የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የ2017 በጀት ዓመት የቅንጅታዊ ስራዎች አፈፃጸም ግምገማና የእውቅና መርሀ ግብር ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የቅንጅታዊ ስራዎች አፈፃጸም ሪፖርት በመገምገም የላቀ አፈጻፀም ላስመዘገቡ ተቋማት እውቅና ሰጥቷል።
በኅብረተሰብ ተሳትፎና በበጎ ፈቃድ ተግባራት ቅንጅት በመፍጠር ከፍተኛ ውጤት እንዲመዘገብ የተቋማት ሚና የላቀ እንደነበር ኮሚሽነር ይመር ከበደ ተናግረዋል። የአካባቢ ልማት ፕሮጀክቶች፣ የሠላም እሴት ግንባታ ሥራዎች፣ የሞዴል ብሎክ ልማቶች እንዲሁም የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን ተደራሽና ስኬታማ ለማድረግ የተቋማት ቅንጅት አስፈላጊ መሆኑን ያነሱት ኮሚሽነሩ በዚህም ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል።
የኅብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታትና የበጎነት እሴቶችን አጠናክሮ ለመቀጠል የተናበበና የተቀናጀ የጋራ እቅድ ማዘጋጀትና በትብብር መፈፀም ከተቋማት ይጠበቃል ብለዋል ኮሚሽነሩ።
የተቋማት ተወካዮች በበኩላቸው ከኮሚሽኑ ጋር በትብብር ለማከናወን የተለዩ ሰው ተኮርና የኅብረተሰብ ተሳትፎ ስራዎች ውጤማ እንዲሆኑ በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ኮሚሽኑ የ2018 በጀት ዓመት የትስስር መስኮችን በመለየትና ከተቋማት ጋር በመገምገም የቅንጅትና ትብብር ሰነድ ተፈራርሟል።
የዲጂታል ሚዲያ አማራጮቻችን!
1) Facebook: https://www.facebook.com/cpvcc.2015
2) Telegram: https://t.me/CommunityPVC
3) Tiktok: https://www.tiktok.com/@aacpvcc
4) Youtube: https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714?si=RNmSo5FzDi1EkyMD
5) Whatsap: https://whatsapp.com/channel/0029VbBAQRrGOj9kUsLU7A0Z
6) Twiter (x): https://x.com/CommunityPVC?t=PRD3UiV1YfxmafpO9JYIsg&s=09
7) Instagram: https://www.instagram.com/aacpvcc?igsh=MW9lbWNtNG9jZmRrcw==
8) LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/community-participation-voluntarism-coordination
9) Flickr: https://flic.kr/p/2rf6mvb
10) Pinterst: https://pin.it/2sN6xZ86G
11) Imo: https://s.channelcom.tech/XtWqAG?from=copy_link
12) Website: www.aacpvcc.gov.et
13) Email: cpvcc2015@gmail.como
ቤተሰብ ይሁኑ!

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍3
በ2017 በጀት ዓመት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ ስራን ተቋማዊ በማድረግ አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየአመቱ አያሌ ወጣቶች ፣ ሴቶች፣ ጎልማሶች ፣ በተለያዩ የሞያ መስመር ውስጥ ያሉ ዜጎች ፣ ባለሀብቶችና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ያላቸውን በማዋጣት በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አግልግሎቶች ላይ በመሳተፍ ድጋፍ ለሚያሻቸው ዜጎቻችን ደርሰውላቸዋል።
በዚህም በእዉቀት ፣ በጊዜ ፣ በገንዘብ ጉልህ አስተዋፆ በማበርከት ላይ ይገኛሉ ።
የከተማ አስተዳደሩ የተጀመረውን የእውቀት ፣ የገንዘብና የጉልበት አስተዋጽዎችን በማላቅ ድጋፍ የሚሹ ዜጎቻችንን እፎይ ለማሰኘት በጎ ፈቃደኝነትን ተቋማዊ ለማድረግ አበክሮ እየሰራ ይገኛል።
ቅን ልቡናን የተቸሩ በጎ ፈቃደኞች እያደረጉ የሚገኙት ይህ ተግባር እሳቤዉ አሁን ላይ በህብረተሰባችን ዉስጥ ባህልና የኑሮ ዘይቤ ወደመሆን ደረጃ እየተሸጋገረ ይገኛል።
በዘንድሮዉ የበጀት አመት ብቻ 18 ቢሊዮን ብር ያህል የሚተመን ሀብት በእዉቀት፣በጊዜ ፣በአይነት ለከተማችን ማበርከት የቻለ ዘመን ተሻጋሪ ተግባር ሆኗል ።
አሁንም የ90 ቀናት የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎችም ተጠናክረው ቀጥለዋል።
“አገሬ ምን አደረገችልኝ ? ሳይሆን ለአገሬ ምን አደረኩላት ? “ በሚል ቁጭት ወቅቱ የሚዋጀዉን የአርበኝነት ተግባር በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት ለከወናችሁ መላዉ የከተማችን በጎ ፈቃደኞች የከተማ አስተዳደሩ ላቅ ያለ እውቅናና ክብር አለው።

👍4
5 ቀን ቀረው!
ሐምሌ 24 ፣2017 700 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር። እንዘጋጅ!
5 days5 days#PMOEthiopia remaining!
July 31, 2025 #Ethiopia will attempt planting 700 million seedlings in one day. Let’s get ready as the count down begins.
#አረንጓዴዐሻራ
#GreenLegacy
#PMOEthiopia

ከተማችንን የምንሰራት ፣ ጤናማ ትውልድ እንዲገነባ፣ እንዲረከባት እና እንዲያበለፅጋት ነው !
በ2017 በጀት ዓመት ከገነባናቸዉ 28 የጤና ፕሮጀክቶች መካከል 22 ያህሉን በዛሬው እለት አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።
በሁሉም ክፍለ ከተሞች ዛሬ አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት ያደረግናቸው የጤና ጣቢያዎች ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት ጋር እኩል ደረጃ ያላቸው ሲሆን የሚሰጡት አገልግሎት ጥራት ከፍ እንዲል ከ4 ቢልዮን በላይ ወጪ የተደረገባቸዉ በዘመናዊ የህክምና መሳሪያ ግብአት እና ባለሙያዎች ጭምር እንዲደራጁ ተደርገዋል ።
እነዚህም ለከተማችን ነዋሪዎች ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ፤ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎትን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እንዲሁም በቅንነት፣ በትጋት እና በታማኝነት የማገልገል ማሳያችን ናቸው።
ፕሮጀክቶቹ በጥራትና በፍጥነት ተጠናቅቀው ለህዝብ አገልግሎት እንዲበቁ ያደረጋችሁ በሙሉ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም የላቀ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ዓድዋን በደማችን፤ ዓባይን በላባችን!
(ፍቃዱ ከተማ)
ታሪክ በሁለት መልኩ ይፃፋል፤ አንድም በደም ሌላም በላብ፡፡ ታሪክ ሠሪዎቹ ኢትዮጵያውያን እነዚህን ገድሎች በደም ዓድዋ ላይ ፤ በላብ ደግሞ ጉባ ላይ ፈጽመውታል፡፡
የካቲት 23/1833 በሰው ልጆች ታሪክ እስከዚያኔው ያልተፈጸመን አንድ ገድል ኢትዮጵያውያን በደማቸው ጻፉ፡፡ ይኽ ገድል ድሆችና ኋላ ቀሮች ናቸው በሚል ንቀት ኢትዮጵያን በወረረው የፋሺስት ወራሪ ኃይል ላይ ዓድዋ ላይ የተመዘገበ ነበር፡፡ በዚህም ፍትሃዊነትና ሃገር ወዳድነት በተግባር እስካሉ ድረስ ተጨቋኞች ጨቋኞችን፤ ጥቁሮች ነጮችን በሚገባ እንደሚያሸንፉ ለዓለም እስተምረዋል፡፡
በዓድዋ ጦርነት ኢትዮጵያውያን በጊዜው የነበራቸውን የውስጥ ልዩነት ወደ ጐን ትተው ብሔር፣ እምነት፣ ጾታ፣ ዕድሜ፣ ባህል ወዘተ… ሳይለያቸው ደማቸውን በአንድነት አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለጭቁን ሕዝቦችና ለጥቁሮች ኩራት የሆነ ወርቃማ ድል በክብር ጽፈዋል፡፡
ሲተባበሩ ታሪክ መስራት የሚቀላቸው ኢትዮጵያውያን፤ ከዓድዋ ድል ከ129 ዓመታት በኋላ በደም ሳይሆን በላባቸው ዓለምን የሚያስገርምና ኢፍትሃዊነትን የሚሰባብር ድል ጉባ ላይ ደገሙ፤ በታላቁ የዓባይ ግድብ!
ከዓባይ ግድብ ዕውን መሆን በፊት የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያውያን የሚያዩት ግን የማይጠቀሙበት የቁጭት ምንጭ ነበረ፡፡ ለዓባይ የሚዘፈኑ ዘፈኖች ሁሉ ቁጭትንና ሃዘንን የሚያንጸባርቁም ነበሩ፡፡ በደጃፏ የዓባይ ወንዝ ውኃ የሚፈስ ኢትየጵያዊ እናትም የኤሌክትሪክ ኃይል አጥታ ዓይኗ በከሰልና ማገዶ ጭስ እየተጨናበሰ ዘመናትን በችግር ገፍታለች፡፡
ዓባይ በሱዳን በተለይም በግብጽ የኃይል፣ የመስኖ የመዝናኛ ምንጭ ከመሆን አልፎ መጫወቻ ተደርጎ ወደ በረሃ በመውሰድ ውኃው ሲባክን፣ ከ85% በላይ የውኃው አመንጪ የሆነችው ኢትዮጵያ ግን በሴራ በገዛ ሃብቷ እንዳትጠቀም ተደርጋ ኖራለች፡፡
ይኸ እውነታ ግን በ2003 መጋቢት 24 የዓድዋ የመንፈስ ልጆች በሆኑ ኢትዮጽያውያን ላብ ለአንዴና ለመጨረሻ እንዲለወጥ ተወሰነ፡፡ ተወስኖም አልቀረ፤ በማህፀን ካለ ጽንስና በመቃብር ካለ አስክሬን በስተቀር ኢትዮጵያውያን ደመወዛቸውን፣ ጡረታቸውን፣ እንስሳታቸውን ወዘተ… ለግድቡ እውን መሆን አዋጥተው የዘመናት ቁጭትን ወደላቀ ኩራት አሸጋገሩ፡፡ ከቀጥተኛ የመንግሥት በጀት ውጪ በሀገር ውስጥና በውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን የ23 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
በዚህም በዓባይ ወንዝ እንዳንጠቀም አይኤምኤፍ እና ዓለም ባንክን ጨምሮ አበዳሪ ተቋማት ገንዘብ እንዳይሰጡ ለማድረግ ተጋርጦ የነበረው የጅሎች ሴራ በኢትዮጵያውያን ተደረመሰ፡፡
ዛሬ ላይ ኢትዮጵያውያን የግድቡን ሥራ ለፍጻሜ አብቅተው የመስከረም ሙሽራቸውን የዓባይ ግድብን ምረቃ ለማብሰር ድል ያለ ሠርግ እየደገሱ ነው፡፡ በሠርጉም በዓድዋ በደም፤ በዓባይ ደግሞ በላብ ኢትዮጵያውያን አሳምረው ድል ማድረጋቸው ለዓለም ይበሠራል፡፡ ለኢትዮጵያ ብልጽግና መሠረት የመጣሉም ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቃል የሚገባበት ይሆናል!

👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የቅዱስ ፓውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ከ100 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ነጻ የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ገለፀ።
በተያዘው ክረምት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ100 ሺህ በላይ ለሚሆኑና ከፍለው መታከም ለማይችሉ ዜጎች ነጻ ህክምና አገልግሎት የመስጠት ሥራውን በዛሬው እለት መጀመሩን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ገልጿል፡፡
የሜዲካል ኮሌጁ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ጀማል ሺፋ፤ "የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ ሁሌም የሚሰራ ቢሆንም በዚህ ዓመት ከሐምሌ 21 እስከ ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት ሰባት ተከታታይ ቀናት ብቻ በሚሰጠው የነጻ ምርመራ 100 ሺሕ ሰዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተይዟል" ብለዋል፡፡
በ2016 ዓ.ም. ተመሳሳይ ወቅት ከ94 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች የነጻ ሕክምና አገልግሎት እንደተሰጠ አስታውሰው፤ የዘንድሮውን መርሃ-ግብር "በጎ ፈቃደኝነት ለጤናማ ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡
ነጻ ምርመራው በተለይ የካንሰር፣ የጎሮሮ፣ የዓይን እና መሰል ትላልቅ የበሽታ አይነቶችን የነጻ ምርመራ እንደሚያደርጉ ከ50 በላይ የሕክምና መሳሪያዎች ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡
የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ በምርመራ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ለአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ፣ ደም መለሰገስ፣ እና ሌሎችም የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ መሳተፍን እንደሚጨምር አሀዱ ሬድዮ ዘግቧል፡፡

👍6
Join this link to help our channel: https://t.me/reallyzvezdabot?start=_tgr_QIw8vuU5MDg0
👍1
የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግርና የልምድ ልውውጥ መድረከ ተካሔደ።
በዛሬው የኮሚሽኑ የወርቃማ ሰኞ መርሀ ግብር ልምዳቸውን ያካፈሉት የበጎ ፈቃድ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ወይዘሮ አስራት ንጉሴ ናቸው፡፡
በተለየዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ማገልገላቸውን የገለጹት ወይዘሮ አስራት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወገንን ማገልገል የሚሰጠው የሕልና እርካታ የላቀ መሆኑን ገልፀዋል። ምክትል ኮሚሽነሯ በማህበራዊ ትረስት ፈንድ ተቋም የነበራቸው ቆይታ በሕይወታቸው ትልቅ ቦታ የሚሰጡት እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡
በማኅበራዊ ትረስት ፈንድ ጽህፈት ቤት ይተገበሩ የነበሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ከበጎ ፈቃድና ኅብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባባሪያ ኮሚሽን ጋር እንዲዋሀዱ መደረጋቸው ተግባራት ይበልጥ እንዲጠናከሩና ውጤታማ እንዲሆኑ አስተዋዖ እንደሚኖራቸው አብራርተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና በማሻሻል ማኅበራዊ ትረስት ፈንድ ፅህፈት ቤትን ከኮሚሽኑ ጋር እንዲዋሃድ ማድረጉ ይታወሳል።
የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች ለምክትል ኮሚሽነሯ የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

👍2
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በቦሌ ክፍለ ከተማ በክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮግራም ለ5,000 ከፍለው መታከም የማይችሉ ነዋሪዎች ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና አገልግሎት ተጀመረ፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የክረምት በጎ ፍቃድ ነፃ የጤና ምርመራና የሕክምና አገልግሎት ዛሬ አስጀምረዋል። በፕሮግራሙ ላይ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሸቱ ለማ ባደረጉት ንግግር በጎነት በቅንነት የሚከናወን መልካም ሥራ መሆኑን አውስተው፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ በልዩ ልዩ መስኮች እየተከናወኑ ያሉ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን በማገዝና አብሮነትን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አሥራት ንጉሤ በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከሚከናወኑ ተግባራት አንዱ በሆነው የጤና ዘርፍ ክፍለ ከተማው በነፃ ሕክምና እና በደም ልገሣ ሰፊ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው “ዛሬ የተጀመረው የነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና አገልግሎት የጤና ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ትልቅ እድል መሆኑን ተናግረዋል።
በመዲናዋ ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ምክትል ኮሚሽነሯ የተናገሩት። ወ/ሮ አስራት መርሐ ግብሩን ያዘጋጁትን የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደርን እና የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ምስጋና አቅርበዋል።
የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንደ ጤና እና የትምህርት ተቋምነቱ ከመደበኛ ሥራው ጎን ለጎን ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በስፋት እንደሚንቀሳቀስ የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዶ/ር አብዱራዛቅ አሕመድ ገልፀው ሆስፒታሉ ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና አገልግሎት በመስጠት ለወገን ደራሽነቱን በተግባር ማሳየቱን ጠቅሰዋል።
ከሐምሌ 28-30/2017 ዓ.ም ለሶስት ቀባት በሚቆየው በዚህ ነፃ የህክምና አገልግሎት 180 የጤና ባለሙያዎች እንደሚሳተፉ ተመላክቷል።

❤4👍2