የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
826 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ባለፉት ስምንት ዓመታት በህፃናት ድጋፍና "አንድ ቤተሰብ ለአንድ ሰው" በተሰኙ ሰብዓዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ከ200 ሺህ በላይ ድጋፍ የሚሹ ወገኖች ተጠቃሚ ሆነዋል።

ባለፉት ስምንት ዓመታት "በአንድ ቤተሰብ ለአንድ ሰው" የተሰኘው መርሃ ግብር ድጋፍ ፈላጊን ከደጋፊ ጋር በቀጥታ በማገናኘት አስተማማኝ የመረዳዳት ባህልና ዘላቂ ስርዓት መዘርጋት ተችሏል። በዚህ ሂደት ውስጥ ባለሀብቶች፣ በጎ አድራጊ ድርጅቶችና የሃይማኖት ተቋማት ተቀናጅተው መስራታቸው የድጋፍ ስራው በአንድ ወገን ላይ ብቻ እንዳይወድቅ ከማድረጉም በላይ፣ 199,426 አቅመ ደካሞችን ተጠቃሚ በማድረግ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን የኑሮ ጫና መቀነስ አስችሏል።

ይህ ተግባር ከቁሳዊ ድጋፍ ባለፈ፣ በማህበረሰቡ መካከል ያለውን መተጋገዝና መተሳሰብ አጠናክሮ የዘለቀ ሲሆን ችግርን በብቸኝነት ሳይሆን በጋራ መጋፈጥ እንደሚቻል በተግባር የታየበት ታላቅ ስኬት ነው። ድጋፉ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ በማድረግ፤ አቅመ ደካሞች የነገ ተስፋቸው እንዲለመልም እና አስተማማኝ የኑሮ ዋስትና እንዲሰማቸው በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ ነበረው። ይህም ማህበራዊ ትስስር ችግርን በጋራ የመወጣት ትልቅ አቅም መሆኑን በተግባር አሳይቷል።

በሌላ በኩል፣ የነገ ሀገር ተረካቢ ለሆኑ ህጻናት ልዩ ትኩረት በመስጠት ወላጆቻቸውን ያጡና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ 2,351 ህጻናትን መደገፍ ተችሏል። ይህ በጎ አገልግሎት ለሀገር ቀጣይነት የሚደረግ ትልቅ መዋዕለ ንዋይ ነው። እነዚህ ህጻናት የሚደረግላቸው ድጋፍ በችግር ምክንያት ለተለያዩ ጥቃቶች እንዳይጋለጡ ከማድረጉም በላይ፣ በትምህርትና በጤና ዘርፍ ተገቢውን እንክብካቤ አግኝተው ለቁም ነገር እንዲበቁ መሰረት ጥሏል። ይህ ተግባር የሰብአዊነት ስራዎች በዘመናዊና ስልታዊ በሆነ መንገድ ከተመሩ ምን ያህል ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ትልቅ ማሳያ ነው።

በአጠቃላይ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑት ተግባራት "አብሮነት ተደማሪ አቅም ነው" የሚለውን መርህ በመከተል የተገኙ ውጤቶች ናቸው። ይህንን ስኬታማ ተሞክሮ መሰረት በማድረግ፣ የተጀመሩ የትስስርና የድጋፍ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል የማህበረሰባችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ሰብአዊነትን በተግባር በመግለጽና ለተጎዱ ወገኖች ፈጥኖ በመድረስ የምናደርገው ጉዞ ሀገራዊ አንድነታችንን ይበልጥ የሚያጸና ይሆናል።

"ሰብዓዊነት ይለምልም!"
የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን

#ሰብአዊነት #ነጻህክምና #የህጻናትድጋፍ #ትስስር #አብሮነት #ኢትዮጵያዊነት
1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ባለፉት ዓመታት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ከፍለው መታከም የማይችሉ የመዲናዋ ነዋሪዎች ነፃ የህክምና አገልግሎት አግኝተዋል።

የጤና አገልግሎትን ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት የከተማዋ ሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዋና መገለጫ ነው። ይህም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ከከፍተኛ የህክምና ወጪ በመታደግ ማህበራዊ ፍትህን የማረጋገጥ ስራ ነው። ባለፉት ስምንት ዓመታት 547,990 ዜጎች ከቅድመ ምርመራ እስከ ከፍተኛ ቀዶ ጥገና ድረስ ያለውን የህክምና አገልግሎት በነጻ እንዲያገኙ ተደርጓል። ይህ ሰብዓዊ ተግባር በገንዘብ ሲተመን ከ661.8 ሚሊዮን ብር በላይ ሲሆን በጎ ፈቃደኝነት ለሀገር ኢኮኖሚና ለዜጎች ደህንነት ያለውን የማይተካ ሚና አመላካች ነው። አገልግሎቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎችን ህይወት በመታደግ ረገድም የከተማዋን የማህበራዊ ልማት ግቦች ስኬታማ አድርጎታል።

ከተማ አስተዳደሩ በሰው ተኮር ስትራቴጂው የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ለማህበረሰባዊ ደህንነት እንዲውል በማድረግ፣ ጤናማና አምራች ዜጋን ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት ትልቅ አቅም ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። "በጎነት ለጤና!" የበጎ ፈቃድ ሰው ተኮር አገልግሎት ከከተማዋ የረጅም ጊዜ የማህበራዊ ልማት ግቦች ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው። ዓላማውም ማንኛውም ዜጋ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ህይወቱ እንዳያልፍ ዋስትና መስጠት ነው።

ይህንን የተጀመረ ጥረት ይበልጥ በማጠናከር፣ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች እኩል ተጠቃሚ የሚያደርግና የዜጎችን ሰብአዊ ክብር የሚጠብቅ የጤና ስርዓት በመገንባት ሂደት ውስጥ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሚና ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን

#ሰብአዊነት #ነጻህክምና #የህጻናትድጋፍ #ትስስር #አብሮነት #ኢትዮጵያዊነት
በአዲስ አበባ ባለፉት ስምንት ዓመታት 369,220 ዩኒት ደም ተሰብስቧል።

ባለፉት ስምንት ዓመታት በአዲስ አበባ 369,220 ዩኒት ደም ከበጎ ፈቃደኛ ለጋሾች ተሰብስቧል። የከተማዋ ነዋሪዎች ለወገን ያላቸውን የማይናወጥ ፍቅርና ጥልቅ ሰብዓዊነት በተግባር ያረጋገጡበት ይህ በጎ አገልግሎት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖችን ከሞት አፋፍ ከመታደጉም በላይ በወሊድ ምክንያት የሚከሰትን የእናቶች ሞት ቀንሷል።

በሕክምና ሳይንስ አንድ ዩኒት ደም ለሦስት ዋና ዋና የደም ክፍሎች (ቀይ የደም ሴል፣ ፕላቴሌት እና ፕላዝማ) ተከፍሎ ጥቅም ላይ ስለሚውል አንድ ለጋሽ ብቻውን የሦስት ሰዎችን ሕይወት መታደግ የሚያስችል አቅም አለው። በዚህም ስሌት መሠረት በአዲስ አበባ ባለፉት ስምንት ዓመታት የተሰበሰበው 369,220 ዩኒት ደም ከአንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን ሕይወት ከሞት ታድጓል። ይህ አኃዝ በድንገተኛ አደጋ፣ በወሊድና በሌሎች ህመሞች ምክንያት ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የተደረገ ታላቅ የሰብዓዊነት ስጦታ ነው።

ደም መስጠት በምንም ዓይነት ቁሳቁስ የማይተካ፣ በገንዘብ የማይለካ፣ የሕይወት ገፀ በረከት፣ ምትክ የሌለውን የሰው ልጅ ህይወት በራስ ህይወት የመታደግ አገልግሎት ነው። ደም መለገስ ከምንም በላይ የላቀና ንጹህ የፍቅር ስጦታ፣ የአብሮነት ማስተሳሰሪያና የሰብዓዊነት ትልቁ መገለጫ ምግባር ነው።

#ደምልገሳ #ህይወትንመታደግ #በጎፈቃደኝነት #ሰብአዊነት #ኢትዮጵያ
2👍1
ዛሬ ጠዋት የስራ ዘመኑን ሶስተኛ የ100 ቀናት የመንግሥት ሥራ አፈፃፀም ከዘጠኝ ወራት አጠቃላይ አፈፃፀም ጎን ለጎን መገምገም ጀምረናል።

‎ለእድገት አመቺ ካልነበረው እና በደካማ የተቋማት እና የፖለቲካ ማዕቀፍ ፣ በታጠረ የግል ዘርፍ ተሳትፎ እንዲሁም ውጤታማ ባልነበረ የቁጥጥር ከባቢ ከሚገለጠው የኢኮኖሚ መልክ ወጥተናል። የግሉ ዘርፍ ደካማ ውድድር ውስጥ ነበር፤ በመንግሥት ሥር የነበሩ በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው የንግድ ተቋማትም ከፍ ባለ የዕዳ ሸክም ተዘፍቀው ከአቅም በታች ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ይታወቃል። ምርታማነት አሽቆልቁሎ ኢኮኖሚውም ለአየር ንብረት ለውጥ በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የነበረውን ነባራዊ ሁኔታ ምላሽ በሚሰጥ አዲስ ገቢር ነበብ የፓለቲካ ኢኮኖሚ መንገድ ቀይሰናል።

‎የቀየስነው አዲሱ የኢኮኖሚ አካሄድ በአጭር ጊዜ ትግበራ ጠንካራ ባለሁለት አሃዝ የእድገት ሂደትን አስመዝግቧል። በአሁኑ ወቅት ኢኮኖሚያችን በ9.2 በመቶ እያደገ ይገኛል። ይኽ እድገት በመጪው ዓመት ወደ10.2 በመቶ እንደሚያድግ እንጠብቃለን። በየዘርፉም የታቀዱ ግቦቻችንን ለማሳካት ከፍ ባለ ትጋት ቀጥለን፤ በግብርና 7.9 በመቶ፣ በኢንደስትሪ 13.2 በመቶ፣ በአገልግሎት 9.3 በመቶ ዕድገቶች ሳይቆራረጡ የሚከናወኑ ይሆናል።

‎እነዚህ ጥረቶች የበለጠ ጽኑ፣ ተወዳዳሪ እና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት ያለንን አቋም እና የመተግበር ዐቅም ያሳያሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝግባ ሊጠናቀቅ አንድ ቀናት ብቻ ቀሩት!

እንግዲያውስ ባሉበት ሆነው በ"ምርጫዬ” የሞባይል መተግበሪያ ወይም ስድስት ወር እና ከዚያ በላይ በኖሩበት አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ በአካል በመገኘት በቀላሉ መመዝገብ ይችላሉ።
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የልማት ዕቅድ ማስፈጸሚያ ኢንሼቲቮችን በመለየት መተግበር:-

‎ከ100 ቀናት ሪፖርት እና ከ9 ወራት የሥራ አፈፃፀም የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ሥር የተቀረጹት ስድስት ታላላቅ ውጥኖች በመላ ሀገሪቱ የሚታይ ለውጥ እያመጡ ይገኛሉ።

‎• አረንጓዴ ዐሻራ፦ የሀገሪቱ የደን ሽፋን 23.6% ደርሷል። በዚህም የአርሶ አደሮች ገቢ እያደገ፣ አረንጓዴ የሥራ ዕድሎች እየተፈጠሩ፣ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ሥራዎች እየተከናወኑ እንዲሁም ሥነ-ምህዳሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጤናማ እየሆነ መጥቷል።

‎• ሀገራዊ የስንዴ ልማት፦ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን እና ሉዓላዊነትን እያረጋገጠች ትገኛለች። አዳዲስ የግብርና ዕውቀቶች እየተስፋፉ፣ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ግብዓቶችን እያገኙ፣ ውድ የሆኑ የውጭ ምርቶች በሀገር ውስጥ እየተተኩ፣ የሥራ ዕድሎች እየሰፉና የአርሶ አደሮች ገቢ እየጨመረ ይገኛል።

‎• የሌማት ትሩፋት፦ የግብርና ግብዓቶች አቅርቦት እና ምርታማነት እየጨመረ ነው። የተመጣጠነ ምግብ በቀላሉና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገኝ ከማድረግ ባለፈ፣ አነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲሳለጡና አካባቢው ይበልጥ እንዲጠበቅ እያደረገ ይገኛል።

‎• ዲጂታል ኢትዮጵያ፦ የሕግ፣ የፋይናንስ እና የማንነት መታወቂያ (ID) ሥርዓቶች ወደ ዲጂታል እየተቀየሩ ነው። የኢንተርኔት ተደራሽነትና የኦንላይን አገልግሎቶች እየተስፋፉ፣ የሞባይል ክፍያ ሥርዓት እየተጠናከረ እንዲሁም የኢ-ኮሜርስ ንግድ የዜጎችን ጊዜና ገንዘብ እያተረፈ ነው።

‎• የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማት፦ የከተሞች መሠረተ ልማት በአረንጓዴ ትራንስፖርት እየዘመነ ነው። ይህም የዜጎችን የኑሮ ጥራት እያሻሻለ፣ የአካባቢ ንግድን እያነቃቃ እንዲሁም በከተማና በገጠር መካከል ያለውን ትስስር እያጠናከረ ይገኛል።

‎• ኢትዮጵያ ታምርት፦ የማምረት አቅምና የምርቶች እሴት የመጨመር ሂደት እየተሻሻለ ነው። ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በሀገር ውስጥ እየተተኩ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እያደገ፣ የግብዓት አቅርቦት እየተጠናከረና አዳዲስ የሥራ ዕድሎች እየተፈጠሩ ነው።

‎እያንዳንዱ ምሰሶ ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር፣ ጠንካራ እና ራሷን የቻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው።

#PMOEthiopia

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኅብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኅብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጆሴፍ ሲከላ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ዛሬ ጠዋት ኮሚሽነር ጆሴፍ ሲከላን አግኝቼ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ስላለን የረጅም ጊዜ ትብብር ተወያይተናል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት አካሄደ።

ካቢኔው በዛሬው ስብሰባው በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡

በዚህ መሰረት፡-
1ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሻሻለ የፋይናንስ አስተዳደር ይበልጥ ለማዘመን፣ ተጠያቂነትንና የአሰራር ግልፀኝን ለማጐልበት በተዘጋጀዉ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።

2ኛ. በከተማዉ እየተገነባ ያለዉን ሰፊ የቤት ልማት የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረዉ፣ የቤቶች ኮርፖሬሽን ሪፎርም በማጠናከር እና የማስፈፀም ብቃት ለማሳደግ በተዘጋጀዉን ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።

3ኛ. የመሬት ማስፋፍያ ለጠየቁ ተኪ ምርት ለሚያመርቱ ኢዱስትሪዎች፣ ለወጣቱ የስራ ዕድል የፈጠሩ ፕሮጀክቶች፣ ሆቴሎች እንዲሁም፥ በከተማ አስተዳደሩ ከሐይማኖት ተቋማት ጋር በተደረጉ ተከታታይ ውይይቶች የተነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መፍታት የሚያስችል መሬት በምደባ ለማስተላለፍ የቀረበ የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ፣ ተፈፃሚ እንዲሆን አድፅድቋል።
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝግባ ሊጠናቀቅ አንድ ቀናት ብቻ ቀሩት!

እንግዲያውስ ባሉበት ሆነው በ"ምርጫዬ” የሞባይል መተግበሪያ ወይም ስድስት ወር እና ከዚያ በላይ በኖሩበት አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ በአካል በመገኘት በቀላሉ መመዝገብ ይችላሉ።
1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው ተሾሙ። ሹመቱ የተሰጠው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዘርፉ ላሳዩት አመራር እና ኢትዮጵያ በአህጉሩ የሰው ሰራሽ አስተውሎትንና የፈጠራ ሥራዎችን ለማስፋፋት እየተገበረች የምትገኘውን የላቀ ሚና እውቅና ለመስጠት ነው።

በተላከው የሹመት ደብዳቤ ላይ የሚከተለው ሰፍሯል፦ “የተከበሩ የእርስዎ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስፋፋት ያደረጉት አመራር፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለአፍሪካ ሉዓላዊነት፣ ለውጤታማነት እና ለአሳታፊ እድገት ቁልፍ መሣሪያ ሆኖ እንዲያገለግል በማስቻል ረገድ ትልቅ እገዛ አድርጓል። ስልታዊ በሆነ መልኩ የቴክኖሎጂ ነጻነትን እና ዐቅምን ለመገንባት የሚያደርጉት ተከታታይ ቅስቀሳ፣ አህጉሩ በኃላፊነት እና በፍትሐዊነት በታጀበ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።”

ባለፉት ጥቂት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመራር፣ ኢትዮጵያ በዲጂታላይዜሽን እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፎች ያስመዘገበችው እድገት ከፍተኛ አፈጻጸም ያሳየ ነው። የዲጂታል መሰረተ ልማትን ማስፋፋት፣ የኢ-መንግሥት (e-government) አገልግሎቶችን ሥራ ላይ ማዋል፣ በፈጠራ ሥነ-ምህዳር ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩትን ማቋቋም እንዲሁም ሀገራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስትራቴጂ መንደፍ ለለውጡ ጠንካራ መሰረት የጣሉ ተግባራት ናቸው። በተጨማሪም ራሱን የቻለ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም የታቀደው ዕቅድ፤ ምርምርን፣ የክህሎት ልማትን እና አህጉራዊ ትብብርን ይበልጥ እንደሚያጠናክር ይጠበቃል።

Prime Minister Abiy Ahmed has been appointed as the African Union Champion for Artificial Intelligence and Digital Health. The announcement recognises his leadership and Ethiopia’s growing role in advancing artificial intelligence and innovation across the continent.

The appointment letter noted: “Your Excellency’s leadership in promoting digital transformation and emerging technologies has helped position artificial intelligence as a key tool for sovereignty, efficiency, and inclusive growth in Africa. Your continued advocacy for strategic autonomy and technological empowerment will be instrumental in positioning the continent as a global leader in responsible and equitable AI adoption.”

Ethiopia’s progress in digitization and artificial intelligence launched and accelerated significantly under the Prime Minister’s active engagement over the last few years. Initiatives such as the expansion of digital infrastructure, the rollout of e-government services, investments in innovation ecosystems, and the establishment of an AI institute and development of a national AI strategy have laid a strong foundation for transformation. In addition, plans to establish a dedicated AI university are expected to strengthen research, talent development, and continental collaboration in emerging technologies.

#AIforAfrica
#PMOEthiopia
3👍1
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እንኳን ደስ አለዎት!

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው በመሾምዎ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እንኳን ደስ አለን ለማለት እወዳለሁ።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን የጥረታቸው ፍሬ በአፍሪካ ደረጃ እውቅና አግኝቶ ለዚህ ሹመት መብቃታቸው ለኢትዮጵያን ሁሉ ኩራት ነው ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ !
3👍1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ከሰአት በኋላ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀብለዋል። የመሪዎቹ ግንኙነት ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር በኢትዮጵያ የሚያደርጉት የሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት አካል ነው። የመሪዎቹ ውይይት በሁለትዮሽ ግንኙነቶች እና የወል የትብብር መስኮችን በማጠናከር ላይ እንደሚያጠነጥን ይጠበቃል።

Prime Minister Abiy Ahmed receives H.E. Salva Kiir Mayardit, President of the Republic of South Sudan, at the National Palace this afternoon. The meeting takes place as part of President Kiir’s two-day official visit to Ethiopia. Discussions are expected to focus on bilateral relations and advancing areas of mutual cooperation.

#PMOEthiopia
2
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ቅጠል ተራን  ወደ ውብ መኖሪያ ሥፍራ!

ለመኖር እጅግ ምቹ ያልሆነ፤ ለሰው ልጅ ክብር በማይመጥን፤ በጣም የቆሸሸ፣ የተፋፈገ እና የተጨናነቀ እንዲሁም ከተማ እምብርት ላይ ሆነው በተተበተበ ለአደጋ አጋላጭ  የሆነ የኤሌክትሪክ  መስመር ብሎም በኩራዝና  በሻማ የሚጠቀሙ ነዋሪዎች ይኖሩበት የነበረውን የቅጠል ተራ ሰፈርን፣ ወደ ውብ መኖሪያ አካባቢነት ለመቀየር ዛሬ ባለ 8 ወለል የሆኑ ብዛታቸው 9 ህንጻዎች ከ500 በላይ ቤቶችን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠናል።

ይህ ፕሮጀክት አካባቢው መንገድ ያልነበረው፣ እንደ ሸረሪት ድር የተጠላለፉ ገመዶች የበዙበት፣  ነዎሪዎች በድህነት ምክንያት ኑሯቸውን ለመደጎም ቤታቸው ውስጥ ቆጥ ሰርተው አልጋ  የሚያከራዩበትና ሰዎች ላይ ቆልፈው በሚሄዱበት ጊዜ በሚፈጠር የእሳት አደጋ የሰዎች ህይወት የሚጠፋበት፣ ንብረት የሚወድምበት፣ እጅግ ብዙ ገመናዎችን የያዘ  አስከፊ  የሰው ህይወትን  የሚቀይር  ፕሮጀክት ነው።

አካባቢው የከተማ እምብርት ሆኖ ሳለ፣ ነገር ግን በብዙዎቹ  የገጠር አካባቢዎች እንኳን የቀረውን ሻማ እና ኩራዝ የሚጠቀም ነዋሪ ያለበት አካባቢ ነው።

መርካቶ አካባቢ ብዙ  “ተራ”  የሚል ስያሜ የተሰጣቸው - ቅጠል ተራ፣ ጭድ ተራ፣ ገብስ ተራ፣ ሳር ተራ፣  ቦንብ ተራ … ጠጋ ብለን ስናያቸው የነዋሪዎቻችን የአኗኗር ሁኔታ እና ገፅታውን የሚያሳዩ ናቸው። እንደዚህ ዓይነት ችግሮችን ደጋግመን በማውራት ነዋሪው ሆድ እንዲብሰው ማድረግ ሳይሆን፣ መፍትሄው ሰርተን ህይወቱ እንዲቀየር እና ለሰው ልጆች የሚመጥን የክብር ኑሮ እንዲኖር እዚያው የመኖሪያ ቤት እና የንግድ ቦታዎች እንዲያገኝ ማድረግ ነው ።

በከተማችን ዋነኛ የስራዎቻችንን ማዕከል ሰው ተኮር ስራዎች አድርገን እየሰራን እንገኛለን ።
በቅጠል ተራ ያስጀመርነው የቤት ግንባታ 10ሺህ ካሬ ላይ ያረፈ፤ ተገንብቶ ሲጠናቀቅም ከ20,000  በላይ ሰዎችን ንፁህ፤  ለሰው ክብር የሚመጥን ዘመናዊ አኗኗር ያለው መኖሪያ ቤት  ተጠቃሚ የሚያደርግ ትልቅ ፕሮጅክት ነው ።

ፕሮጀክቱ ልጆች ቦርቀው እንዲያድጉ የስፖርት ሜዳ እንዲሁም የንግድ ሱቆች እና  ሊሎች አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ ተሟልተውለት  በጥራት እና በፍጥነት ተገንብቶ ይጠናቀቃል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
1