የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
827 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
#ከመጋቢት_እስከ_መጋቢት
ባለፉት ሰባት ዓመታት በመዲናችን አዲስ አበባ ከ35 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሰጥቷል።

ከለውጡ ወዲህ በመዲናችን አዲስ አበባ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ከ35 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን በመስጠት ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የነበሩ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

በከተማችን በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር ዘርፈ ብዙ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን ከተማ አስተዳደሩ የክረምትና የበጋ ፕሮግራሞችን በመቅረፅ የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

በተጎሳቆሉና በተዛመሙ ጎጆዎች ውስጥ ህይወታቸውን ይገፉ የነበሩ በርካታ ነዋሪዎች የተሻለ ኑሮ እንዲመሩ በተነደፈው የቤት ግንባታና እድሳት ፕሮግራም 38 ሺህ 522 መኖሪያ ቤቶችን መልሶ በመገንባት ከ160 ሺህ በላይ ቤተሰቦች ያሏቸው አቅመ ደካሞች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የሀገር ባለውለታዎችና አረጋውያን ተጠቃሚ ሆነዋል።

ባለፉት ሰባት ዓመታት በኑሮ ውድነት ምክንያት የሚፈጠርን የዋጋ ግሽበት መቋቋም የማይችሉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ነዋሪዎች ለማገዝ 10.6 ቢሊዮን ብር የሚገመት የማዕድ ማጋራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሰጥቷል። በዚህ በየዓመቱ በአማካኝ ከ750 ሺህ በላይ ነዋሪዎች በድግግሞሽ ማዕድ እንዲጋሩ ተደርጓል። በተጨማሪም 132 ሺህ 300 ሰርተው መመገብ የማይችሉ ዜጎች ከተለያዩ ተቋማት ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ ድጋፍ እያገኙ ሲሆን 3 ሺህ 500 ወላጆቻቸውን በተለያየ ምክንያት ያጡና ለማኅበራዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ ህፃናት ቋሚና ጊዜያዊ ድጋፎችን እንዲያገኙ ተደርጓል።

ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር በተነደፈ የጤና በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር 266 ሺህ 756 ከፍለው መታከም የማይችሉ ነዋሪዎች ነፃ የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል። በደም እጥረት ምክንያት ሊከሰት የሚችልን ሞት ለመቀነስ በተሰራው የበጎነት ስራ 285 ሺህ 946 ዩኒት ህይወት አድን ደም ከበጎ ፈቃደኞች ተሰብስቧል።

በማጠናከሪያ ትምህርት፣ በመንገድ ትራፊክ ደህንነት፣ በሙያ አገልግሎት፣ በወሰን የለሽ መርሃ ግብር እንዲሁም በሌሎች ከ14 በላይ በሆኑ ፕሮግራሞች በየዓመቱ በአማካኝ 3 ሚሊዮን በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ በየአመቱ 1.2 ሚሊዮን የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

የከተማ አስተዳደሩ ለሰው ተኮር ስራዎች ትኩረት በመስጠቱም የበጎ ፈቃደኞች ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅዖ ከአመት ዓመት እድገት አሳይቷል። በዚህም በኅብረተሰቡ ዘንድ ነባር የሆነው የመረዳዳትና የመተሳሰብ ባህል እየጎለበተ የመጣ ሲሆን በጎ ፈቃደኝነት ለአገራዊ አንድነት፣ ለጋራ ልማትና ለዲሞክራሲ ግንባታ ብሎም በሥነ-ምግባርና ሰብዕና የታነፀ ሀገር ወዳድ ዜጋ ለማፍራት ጉልህ አስተዋፅዖ እያበረከተ ይገኛል።

"ትላንት፣ ዛሬና ነገ ለኢትዮጵያ ልዕልና!"

መጋቢት 24/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
https://linktr.ee/cpvcc
👏2👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በለውጡ 7 ዓመታት ብዙ ተግዳሮቶች የታለፉበት እና በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው!!
:- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በለውጡ 7 ዓመታት ብዙ ተግዳሮቶች የታለፉበት እና በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

በተለይም የፖለቲካ ባህል ላይ ያለውን ስብራት በመጠገን የፖለቲካ ባህል እየተለወጠ የመጣበት፣ ሀገራዊ ስብራቶች መጠገን የጀመሩበት፣ የኢኮኖሚ ስብራቶችም ከመሠረቱ መታከም የጀመሩበት፣ መሠረት የተጣለበት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

በዚህ ረገድ አዲስ አበባ ትልቅ የለውጡ ማሳያ መሆኗን ያነሱት ከንቲባዋ፣ ለውጡን ማየት እና ማገናዘብ ለፈለገ አዲስ አበባ ዋና ማሳያ ናት ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በመዲናዋ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማሳካት የሚያስችሉ መሠረቶች መጣላቸውንም ነው ያመላከቱት፡፡

ለዚህም ዋነኛው ማሳያ የሥራ ባህላችን መቀየሩ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ የሥራ ሰዓት ተጠብቆ እና እረፍት ተደርጎ ብልፅግናን ማረጋገጥ የማይቻል በመሆኑ ሌት ተቀን የመስራት አስፈላጊነት ላይ ታምኖበት ወደ ተግባር መገባቱ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በድህነት የተጎዳች ሀገር እንደመሆኗ ኢትዮጵያውያን ክብራቸው የሚነካበት እና የሀገር ክብር የሚዋረድበት ሁኔታ የነበረበትን በማስታወስም፣ ከዚህ ዝቅታ ለመውጣት ለከተማዋ ነዋሪዎችና ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ለመስራት የተደረገው ጥሪ በጎ ምላሽ በማግኘቱ አዲስ አበባ ላይ የሀገርን መፃኢ ዕድል የሚያሳዩ መሠረታዊ ሥራዎች መሰራት መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡

እጦት የአስተሳሰብ እንጂ በኢትዮጵያ መሬት ላይ እሴት ተጨምሮበት ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሀገርን የሚያበለፅግ እጦት ኖሮ አለመሆኑንም አመላክተዋል፡፡

ከምጣኔ ሀብት አኳያም አዲስ አበባ ከሀገሪቱ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ 40 ከመቶ ድርሻ እንዳላት የጠቀሱት ከንቲባ አዳነች፣ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረው ከ8 እጥፍ በላይ እድገት ማሳየቱን ነው የገለጹት፡፡

2010 ዓ.ም ላይ የከተማዋ ዓመታዊ ገቢ ከነበረበት 30 ቢሊየን ብር በ2017 በጀት ዓመት እስከ መጋቢት ወር ወደ 150 ቢሊየን ብር ገቢ እንደተሰበሰበ እና በዓመቱ መጨረሻ 230 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ይህም ሊሆን የቻለው በህዝቡላይ ግብር በመጨመር ሳይሆን ግብር የማይከፍሉ ወደ ግብር ሥርዓቱ እንዲገቡ በማድረግ የግብር ፍትሀዊነትን በማረጋገጥ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በለውጡ ዓመታት በርካታ ፕሮጀክቶች መገንባታቸውን በማንሳትም ፕሮጀክቶቹ የመዲናዋን የኢኮኖሚ ዕድገት ከመጨመር ባለፈ ለነዋሪዎች የኑሮ ጫናን የሚያቀሉ ስለመሆናቸው ተናግረዋል፡፡
👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ ዐበይት ክንውኖች
👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ሰብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳረፉ፤
👉ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ ጋር የአቃቂ ቃሊቲ የሀገር አቋራጭ መነኻሪያ ግንባታን መጎብኘታቸው፤
👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የታንዛኒያ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሳሚሀ ሱሉሁ ሀሰንን ልዩ መልዕክተኛ ዶ/ር ጃካያ ሚሪሾን በቢሯቸው ተቀብለው ማነጋገራቸው፤
👉የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2017 የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑን መገምገሙና በቀጣይ 3 ወራት ሥራዎች ላይ መወያየቱ፤
👉አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው።
👉የተቀናጀ ሞዴል ብሎኮች መስፋፋት አዲስ አበባ ከተማን ምቹ የመኖሪያና የስራ ከተማ ለማድረግ የላቀ ፋይዳ እንዳለው መገለፁ፤
👉የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና ማኅበራዊ ኃላፊነትን ተቋማዊ ለማድረግ በተዘጋጀው ደምብ ቁጥር 161/2016 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉ፤
👉አመራሩ ኅብረተሰቡን በማሳተፍ በሁሉም የልማት መመዘኛዎች ለመኖሪያ ምቹ የሆኑ ሞዴል ብሎኮችን ለመፍጠር የተጀመረውን ተግባር ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባው ኮሚሽነር ይመር ከበደ ማሳሰባቸው፤
👉የኮሚሽኑ አመራሮች በልደታ ክፍለ ከተማ የኮሪደር ልማት ለተሰማሩ ሰራተኞች ለሁለት ቀናት የእራት ማዕድ ማጋራታቸው፤
👉መጪውን የትንሳኤ በዓል በተለያዩ የበጎነት ተግባራት ለማሳለፍና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ፤ የሳምንቱ ሀገር አቀፍ፣ የከተማችንና የኮሚሽናችን ዐበይት ክንውኖች ነበሩ፡፡
👍4
ከተማ አስተዳደሩ በነገው ዕለት የኑሮ ጫና ላለባቸው ነዋሪዎች የትንሳኤ በዓል የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ያካሂዳል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት ከማዕከል እስከ ብሎክ ድረስ የኑሮ ጫና ላለባቸው ከ200 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የትንሳኤ በዓል የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ያካሂዳል።

ከተማ አስተዳደሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የከተማዋ ነዋሪዎች በዓላትን በደስታ እንዲያሳልፉ፣ አብሮነትና መልካም ጉርብትና እንዲጠናከር እና ኢትዮጵያዊ የመረዳዳት እሴት ተጠናክሮ ለትውልድ እንዲተላለፍ ሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ ፕሮግራሞችን ቀርፆ በመተግበር ላይ ይገኛል።

በዚህ ሰው ተኮር የበጎነትና የልግስና ተግባር ላይ በርካታ መልካም ልብ ያላቸው ግለሰቦችና ተቋማት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
#viralreelschallenge
#everyonefollowers
#addisababa
#Ethiopia@CommunityPVC
👏6👍41
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!
❤‍🔥4👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ ዐበይት ክንውኖች
👉የወርቃማው ሰኞ የእውቀት ሽግግርና የስራ ላይ ልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡
👉የትንሳኤ በዓል የበጎ ፈቃደኞች የስራ ስምሪት ላይ የሚሠማሩ ወጣት በጎ ፈቃደኞች ማኅበረሳባቸውን በቅንነት ማገልገል የሚያስችላቸው ግንዛቤና የስራ አቅጣጫ ተሰጠ።
👉ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ፡፡ በከተማ አስተዳደሩ እስከ ወረዳ ድረስ ለ200 ሺህ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ነዋሪዎች የትንሳኤ ማዕድ ተጋርተዋል፡፡
👉ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገነቡ 446 ቤቶችን ለአቅመ ደካሞችና ለልማት ተነሽዎች አስተላለፉ፡፡
👉የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ሶስት የተለያየ ውሳኔውችን አስተላለፈ፡፡
👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ትንሳኤን በማስመልከት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ፡፡
👉ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለትንሳኤ በዓል የእንኳ አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በትንሳኤ በዓል ዕለት አቅመ ደካሞችን መገቡ፡፡
👉ከንቲባ አዳነች አቤቤ 25ኛውንና 26ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት አገልግሎት አስጀመሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትንሳኤን በገላን ጉራ ከሚገኙ የካሳንቺስ ልማት ተነሺዎች ጋር አሳለፉ፡፡
መልካም ሳምንት
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Video
የሳምንቱ ዐበይት ክንውኖች

👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የካዛንችስ የኮሪደር ልማትን መርቀው ከፈቱ፡፡ “የተጎሳቆሉ እና በእጅጉ የተጎዱ ቤቶች እና ከባቢ መገኛ የነበረው ካዛንቺስ ዛሬ የጋራ ጥረት እና ለውጥ ሽልማታችን ሆኖ ተገኝቷል።” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ

👉የካዛንችስ አካባቢ የልማት ተነሺ ነዋሪዎች የካሳንችስን የኮሪደር ልማት ጎበኙ፡፡ “ካዛንቺስ አካባቢ የነበሩ የልማት ተነሺዎች በኮሪደር ልማት የተቀየረውን አዲሱን ካዛንቺስ ጐብኝተዋል ፤ ባዩት የልማት ስራ መደሰታቸውን የገለፁበት መንገድ ደግሞ ለቀጣይ ሥራ አቅም ሆኖናል።” ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡

👉የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሀገራዊ ቁልፍ ጉዳዮችና በፓርቲ ተኮር ጭብጦች ለሁለት ቀናት መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ፡፡ ፓርቲው በማህራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም በዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት በመምከርና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቋል፡፡

👉ከንቲባ አዳነች አቤቤ የጣይቱ የባህልና የትምህርት ማዕከልን መርቀው ከፈቱ፡፡ 120 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ የቅርስ ቤት የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የንግድና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የአዲስ አበባ 2ኛ ከንቲባ የነበሩት ቢትወደድ ኃይለጊዮርጊስ ወልደሚካኤል መኖሪያ ቤት እንዲሁም የመጀመሪያ የማዘጋጃ ቤት እና የፍትህ ማዕከል ሆኖ ያገለገለ ታሪካዊ ቤት ነው።

👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ “መሶብ” የተሰኘ የአንድ መዐከል አገልግሎት አስጀመሩ፡፡ አገልግሎቱ በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን በማጣመር ምርጥ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሚሰጥ አገልግሎት ነው።

👉ኮሚሽኑ የ2017 ዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃጸሙን ከተቋሙ ባለሙያዎች ጋር ገምግሟል፡፡ ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ ያቀዳቸውን ተግባራት በውጤታማነት ማከናወኑ የተገለጸ ሲሆን ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ የኅብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጥቷል።

የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን

ሚያዚያ 20/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ያነሷቸው ሃሳቦች:-

- ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልን እውን ለማድረግ በታቀደው መሰረት ለወጣቶች እና ለሴቶች ሰፋፊ የሆኑ የስራ ዕድሎች መፈጠራቸውን አንስተዋል።

- በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድም ተስፋ ሰጪ የሆኑ ስራዎች መሰራታቸውን ነገር ግን ልክ በኮሪደር ልማት፣ መልሶ ማልማት እና በወንዞች ዳርቻዎች ልማት አመርቂ ውጤቶች እንደተመዘገቡ ሁሉ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይም መሰረታዊ ለውጦችን ለማምጣት የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት መስራት እንደሚገባው በአስተያየት እና ጥያቄ መልክም ተነስቷል።

- የሰው ተኮር ስራዎች በተለይም ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ያሉ ዜጎች ከተማ አስተዳደሩ ከሚያመነጨው ኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስቻለ ከመሆኑም በላይ ህዝቡም ተገቢውን እውቅና እየሰጠ ይገኛል።

- የውሀ ስርጭት በስታንዳርድ እንዲሆን እየተሰራ ቢሆንም ፍትሀዊ ስርጭት እንዲኖር አሁንም ትኩረት እንዲሰጠው የህዝቡ ጥያቄ መሆኑን አንስተዋል።

- ከመብራት ጋር ተያይዞ በተለይም መኃል ከተማ በሚገኙ ክፍለ ከተሞች ያረጁ እና ሊወድቁ የደረሱ ፖሎች በነዋሪዎች ዘንድ ስጋት የደቀኑ በመሆናቸው አስቸኳይ እልባት ያስፈልጋል።

- ከኑሮ ውድነት አንፃር የሰብል ምርቶች የዋጋ መረጋጋት ያሳየ መሆኑን ሆኖም የዘይት ዋጋን ጨምሮ በሌሎች ምርቶች ዙሪያ ዘላቂ እልባት እንዲሰጥ::

- የእሁድ ገበያዎች፣ የተማሪዎች ምገባ ፣ የትራንስፖርት አቅርቦት፣ በጤና መድህን እንዲሁም ዓለም አቀፍ አንድምታ ያለው የኑሮ ውድነትን ለማቃለል የሚከናወኑ ሰው ተኮር ተግባራት አበረታች ውጤቶችን በማስመዝገብ ላይ ይገኛሉ።
👍1
ኢ/ር ወንድሙ ሲታ በም/ከንቲባ ማአረግ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ

👉የከተማዋን የፍሳሽ ማስጋጃ ስርዓት የማዘመንና በአዲስ መልከ የመገንባት ስራ በስፋት እየተከነወነ ይገኛል፡፡

👉የአደጋ ስጋት ተጋላጭነትን ለመቀነስ በልዩ በትኩረት አካባቢዎችን በመለየት እየሰራ ነው፡፡

👉የቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት ላይ ያመጣነው ለውጥና ያስገኘነው ውጤት በከተማችን ገፅታ ላይ ግልፅ ለውጥ እያመጣ ነው::

👉ቆሻሻን ወደ ኢነርጂ ከመቀየር አንፃር አሁንም የሚቀሩን ስራዎች አሉ፤ የከተማዋን ፅዳት አረጋግጠን ቆሻሻን ወደ ኢነርጂ መቀየር ላይ በትኩረት መስራት ይኖርብናል።

👉ከውሃ ፍትሃዊ ስርጭት አንፃር 377,000 ሜ.ኪዩብ ውሃ የማምረት አቅም በማጎልበት ተደራሽነታችንን ለማሰደግ የተሰራ ሲሆን በቀጣይ 100,000 ሜ.ኪዩብ ተጨማሪ የውሃ አቅርቦት አቅም ለመፍጠር በትኩረት እየሰራን ነው::

👉የመብራት መቆራረጥ ችግር መንስኤዎች በነባር መንደሮች ያለውን አሮጌ መሰረተ ልማት ጋር የተገናኘ በመሆኑ በቀጣይ የመብራት ሃይል አቅርቦት መሰረተ ልማትን በአዲስ መልክ ለመገንባት በማስተርፕላኑ ውስጥ ማስገባት በዘላቂነት ለመፍታት ያግዘናል ፡፡

👉የኮሪደር ልማት ሰራችን ይህንን የመሰረተ ልማት ችግር ለመቅረፍ በሚያስችል መልኩ እየተሰራ ይገኛል፡፡
👍1
ማህበራዊ ችግር ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ከተረጂነት ባለፈ በቂ ስልጠና በመስጠት መስራት የሚችሉትን የማሸጋገር ስራ ሰርተናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የኑሮ ውድነትና ጫናን ለማቃለል አለሜቀፋዊ ሁኔታን አገናዝበን ምላሽ ለመስጠት ሞክረናል።

* ኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ አቅርቦትን ማሳደግ ላይ በትኩረት በመስራት በአምስቱም የከተማችን መግቢያ በሮች የግብርና ምርቶችን አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግና የደላሎችን ሰንሰለት መበጣጠስ ችለናል።

* የኑሮ ውድነት ችግርን ማቃለል የምንችልበት መንገድ አምራችነትን በማሳደግ እንደመሆኑ መጠን የከተማችን ነዋሪ በተለያዩ አግባባች አምራችነቱ እንዲያድግ ስልጠና የመስጠትና የግብአት አቅርቦት እገዛ እያደረግን ነው።

* የገበያ ማረጋጋት ስራን በተመለከተ በቁጥጥር፣ በክትትልና፣ በድጎማ ህቦረተሰባችንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራን ነው።ውጤትም አግኝተንበታል።

* ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችና የእናቶችን የኑሮ ጫና ለማቃለል የሰራነው ስራ ሁሌም የምንኮራበት ነው።

* 26 የምገባ ማዕከላን በመክፈት ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመመገብ ፍትሀዊ ተጠቃሚነታቸዉን ከማረጋገጥ ባሻገር ዜጎች አብሮ የማደግ ባህል እንዲጎለብት አድርገናል።
👍2
የኮሪደር ልማቱ ዙሪያ

👉በኮሪደር ልማት የመጣው ለውጥ "አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እናደርጋታለን" ብለን ለህዝባችን ከገባነው ቃል የመነጨ ነው። ለአብነት የኮሪደር ስራችን ከመጀመራችን በፊት ባደረግነው ጥናት የአዲስ አበባ የመንገድ መሰረተ ልማት እና የአረንጓዴ ሽፋን እጅጎ ከፍ እንዲል ያስቻለን ሲሆን ይህም ለከተማችን ነዋሪዎች አጠቃላይ ጤና ያለው ፋይዳ የላቀ መሆኑን ሁሉም የሚገነዘበው ጉዳይ ነው።

👉በኮሪደር ልማት መኪና መንገድ ብቻ ሳይሆን 80% በላይ ተሽከርካሪ የሌለውን የከተማችን ነዋሪዎች በቀላሉ ሊጠቀሙበት የሚችሉትን የእግረኛ መንገዶችን አስፋፍተናል የሳይክል መንገዶችንም ማስፋፋት በመጀመራችን ህዝቡ ተጠቃሚ ሆኗል።

👉 በኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ስራ የታየው ወሳኘ ጉዳይ የህዝባችን ያላሰለሰ ድጋፍና ትብብር የተረጋገጠበት መሆኑ ነው። በዚህ ስራ ውስጥ ወጣቶች እና ሴቶች በጉልበታቸው አግዘዋል፤ ባለሀብቶች ገንዘባቸውን አፍስሰዋል፤ የልማት ተነሺዎች አስደናቂ ትብብር አድርገዋል።

👉ኮሪደር ልማቱ የከተማችንን ገፅታ መቀየሩ እና ለህዝባችን ምቹ መኖሪያ እንድትሆን ከማድረጉ ጎንለጎን ለበርካታ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል ፈጥሯል።

👉 የከተማችን ነዋሪዎች ልማቱ ወደ ሁሉም የከተማችን አካባቢዎች እንዲመጣ መጠየቃቸው አግባብነት ያለው ጥያቄ ቢሆንም ስራው ሰፊ ሀብት እና ጊዜ የሚፈልግ በመሆኑ በጥናት እና በቅደም ተከተል ወደ ሁሉም የከተማችን ክፍሎች በመምጣት የምናለማ ይሆናል::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍2
የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጨማሪ በጀት አፀደቀ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለ2017 ዓ.ም የሚውል ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት አፅድቋል፡፡

ተጨማሪ በጀቱ በከተማዋ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ ልማቶችን ለማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑ በምክር ቤቱ ተገልጿል፡፡
#followerseveryone
#viralreelschallenge
#highlighteveryone
#አዲስ_አበባ
👍1