የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
826 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ከተማ አስተዳደሩ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ400 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የኑሮ ጫና ላለባቸው ነዋሪዎች ማዕድ አጋራ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ400 ሺህ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ አረጋውያን ፣ አቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞች 1.6 ቢሊዮን ብር የሚገመት ማዕድ አጋርቷል።

በማዕከል ደረጃ በተዘጋጀ የማዕድ ማጋራት መድረክ ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ማዕድ ስናጋራ የኑሮ ጫና ያለባቸው ዜጎቻችን በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ማድረግ ብቻ ሳይሆን እርስ በርስ መረዳዳት ፣ ያለንን መካፈልና የአብሮነት ባህላችን ከከተማችን ዕድገት ጋር አብሮ እንዲዳብር ለማድረግ ነው ብለዋል።

የህዝባችን የኑሮ ጫና ተቃልሎ ማዬት እንፈልጋለን ያሉት ከንቲባ አዳነች ለዚህ የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር ሀብታቸውን በማካፈል ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ በጎ ፈቃደኛ ባለሀብቶች ምስጋና አቅርበው መጭው የገና በበዓል ያማረ፣ የደመቀና ፍቅር የሚዳብርበት እንዲሆን ተመኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይመር ከበደ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ በዘላቂነት ለማሻሻል እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው
በዛሬው ዕለት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከማዕከል እስከ ብሎክ ድረስ 400 ሺህ ለሚሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች 1.6 ቢሊዮን ብር የሚገመት ማዕድ መጋራቱን ተናግረዋል።

ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እየፈቱ የሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ባለሀብቶች የበጎነት ስራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል።

"በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!"
የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ።

የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ “ፀሐይ ለማንም ሳታዳላና ሳትዘገይ ለሁሉም እኩል ብርሐኗን እንደምትሰጥ” ሁሉ ክርስቶስም የሰውን ልጆች በዘርና በቀለም ሳይነጣጥል፣ በእኩልነት ወዶና ፈቅዶ፣ ከገባበት ፈተናና መከራ ሊያወጣው የተወለደበት፣ የርህራሄ፣ የፍቅርና የመተሳሰብ በዓል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

የልደት በዓል አምላክ ከዙፋኑ ዝቅ ብሎ በከብቶች በረት ተወልዶ፣ የሰውን ልጅ እንዳገለገለ ሁሉ እኛም ከባለፀግነታችን፣ ከስልጣናችንና ከክብራችን አንድ ደረጃ ዝቅ ብለን በኑሮ ጫና ውስጥ ከሚገኙ ወገኖቻችን ጋር ደስታና ፍቅር የምንጋራበት ፣ የአብሮነት ስጦታ የምናበረክትበት ቀን ነው፡፡ በዚህ ቀን ጎረቤቶቻችን በማጣታቸው ምክንያት አዝነውና ተክዘው እንዳይውሉ የልግስና እጃችንን የምንዘረጋበት፣ በጎነታችን የሚገለጥበት ዕለት መሆን አለበት፡፡

የከተማችን አስተዳደር ነባርና ቀደምት እሴታችን ሆኖ የቆየው ለሰው ልጅ በጎ የማድረግ ባህል ይበልጥ እንዲጎላ በተቋም ደረጃ እንዲመራ በማድረግ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን እያቃለለ ይገኛል፡፡ በሚሰጡ ባለፀጎች አማካኝነት የበርካታ ዜጎቻችን ህይወት ተለውጧል፡፡ ከተጎሳቆለ አኗኗር የተላቀቁ የከተማችን ነዋሪዎች ቁጥር ጨምሯል፡፡ የበጎነት ኢኮኖሚያዊ አበርክቶው ከማደጉ በተጨማሪ በሚሰጡና በሚቀበሉ ሰዎች መካከል የልብ ለልብ ግንኙነትን (ማህበራዊ መስተጋብርን) አንድ ደረጃ ከፍ እንዲል አድርጓል፡፡

ይህ የበጎነት ተግባር በገና በዓልም እንዲጠናከር በጎ ፈቃደኞች የተለመደ የልግስና እጃችሁን እንዳታጥፉ፣ የከተማችን ነዋሪዎች እርስ በርስ የመተሳሰብ ልምዳችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እየጠየኩ መልካም የልደት በዓል እንዲሆን እመኛለሁ።

አቶ ይመር ከበደ - የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር
👍1👎1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ከ12 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች መጪው የከተራና የጥምቅት በዓል በሠላም እንዲጠናቀቅ የማስተባበር አገልግሎት ይሰጣሉ።

በመዲናዋ መጪው የከተራና የጥምቀት በዓል በሠላም እንዲጠናቀቅ ከ12 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች የማስተባበር አገልግሎት ይሰጣሉ።

በወረዳና በክፍለ ከተማ በተካሄዱ መድረኮች በዓሉ ኃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር በጎ ፈቃደኞች የማስተባበር ሚናቸውን መወጣት እንዲችሉ የአገልግሎት ስምሪትና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን በዛሬው ዕለት በከተማ ደረጃ የማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል።

በሁሉም የጥምቀት ማክበሪያ ቦታዎች በጎ ፈቃደኞች ሚናቸውን ለይተው ከበዓሉ ባለድርሻዎች ጋር በመቀናጀት ለበዓሉ በድምቀት መከበር ኅብረተሰባቸውን በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው ተጠቁሟል።

በጎ ፈቃደኞች በበኩላቸው በዓሉ ከተማዋ የምትደምቅበትና በርካታ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች የሚታደሙበት በመሆኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በትጋት እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል።

ኃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት ማህበራዊ መስተጋብሮችን በመፍጠር የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህል ይበልጥ የሚገለጡባቸው እሴቶቻችን ናቸው።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ተገልጋይ በሚበዛባቸው የመንግስት ተቋማት የሚያገለግሉ 1 ሺህ 200 በጎ ፈቃደኞች የስራ ስምሪት ወሰዱ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ተገልጋይ በሚበዛባቸው የመንግስት ተቋማት በሙያቸው አገልግሎት ለመስጠት ለተዘጋጁ በጎ ፈቃደኞች የስነ-ምግባር ስልጠናና የስራ ስምሪት መርሀ ግብር አካሂዷል።

የሙያ በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተቋማት ውስጥ የአገልግሎት እንግልት ችግሮችን በማቃለልና የመንግስት ወጪ በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያበረከተ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን በጎ ፈቃደኞች አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት የበጎ ፈቃድ መርሆዎችንና የስነ ምግባር ደንቦችን አክብረው ማገልገል እንደሚጠበቅባቸው በመድረኩ ተመላክቷል።

በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ህዝብን ለማገልገል ዛሬ የስራ ስምሪትና የስነ ምግባር ስልጠና የወሰዱት 1 ሺህ 200 በጎ ፈቃደኞች ሲሆኑ በገቢ አሰባሰብ ግንዛቤ ማስጨበጥና መረጃ የማደራጀት ስራ ላይ ይሰማራሉ።

በሚሰማሩበት የሙያ ዘርፍ ህዝባቸውን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን በመድረኩ የተገኙ በጎ ፈቃደኞች ተናግረዋል።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ከ11 ሺህ በላይ የአካባቢ ቅጥር ጥበቃዎች ስምሪት መሠጠቱ ተገለጸ።

ኮሚሽኑ ለጥምቀት በዓል በህብረተሰብ ተሳትፎ ለተቀጠሩ ቅጥር የአካባቢ ጥበቃዎችና ለብሎክ ካውንስል አባላት ስምሪት መስጠቱን አስታውቋል ።

በዓሉ ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በሠላም እንዲከበር ለብሎክ ካውንስል አባላትና ለአካባቢ ቅጥር ጥበቃዎች ስልጠና በመስጠት ስምሪት መስጠቱን የህብረተሰብ ተሳትፎ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ፀሐይ ኪባሞ ገልፀዋል ።

የብሎክ ካወንስል አባላትና አመራሮች ነዋሪውን በማስተባበር የበዓል ማከበሪያ ቦታዎችንና መኖሪያ አካባቢያችን በንቃት መጠበቅ አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ደግሞ ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት የሚያስችል ስልጠና መሰጠቱንና አደረጃጀት መፈጠሩን ምክትል ኮሚሽነር ፀሐይ ኪባሞ አክለው ገልጸዋል ።

በመድረኩ የተገኙት አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ በየደረጃው ያለዉ የፀጥታ ኃይል በዓሉን በሠላም ማክበር የሚያስቸል በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገልፀው የቅጥር ጥበቃ አባላትም የኋላ ደጀን በመሆን የመኖሪያ ቤቶችንና ድርጅቶችን በንቃት መጠበቅ የሚያስችል ስምሪት መውሰዳቸው የተቀናጀ ውጤት ማምጣት የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል ።

በስልጠና ማጠቃለያ መድረኩ የተሳተፉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከፀጥታ ኃይሉና ከወጣቱ ጋር በመቀናጀት በዓሉ ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር ለመኖሪያ አካባቢዎች ትኩረት ሰጥተው በንቃት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል ።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍4
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ባለፉት ስድስት ወራት በኅብረተሰቡ ተሳትፎ 62.9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የአካባቢ ልማት ማከናወኑን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው ለኮሚሽኑ ኮሙኒኬሽን እንዳስታወቁት በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት የክፍለ ከተማውን ኅብረተሰብ በማሳተፍ 31 ሚሊዮን ብር በጥሬ ገንዘብ፣ በዓይነትና በጉልበት ለመሰብሰብ ታቅዶ 62.9 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል። ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውና ለመሰረተ ልማት ተግባር ማዋጣት ለማይችሉ ነዋሪዎችም ፕሮጀክት በመቅረፅና 1.1 ሚሊዮን ብር በመሰብሰብ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች መከናወናቸውን ነው ኃላፊዋ የተናገሩት።

ኅብረተሰቡን በአካባቢ ልማት በስፋት በማሳተፍም 19.6 ኪ.ሜ ሰቤዝና 16.1 ኪ.ሜ ኮብል ጥገና ተከናውኗል ብለዋል። የኅብረተሰቡን የልማት ፍላጎት መሰረት በማድረግ 4 አነስተኛ ድልድዮች፣ 10.7 ኪ.ሜ ቱቦ ቀበራ፣ 10 ኪ.ሜ ቱቦ ጥገና፣ 3 የማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ማዕከላት እንዲሁም 5 የጋራ መፀዳጃ ቤቶች ተገንብተዋል።

የተሰሩ ልማቶች ለኅብረተሰቡ የረጅም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ መሆናቸውን የተናገሩት ወ/ሮ እቴማር 9.4 ኪ.ሜ የዲች ስራ፣ 4 ኪ.ሜ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መብራት ዝርጋታ እና 2.8 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ መሰራቱን ገልፀዋል። 5 ኪ.ሜ ቴራዞ ንጣፍ እና 2 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ መከናወኑን ኃላፊዋ አክለዋል።

በክፍለ ከተማው በተከናወኑ መሰረተ ልማቶች ለ628 ወጣቶች ጊዜያዊ የስራ እድል እንዲሁም 62.9 ሚሊዮን ብር የገቢያ ትስስር ተፈጥሯል።

ማኅበረሰቡን በአካባቢ ሰላም፣ በፅዳት፣ በልማት፣ በመልካም አስተዳደር እና በሌሎች ተግባራት በማስተባበርም 64 ብሎኮችን ሞዴል ማድረግ መቻሉን ያብራሩት ኃላፊዋ ኅብረተሰቡ በአካባቢ ልማትና ሰላም እያሳየ ያለውን የነቃ ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍6
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት በበጎ ፍቃድ ስራ ያስመዘገባቸዉን ዉጤቶች በሚመለከት ለምክር ቤት ያቀረቡት ሪፖርት

👉የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለዘላቂ ልማት ያለውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ በተከናወኑ የሰው ተኮርና የበጎ ፈቃድ ተግባራት 1,197,413 (ከ100% በላይ) የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

👉በዚሁ መሰረት 24 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በመክፈት በየቀኑ በአማካይ እስከ 36,000 ለሚደርሱ በቀን አንድ ጊዜ እንኳን ምግብ ለማግኘት የሚቸገሩ ነዋሪ ወገኖቻችንን መመገብ ተችሏል፡፡

👉ለአቅመ ደካሞች፣ ለአረጋውያን፣ ለሀገር ባለውለታዎችና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች 3,737(74%) ቤቶችን በመገንባት 20,484 (77%) ቤተሰቦችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

👉 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ከ917,829 (ከ100% በላይ) የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ ማጋራት ተችሏል።

👉በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰሩ መሰረተ ልማት ስራዎች ብር 479,361,717.8 እንዲሁም በበጎ ፈቃድ 8,714,683,077 በድምሩ ብር 9,194,044,794.80 ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል።

👉ማህበራዊ ሀላፊነትን በመወጣት ረገድ የመጡ ለዉጦች ተግባሩ እለት ከእለት እየተጠናከረ መሄዱን የሚያሳይና የበርካቶች ገመናን የሸፈነ የበጎነት ተግባር በመሆኑ ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል ፡፡
👍1
ከተማ አሰተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት የቤት መሰረተ ልማትን በተመለከተ

👉ከቤቶች ልማት አንጻር በበጀት ዓመቱ የከተማዋን የቤት አቅርቦት ለማሻሻል በመንግስት አስተባባሪነት፣ በሪል ስቴት እና በግል አልሚዎች በተለያዩ መርሃ-ግብሮች 27,304 የቤቶች ተገንብተው አቅርቦት መጨመር ተችሏል፡፡

👉በልዩ ልዩ የቤት አቅርቦት አማራጮች 120,000 ( መቶ ሃያ ሺህ) ቤቶች ግንባታ ፕሮግራም የተጀመረ ሲሆን፣ ከተጠናቀቁት ውስጥ በከተማችን ለሚሰሩ የህዝብ ልማት ስራዎች (ኮሪድርን ጨምሮ) ለሚነሱ የልማት ተነሺዎች እና የተለያዩ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ታሳቢ 9ሺ 20 ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ተችሏል።

👉ህገ-ወጥነትን ከመከላከል አንፃር 113 የጋራ መኖሪያ ቤት፣ 71 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት፣ 172 የቀበሌ ቤት ማስለቀቅ ተችሏል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍2
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት 6 ወራት በመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታ ያሳካቸዉ ዉጤቶች በተመለከተ:-


የአዲስ አስፋልት መንገድ ግንባታ ከ25.7 ኪ.ሜ በላይ የአስፋልት ግንባታ ስራ የተከናወነ ሲሆን የጠጠር መንገድ ግንባታ አፈፃፀም 8.32 (38 %) ኪ.ሜ መገንባት ተችሏል።


748.90 ኪ.ሜ የመንገድ ጥገና ስራዎችም በማከናወን አፈጻጸሙን ማሳደግ ተችሏል።

በአጠቃላይ በግማሽ ዓመቱ ሁሉም ዓይነት የግንባታ በታቀደው መሰረት 87.66 ኪ.ሜ መፈጸም ተችሏል።

የውስጥ ለውስጥ በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ እየተገነቡ ያሉ መንገዶችን በቀሪ ወራት ተገቢ ትኩረት ሰጥቷቸዉ የሚሰሩ መሆናቸዉ ተገልፃል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከተማ አሰተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት መሬት ዝግጅትን በተመለከተ

👉ለልማት ጥያቄዎች መሬት ከማዘጋጀት እና ወደ መሬት ባንክ በዳታ ቤዝ መመዝገብ አንጻር ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል 618.35 ሄ/ር ማዘጋጀት ተችሏል።
የለማ መሬት ከማስተላለፍ አንፃር ለመካከኛና ለከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ለልማት ተነሺዎች፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ለተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት፣ ለጥቃቅንና አነስተኛ የስራ እድል ፈጠራ፣ ለጊዜያዊ መጠቀሚያ፣ ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች የሚውል 402.64 ሄ/ር መሬት ማስተላለፍ ተችሏል። በተጨማሪም ለ3,935 በላይ የልማት ተነሺዎች ምትክ ቦታ እንዲሰጣቸው ተደርጓል።

👉በየጊዜው አዲስ የሚመጡ የይዞታ ማህደራት ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አገልግሎት ለመስጠት ማህደራት ላይ የአሰራር ጥራት ኦዲት ማድረግ በተከታታይነት እየተሰራ ነው፡፡
ለልማት ለተነሺዎች ካሳ ለመክፈል በታቀደው መሰረት ብር 9.5 ቢሊዮን መክፈል ተችሏል። አሰራርን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ እየተደረገ ያለው ጥረት ውጤት እያስገኘ ነው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ