የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
827 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
605 ሚሊዮን ብር የሚገመት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በለሚኩራ ክፍለ ከተማ

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ" በሚል መሪ ቃል ከ300 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች የሚሳተፉበት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀመረ።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሪት ወይንሸት አስናቀ የብልጽግና መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ሰው ተኮር ተግባራትን ማካሄዱንና እርስ በርስ በመደጋገፍ የእህትማማችነትና የወንድማማችነት ስሜትን ለመፍጠር ብዙ ጥረቶችን ማድረጉን ጠቅሰው በቀጣይም ሰፋፊ የሰው ተኮር ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

የክፍለ ከተማው የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ገ/ጊዮርጊስ በበጋው መርሃ ግብር በርካታ የበጎ ፈቃድ ስራዎች በስኬት መጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል።

ከሰኔ/2017 ጀምሮ እስከ መስከረም 30/ 2018 በሚቆየው የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር ከ300 ሺ በላይ በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ በ18 የበጎ ፈቃድ ዘርፎች 77 ሺ ዜጎችን ተጠቃሚ በማድረግ መንግስት ሊያወጣው የሚችለውን ከ605 ሚሊዮን በላይ ብር ለማዳን መታቀዱ ኃላፊው መናገራቸውን የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ዘገባ ያስረዳል።

#volunteersmakeadifference
#addisababa
#vol@CommunityPVC
1👍1
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በልደታ ክፍለ ከተማ!

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን በተለያዩ መርሃ ግብሮች አስጀምሯል።

መርሃ ግብሩ በይፋ መከፈቱን ያበሰሩት የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሓፍቱ ብርሃኑ ለሰው ተኮር ተግባሮቻችን ስኬት የባለሀብቶችና የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው ምስጋናቸው አቅርበዋል። በመጭው የክረምት ወቅት በተቀረፁ ሁሉም ሰው ተኪር መርሃ ግብሮች ተሳትፎን ማጠናከርና የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ነው ኃላፊው ያሳሰቡት።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመዳጋገፍ ባህል ከምንጊዜውም በላይ ጎልቶ የታየበት ተግባር መሆኑን የተናገሩት የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ነፃነት ደረሰ የክረምቱ መርሃ ግብር ውጤታማ እንዲሆን ከህብረተሰቡ፣ ከባላሀብቶች እና ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የላቀ ተሳትፎና ድጋፍ እንጠብቃለን ብለዋል።

የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንግዳው ጓዴ በበኩላቸው በ2017 ዓ.ም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በልማት በሰላምና ፀጥታ አጠባበቅ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርትና በቀጣይ ክረምት የሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ ስራዎች እቅድ ያቀረቡ ሲሆን ለእቅዱ መሳካት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።

መርሀ ግብሩ በአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታና በደም ልገሳ ስነ-ሥርዓት መከፈቱን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመልክታል።

#volunteersmakeadifference
#vol@CommunityPVC
1👍1
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ "በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!" በሚል መሪ ቃል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን ከፈተ።

በብልጽግና ፓርቲ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ጥላሁን መርሃ ግብሩ ሲከፍቱ ሰው ተኮር ተግባሮቻችን መሳካት የባለሀብቶችና የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ድርሻ ትልቅ መሆኑን ገልፀዋል። ኃላፊው በመጭው የክረምት ወቅት የተያያዘው ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆንም የነዋሪዎችና የአስተዳደሩ የጋራ ርብብር አስፈላጊ በመሆኑ በቁርጠኝነት መሳተፍ ይገባል ብለዋል።

የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው በበኩላቸው ባለሀብቶች፣ ወጣቶችና ተቋማት ባዳረጉት የተቀናጀ ስራ ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለሁ ጠቁመው በተያዘው የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም ስኬት ለማምጣት ለመሆን ሁሉም የተለመደ ትብብርና ተሳትፎውን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል ሲል የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

የመክፈቻ መርሃግብሩ በጉድጓድ ዝግጅት፣ በቤት ግንባታና በፎቶ አውደ ርዕይ መካሄዱ ተመላክቷል።

#volunteersmakeadifference
#volu@CommunityPVC
👍1
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮግራሞችን በነፃ ህክምና በደም ልገሳ አስጀምሯል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "በጎ ፈቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ!" በሚል መሪ ሃሳብ የ2017 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራሞችን በደም ልገሳና በነፃ የህክምና አገልግሎት አስጀምሯል።

መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አዲሱ ሻንቆ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ዜጎች ውስጣቸው ከሚሰማቸው ሰብዓዊ አመለካከት ተነስተው የሚከውኑት መልካም ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።

በጎ ፈቃደኞች በክፍለ ከተማው በበጋ ወቅት በተከናወኑ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጋቸውን የገለፁት ዋና ስራ አስፈጻሚው በአስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበውላቸዋል።

በበጋ በጎ ፈቃድ 45 ሺ 987 ፈቃደኞችን በማስተባበር የአቅመ ደካሞችን ቤት መገንባት መቻሉን የገለጹት የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም አባስ በሌሎች የበጎ ፍቃድ ተግባራትም ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ጠቁመዋል ሲል የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በከተማ ደረጃ ባለፈው ሳምንት በ15 ፕሮግራሞች በከንቲባ አዳነች አቤቤ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

#volunteersmakeadifference
#voou@CommunityPVC
👍5