የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
826 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
ፍትሃዊ የትምህርት ሽፋንና ተደራሽነትን ከማሳደግ አኳያ የተማሪ ቅበላን 1,253,737(106%) ማድረስ ተችሏል፤ ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር አፈፃፀሙ ሲነፃፀር 89,049 ብልጫ ያለዉ ነዉ፡፡

👉 የትምህርት ፍትሀዊነትን ከማስፈንም አካያ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት የተማሪዎች ቁጥር 33,672(100%) ማድረስ ተችሏል።

👉 በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በተሰራዉ ስራ በገንዘብ 3,841,682,948.15፣ በዓይነት 137,566,563.36፣ በጉልበት 19,800,640.85 እና በእውቀት 26,380,054.45 በድምሩ ብር 4,025,430,206.81 በመሰብሰብ የትምህርት ግብዓትን ማሟላት ተችሏል፡፡

👉 በዘላቂነት የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል ግብዓትን ከማቅረብ አንፃርም ለ1,037,500 (100%) ተማሪዎች ዩኒፎርም፤ለ9,125,435 (100%) ተማሮዎች ደብተር በማሰራጨት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።

👉 በተማሪ ምገባ አገልግሎት 835,069 (100%) ተማሪዎችን በቀን ሁለት ጊዜ መመገብ የተቻለ ሲሆን የተማሪ የቅበላ አቅም ለማሻሻልና የትምህርት ፍትሀዊነት ለማረጋጋጥ የተሰራው ስራ አበረታች ዉጤት አምጥቷል፡፡

👉በከተማችን የትምህርትና ስልጠና ጥራት ተገቢነትን ለማረጋገጥ በተሰራው ስራ በ126 ተቋማት ላይ የውጭ ኢንስፔክሽን በማካሄድ የደረጃ ምደባ እና የኢንስፔክሽን ስራዎች ተደራሽ ተደርጓል።

👉 ለትምህርትና ስልጠና የእውቅና እና የእድሳት አገልግሎት ጥያቄ ላቀረቡ 660 (94.7%) ተቋማት የእውቅና እና የእድሳት ተሰጥቷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍5
‘የአዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ራዕይ መዲናችን አዲስ አበባ በአህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ኩነቶች መስተንግዶ በአፍሪካ ቀዳሚ ሆና ማየት ሲሆን፣ ይህ ታላቅ ጉዞ በይፋ መጀመሩ ለመላው ኢትዮጵያውን ከፍ ያለ ኩራት ነውና በድጋሚ እንኳን ደስ አለን!!’

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍3
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ዐድዋ ለሰላም የተደረገ ዘመቻ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዐድዋ ለሰላም የተደረገ ዘመቻ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለ129ኛው የዐድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ መልእክት እንደሚከተለው ቀርቧል-

ለ129ኛው የዐድዋ ድል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ። ዐድዋ ለሰላም የተደረገ ዘመቻ ነው።

ከዐድዋ ዘመቻ በፊት ኢትዮጵያውያን ለሰላም ያላቸውን የጸና አቋም ደጋግመው ገልጸዋል። ለሰላም ያላቸው አቋም የጠላት ፉከራዎችንና ትንኮሳዎችን በትዕግሥት እስከማለፍ የደረሰ ነበር።

እንደሚታወሰው የወራሪው የኢጣልያ ጦር ባንዳ ይመለምል ነበር። ባንዳ ያስታጥቅ ነበር።
የባንዳ ተላላኪዎችን በመንግሥት ውስጥ ለማሥረግ ይሞክር ነበር። ሽብር ይነዛ ነበር። የኢትዮጵያን መንግሥት ይከስ ነበር። አንዳንድ ቦታዎችን ለመያዝ ይሞክር ነበር። በዓለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያን ለማሳጣት ይፍጨረጨር ነበር።

ኢትዮጵያ ይሄንን ሁሉ በትዕግሥት እና በዝግጅት ትመለከተው ነበር።

ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ በጦርነት ኖረዋል። በዚህ የተነሣ የጦርነትን አስከፊ ገጽታ ያውቁታል። ስለሚያውቁትም በቻሉት አማራጭ ሁሉ ይሸሹታል። ለሰላማዊ አማራጭ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋሉ። አንዳንድ ጊዜም ለሰላም ሲሉ ከአስፈላጊው በላይም ያደርጋሉ። ይሄንን ሁሉ ገፍቶ የሚመጣ ጠላት ሲገጥማቸው ግን ለሰላም ሲሉ ዘምተው፤ ለሰላም ሲሉ ያሸንፋሉ።

የዐድዋ ዘመቻም እንደዚሁ ነው። የወራሪው የኢጣልያ ጦር ወደ ጦርነት እንዳይገባ ተለምኗል። የሰላም አማራጮች ቀርበውለታል። "ኩራትና ትዕቢት የሞሉት አናት፣ ሰይፍና ጎራዴ የመቱት አንገት" እንደሚሉት ሆነ። የኢትዮጵያን ትዕግሥት እንደ ፍርሃት፣ የኢትዮጵያን የሰላም መንገድ እንደ ሽንፈት ቆጠረው።

ጠላቶቻችን ምንጊዜም የስሌት ስሕተት ይሠራሉ። ትኅትናችን፣ ትዕግሥታችንና ሰላም ወዳድነታችን ያሳስታቸዋል። ወራሪው የኢጣልያ ጦርም ተሳሳተ።

ኢትዮጵያውያን ግን እየታገሡ ይዘጋጁ ነበሩ። በሁሉም ረገድ ሰላማቸውን ለመጠበቅ ዝግጁ ነበሩ። ነጻነት ፣ ሉዓላዊነት እና ክብር የሚገኙት የሀገር ሰላምን በመጠበቅ መሆኑን ያውቃሉ። ስለዚህ ሰላማቸውን በክንዳቸው ለመጠበቅ ተዘጋጁ።

የዐድዋ ጦርነት ለሰላምና ለጦርነት በሚዋጉ ኃይሎች መካከል የተደረገ ጦርነት ነው። የአሸናፊነታችን አንዱ ምሥጢርም ይሄው ነው። ከጦርነቱ በኋላ ወደ በቀልና ጥላቻ እንዳናመራ ያደረገንም ይሄው ነው። ለሰላም ስንል እንጂ ለጦርነት ስንል አልተዋጋንምና።

የዐድዋ ድል ለሰው ልጅ ሉላዊ ዕሴቶች ያለንን ዋጋ አሳይተንበታል። በምርኮኛ አያያዛችን፣ ከተዋጉን ጋር መልሰን ለሰላማዊ ውይይት በመቀመጣችን፣ ለዘላቂ ሰላም በመሥራታችን።
እናቶቻችንንና አባቶቻችንን በድል አድራጊነታቸው ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጅ ዕሴቶች በከፈሉት ዋጋ ጭምር እናመሰግናቸዋለን። የተዋጉት ለሰላም ሲሉ ነው። የተዋጉት ሰላምን እና ሰላማዊ መንገድን እምቢ ካለ ኃይል ጋር ነው።

የዐድዋ ዘማቾች ልጆች ነን። ለሰላም ቅድሚያ እንሰጣለን። ዛሬም ጠላቶቻችን ከተሳሳተ ስሌት እንዳልወጡ እናውቃለን። በሰላማዊ መንገድ የሚመጡትን መቀበል ከዐድዋ ዘማቾች ተምረናል። በሰላም የማይመጡትንም መቅጣት ከዐድዋ ዘማቾች አይተናል። እኛም እንደቀደምቶቻችን የሰላሙን መንገድ እንመርጣለን። ነገር ግን እንደ ቀደምቶቻችን ሁሉ፣ ለሁለቱም ምንጊዜም ዝግጁዎች ነን። የዐድዋ ዘማቾች ልጆች ነንና።

መልካም በዓል ይሁን።
👍4
ዛሬ በይፋ የሚመረቀው የአዲስ አለምአቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል:-

👉 40 ሄክታር መሬት ላይ አርፏል፣
👉እያንዳንዳቸው ከ3 ሺሕ እስከ 4 ሺሕ ሰዎችን የመያዝ አቅም ያላቸው 2 ትላልቅ አዳራሾች፣ 8 አነስተኛ እና መካከለኛ የመሰብሰቢያ አዳራሾች በጠቅላላ እስከ 10 ሺሕ ሰዎችን የሚያስተናግዱ፣

👉 እስከ 1 ሺሕ ሰዎችን የሚያስተናግዱ አልጋዎችን የያዙ 2 ሆቴሎች ፣
👉ከቤት ውጪ እስከ 50 ሺሕ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል የኤግዚቢሽን ስፍራ፤
👉ሁለት አንፊ ቴአትር፣
👉2 ሄክታር የዉጪ ኤግዚቢሽ ቦታ፣
👉ሁለት ሞሎች፣
👉ሬስቶራንቶች፣ በርካታ የንግድ ሱቆች፣ ባንኮች እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣
👉በሀገራችን ትልቁ የኮንፍራንስ ማዕከል፣
👉አለምአቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሁነቶችን የሚያስተናግድ፣
👉 በከተማችን ከመስቀል አደባባይ ቀጥሎ ሁለተኛው ግዙፍ አደባባይ ከሆነው የለሚ ፓርክ ጋር ተያይዞ የተሰራ በአጠቃላይ እስከ 2 ሺሕ መኪናዎችን የማቆም አቅም ያላው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።
👍8
"አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ኢትዮጵያ ሰርታ የምታሳይ ሀገር መሆኗን የሚያሳይ ነው።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

“በዚህ ዓለም ዐቀፍ ማዕከል ንግድ እንነግድበታለን፣ እውቀት እንለዋወጥበታለን፣ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን እንቀምርበታለን” ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ማዕከሉ በኢትዮጵያ ሀሳብን አልቆ መፈፀም ልምድ እየሆነ መምጣቱን ማሳያ ነውም ብለዋል።

በሀሳብ ደረጃ የነበረውን ጅምር ከዕቅዱ በላይ ዓለም አቀፍ ደረጃውን ያሟላ አድርገን አልቀን መስራታችንም ለዚህ ዋቢ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

“መፍጠን፣ መፍጠር፣ መስራት ይጠበቅብናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመሩት ስራዎች ውጤት እያሳዩ ነው ብለዋል።

“ነገር ግን ስራዎች በችግር ውስጥ እንደሚሰራ መረዳት ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የምንፈልገውን ለውጥ እስክናመጣ አበክረን መስራት ይገባናል ሲሉ ነው ያሳሰቡት።

“ኢትዮጵያን የሚያህል አዲስ አበባን የሚመጥን ለውጥ ማምጣት አላማችን ነው። ለልጆቻችን በረከት ለማውረስ የምታኮራ ሀገር ለማስረከብ እንሰራለን። ኢትዮጵያም ይህንን ማድረግ ትችላለች” ብለዋል።

አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ለቀጣዮቹ 10 ቀናት ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ህዝቡ መጥቶ እንዲጎበኝም ጋብዘዋል።
ከሁሉ በማስቀደም የረዳን እና ያከናወነልን ፈጣሪ ይመስገን!

ዛሬ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ያስመረቅነው የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከል ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን አዳዲስ እድሎችን የሚከፍት፣ የማያቋርጥ የሃብት ምንጭ መፍጠሪያ የሚሆን እንዲሁም ለገጽታ ግንባታ እና ለቱርስት ስበት ትልቅ ሚና የሚጫወት ማዕከል ነው::

ማዕከሉ አለምአቀፋዊ ኮንፍራንሶችን፣ የንግድ ውይይቶችንና ስምምነቶችን፣ ባህላዊ መድረኮችንና ልዩ ልዩ ኤግዚቢሽኖችን ለማስተናገድ እንዲሁም አዳዲስ ሃሳቦች የሚንሸራሸሩበት የንግድና የኢኮኖሚ ስምምነቶች የሚጎለብቱበት ነው::

15ሺ ካሬ የውጪ ሁነት ማስተናገጃ ቦታ ያለው የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከል ባለ 5 ኮከብ ዘመናዊ ሆቴል፣ ሪስቶራንቶች፣ የስፖርት፣ የጤና፣ የመዝናኛ እና የልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫን ያከተተ ግዙፍ ማዕከል ነዉ።

ከዚህም ባሻገር፣ በአንድ ጊዜ እስከ 2000 ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚችል ፓርኪንግ ያለዉ ሲሆን የለሚ ፓርክ እና በቀጥታ ከአየር መንገድ ጋር የሚያገናኝ ሰፊ የመንገድ መሰረተ ልማትም ከማዕከሉ ጋር ተያይዞ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ፤ይህም ኢኮኖሚያችንን የሚያነቃቃ፣ ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር ከመሆኑ በላይ እንግዶች ሲመጡ ያለምንም እንግልት ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ስፍራ እንዲያገኝ ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡

ይህ ስራ ከዳር እንዲደርስ የቅርብ ድጋፍና ክትትል ላደረጉልን ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ከፍ ያለ ምስጋናና አክብሮቴን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላቀርብ እወዳለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍4
እንኳን ለ129ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ አደረሰን

የአደዋ ድል የኢትዮጵያዊያን ሕብረ ብሔራዊነት መገለጫ፣ የይቻላል መንፈስ ምንጭ፣ ያለፉ እና የቀጣይ ትውልዶች የወል ትርክት ነው።
የአደዋ ድል በዓልን ስናከብር ድሉ በፈጠረልን የአንድነት እና የይቻላል መንፈስ የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ያለንን ቁርጠኝነት በመግለፅ እንዲሆን ጥሪየን አስተላልፋለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍5🙏2