላፕቶፓችን ላይ ያገኘነውን ፍላሽ ዲሰክ የምንሰካ ከሆነ ደሞ ላፕቶፓችን አደጋ ውስጥ ይገባል፡፡
ምክንያቱም ፍለሽ ዲሰክ ፋይሎችን ብቻ ሳይሆን ቫይረሶችንም ስለሚያስቀምጥ ያገኘነውን ፍላሽ ላፕቶፓችን ላይ የምንሰካ ከሆነ በፍላሽ ዲሰኮች አማካኝነት ቫይረሶች ወደ ኮፒውተራችን በመግባት ላፕቶፓችን ላይ አደጋ ሊያደርሱ ይችላል፡፡

ከኛ ፍቃድም ውጪ ሳናውቀው አንድ ሰው ተደብቆ ላፕቶፓችን ላይ ፍለሽ ዲሰክ በመሰካት ላፕቶፓችንን ክጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡

ስለዚህ በተለይ ያለኛ ፍቃድና እውቀት ላፕቶፓችን ፍላሽ ዲሰክ እንዳይቀበል ለማድረግ የሚከተሉትን ስቴፖች መከተል ነው፡፡

1ኛ፡-መጀመሪያ Start በተንን ክሊክ እናደርግና gpedit.msc ብለን እንፅፍና ኢንተር እንጫናል፣

2ኘ፡- የተለያዩ አማራጮች የያዘ ሊስት ይመጣል፤ ሊስቱ ውስጥ “Local Group Policy Editor” የሚለውን ምረጡ፣

3ኛ፡-ከዚያ የሚከተለውን መንግድ ተከተሉ ፤ computer configuration>administrative templates>system>Removable storage access

4ኛ፡-አሁን በቀኝ በኩል ከሚመጡ አማራጮች ውስጥ “All Removable Storage Classes: Deny all access” የሚለውን ክሊክ ማድረግ፣

5ኛ፡- “Enable” የሚል አለ እሱን መምረጥ፣

6ኛ፡- “Apply”> “Ok” ሁለቱንም ተራ በተራ ክሊክ ማድረግ፡፡

አለቀ፡፡ ካሁን በኋላ ማንም ሰው ፍላሽ ዲስኩን ላፕቶፓችሁ ላይ መሰካት አይችልም፡፡

ምናልባት ይህንን የከለከላችሁትን አክሰስ መመለስ ስትፈልግ ከላይ ከ1 እስከ 4 ስቴፖችን እንዳሉ ተከተሉ እና፣

5ኛ፡- “Not Configure” የሚል አለ እሱን መምረጥ፣

6ኛ፡- “Apply”> “Ok” ሁለቱንም ተራ በተራ ክሊክ ማድረግ፡፡
@Computersalesjava
@Computersalesjava
Channel name was changed to «Computeck»