ትውልድን መገንባት ቀዳሚው ሥራችን ነው!
ዛሬ የመረቅናቸዉ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች በታማኝነት የማገልገል እና የትጋት ዉጤቶች ናቸዉ።
በእርጅና ብዛት የተጎሳቀሉ ፣ግብአት የያልተሟላላቸዉ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት እንቅፋት የፈጠሩ፣ በሂደትም በተማሪዎቻችን የ12ኛ ክፍል አጠቃላይ ውጤት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የፈጠሩ እና የትምህት ጥራት ያጓደሉ ችግሮችን ቀርፈን በአጭር ጊዜ 6ኛ እና 8ኛ ክፍልን ጨምሮ በ2ኛ ደረጃ የተማሪዎቻችን አበረታች ውጤት አስመዝግበናል ።
የተሻሻሉ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መፃህፍትና ቤተ ሙከራ፣ የህፃናት ማረፊያ፣ ፅዱና አረንጓዴ ቅጥር ጊቢ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ያላቸውን የትምህርት መሰረተ ልማቶች እያስፋፋን እንገኛለን። የተቀናጀና የተናበበ እቅድ በመንደፍ የስራ ባህላችንን በማሻሻል በሰራናቸው ስራዎች ውጤታማ ሆነናል።
በዚህ ስራ በመሳተፍ ትውልዱ ላይ መልካም ዘርን የዘራችሁትን ሁሉ ላመሰግን እወዳለሁ።
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የከተማዋን የትምህርት ተደራሽነት ለማረጋገጥ እና የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል በያዘው እቅድ ባለፉት አምስት ዓመታት 110 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል። በነባር ትምህርት ቤቶች ውስጥ የማስፋፋያ ስራ በመስራትም ከ30 ሺህ በላይ የመማሪያ ክፍሎችን መገንባት እና 334 መመገቢያ አዳራሾች፣ 206 ቤተ ሙከራ እና ቤተመጽሐፍት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ መገንባት ችለናል። እንዲሁም ትምህርት ቤቶች አካታች፣ ምቹ፣ ውብና ንፁህ፣ የደህንነትና የውበት ደረጃን የጠበቀ አጥር መገንባት ተችሏል፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን የባርክ
ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ

👍3
የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን!
ዛሬ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ማካሄድ ጀምረናል።
የ2017 በጀት ዓመት ከመቼውም የበለጠ ስኬት ያስመዘገብንበት ነው ፤ የእቅድ አፈፃፀማችን 95 በመቶ ተሳክቷል።
መዲናችንን ለሀገር ክብር የምትመጥን፣ እንደ ስሟ “ውብ አበባ" ለማድረግ በኮሪደር ልማት፣ በከተማ መልሶ ማልማት እና በወንዞች ዳርቻ ልማት ስራዎች፤ በስራ እድል ፈጠራ እና የገቢ እቅድን በማሳካትና ያገኘነውን ገቢ በቁጠባና ብክነትን በማስወገድ ለዘላቂ ልማትና ድህነት ቅነሳ በማዋል ዙሪያ በተከናወኑ ስራዎች አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግበናል።
በሁሉም ስራዎቻችን ውስጥ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ቀጣይነትን ያረጋገጥንበት፣ የበጀት ጉድለትን በህብረተሰብ ተሳትፎና በጐ አገልግሎት እየሞላን ከህዝብ ጋር ተቀራርበን በመስራት ውጤታማ የሆንበት በጀት ዓመት ነው።
ለነዚህ ሁሉ ስኬቶች አብራችሁን የለፋችሁ፣ ከራሳችሁ በላይ ህዝባችንን ያስቀደማችሁ የከተማችን ነዋሪዎች እና የደከማችሁና ውጤት ያስመዘገባችሁ አመራሮቻችንን እና ሰራተኞቻችንን ከልብ እናመሰግናችኋለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ምቹ መኖሪያ አካባቢ ለመፍጠር እየሰሩ መሆኑን የኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
አዲስ አበባን ለስሟ የሚመጥን ገፅታ አላብሶ እንደ ስሟ ውብ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ወደ ከተማይቱ ጎራ ለሚሉት ደግሞ ሳቢ በማድረግ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን በእቅድ ተይዞ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ። ከነዚህ አበይት ተግባራት መካከል አንዱና ዋነኛው ሞዴል ብሎኮችን መፍጠር ነዉ።
በክፍለ ከተማው ወረዳ 03 አስተዳደር የተቀናጀ ሞዴል ብሎኮችን በመፍጠር ምቹና ውብ አካባቢን እውን ለማድረግ ነዋሪዎችን ያሳተፈ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በወረዳው የረጲ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች እንደሚሉት አካባቢያቸውን ሞዴል ለማድረግ የተሟላ መሰረተ ልማት፣ አስተማማኝ ጥበቃ፣ መናፈሻና መዝናኛ፣ ፅዳትና ውበት እንዲሁም የህጻናት መጫወቻ ሠርተዋል።
ነዋሪዎች ብሎካቸውን በማልማት፣ በማፅዳት፣ በማስዋብና ሠላማዊ በማድረግ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም የተጀመሩ ሞደል ብሎኮችን አጠናክሮ በማስቀጠል ሌሎች ተጨማሪ ምቹ ብሎኮችን ለመፍጠር ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ዘግቧል።
#reelschallengereelschallenge
#housedevelopment
#GreenLegacy

ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለውን አመራር ያሳተፈ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት መካሄዱን ቀጥሏል።
የግምገማ መድረኩ መሰረታዊ ጭብጦች፦
👉የአመራር ውህደት እና ቅንጅት በከተማዋ ለተመዘገቡ እመርታዎች መሰረት መሆኑ፤
👉ከማዕከል እስከ ወረዳ እና ቀጠና ያለው የፓርቲ እና መንግሥት አመራር በቁርጠኝነትና በትጋት በመስራታቸዉ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን፤
👉በተለይም በአመራሩ መካከል ያለው ጤናማ የውድድር መንፈስና የላቀ የስራ ተነሳሽነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን፤
👉በማህበራዊ ጉዳዮች በተለይም በትምህርት እና ጤና ዘርፎች ከፍተኛ ውጤቶች መኖራቸውን፤
👉ከኢኮኖሚ አኳያ በርካታ ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል በመፍጠር የሴቶችና ወጣቶች ተጠቃሚነትን በስፋት ማሳደግ መቻሉን
👉አምራችና ሸማችን በቀጥታ ማገናኘት የሚያስችሉ የገበያ ማዕከላትን በመገንባት አገልግሎት ውስጥ ማስገባት በመቻሉ የገበያ ትስስርን በማሳለጥ የህዝባችንን የኑሮ ጫና ማቅለል መቻሉ፤
👉ከፍተኛ የገቢ አሰባሰብ አቅም በመፍጠርና ከተሰበሰበዉ አጠቃላይ ገቢ 71%ቱን ለዘላቂ ልማቶችና የድህነት ቅነሳ ተግባራት በማዋል የህዝባችንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉ፤
👉የኮሪደር ልማቱ የፈጠረው የከተማ ውበት፣ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ፍሰት፣ የማኑፋክቸሪግ ዘርፉ መነቃቃት፣
👉የከተማዋን ሰላምና ደህንነት በመንግሥትና በህዝብ ትብብር እውን በማድረግ አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ምቹ ፣ ሰላማዊ እና ለጎብኚዎቿ ምርጥ መዳረሻ መሆን መቻሏ፤
የከተማዉ ነዋሪ ከመቼውም ጊዜ በላቀ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የአካባቢ የልማት ስራዎችን በመስራት ይበልጥ ተጠቃሚ እየሆነ መምጣቱ ወዘተ በግምገማ መድረኩ የተነሱ ዋነኛ የትኩረት ማዕከላት ሆነዉ ቀጥለዋል ።

የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በተያዘው የክረምት በጎ ፈቃድ 90 ቀናት ንቅናቄ ከበጎ ፈቃደኞች 60 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታወቀ፡፡
በተያዘው የክረምት በጎ ፈቃድ የ90 ቀናት ንቅናቄ 60 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ከአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመተባበር ትላንት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገ የደም ልገሳ መርሀ ግብር ከ1 ሺህ 1 መቶ በላይ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ደም እንዲለግሱ አድርጓል፡፡
በከተማ ደረጃ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለያዩ ሁነቶች እንደቀጠለ ይገኛል፡፡ በሻምበል አበበ ቢቂላ ስታዲየም የአዲስ አበባ በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመተባበር ከ1 ሺህ 1 መቶ በላይ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች የመርሃ ግብሩ አካል የሆነ የደም ልገሳ አካሂደዋል።
በዚህም ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች እንዲሳተፉ መደረጉ ነው የተመላከተው፡፡
በዚህ የክረምት የ90 ቀን በጎ ፈቃድ ንቅናቄም ከ60 ሺህ ዩኒት በላይ ደም ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝና እስካሁንም ድረስ ከ20 ሺህ ዩኒት በላይ ደም እንደተሰበሰበ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይመር ከበደ ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸው አባላቱ ህግ ከማስከበር በተጨማሪ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ በፈቃደኝነት ደም ልገሳ እና ሌሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ላይ በነቂስ እየተሳተፉ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ተመሳሳይ የደም ልገሳዎችም ቢያንስ በየሶስት ወሩ በማካሄድ የማህበረሰቡ አለኝታ መሆናቸዉንም ለማሳየት በትጋት እንደሚሰሩ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡
#AMN

የበጎ ፈቃድ ተግባር መደጋገፍንና አብሮነትን የሚያጎለብት በመሆኑ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ በጎ ፈቃደኞች ተናገሩ።
የበጎ ፈቃድ ተግባር መደጋገፍንና አብሮነትን የሚያጎለብት በመሆኑ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ በጎ ፈቃደኞች ተናግረዋል፡፡
በበጎ ፈቃደኝነት ሰዎችን መርዳት የህሊና እርካታ የሚሰጥ፤ መደጋገፍን እና አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን የተናገሩት በጎ ፍቃደኞቹ በአሁኑ ወቅት በትራፊክ አገልግሎት፤ በቤት ግንባታ እንዲሁም በሆስፒታል ተሰማርተዋል።
ከበጎ ፈቃደኞች መካከል በትራፊክ ማስተባበር አገልግሎት ላይ የተሰማራው ከድር ሰኢድ እንደሚለው፤ የበጎ ፈቃድ ስራ በራስ ተነሳሽነት የሚከናወን መልካም ተግባር መሆኑን አንስቶ፤ ለሰዎች መልካም በማድረግ በርካታ ጥቅሞችን እንዳገኘ ተናግሯል፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከሁሉም ማኅበረሰብ ጋር ተግባብቶ በአብሮነት የመኖር ልምድን የሚያሳድግ መሆኑን ጠቅሶ፤ አገልግሎቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
ሌላኛው የትራፊክ አስተባባሪ በጎ ፈቃደኛ አህመድ ሁሴን፤ የበጎ ፈቃድ ስራ የሚያስደስት መሆኑን በማንሳት፤ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በበጎ ፈቃድ ስራ ሰዎችን በማገልገል እንደሚቀጥል ነው የተናገረው፡፡
በሆስፒታል አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት ወጣቶቹ በበኩላቸው ህሙማንን ከመንከባከብ ባለፈ የተለያዩ የበጎነት ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ በተለይም ታካሚዎች ወደ ሆስፒታል ሲመጡ ስለሚፈልጉት አገልግሎት መረጃ በመስጠትና ቦታ በማመላከት እንዲሁም በመንከባከብ በጎነትን በተግባር እየገለጠ መሆኑን የተናገረው ያሬድ ታደሰ ነው።
በጎ ፈቃደኛ ተስፋየ ነጋሽ በበኩሉ ፅኑ ህመማንን ወደ ህክምና ክፍል በማድረስ፤ የህክምና ካርድ በማውጣትና ሌሎች የሚያጋጥማቸውን ተግዳሮቶች እንዲፈታላቸው የመርዳት ተግባር እያከናወነ መሆኑን አስረድቷል፡፡
በቤት ግንባታና እድሳት አገልግሎት የተሰማራችው ብሩክታዊት ዮሴፍ እንዳለቸው፤ የበጎ ፈቃድ ተግባር ህዝብን ያለልዩነት ለማገልገል እድል የሚፈጥር ትልቅ ተግባር መሆኑን ተናግራለች።
የበጎ ፈቃደኝነት ተግባር ያለገደብ እና መስፈርት ለሰብዓዊነት የሚከናወን መሆኑን ገልጻ፤ በተለይም አቅመ ደካሞችን በማገዟና የቤት ግንባታና እድሳት በማድረጓ ትልቅ የህሊና እርካታ እንደሰጣት ተናግራለች።
"በጎ ፈቃደኝነት፣ ለማኅበረሰብ ለውጥ!"
#Ethiopian_News_Agency
#Ethiopia

❤2
እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በከተማ ደረጃ በተካሄደው የ2017 ዓ.ም የምዘና ውጤት የላቀ አፈፃጸም በማስመዝገብ ከፍተኛ ደረጃ ከያዙ ተቋማት አንዱ በመሆኑ አረንጓዴ ሰርተፍኬት ተሸልሟል።
ኮሚሽኑ ለዚህ ውጤት መሳካት ድርሻ ለነበራችሁ በየደረጃው ለምትገኙ የኮሚሽኑ የስራ ኃላፊዎች፣ ሰራተኞች፣ በጎ ፈቃደኞች፣ የካውንስል አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ከፍ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል!

❤8
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ሙሉ በሙሉ በራስ አቅም በመንግስትና ህዝብ የተገነባ ነው
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መቶ በመቶ በራስ አቅም በመንግስትና ህዝብ የተገነባ ነው አለ የግድቡ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት፡፡
ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው፥ በበጀት ዓመቱ ለግድቡ 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል፡፡
በበጀት አመቱ የተሰበሰበው ገንዘብ ከዕቅዱ የ7 በመቶ ብልጫ እንዳለው የጽህፈት ቤቱ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍቅርተ ታምር በመግለጫው ላይ ጠቅሰዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን በሞራል፣ በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በዕውቀት፣ በፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና በአካባቢ ጥበቃ በመረባረብ የተመዘገበው ስኬት በትውልድ የሚዘከር ህያው ድል ነው ብለዋል፡፡
ግንባታው ከተጀመረበት ግዜ ጀምሮ በቦንድ ግዥና በስጦታ በሀገር ውስጥ 20 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር እንዲሁም ከዳያስፖራው ማህበረሰብ 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰብ ተችሏል፡፡
በተጨማሪም ከልዩ ልዩ ገቢዎች 1.7 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የገለጹት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፥ በአጠቃላይ እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ከህብረተሰቡ ከ23 ነጥብ 6 ቢሊየን በላይ ብር ተሰብስቦ ለግድቡ ግንባታ ውሏል ነው ያሉት።
እንደዚሁም በጠቅላላው የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት አንስቶ ከ84 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የጉልበትና የተፋሰስ ሥራዎች መሰራቱም በመግለጫው ላይ ተነስቷል።

👍3❤1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የ2017 በጀት ዓመት የቅንጅታዊ ስራዎች አፈፃጸም ግምገማና የእውቅና መርሀ ግብር ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የቅንጅታዊ ስራዎች አፈፃጸም ሪፖርት በመገምገም የላቀ አፈጻፀም ላስመዘገቡ ተቋማት እውቅና ሰጥቷል።
በኅብረተሰብ ተሳትፎና በበጎ ፈቃድ ተግባራት ቅንጅት በመፍጠር ከፍተኛ ውጤት እንዲመዘገብ የተቋማት ሚና የላቀ እንደነበር ኮሚሽነር ይመር ከበደ ተናግረዋል። የአካባቢ ልማት ፕሮጀክቶች፣ የሠላም እሴት ግንባታ ሥራዎች፣ የሞዴል ብሎክ ልማቶች እንዲሁም የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን ተደራሽና ስኬታማ ለማድረግ የተቋማት ቅንጅት አስፈላጊ መሆኑን ያነሱት ኮሚሽነሩ በዚህም ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል።
የኅብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታትና የበጎነት እሴቶችን አጠናክሮ ለመቀጠል የተናበበና የተቀናጀ የጋራ እቅድ ማዘጋጀትና በትብብር መፈፀም ከተቋማት ይጠበቃል ብለዋል ኮሚሽነሩ።
የተቋማት ተወካዮች በበኩላቸው ከኮሚሽኑ ጋር በትብብር ለማከናወን የተለዩ ሰው ተኮርና የኅብረተሰብ ተሳትፎ ስራዎች ውጤማ እንዲሆኑ በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ኮሚሽኑ የ2018 በጀት ዓመት የትስስር መስኮችን በመለየትና ከተቋማት ጋር በመገምገም የቅንጅትና ትብብር ሰነድ ተፈራርሟል።
የዲጂታል ሚዲያ አማራጮቻችን!
1) Facebook: https://www.facebook.com/cpvcc.2015
2) Telegram: https://t.me/CommunityPVC
3) Tiktok: https://www.tiktok.com/@aacpvcc
4) Youtube: https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714?si=RNmSo5FzDi1EkyMD
5) Whatsap: https://whatsapp.com/channel/0029VbBAQRrGOj9kUsLU7A0Z
6) Twiter (x): https://x.com/CommunityPVC?t=PRD3UiV1YfxmafpO9JYIsg&s=09
7) Instagram: https://www.instagram.com/aacpvcc?igsh=MW9lbWNtNG9jZmRrcw==
8) LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/community-participation-voluntarism-coordination
9) Flickr: https://flic.kr/p/2rf6mvb
10) Pinterst: https://pin.it/2sN6xZ86G
11) Imo: https://s.channelcom.tech/XtWqAG?from=copy_link
12) Website: www.aacpvcc.gov.et
13) Email: cpvcc2015@gmail.como
ቤተሰብ ይሁኑ!

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍3
በ2017 በጀት ዓመት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ ስራን ተቋማዊ በማድረግ አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየአመቱ አያሌ ወጣቶች ፣ ሴቶች፣ ጎልማሶች ፣ በተለያዩ የሞያ መስመር ውስጥ ያሉ ዜጎች ፣ ባለሀብቶችና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ያላቸውን በማዋጣት በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አግልግሎቶች ላይ በመሳተፍ ድጋፍ ለሚያሻቸው ዜጎቻችን ደርሰውላቸዋል።
በዚህም በእዉቀት ፣ በጊዜ ፣ በገንዘብ ጉልህ አስተዋፆ በማበርከት ላይ ይገኛሉ ።
የከተማ አስተዳደሩ የተጀመረውን የእውቀት ፣ የገንዘብና የጉልበት አስተዋጽዎችን በማላቅ ድጋፍ የሚሹ ዜጎቻችንን እፎይ ለማሰኘት በጎ ፈቃደኝነትን ተቋማዊ ለማድረግ አበክሮ እየሰራ ይገኛል።
ቅን ልቡናን የተቸሩ በጎ ፈቃደኞች እያደረጉ የሚገኙት ይህ ተግባር እሳቤዉ አሁን ላይ በህብረተሰባችን ዉስጥ ባህልና የኑሮ ዘይቤ ወደመሆን ደረጃ እየተሸጋገረ ይገኛል።
በዘንድሮዉ የበጀት አመት ብቻ 18 ቢሊዮን ብር ያህል የሚተመን ሀብት በእዉቀት፣በጊዜ ፣በአይነት ለከተማችን ማበርከት የቻለ ዘመን ተሻጋሪ ተግባር ሆኗል ።
አሁንም የ90 ቀናት የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎችም ተጠናክረው ቀጥለዋል።
“አገሬ ምን አደረገችልኝ ? ሳይሆን ለአገሬ ምን አደረኩላት ? “ በሚል ቁጭት ወቅቱ የሚዋጀዉን የአርበኝነት ተግባር በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት ለከወናችሁ መላዉ የከተማችን በጎ ፈቃደኞች የከተማ አስተዳደሩ ላቅ ያለ እውቅናና ክብር አለው።

👍4
5 ቀን ቀረው!
ሐምሌ 24 ፣2017 700 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር። እንዘጋጅ!
5 days5 days#PMOEthiopia remaining!
July 31, 2025 #Ethiopia will attempt planting 700 million seedlings in one day. Let’s get ready as the count down begins.
#አረንጓዴዐሻራ
#GreenLegacy
#PMOEthiopia

ከተማችንን የምንሰራት ፣ ጤናማ ትውልድ እንዲገነባ፣ እንዲረከባት እና እንዲያበለፅጋት ነው !
በ2017 በጀት ዓመት ከገነባናቸዉ 28 የጤና ፕሮጀክቶች መካከል 22 ያህሉን በዛሬው እለት አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።
በሁሉም ክፍለ ከተሞች ዛሬ አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት ያደረግናቸው የጤና ጣቢያዎች ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት ጋር እኩል ደረጃ ያላቸው ሲሆን የሚሰጡት አገልግሎት ጥራት ከፍ እንዲል ከ4 ቢልዮን በላይ ወጪ የተደረገባቸዉ በዘመናዊ የህክምና መሳሪያ ግብአት እና ባለሙያዎች ጭምር እንዲደራጁ ተደርገዋል ።
እነዚህም ለከተማችን ነዋሪዎች ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ፤ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎትን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እንዲሁም በቅንነት፣ በትጋት እና በታማኝነት የማገልገል ማሳያችን ናቸው።
ፕሮጀክቶቹ በጥራትና በፍጥነት ተጠናቅቀው ለህዝብ አገልግሎት እንዲበቁ ያደረጋችሁ በሙሉ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም የላቀ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።