የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በአዲስ አበባ የትንሳኤ በዓል ገበያ፣ በተተመነ ዋጋ ላይ ጭማሪ ባደረጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ
በአዲስ አበባ ከተማ ለትንሳኤ በዓል በተዘጋጁ የገበያ ማዕከላት ውስጥ በመንግስት ከተቀመጠው የዋጋ ተመን በላይ ሲሸጡ በተገኙ ሰባት የንግድ ድንኳኖች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የከተማዋ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ በከተማዋ በሚገኙ ስድስት የግብርና ምርት ማዕከላት፣ 246 የሰንበት ገበያዎች እና 11 ባዛሮች ላይ የንግድ ቢሮው የዋጋ ተመን አውጥቶ ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል።
ኃላፊዋ እንዳሉት፣ በ8588 ነፃ የስልክ መስመር በኩል ከህዝብ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በተደረገ ክትትል፣ ሰባት የንግድ ድንኳኖች በተለጠፈው የዋጋ ተመን ሳይሆን ከዚያ በላይ ሲሸጡ ተገኝተዋል። በዚህም የተነሳ፣ ሰባቱም የንግድ ድንኳኖች ከስራ እንዲታገዱ ተደርጓል። እነዚህ ነጋዴዎች ዳግም መሰል የገበያ አማራጮችና ባዛሮች ላይ እንዳይሳተፉ ተወስኖባቸዋል።
ወይዘሮ ሀቢባ አክለውም፣ ከተማ አስተዳደሩ ሰፊ በጀትና ጊዜ መድቦ የሸማቹን ማህበረሰብ ጫና ለመቀነስ እየሰራ ባለበት ወቅት፣ እንዲህ ያሉ ህገ-ወጥ ተግባራትን መፈጸም ተቀባይነት እንደሌለው አስገንዝበዋል።
ድርጊቱን እንደ ሀገር ክህደት ነው የምንቆጥረው ያሉት ኃላፊዋ፣ ለህገ-ወጥ ነጋዴዎች ምንም ዓይነት ትዕግስት እንደማይኖርና ፈጣን እርምጃ መውሰዱ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የንግድ ቢሮው ነዋሪዎች በማንኛውም የግብይት ሂደት ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ወይም ህገ-ወጥ ተግባር ሲያጋጥማቸው በ 8588 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ መስጠታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል። እያንዳንዱ ጥቆማ በአግባቡ ተፈትሾ አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድም ተገልጿል።

❤2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግም፣ ዛሬ ጠዋት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እና ጽሕፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው ሕጻናት ማዕድ አጋርተዋል።
On the occasion of the upcoming Easter holiday, Prime Minister Abiy Ahmed shared items this morning with low income staff members of the Office of the Prime Minister and also with orphaned children the PMO is helping to raise.
#PMOEthiopia
On the occasion of the upcoming Easter holiday, Prime Minister Abiy Ahmed shared items this morning with low income staff members of the Office of the Prime Minister and also with orphaned children the PMO is helping to raise.
#PMOEthiopia
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የዓለም-አቀፍ ኮንፈረሶች የስህበት ማዕከል፥ አዲስ አበባ!
አዲስ አበባ፥ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና እና የዓለም-አቀፍ ስብሰባዎች ቀዳሚ መዳረሻ መሆኗን በተለያዩ ዘርፎች በተግባር እያረጋገጠች ትገኛለች። ከተማዋ ያላትን ጠንካራ የማስተናገድ አቅም፣ የሆቴል መሰረተ ልማት እና ልዩ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል፣ ለበርካታ ታላላቅ ጉባኤዎች ተመራጭ እንድትሆን አስችሏታል።
መዲናችን ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ተመራጭ እንድትሆን ካደረጓት ዋና ዋና ምክንያቶች፣ በከተማዋ ከ210 በላይ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ፅ/ቤቶች፣ ታላቁ የአፍሪካ ኅብረት እና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ መሆኗ እና በአጭር ጊዜ ያመጣችውን አስደማሚ የዕድገት መንገድ ተደምሮ ለአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ውሳኔዎች ቁልፍ ስፍራ አድርጓታል።
በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፥ ከተማዋ ለነዋሪዎቿም ሆነ ለጎብኚዎች ምቹ፣ ውብ እና ሳቢ ለማድረግ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ለዓለም አቀፍ ጉባኤዎች እና ጎብኚዎች ያላትን ተመራጭነት ይበልጥ አልቆታል።
በሌላ በኩል፥ ከተማዋን የቱሪዝም እና የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ የተገነባው “አዲስ ዓለም-አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል” ለከተማዋ ተጨማሪ የማስተናገድ አቅም የፈጠረ እና ለትላልቅ አለም አቀፍ ስብሰባዎችና ኤግዚቢሽኖችን ለማዘጋጀትም ዓቅም የፈጠረ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡
እንዲሁም “የዓድዋ ድል መታሰብያ ሙዝየም” ከታሪክና ቅርስ ማዕከልነቱ ባሻገር፣ በርካተ ስብሰባዎችን እና ኤግዚብሽኖችን በአንድ ጊዜ የማስተናገድ ማስተናገዱ ሌላው ለኮንፈረንስ ማዕከልነቷ ገፀ-በረከት ነው።
በአጠቃላይ አዲስ አበባ፣ በታሪክ ብቻ ከመኖር በአሁናዊ መሬት ላይ በፈጠረችው አስደማሚ የዕድገት እና ሁለንተናዊ ከፍታ፣ “ከሀገራችን ዋና ከተማነት ባሻገር" የዓለምን ቀልብ እየሳበች፣ በፈጣን ለውጥ ላይ ያለች እና ለዓለም-አቀፍ ባለሀብቶች፣ እንዲሁም ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ምቹ እየሆነች የመጣች ከተማ ናት።

👍2❤1
የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ክቡር ኤቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ፤ በድንቅ ህዝቦቿና ባህሏ ወደ ምትቀበሎት ሀገሬ ኢትዮጵያ እንኳን በሰላም መጡ ስል በታላቅ ክብር ነው። ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ ጥልቅ የሆነ የወንድማማችነት እና የጋራ መከባበር ታሪክ ያላቸው ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘላቂ ትስስርም በከፍተኛ ሁኔታ እንደምናከብር ላስታውሶት እወዳለሁ። በዚህ ይፋዊ የስራ ጉብኝትዎ፣ ለወደፊቱ ያለንን የጋራ ትልም ወደ እውነት ለመቀየር በምናደርገው ጥረት፤ ቆይታዎ ግንኙነታችንን የበለጠ እንደሚያጠናክረው አልጠራጠርም። በድጋሚ እንኳን ወደ ሁለተኛ ቤትዎ በደህና መጡ ለማለት እወዳለሁ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
ዛሬ የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ-መንበር ክቡር ኢቫሪስት ንዴሺሚዬን በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀብለናቸዋል።
ክቡር ፕሬዝዳንቱ በአድዋ ጀግኖች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን ያኖሩ ሲሆን፤ ለመላው ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ፋና ወጊ የሆነውን የአድዋ ድል ታሪክም አስጎብኝተናቸዋል።
ክቡር ፕሬዝዳንት፤ በአድዋ ድል መታሰቢያ ለነበረዎት ቆይታ እያመሰገንኩ፤ በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካውያን ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ የሚኖርዎት ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እመኛለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ የከተማ ትራንስፎርሜሽን ሞዴል በአፍሪካ የከተሞች ፎረም ላይ ተሞክሮ ሆኖ ቀረበ ።
በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ በሚገኘው 2ኛው የአፍሪካ የከተሞች ፎረም ላይ፣ በአዳዲስ ፈጠራዎችና ስልቶች የታጀበው "የአዲስ አበባ የከተማ ትራንስፎርሜሽን ሞዴል" ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ተሞክሮ ሆኖ ቀረበ።
ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 2 ቀን 2018 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) በሚቆየው በዚህ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ፣ አዲስ አበባ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያስመዘገበቻቸው ተጨባጭ የለውጥ ውጤቶች በዝርዝር ቀርበዋል። በተለይም ከተማዋ በከተማ አመራር ሥርዓት፣ በአዳጊና ተከታታይ የገቢ አሰባሰብ፣ እንዲሁም ውጤታማ በሆነ የፕሮጀክቶች ፋይናንሲንግ ረገድ ያገኘቻቸው ስኬቶች በፎረሙ ተሳታፊዎች ትኩረት አግኝተዋል።
በተጨማሪም የከተማዋን ገጽታ የቀየሩት የወንዞችና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች፣ እንዲሁም ማኅበራዊ ፋይዳ ያላቸው የቀዳማይ ልጅነት (Early Childhood Development) ፕሮጀክቶች አፈጻጸም “የአዲስ አበባ አዲሱ የከተማ ትራንስፎርሜሽን ሞዴል” ተብለው ተቀምረው ለቀሩት የአፍሪካ ከተሞች በልምድ ተምሳሌትነት ቀርበዋል።
የኢትዮጵያ ልዑክ በፎረሙ ላይ እንደገለጸው፣ አዲስ አበባ ተሞክሮዋን ለሌሎች ከማካፈል ባለፈ፣ በከተማዋ የተጀመረውን ፈጣን ዕድገት ይበልጥ ለማስቀጠል የሚያግዙ አዳዲስ ልምዶችንም እየቀሰመች ይገኛል። በዚህም በተለይ በቤት አቅርቦትና ፋይናንሲንግ እንዲሁም በከተማ ቱሪዝም መዳረሻዎች አስተዳደር ዙሪያ ከሌሎች አገራት ጠቃሚ ተሞክሮዎችን ማግኘት መቻሉ ታውቋል።
ይህ መድረክ አዲስ አበባ በአህጉሪቱ ያላትን የዲፕሎማሲያዊና የከተማ ልማት ሚና ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ይጠበቃል።

👍1
ለበዓላት ግብኣት አለኝታ መሆን የቻለው የከተማ ግብርና!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለከተማ ግብርና ልዩ ትኩረት በመስጠት እና የተቀናጀ የአኗኗር ዘይቤን በመፍጠር በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡
በተለይም በሌማት ትሩፋት ስራ፣ ሰዎች በምግብ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን መመግብ እንዲችሉ፣ በሚኖሩበት አካባቢ እና ባላቸው አነስተኛ ቦታ ለዕለት-ተዕለት የምግብ ፍጆታ የሚውሉ የግብርና ምርቶችን እንዲያመርቱ የግብአት ድጋፍና ክትትል እያደረገ ይገኛል፡፡
በዚህም የእንስሳት ማድለብ፣ የዶሮ እርባታ፣ የወተት ላም እርባታ እና ንብ ማነብን ጨምሮ፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች በስፋት እንዲመረቱ በማድረግ፣ የቤተሰብን ፍላጎት ከማሳካት በሻገር ለገበያ በማቅረብ ብዙዎች ተጨማሪ ገቢ እና የስራ ዕድል እንዲያገኙ ምክንያት ሆኗል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ በተለይም በበዓላት ወቅት ተፈላጊነታቸው የሚጨመሩ እንደ ዶሮ፣ እንቁላል፣ አትክልትና ፍራፍሬ ያሉትን ለተጠቃሚው በቀጥታ እንዲደርስ ለማድረግ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የገቢያ ቦታዎችን በማዘጋጀት ሸማቹና ተገልጋዩ በቀጥታ እንዲገናኙ እያደረገ ይገኛል፡፡
ከዚህ ቀደም፥”ኢትዮጵያ በቤተሰብ ደረጃ በምግብ ራስን መቻል ካረጋገጠች በሀገር ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ጥረት እንደሚሳካ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መግለጻቸው ልብ ይለዋል።

👍2
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
"ማዕድ ማጋራት" የኢትዮጵያዊነት የሞራል ልዕልናና የሰው ተኮር ጉዞ ስኬት
መጋቢት 2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ ማኅበራዊ ምህዳር ውስጥ የተከሰተው ለውጥ፣ ዜጎችን ከችግር አረንቋ ለማውጣት የተወጠነ ትልቅ የተስፋ ብርሃን ይዞ ብቅ ያለ የታሪክ አሻራ ነው። በዚህ ስምንት ዓመት የጉዞ መስመር ውስጥ "ሰው ተኮር" የሚለው መርህ በንድፈ-ሐሳብ ብቻ ሳይታጠር፣ በኑሮ ጫና ለደከሙና ለተጎሳቆሉ ወገኖች የተዘረጋ የፍቅር እጅ ሆኖ ታይቷል። በተለይም በበዓላትና በተለያዩ ወቅታዊ ፈተናዎች ምክንያት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች የሚሰማቸውን የስነ-ልቦና ስብራት ለመጠገን የተወጠነው የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር፣ በኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ ያለውን "የመተሳሰብ" ጥንታዊ እሴት ዳግም እንዲያንሰራራ አድርጓል። ይህ ተግባር መንግሥት ለአገልጋይነትና ለዜጎች ሰብዓዊ ክብር የሰጠውን የላቀ ዋጋ የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ፣ የወንድማማችነትንና የእህትማማችነትን ጥምረት በጽኑ መሠረት ላይ ያቆመ የፍቅር መገለጫ ነው።
ይህ ግዙፍ ሰብዓዊ ንቅናቄ ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ ያስመዘገበው ውጤት በቁጥር ሲሰላ፣ ከመጋቢት 2010 እስከ 2018 አጋማሽ ድረስ በአማካኝ ከ950 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን የለውጡ መንግሥት ለሕዝብ ማህበራዊ ደህንነት ያለውን ቁርጠኝነት ያመለክታል። የችግር ድቅድቅ ጨለማ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ባሉ እናቶችና አባቶች ቤት ውስጥ ሲያንዣብብ፣ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር እንደ ደራሽ ብርሃን በመፈንጠቅ የቤታቸውን ማዕድ ብቻ ሳይሆን የልባቸውን ስብራት ጭምር ጠግኗል። በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች በበዓላት ወቅት የሚሰማቸውን የብቸኝነት ስሜት ወደ የጋራ ደስታ የለወጠው ይህ ተግባር፣ የለውጡ ጉዞ ዋነኛ ፍሬ ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባው የድል አምድ ነው።
በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ያለውን የማይጠፋ የቸርነትና የበጎ ፈቃደኝነት ባህል ዳግም ለቀሰቀሰው ለዚህ ትልቅ ስኬት ከ16.5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ጥቅም ላይ ውሏል። ይህ ሀብት ከበጎ ፈቃደኛ ለጋሾችና ከግል ባለሀብቶች የተገኘ ሲሆን፣ ማኅበረሰቡ ለጋራ ዕድገትና ለመተሳሰብ ያለውን ዝግጁነትና አንድነት በጉልህ ያሳየ ተግባር ነው።
በመጋቢት ወር የተዘራው የመተሳሰብ ዘር ዛሬ ላይ ፈርጥሞና አብቦ ኢትዮጵያ ወደፊት ለምትገነባው ጠንካራ ማኅበራዊ ሥርዓት እንደ ዋስትና የሚያገለግል ነው። ይህ ከገንዘብ በላይ የሆነ የልብ ትስስር፣ ዜጎች በችግር ጊዜ የሚደጋገፉበት፣ በደስታ ጊዜ አብረው የሚፈኩበትና በጋራ የድል ፍሬዎች የሚደምቁበት አዲስ የብሔራዊ አንድነት መገለጫ ሆኖ ይቀጥላል።

ድጋፍ–ለዓቅመ-ደካሞች እና ድጋፍ ለሚሹ ሁሉ!
በአዲስ አበባ፥ በበዓላት ዋዜማ ለዓቅመ-ደካሞች እና ድጋፍ-ለሚሹ ሁሉ የሚደረገው ድጋፍ፣ የከተማዋን የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህል በተግባር የሚያሳይ ትልቅ ማህበራዊ እሴት ነው።
ከተማ አስተዳደሩ፣ ከግብረ-ሰናይ ድርጅቶችና ባለሀብቶች በመቀናጀት፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች፣ አረጋውያንና ወላጅ አልባ ሕፃናት መሰረታዊ የሆኑ የበዓል መዋያ ምርቶችን በነጻ ያጋራል ወይም በታላቅ ቅናሽ ያቀርባሉ።
ይኽም፥ በኢኮኖሚ አቅም ማነስ ምክንያት፣ በዓሉን ማክበር ለሚከብዳቸው ወገኖች ትልቅ ተስፋና እፎይታን እየፈጠረ ሲሆን፤ ድጋፉ በዓሉን በደስታ እና ሳይጎድልባቸው እንዲያከብሩ እያደረገ የሚገኝ፤ የበጎነት ውብ ገፅታዋ እየኾነ ነው ፡፡
“50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ፤ ለ50 ሰው ጌጥ”ነውና አባባሉ፣ በከተማችን አዲስ አበባ መደጋገፍ፣ መተባበር እና መተጋገዝ፥ ድጋፍ ለሚሹ ዓቅመ-ደካሞች ተስፋ፣ የበዓል ፌሽታ መኾን ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡
“በጎነት አያጎድልም”!

❤1