የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
637 subscribers
2.17K photos
47 videos
267 links
Download Telegram
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በመዲናዋ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር 10 ሺህ በጎ ፈቃደኞች አገልግሎት በሚበዛባቸው የመንግስት ተቋማት ይሰማራሉ።

በከተማችን የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት በየጊዜው እያደጉ መምጣታቸውን የሚያሳይ "በጎነት በገልግሎት ሰጪ ተቋማት!" የተሰኘ የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር ተጀምሯል። ዛሬ በተካሄደው መድረክ፣ አገልግሎት በሚበዛባቸው የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ውስጥ ተሰማርተው ህዝባቸውን የሚያገለግሉ በጎ ፈቃደኞች የስራ ስምሪት ተሰጥቷቸዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ይመር ከበደ ለበጎ ፈቃደኞች የስራ መመሪያና አቅጣጫ ሰጥተዋል። ዋና ኮሚሽነሩ በንግግራቸው "በጎ ፈቃደኞች በሚሰማሩባቸው ተቋማት ሁሉ ዓለም አቀፍ የበጎ ፈቃድ መርሆዎችን በጥብቅ መከተል ይኖርባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማ ለማድረግ የተቋማቱን የአሰራር እሴቶችና ስነ-ምግባር አክብሮ መስራት ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል።
 
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አስራት ንጉሴ በበኩላቸው፣ በከተማዋ የበጎነት ባህል እንዲዳብርና የህብረተሰቡ የጋራ እሴት እንዲሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ዘርፈ ብዙና አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። ይህ የዛሬው የስምሪት መርሃ-ግብርም የዚሁ ስኬታማ ጉዞ አካል መሆኑን ጠቁመዋል።
 
የበጎ ፈቃደኞቹን የስራ አካባቢ ምቹ የማድረግና የመደገፍን አስፈላጊነት ያነሱት ደግሞ በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ የቢሮው አማካሪ አቶ አቡበክር ሀሽም ናቸው። አቶ አቡበክር በመንግስት ተቋማት ውስጥ ለሚሰማሩት ለእነዚህ በጎ ፈቃደኞች ተቋማቱ አስፈላጊውን ድጋፍና ቀጣይነት ያለው ክትትል እንደሚያደርጉላቸው አረጋግጠዋል።

 ታዋቂው የስራ ፈጣሪና በጎ ፈቃደኛ ኢንጂነር ቢጄአይ ናይከር እና በመከላከያ ሰራዊትነት ለረዥም ጊዜ አገራቸውን ያገለገሉት 50 አለቃ ብርሃኑ አማረ በመድረኩ ተገኝተው ለበጎ ፈቃደኞቹ የረጅም ዘመን የስራ፣ የህይወትና የሀገር ፍቅር ልምዳቸውን አጋርተዋል።

ታዋቂ ግለሰቦች ያጋሩት ልምድና የተሰጣቸው የስራ አቅጣጫ ወደ አገልግሎት ከመግባታቸው በፊት የስነ-ልቦና ዝግጅት እንዲያደርጉ እንዳገዛቸውና መነሳሳት እንደፈጠረላቸው በጎ ፈቃደኞቹ ገልፀዋል።

ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በዜጎች መካከል የመረዳዳትና አብሮነትን የማጠናከር ትልቅ አገራዊ ፋይዳ ይኖረዋል። 
 
👍32
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የኅብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ስራዎች የለውጡ እሳቤ በተግባር የተገለጠባቸው መሆናቸው ተገለጸ።

አዲስ አበባ| ሰኔ 11/2018 ዓ.ም ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ የኅብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ውጤቶች የለውጡ እሳቤ በተግባር የተገለጠባቸው ተግባራት መሆናቸውን የአዲስ አበባ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ ተናገሩ። ምክትል ኮሚሽነሯ ይህንን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያካሄደ በሚገኘው የ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃጸም ግምገማ መድረክ ወቅት ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም እና ያለፉት 5 ዓመታት የስራ አፈፃጸም ግምገማ ከሰኔ 10/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት እየተካሄደ ይገኛል። በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የኮሚሽኑን የስራ አፈፃጸም አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ፤ ባለፉት 5 የለውጥ ዓመታት የህዝብ ተሳትፎን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ረገድ በርካታ ዘርፈ ብዙና ሰው ተኮር የሆኑ ተግባራት ስኬታማ በሆነ መንገድ መከናወናቸውን አስገንዝበዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ቀዳሚ መሪነት የተጀመረው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤት የመገንባት ስራ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ውስጥ ትልቅ እምርታ ማሳየቱን ምክትል ኮሚሽነሯ አብራርተዋል። ይህ የበጎ ፈቃድ ንቅናቄ ቀደም ሲል ከነበረበት የግለሰብ ቤቶች እድሳት ደረጃ በመውጣት፣ በአሁኑ ወቅት ሰፋፊ የሆኑ የ"በጎነት መንደር" ግንባታዎችን ወደ ማካሄድ መሸጋገሩንና በከፍተኛ ደረጃ መስፋቱን አስረድተዋል።

ባለፉት 5 የለውጥ ዓመታት ውስጥ ብቻ በዚህ በጎ እሳቤ ተመርቶ በተከናወነ የተቀናጀ ስራ የዜጎችን ማኅበራዊ አኗኗር የሚመጥኑና የከተማዋን ገጽታ ያዘመኑ ከ46 ሺህ 441 በላይ መኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ለተጠቃሚዎች መተላለፋቸውን ወ/ሮ ፀሐይ ገልጸዋል። አያይዘውም ይሄው አበረታች የበጎ ፈቃድ ስራ በሚቀጥለው የ2019 በጀት ዓመትም ከከተማዋ ሁለንተናዊ እድገትና ለውጥ ጋር ተመጋጋቢ በሆነ መንገድ፣ ይበልጥ በላቀ የሰው ተኮር እሳቤ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በተያዘው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 2 ሺህ 500 አዳዲስ መኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞችና ለችግረኛ ወገኖች ለመገንባት ታቅዶ ርብርብ እየተደረገበት እንደሚገኝና ስራዎችም በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ። በተቋሙ "በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል የሚመሩት እነዚህ ማኅበራዊ አገልግሎቶች የነዋሪውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ያለሙ ናቸው።

#በጎነት_ለአዲስ_አበባ_ከፍታ
#የበጎ_ፈቃድ_አገልግሎት
#humanitarian
#አዲስ_አበባ
#Ethiopia
👍2
የመምህርነት የስራ ቅጥር ምዝገባ ማስታወቂያ!

(ሀምሌ 13/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ10/11/2018 ዓ.ም ያወጣው የመምህርነት የስራ ቅጥር ማስታወቂያ ምዝገባ ከዛሬ ማለትም ከ13/11/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚከናወን ይሆናል፡፡

የመምህርነት የስራ ቅጥር መመዝገቢያ ሊንክ

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfszWEujUr29knX3mhUsQJfzvosKBGCg7Jw2WznB0EsBMybGQ/viewform?usp=publish-editor
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ኤካ ኮተቢው አጠቃላይ ሆስፒታል በክረምት በጎ ፈቃድ መርሀ ግብር ከ200 ሺህ በላይ ዜጎችን ነፃ የሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚ አደረገ።

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም
በየካ ክፍለ ከተማ የሕክምና ወጪ መሸፈን ለሚቸገሩ በርካታ ነዋሪዎች እፎይታን ሲሰጥ የቆየውና ከ200 ሺህ በላይ ነፃ የሕክምና አገልግሎቶች የተሰጡበት የ11 ቀናት የበጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር ዛሬ ተጠናቋል። በጤና ሚኒስቴር፣ በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል እና በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትብብር የተዘጋጀው ይህ ነፃ የሕክምና አገልግሎት፣ የብዙዎችን የጤና ችግር በመቅረፍና ለዜጎች አስፈላጊውን የሕክምና ድጋፍ ተደራሽ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተገልጿል።

በማጠናቀቂያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የሜዲካል ሴንተሮች መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢሊባቡር ቡኖ እንደተናገሩት፣ በዘንድሮው ዓመት ብቻ በመላ ሀገሪቱ ከ20 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የዚህ ነፃ የሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ። የኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር መገርሳ አለሙ በበኩላቸው፣ ባለፉት 11 ቀናት ለሕብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት በመቻሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ለህክምናው መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ የጤና ባለሙያዎችና አጋር አካላት ምስጋና በማቅረብ መሰል ሰብዓዊ አገልግሎቶች ወደፊትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ኢምሮ፣ ላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የሕክምና ወጪ መሸፈን ለማይችሉ ወገኖች አገልግሎት ሲሰጥ ለቆየው ለኤካ ኮተቤ ሆስፒታልና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል። በዚህ የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር ላይ እንደ ዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተር፣ ላንሴት ሆስፒታል እና ጂአይቪ ሆስፒታል ያሉ የግል ተቋማትም በመሳተፍ የዜጎችን ህይወት ለመታደግ በተደረገው ጥረት ድጋፍ አድርገዋል ሲል የዘገበው የካ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ነው።
👍2
የቅጥር ማስታወቂያ

አአ ጤና ቢሮ ሐምሌ 22/2018 ዓም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ለኮልፌ አጠቃላይ ሆስፒታል በተለያዩ የሥራ መደቦች ላይ ሰራተኞችን በቋሚነትና በኮንትራት አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም

ለኮንትራት ቅጥር ፈላጊዎች Contract Position የሚለውን ሊንክ በመጫን እንዲሁም
ለቋሚ ቅጥር ፈላጊዎች Permanent Position የሚለውን ሊንክ በመጫን በስራቸው የተዘረዘሩ የስራ መደቦች ላይ በመመዝገብ ማመልከት የሚቻል መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
Contract Position (ለጊዜያዊ የስራ መደብ )
Permanent Position (ለቋሚ የስራ መደብ )

ማሳሰቢያ፡-
ለጊዜያዊ የስራ መደብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከሀምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ብቻ እንዲሁም
ለቋሚ የስራ መደብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከሀምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ብቻ ሆኖ ከጠዋቱ 2.30 እስከ ማታ 11.30 ብቻ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
በአንድ ኢሜል አድራሻ አንድ ጊዜ ብቻ ነው መመዝገብ የሚቻለው፡፡

ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑት።

https://forms.gle/eNbU1f5HbPiPsDUQA
3👍2
"በጎ ልብ፤ ትንሽ ስጦታ፣ ግዙፍ ዓላማ!"

​በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባህልን በማሳደግ የብዙዎችን ሕይወት በአንድ ላይ መቀየር እንችላለን!

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ባዘጋጀው "የዲጂታል በጎነት" ፕሮጀክት አማካኝነት ማህበረሰባችንን ለመደገፍ የእርስዎ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ዋጋ አለው።

​የለውጡ አካል ለመሆን አሁኑኑ ይሳተፉ፣ ወደ 6400 "A" ብለው መልዕክት ይላኩ! መልካምነትዎን በዲጂታል መንገድ ያጋሩ!

#ዲጂታልበጎነት #6400A #ኢትዮቴሌኮም #የበጎፈቃድአገልግሎት #አዲስአበባ #EthioTelecom #AddisAbaba
👍5
በቀን አንድ ብር ብቻ በመለገስ የሌሎችን ጉድለት መሙላት ይችላሉ! አሁኑኑ ወደ 6400 "A"ን በመላክ ደጋግ ልቦችን ይቀላቀሉ።

መልካም ቀን ይሁንልዎት!
👍3