የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
826 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የተቋም ግንባታና አገልግሎነት አሰጣጥ በተመለከተ

👉በተቋማት ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር ከ2 ሽህ 147 በላይ የመንግስት ሰራተኞች በህጻናት ማቆያ ልጆቻቸውን እንዲከባከቡ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል።

👉በተቋማት ከ185 በላይ የመንግስት ሰራተኞች ካፍቴሪያዎችን በመገንባት እና አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ እንዲሁም ከ150 የሸማች ሱቆችን ወደ ስራ በማስገባት ሰራተኞ የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋም የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።

👉ከ21 ሽህ 046 የተገልጋይ ማረፊያ በማዘጋጀት ምቹ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ተገንብተዋል።

👉በተቋማት 347 አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ብልሹ አሰራር፣የተገልጋይ እንግልትና ምልልስ በማስቀረት የሚቀርቡ ቅሬታዎች እንዲቀንሱ አድርጓል።

👉በሌብነትና ብልሹ አሰራር ተግባር ውስጥ የገቡ 4 ሽህ 965 አመራሮች፣ ፈጻሚዎች እና ተገልጋዩችን ተጠያቂ በማድረግ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃዎች ተወስዷል።
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በበጀት ዓመቱ የትምህርት ዘርፍ በተመለከተ

👉የትምህርት ዘርፉ ዋና ትኩረት የነበረውን የትምህርት ተሣትፎና ፍትሐዊነት በማሳደግ በዕውቀትና በሥነ- ምግባር የታነፀ ትውልድን ለማፍራት በተሻሻለው ስርአተ ትምህርት መሰረት

👉በበጀት ዓመቱ የትምህርት አጠቃላይ ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ቅበላ ሥራችንን ከ1,159,684  ወደ 1,184,326 ለማድረስ ታቅዶ ክንውን 1,253,737 (105.86%) ማድረስ መቻሉ፤ይህም  ከ 2016 የትምህርት ቅበላ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 98,129 ዕድገት አሳይቷል፡፡

👉የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማስፈን በተደረገው ጥረትም በሁሉም ት/ቤቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት የተማሪዎችን ቁጥር ከ 33,203 ወደ 33,604 ለማድረስ ታቅዶ 34,015 (101.22%) ማድረስ ተችሏል፡፡

👉ትምህርት ቤቶች ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች አመቺ እንዲሆኑ ለማድረግ የተማሪ መማሪያና የመምህሩ መምሪያ መፅሃፍትን በድምፅ በመቅረፅና አዘጋጅቶ በማሰራጨት 10,294 የዕይታ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች ተጠቃሚ በማድረግ ውጤታቸው እንዲሻሻል አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡

👉የት/ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል በሶስተኛው ዙር “ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ በተሰራው ሥራ  በገንዘብ፤ በጉልበትና በዕውቀት በአጠቃላይ ከ 4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት በማሰባሰብ የት/ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል ለመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ተችሏል፡፡

👉ትውልድ ላይ ኢንቨስት እናድርግ በሚለው የመንግስት አቅጣጫ መሰረት በተማሪዎች ምገባ 840,585 በላይ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ እንዲመገቡ የተደረገ ሲሆን የተማሪ ዩኒፎርም፣ የትምህርት ቁሳቁስ እና የመምህራን ጋዋን ጨምሮ እንዲደርሳቸው ከማድረግ በተጨማሪ የተማሪ ውጤት ለማሻሻል እየሰራን ያለዉ ስራ ከፍተኛ ውጤት እያመጣ ይገኛል፡፡

👉በ2017 ትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና 50% በላይ በማምጣት ወደ ቀጣይ ክፍል የተሸጋገሩ ተማሪዎችን ከነበረበት 94.3% ወደ 95% ለማድረስ ታቅዶ 95% (100% ) ማድረስ የተቻለ ሲሆን በተመሳሳይ የ8ኛ ክፍል ከተማ ዓቀፍ ፈተና ውጤት  ከነበረበት 79% ወደ  82% ለማድረስ ታቅዶ 88.8% (108.3) ማድረስ ተችሏል፡፡
👏1
ቀዳማይ ልጅነትን ልማት ፕሮግራምን በተመለከተ

👉ፐሮግራሙ የከተማችንን 1.3 ሚሊዮን ህጻናትን በተለይ ደግሞ 330‚000 አነስተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰብ የተገኙ ህጻናት ለመድረስ ያለሙ አምስት አንኳር ኢኒሼቲቮሽን አቅደን ስንተገብር ቆይተናል።

👉ከተቀመጡት ግቦች አንጻር የወላጆችን እና አሳዳጊዎች የምክር እና የሙያ አገልግሎት የሚሰጡ 5‚000 ሰራተኞችን በማሰማራት በ 4‚979 የመኖሪያ ብሎኮች ለሚገኙ ለ 487,544 ወላጆች/አሳዳጊዎች በየአስራ አምስት ቀኑ የቤት ለቤት የምክር አገልግሎት ተሰጥቷል።

👉ለ11,900 አነስተኛ ገቢ ላላቸው እና ለድገት ውስኑነት ተጋላጭ የሆኑ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም ከ 3 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት የቀጥታ አልሚ ምግብ ድጋፍ በየወሩ ተሰጥቷል።

👉ስራውን አጠናክሮ ለመቀጠል በዚህ በጀት አመትም ከ 5ዐዐ ሚሊየን በላይ በጀት ለአልሚ ምግብ በጅተናል፡፡

👉እድሜያቸው ከ 0 እስከ 3 ዓመት የሆኑ እና በኢኮኖሚ ሁኔታቸው ለዕድገት ውሱንነት ተጋላጭ የሆኑ ህጻናት የዕድገት ሁኔታ ፕሮግራሙ በተጀመረበት ወቅት ከነበረበት 66.9% ወደ 73.1% በማደግ የ 6.2 በመቶ መሻሻል አሳይቷል።

👉በጨዋታ መልክ በማስተማር በቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ይታይ የነበረው የትምህርት ዝግጁነት ምጣኔም ከነበረበት ዝቅተኛ ደረጃ ወደ 89.03% ከፍ በማለት የልጆች ሁለንተናዊ ዕድገት ማረጋገጥ ችለናል፡፡
የፍትህ ሥርዓትና የሕግ የበላይነትን ማስከበር በተመለከተ

👉በፍትህ ሥርዓታችን የሕግ የበላይነትን በማስከበር የሰብዓዊ መብት አያያዝ እንዲጎለብት ለማድረግ በፍትሐብሔር ጉዳዮች የከተማ አስተዳደሩንና የነዋሪውን መብትና ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር ክርክር በፍ/ቤት የመርታት አቅም 96.05 % ማድረስ ታቅዶ በፍርድ ቤት ክርክር የቀረቡ 6,379 መዝገቦች፣ በፍ/ቤት ውሳኔ ካገኙ 3,963 መዝገቦች 3,683 ለአስተዳደሩ ማስወሰን በመቻሉ አፈፃፀሙ 96.8% ደርሷል፡፡

👉የመንግስት እና ሕዝብ መብትና ጥቅም በማስከበርም በገንዘብ 5,608,175,281.16 ብር ሆኖ በአይነት ደግሞ 272 ቤቶች፣ 64 ሼዶች እንዲሁም 260.32 ሄክታር መሬት ማስከበር መቻሉ፤ምርመራ ከተጠናቀቀ 12,828 የግል አቤቱታ የወንጀል ምርመራ መዝገቦች ውስጥ 88% በእርቅ ለመጨረስ ታቅዶ 9,822 መዛግብት በፖሊስና በዐቃብያን ሕግ፣ 1,048 መዛግብት በፍርድ ቤት በአጠቃላይ 10,870 ክንውኑ 84.7% ሲሆን አፈፃፀሙ 96.2% ነው፡፡
2
በበጀት ዓመቱ ቱሪዝምን በተመለከተ

👉1ሚሊዮን የውጪ ሀገር ቱሪስቶች ከተማችንን እንዲጎበኙ በማድረግ፣ከ15ዐ በላይ ኮንፍረንሶች፣ እግዚቢሽኖችና ኤክስፖዎች በማካሄድ ከ143 ቢሊየን በላይ ገቢ ተሰብስቧል፡፡

👉ከ9 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች ከ56 ነጥብ 6 ቢሊዮን በላይ የሚሆን ገቢ ወደ መዲናችን ኢኮኖሚ ፈሰስ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
የድህነት ቅነሳና ስራ እድል ፈጠራን በተመለከተ
👉በከተማችን ለሚገኙ ለ366,044 ስራ ፈላጊዎች ቋሚ የስራ እድል መፍጠር ተችሏል፡፡

👉በከተማ ግብርና ዘርፍ 40,230 በኢንዱስትሪ ዘርፍ 91,737 እና በአገልግሎት ዘርፍ 234,077

👉ለሴቶች የስራ እድል ፈጠራ 201,309
👉ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ 290,360 ምሩቃን 52,866 የስራ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል።

👉ተረጂነትን በማስቀረት ምርታማነት ለማሳደግ የልማታዊ ሴፍትኔት ሦስት ዓመት የሆናቸው የሁለተኛ ምእራፍ ተጠቃሚዎች የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግና ስልጠና በመስጠት 31,002 የቤተሰብ ተወካዮች በማስመረቅ የራሳቸውን ገቢ የሚፈጥሩበት ቌሚ የስራ መስክ ማስገባት ችለናል፡፡

👉በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ምክንያት የሚጎዳ የህብረተሰብ ክፍል እንዳይኖር 130,135 በላይ በዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የከተማችን ነዋሪዎችን ለቀጣይ ሶስት ዓመት የሚደግፍ ስራ በበጀት ዓመቱ አስጀምረናል፡፡

👉የቁጠባ ባህልን ለማሳደግ በተሰሩ ስራዎች 27,293 ኢንተርፕራይዞች 5,132,495,487 ብር ቁጠባ እንዲቆጥቡ ተደርጓል፡፡
👉 ለኢንተርፕራይዞች ብድር በማመቻቸት 3,559,287,049 ብር ማበደር ተችሏል፡፡
2
በበጀት ዓመቱ የተጠናቀቁ የፕሮጀክቶችን አስመልክቶ

የሕዝባችንን የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎችን ከመመለስ አንጻር በመንግስትና በህብረተሰብ ተሣትፎ 15‚69ዐ ግንባታዎችን ማጠናቀቅ የተቻለ ሲሆን፤ ካቀድነው በላይ ማከናወን ተችሏል፡፡

👉 205 በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰሩ የተለያዩ ኘሮጀክቶች
👉 8,786 በበጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር ለአቅመ ደካሞች የተገነቡ ቤቶች
👉 5,176 በከተማ አስተዳደር የተገነቡ ቤቶች
👉 1064 የመስሪያ ሼዶች
👉 5,563 ሱቆች / ካዛንቺስ፣ ቦሌ፣ ላፍቶ፣ ልደታ፣ አራዳ እና አራት ኪሎ ሽሮሜዳ/ የተገነቡ
👉 1,155 የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች
👉 122 የእስፖርት ማዘወተሪያ ሜዳዎች
👉 245 የአረንጓዴ ልማት ስራ
👉 153 የመኪና ፓርኪንጎችና ተርሚናሎች
👉ከዚህ ውስጥ 16 ቱ ሜጋ ኘሮጀክቶች ሲሆኑ ወደ 9ሺ ኘሮጀክቶች በህብረተሰብ ተሳትፎና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰሩ ናቸው፡፡
በበጀት ዓምእቱ የኑሮ ውድነት ቅነሳን በተመለከተ

👉በከተማዋ አምራቾች ምርታቸውን በቀጥታ በገበያ በማዕከላት እንዲያቀርቡ በተፈጠረው እደል 3.5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንዲቀርብ ተደርጓል።

👉የቅዳሜና እሁድ የገበያ ቦታዎችን በማስፋት ከ193 ወደ 219 በማሳደግ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ይገኛል፡፡

👉በድጎማ ከሚቀርቡ ምርቶች የስኳር ምርት 305,295 ኩንታል፤ የምግብ ዘይት 4,382,179 ሊትር በትስስር ማሰራጨት ተችሏል።

👉በትራንስፖርት፣በጤና መድን፣ በዳቦ አቅርቦት፣ በምገባና በምርት አቅርቦት ከ14 ቢሊዬን ብር በላይ በመደጐም የነዋሪዎቻችን የኑሮ ጫናን የማቅለል ስራ ተሰርቷል፡፡

👉የዳቦ አቅርቦትን ለመጨመር በመንግስትና በግል ባለሀብቶች የጋራ ጥምረት በተሰራው ሥራ የሸገር ዳቦና ብረሃን ዳቦ ፋብሪካ ውደ ስራ በማስገባት፤በአጠቃላይ በ26 ዳቦ ፋብሪካዎች በሚሊዮኖች ዳቦ በማምረት የነዋሪውን ኑሮ ለመደገፍ ጥረት ተደርጓል።

👉በ26 የምገባ ማእከልላት በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ማግኘት ችግር ላለባቸው 36ሺ ሰዎችን በምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
በበጀት ዓመቱ አምራች ኢንዱስትሪውን በተመለከተ

👉የምርት ጥራት፣ ምርትና ምርታማነታቸውን ከማሳደግ አንፃር ለ566 አምራች ኢንዱስትሪዎች 4,235 ማሽነሪ መሳሪያ እና በብር ደግሞ 1,860,822,877 በማቅረብ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
🥰2
ገቢን በተመለከተ
👉በመዲናዋ ከ241.46 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ233 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 96.5% በመቶ መፈፀም የተቻለ ሲሆን ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 83.3 ቢሊዮን ብር ወይም 57% እድገት አሳይቷል::

👉ባለፉት 11 ወራት ደረሰኝ ባለመስጠት በድምሩ 11,283 ያህል የተቀመጡ የግብይትና የታክስ ህጎችን ያላከበሩ ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡

👉በገቢ አሰባሰቡ ሂደት ላይ በሌብነትና ብልሹ አሰራር በተለዩ 247 ሰራተኞች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡
2