ከተማ አሰተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት መሬት ዝግጅትን በተመለከተ
👉ለልማት ጥያቄዎች መሬት ከማዘጋጀት እና ወደ መሬት ባንክ በዳታ ቤዝ መመዝገብ አንጻር ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል 618.35 ሄ/ር ማዘጋጀት ተችሏል።
የለማ መሬት ከማስተላለፍ አንፃር ለመካከኛና ለከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ለልማት ተነሺዎች፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ለተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት፣ ለጥቃቅንና አነስተኛ የስራ እድል ፈጠራ፣ ለጊዜያዊ መጠቀሚያ፣ ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች የሚውል 402.64 ሄ/ር መሬት ማስተላለፍ ተችሏል። በተጨማሪም ለ3,935 በላይ የልማት ተነሺዎች ምትክ ቦታ እንዲሰጣቸው ተደርጓል።
👉በየጊዜው አዲስ የሚመጡ የይዞታ ማህደራት ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አገልግሎት ለመስጠት ማህደራት ላይ የአሰራር ጥራት ኦዲት ማድረግ በተከታታይነት እየተሰራ ነው፡፡
ለልማት ለተነሺዎች ካሳ ለመክፈል በታቀደው መሰረት ብር 9.5 ቢሊዮን መክፈል ተችሏል። አሰራርን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ እየተደረገ ያለው ጥረት ውጤት እያስገኘ ነው።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከተማ አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ ባለፉት 6 ወራት በብዝሃን ትራንስፖርት አገልግሎት አቅርቦት ያስመዘገባቸዉ ዉጤቶች በተመለከተ፤-
የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት አቅርቦት ከማሳደግ አኳያ 100 አዳዲስ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን በማስገባት በቀን 1,408 (97.5%) አውቶብሶችን በማሰማራት አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡
ጂፒኤስ የተገጠመላቸውን አውቶብሶች ቁጥር ወደ 994 (95%) ማድረስ ተችሏል።
የአንድ አውቶቡስ በቀን በአማካይ ምልልስ ካለፈዉ በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረዉ 8 ወደ 12 እንዲያድግ በመደረጉ አገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል ተችሏል::

ከተማ አሰተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት በጤናዉ ዘርፍ ያስመዘገባቸዉ ዉጤቶች ማሳያ፤-
👉ከእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት አኳያ የቅድመ ወሊድ ክትትል አገልግሎት 94,812 እቅድ ተያዞ 94,548 ለሚሆኑ እናቶች አገልግሎት በመስጠት የእቅዳችንን (99.7% ) ማሳካት ተችሏል፡፡
👉 የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ፕሮግራም አምና ከነበረው 2.3 ሚሊየን አጠቃላይ በፕሮግራሙ የታቀፉ አባላት ቁጥር ዘንድሮ 2.5 ሚሊየን ማድረስ የተቻለ ሲሆን የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚነትንም ለ1,330,562 በማድረስ ተደራሽና ፍትሃዊ የጤና አገልግሎትን መስጠት ተችሏል::
👉የጤና መረጃ ስርዓትን ከማዘመንና ዲጂታል ከማድረግ ረገድም የጤና መረጃ ስርዓታቸውን በሙሉ ወረቀት አልባ ያደረጉ (EMR implement)ካደረጉ 40 ጤና ተቋማት ወደ 91ጤና ተቋማት በማሳደግ እቅዱን ማሳካት ተችሏል፡፡
👉የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት አመላካች መለኪያዎችን ስንመለከት የአስተኝቶ ህክምና ታካሚዎች ሞት ምጣኔ በእቅድ የተያዘው 1.4% እና ከዛ በታች ማድረስ ሲሆን 1.2% በማከናወን እቅዱን ማሳካት ተችሏል፡፡
👉የድንገተኛ ታካሚዎች ሞት ምጣኔን ከታቀደው 0.5% እና ከዛ በታች 0.4% ማከናወን የተቻለ ሲሆን የፅኑ ህሙማን የሞት ምጣኔን ከመቀነስ ረገድም ውጤታማ ስራ ተሰርቷል፡፡
👉በተሰጠዉ የህክምና አገልግሎት ጥራት አመላካቾችም የአለም የጤና ድርጅት በማደግ ላይ ላሉ ሃገራት ያወጣውን ስታንዳርድም ሆነ ሃገራዊ ኢላማ በሚገባ ማሳካት የተቻለ ሆኗል፡፡

❤2
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ በማስከበር ረገድ በየደረጃዉ ያለዉ የፀጥታ መዋቅር ህዝቡን የሰላም ባለቤት ከማድረግ ባሻገር በተናበበና በተቀናጀ አግባብ በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ በመስራት ዉጤት መመዝገቡን ገልፀዉ፣ በከተማዋ የደረቅ ወንጀል መከላከል ከዓምናዉ ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 33 በመቶ ቀንሷል ብለዋል፡:
ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁሉን አካታች መመዘኛዎችን መሰረት ያደረገ ፖሊሲና እስትራቴጂ በመንደፍ በከተማዋ የመልካም አስተዳደር አሰራር እንዲሰፍን በቅንጅት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነዉ
ሲሉ ተናግረዋል::
የበጀት አጠቃቀምን በተመለከተም ቀድሞ 70 በመቶ ለአስተዳደር 30 በመቶ ለእድገት ተኮር የነበረዉን በጥናት በመቀየር 30 በመቶ ለአስተዳደር 70 በመቶ ለእድገት ተኮር በማድረግ ለህዝባችን በገባነዉ ቃል መሰረት ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ጀምሮ በመጨረስ፤የግዥ ስርዓታችንን ግልፀ በማድረግ ፣የክትትል አግባብን በማጠናከር እና ያለ አግባብ የሰዉ ሃይል ቅጥርን በማስቀረት በዘላቂነት የከተማዋን እድገት ማስፈፀም ችለናል ሲሉ ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡
ከንቲባዋ አክለዉም በ2010 የከተማዋ በጀት 30 ቢሊዮን ብር ከነበርበት ዛሬ ላይ በ6 ወራት 111.5 ቢሊዮን መሰብሰብ የተቻለዉ የግብር ምህዳሩን በማስፋት፤የታክስና የኦዲት አሰራርን በማዘመን ገቢያችንን ማሳደግ ነው ብለዋል፡:
በተጨማሪም በማናቸዉም ሁለተናዊ የከተማዋ ስራዎች ህገመንግስቱ ባስቀመጠዉ አሰራር ከተማ አስተዳደሩ ከበጀት ድጎማ ጀምሮ በሌሎችም በቅንጅት እየተሰራ በርካታ የልማት ስራዎች በጥራትና በታቀደዉ ጊዜ በማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
ከኑሮ ውድነት አኳያ አያይዘው ሲገልፁ በአራቱም የገበያ በሮች ገበሬው እና ምርት አቅራቢው በቀጥታ ምርቱን ወደ ከተማ በማምጣት አምራችና ተጠቃሚውን ምርቱን በተገቢው ዋጋ የሚገበያይበት ሰርዓት መዘርጋቱን ፣ የእሁድ ገበያዎች ስታንዳርዳቸዉን በጠበቀ መልኩ መከፈታቸው ጉልህ ሚና እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በትምህርት ስልጠና መምህራንን ከማብቃት አኳያ በከተማ አሰተዳደሩ የአመራር አካዳሚ እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን ይህም ለትምህርት ጥራት ከፍተኛ አሰተዋፅኦ ያበረክታል ሲሉ ከንቲባዋ አክለዋል፡፡
የገርቢ እና ጭቆላ የውሃ ፕሮጀክት ከለውጡ በፊት በውጭ ብድር ለመስራት የታቀደ ቢሆንም በጀቱ በተያዘበት ቀነ ገደብ ባለመለቀቁ እና በአንዳንድ ምክንያቶች ግንባታው በመዘግየቱ የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር በራሱ በጀት ለመስራት አቅጣጫ ይዞ ወደ ስራ ተገብቷል፡
የቤት ግድግድ እና ጣሪያ ጋር በተያያዘ ከንቲባዋ በተጡት ምልሽ በ1968 ዓ.ም በወጣው አዋጀ መሰረት የካሬ ዋጋ ኪራይ መጠን የመቀየር ስራ እንጅ ምን አይነት የሬት ጨማሪ ያልተደረገ መሆኑን ገልፀው ለመኖሪያ ቤት 50 % ለንግድ 75% የክፍያ ሰርዓት እንዲበጀለት ተደርጓል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በህግ ደረጃ የጡረተኛ እና አቅመ ደካሞችን በተመለከተ በህግ ተፈቅዳል ቢሆንም አፈፃፀሙን በተመለከተ በየደረጃ መከታተል ስለሚያስፈልግ እየተሰራበት መሆኑን ገልፀዋል።
የልማት ተነሺ የካሳ ክፍያ ሌሎች ጉዳዩች ጋር ተያይዞ በህግ አሰራር መሰረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ቅሬታ አሁንም ካለ በከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ፅ/ቤት በተቋቋመ ስራ ዴስክ በኩል የሚፈታ መሆኑ ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የአርሶ አደር ይዞታ ማረጋገጪ እና የአቃቂ ድልድይ ጀምር ስራዎችን ለማጠናቀቅ ከተማ አሰተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡

❤1
የምክር ቤቱ ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ በማሳለፍ ተጠናቋል::
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤው የከተማ አስተዳደሩን የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈጸጸም ሪፖርት ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩን የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ፣ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን እንደገና ለማቋቋም የተዘጋጀውን አዋጅ እና የምክር ቤቱን የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ሹመት በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡

ፍትሃዊ የትምህርት ሽፋንና ተደራሽነትን ከማሳደግ አኳያ የተማሪ ቅበላን 1,253,737(106%) ማድረስ ተችሏል፤ ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር አፈፃፀሙ ሲነፃፀር 89,049 ብልጫ ያለዉ ነዉ፡፡
👉 የትምህርት ፍትሀዊነትን ከማስፈንም አካያ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት የተማሪዎች ቁጥር 33,672(100%) ማድረስ ተችሏል።
👉 በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በተሰራዉ ስራ በገንዘብ 3,841,682,948.15፣ በዓይነት 137,566,563.36፣ በጉልበት 19,800,640.85 እና በእውቀት 26,380,054.45 በድምሩ ብር 4,025,430,206.81 በመሰብሰብ የትምህርት ግብዓትን ማሟላት ተችሏል፡፡
👉 በዘላቂነት የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል ግብዓትን ከማቅረብ አንፃርም ለ1,037,500 (100%) ተማሪዎች ዩኒፎርም፤ለ9,125,435 (100%) ተማሮዎች ደብተር በማሰራጨት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።
👉 በተማሪ ምገባ አገልግሎት 835,069 (100%) ተማሪዎችን በቀን ሁለት ጊዜ መመገብ የተቻለ ሲሆን የተማሪ የቅበላ አቅም ለማሻሻልና የትምህርት ፍትሀዊነት ለማረጋጋጥ የተሰራው ስራ አበረታች ዉጤት አምጥቷል፡፡
👉በከተማችን የትምህርትና ስልጠና ጥራት ተገቢነትን ለማረጋገጥ በተሰራው ስራ በ126 ተቋማት ላይ የውጭ ኢንስፔክሽን በማካሄድ የደረጃ ምደባ እና የኢንስፔክሽን ስራዎች ተደራሽ ተደርጓል።
👉 ለትምህርትና ስልጠና የእውቅና እና የእድሳት አገልግሎት ጥያቄ ላቀረቡ 660 (94.7%) ተቋማት የእውቅና እና የእድሳት ተሰጥቷል።

👍5
‘የአዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ራዕይ መዲናችን አዲስ አበባ በአህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ኩነቶች መስተንግዶ በአፍሪካ ቀዳሚ ሆና ማየት ሲሆን፣ ይህ ታላቅ ጉዞ በይፋ መጀመሩ ለመላው ኢትዮጵያውን ከፍ ያለ ኩራት ነውና በድጋሚ እንኳን ደስ አለን!!’
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍3
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ዐድዋ ለሰላም የተደረገ ዘመቻ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ዐድዋ ለሰላም የተደረገ ዘመቻ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለ129ኛው የዐድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ መልእክት እንደሚከተለው ቀርቧል-
ለ129ኛው የዐድዋ ድል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ። ዐድዋ ለሰላም የተደረገ ዘመቻ ነው።
ከዐድዋ ዘመቻ በፊት ኢትዮጵያውያን ለሰላም ያላቸውን የጸና አቋም ደጋግመው ገልጸዋል። ለሰላም ያላቸው አቋም የጠላት ፉከራዎችንና ትንኮሳዎችን በትዕግሥት እስከማለፍ የደረሰ ነበር።
እንደሚታወሰው የወራሪው የኢጣልያ ጦር ባንዳ ይመለምል ነበር። ባንዳ ያስታጥቅ ነበር።
የባንዳ ተላላኪዎችን በመንግሥት ውስጥ ለማሥረግ ይሞክር ነበር። ሽብር ይነዛ ነበር። የኢትዮጵያን መንግሥት ይከስ ነበር። አንዳንድ ቦታዎችን ለመያዝ ይሞክር ነበር። በዓለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያን ለማሳጣት ይፍጨረጨር ነበር።
ኢትዮጵያ ይሄንን ሁሉ በትዕግሥት እና በዝግጅት ትመለከተው ነበር።
ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ በጦርነት ኖረዋል። በዚህ የተነሣ የጦርነትን አስከፊ ገጽታ ያውቁታል። ስለሚያውቁትም በቻሉት አማራጭ ሁሉ ይሸሹታል። ለሰላማዊ አማራጭ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋሉ። አንዳንድ ጊዜም ለሰላም ሲሉ ከአስፈላጊው በላይም ያደርጋሉ። ይሄንን ሁሉ ገፍቶ የሚመጣ ጠላት ሲገጥማቸው ግን ለሰላም ሲሉ ዘምተው፤ ለሰላም ሲሉ ያሸንፋሉ።
የዐድዋ ዘመቻም እንደዚሁ ነው። የወራሪው የኢጣልያ ጦር ወደ ጦርነት እንዳይገባ ተለምኗል። የሰላም አማራጮች ቀርበውለታል። "ኩራትና ትዕቢት የሞሉት አናት፣ ሰይፍና ጎራዴ የመቱት አንገት" እንደሚሉት ሆነ። የኢትዮጵያን ትዕግሥት እንደ ፍርሃት፣ የኢትዮጵያን የሰላም መንገድ እንደ ሽንፈት ቆጠረው።
ጠላቶቻችን ምንጊዜም የስሌት ስሕተት ይሠራሉ። ትኅትናችን፣ ትዕግሥታችንና ሰላም ወዳድነታችን ያሳስታቸዋል። ወራሪው የኢጣልያ ጦርም ተሳሳተ።
ኢትዮጵያውያን ግን እየታገሡ ይዘጋጁ ነበሩ። በሁሉም ረገድ ሰላማቸውን ለመጠበቅ ዝግጁ ነበሩ። ነጻነት ፣ ሉዓላዊነት እና ክብር የሚገኙት የሀገር ሰላምን በመጠበቅ መሆኑን ያውቃሉ። ስለዚህ ሰላማቸውን በክንዳቸው ለመጠበቅ ተዘጋጁ።
የዐድዋ ጦርነት ለሰላምና ለጦርነት በሚዋጉ ኃይሎች መካከል የተደረገ ጦርነት ነው። የአሸናፊነታችን አንዱ ምሥጢርም ይሄው ነው። ከጦርነቱ በኋላ ወደ በቀልና ጥላቻ እንዳናመራ ያደረገንም ይሄው ነው። ለሰላም ስንል እንጂ ለጦርነት ስንል አልተዋጋንምና።
የዐድዋ ድል ለሰው ልጅ ሉላዊ ዕሴቶች ያለንን ዋጋ አሳይተንበታል። በምርኮኛ አያያዛችን፣ ከተዋጉን ጋር መልሰን ለሰላማዊ ውይይት በመቀመጣችን፣ ለዘላቂ ሰላም በመሥራታችን።
እናቶቻችንንና አባቶቻችንን በድል አድራጊነታቸው ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጅ ዕሴቶች በከፈሉት ዋጋ ጭምር እናመሰግናቸዋለን። የተዋጉት ለሰላም ሲሉ ነው። የተዋጉት ሰላምን እና ሰላማዊ መንገድን እምቢ ካለ ኃይል ጋር ነው።
የዐድዋ ዘማቾች ልጆች ነን። ለሰላም ቅድሚያ እንሰጣለን። ዛሬም ጠላቶቻችን ከተሳሳተ ስሌት እንዳልወጡ እናውቃለን። በሰላማዊ መንገድ የሚመጡትን መቀበል ከዐድዋ ዘማቾች ተምረናል። በሰላም የማይመጡትንም መቅጣት ከዐድዋ ዘማቾች አይተናል። እኛም እንደቀደምቶቻችን የሰላሙን መንገድ እንመርጣለን። ነገር ግን እንደ ቀደምቶቻችን ሁሉ፣ ለሁለቱም ምንጊዜም ዝግጁዎች ነን። የዐድዋ ዘማቾች ልጆች ነንና።
መልካም በዓል ይሁን።

👍4
ዛሬ በይፋ የሚመረቀው የአዲስ አለምአቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል:-
👉 40 ሄክታር መሬት ላይ አርፏል፣
👉እያንዳንዳቸው ከ3 ሺሕ እስከ 4 ሺሕ ሰዎችን የመያዝ አቅም ያላቸው 2 ትላልቅ አዳራሾች፣ 8 አነስተኛ እና መካከለኛ የመሰብሰቢያ አዳራሾች በጠቅላላ እስከ 10 ሺሕ ሰዎችን የሚያስተናግዱ፣
👉 እስከ 1 ሺሕ ሰዎችን የሚያስተናግዱ አልጋዎችን የያዙ 2 ሆቴሎች ፣
👉ከቤት ውጪ እስከ 50 ሺሕ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል የኤግዚቢሽን ስፍራ፤
👉ሁለት አንፊ ቴአትር፣
👉2 ሄክታር የዉጪ ኤግዚቢሽ ቦታ፣
👉ሁለት ሞሎች፣
👉ሬስቶራንቶች፣ በርካታ የንግድ ሱቆች፣ ባንኮች እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣
👉በሀገራችን ትልቁ የኮንፍራንስ ማዕከል፣
👉አለምአቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሁነቶችን የሚያስተናግድ፣
👉 በከተማችን ከመስቀል አደባባይ ቀጥሎ ሁለተኛው ግዙፍ አደባባይ ከሆነው የለሚ ፓርክ ጋር ተያይዞ የተሰራ በአጠቃላይ እስከ 2 ሺሕ መኪናዎችን የማቆም አቅም ያላው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።

👍8
"አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ኢትዮጵያ ሰርታ የምታሳይ ሀገር መሆኗን የሚያሳይ ነው።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
“በዚህ ዓለም ዐቀፍ ማዕከል ንግድ እንነግድበታለን፣ እውቀት እንለዋወጥበታለን፣ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን እንቀምርበታለን” ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ማዕከሉ በኢትዮጵያ ሀሳብን አልቆ መፈፀም ልምድ እየሆነ መምጣቱን ማሳያ ነውም ብለዋል።
በሀሳብ ደረጃ የነበረውን ጅምር ከዕቅዱ በላይ ዓለም አቀፍ ደረጃውን ያሟላ አድርገን አልቀን መስራታችንም ለዚህ ዋቢ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
“መፍጠን፣ መፍጠር፣ መስራት ይጠበቅብናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመሩት ስራዎች ውጤት እያሳዩ ነው ብለዋል።
“ነገር ግን ስራዎች በችግር ውስጥ እንደሚሰራ መረዳት ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የምንፈልገውን ለውጥ እስክናመጣ አበክረን መስራት ይገባናል ሲሉ ነው ያሳሰቡት።
“ኢትዮጵያን የሚያህል አዲስ አበባን የሚመጥን ለውጥ ማምጣት አላማችን ነው። ለልጆቻችን በረከት ለማውረስ የምታኮራ ሀገር ለማስረከብ እንሰራለን። ኢትዮጵያም ይህንን ማድረግ ትችላለች” ብለዋል።
አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ለቀጣዮቹ 10 ቀናት ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ህዝቡ መጥቶ እንዲጎበኝም ጋብዘዋል።