የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
826 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ከተማ አስተዳደሩ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ400 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የኑሮ ጫና ላለባቸው ነዋሪዎች ማዕድ አጋራ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ400 ሺህ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ አረጋውያን ፣ አቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞች 1.6 ቢሊዮን ብር የሚገመት ማዕድ አጋርቷል።

በማዕከል ደረጃ በተዘጋጀ የማዕድ ማጋራት መድረክ ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ማዕድ ስናጋራ የኑሮ ጫና ያለባቸው ዜጎቻችን በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ማድረግ ብቻ ሳይሆን እርስ በርስ መረዳዳት ፣ ያለንን መካፈልና የአብሮነት ባህላችን ከከተማችን ዕድገት ጋር አብሮ እንዲዳብር ለማድረግ ነው ብለዋል።

የህዝባችን የኑሮ ጫና ተቃልሎ ማዬት እንፈልጋለን ያሉት ከንቲባ አዳነች ለዚህ የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር ሀብታቸውን በማካፈል ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ በጎ ፈቃደኛ ባለሀብቶች ምስጋና አቅርበው መጭው የገና በበዓል ያማረ፣ የደመቀና ፍቅር የሚዳብርበት እንዲሆን ተመኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይመር ከበደ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ በዘላቂነት ለማሻሻል እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው
በዛሬው ዕለት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከማዕከል እስከ ብሎክ ድረስ 400 ሺህ ለሚሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች 1.6 ቢሊዮን ብር የሚገመት ማዕድ መጋራቱን ተናግረዋል።

ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እየፈቱ የሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ባለሀብቶች የበጎነት ስራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል።

"በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!"
የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ።

የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ “ፀሐይ ለማንም ሳታዳላና ሳትዘገይ ለሁሉም እኩል ብርሐኗን እንደምትሰጥ” ሁሉ ክርስቶስም የሰውን ልጆች በዘርና በቀለም ሳይነጣጥል፣ በእኩልነት ወዶና ፈቅዶ፣ ከገባበት ፈተናና መከራ ሊያወጣው የተወለደበት፣ የርህራሄ፣ የፍቅርና የመተሳሰብ በዓል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

የልደት በዓል አምላክ ከዙፋኑ ዝቅ ብሎ በከብቶች በረት ተወልዶ፣ የሰውን ልጅ እንዳገለገለ ሁሉ እኛም ከባለፀግነታችን፣ ከስልጣናችንና ከክብራችን አንድ ደረጃ ዝቅ ብለን በኑሮ ጫና ውስጥ ከሚገኙ ወገኖቻችን ጋር ደስታና ፍቅር የምንጋራበት ፣ የአብሮነት ስጦታ የምናበረክትበት ቀን ነው፡፡ በዚህ ቀን ጎረቤቶቻችን በማጣታቸው ምክንያት አዝነውና ተክዘው እንዳይውሉ የልግስና እጃችንን የምንዘረጋበት፣ በጎነታችን የሚገለጥበት ዕለት መሆን አለበት፡፡

የከተማችን አስተዳደር ነባርና ቀደምት እሴታችን ሆኖ የቆየው ለሰው ልጅ በጎ የማድረግ ባህል ይበልጥ እንዲጎላ በተቋም ደረጃ እንዲመራ በማድረግ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን እያቃለለ ይገኛል፡፡ በሚሰጡ ባለፀጎች አማካኝነት የበርካታ ዜጎቻችን ህይወት ተለውጧል፡፡ ከተጎሳቆለ አኗኗር የተላቀቁ የከተማችን ነዋሪዎች ቁጥር ጨምሯል፡፡ የበጎነት ኢኮኖሚያዊ አበርክቶው ከማደጉ በተጨማሪ በሚሰጡና በሚቀበሉ ሰዎች መካከል የልብ ለልብ ግንኙነትን (ማህበራዊ መስተጋብርን) አንድ ደረጃ ከፍ እንዲል አድርጓል፡፡

ይህ የበጎነት ተግባር በገና በዓልም እንዲጠናከር በጎ ፈቃደኞች የተለመደ የልግስና እጃችሁን እንዳታጥፉ፣ የከተማችን ነዋሪዎች እርስ በርስ የመተሳሰብ ልምዳችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እየጠየኩ መልካም የልደት በዓል እንዲሆን እመኛለሁ።

አቶ ይመር ከበደ - የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር
👍1👎1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ከ12 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች መጪው የከተራና የጥምቅት በዓል በሠላም እንዲጠናቀቅ የማስተባበር አገልግሎት ይሰጣሉ።

በመዲናዋ መጪው የከተራና የጥምቀት በዓል በሠላም እንዲጠናቀቅ ከ12 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች የማስተባበር አገልግሎት ይሰጣሉ።

በወረዳና በክፍለ ከተማ በተካሄዱ መድረኮች በዓሉ ኃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር በጎ ፈቃደኞች የማስተባበር ሚናቸውን መወጣት እንዲችሉ የአገልግሎት ስምሪትና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን በዛሬው ዕለት በከተማ ደረጃ የማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል።

በሁሉም የጥምቀት ማክበሪያ ቦታዎች በጎ ፈቃደኞች ሚናቸውን ለይተው ከበዓሉ ባለድርሻዎች ጋር በመቀናጀት ለበዓሉ በድምቀት መከበር ኅብረተሰባቸውን በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው ተጠቁሟል።

በጎ ፈቃደኞች በበኩላቸው በዓሉ ከተማዋ የምትደምቅበትና በርካታ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች የሚታደሙበት በመሆኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በትጋት እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል።

ኃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት ማህበራዊ መስተጋብሮችን በመፍጠር የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህል ይበልጥ የሚገለጡባቸው እሴቶቻችን ናቸው።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis