በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በበጋ የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም የተገነቡ ከ20 በላይ የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላለፉ።
በክፍለ ከተማው በሚገኙ ልዩ ልዩ ወረዳዎች በጥቅሉ ከ20 በላይ የሚሆኑ የአቅመ ደካማና አረጋውያን መኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ለባለቤቶቻቸው ተረክበዋል።
የቤት ግንባታ ተጠቃሚ የሆኑት ወ/ሮ አሰገደች አሰፋ ከዚህ ቀደም ይኖሩበት የነበረው ቤት በጣም የተጎሳቆለ፣ ለዝናብና ለፀሀይ የተጋለጠ በመሆኑ ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገው እንደነበር ይናገራሉ። ዛሬ ቤታቸው በሚያስደስት ደረጃ ተገንብቶ በመረከባቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ለበጎ ፈቃደኞች ምስጋና አቅርበዋል።
ሌላኛው የቤት ግንባታው ተጠቃሚ አቶ አያሌው ይማም በበኩላቸው፣ ለብዙ ዓመታት ለመኖሪያነት ፍፁም በማይመችና ሙሉ በሙሉ ቆርቆሮ በቆርቆሮ በነበረ ጠባብ ቤት ውስጥ ይኖሩ እንደነበር ገልጸው፤ "ዛሬ ያ አሰቃቂ ታሪክ ተቀይሮ ቤታችን በብሉኬት ተሰርቶና ዘምኖ በመረከባችን የተሰማንን ደስታ በቃል መግለጽ ይከብዳል" ሲሉ አስተያየታቸውን መስጠታቸውን የላፍቶ ኮሙኒኬሽን ዘገባ ያመለክታል።
የክፍለ ከተማው ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ብዙአየሁ መኮንን ዛሬ ለተጠቃሚዎች የተላለፉት ቤቶች በበጋ ወቅት በልዩ ትኩረት በእቅድ ተይዘው ሲከናወኑ የቆዩ መሆናቸውን ጠቁመው ፕሮጀክቶቹ ከጅምር እስከ ፍጻሜ ስኬታማ እንዲሆኑ ከጎናቸው ላልተለዩ ቅን ባለሀብቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች ምስጋና አቅርበዋል።
በከተማችን ለአቅመ ደካሞች፣ ለአረጋውያን እንዲሁም ለሀገር ባለውለታዎች ደረጃቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ከመስጠት ባለፈ፤ የተዛመሙ ጎጆዎችን ባሉበት መልሶ በመገንባት ለኑሮ ምቹ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል።

👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በአዲስ አበባ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር 2,500 ቤቶች ሊገነቡ ነው።
አዲስ አበባ| ሰኔ 15/2018 ዓ.ም፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተጀመረው የቤት ግንባታና የአካባቢ ማደስ ፕሮጀክት፥ የመንግስትን ፖለቲካዊ ቃል ኪዳን ወደ መሬት የመቀየር ስትራቴጂ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ። ከንቲባዋ "የመረጠንን ህዝብ የምናመሰግነው በቃላት ሳይሆን በተግባራዊ ምላሽ ነው" ያሉ ሲሆን፥ ይህም ብልፅግና ፓርቲ በምርጫ ዳግም ኢትዮጵያን ለመምራት ተጨማሪ የአምስት ዓመት እምነት በተሰጠው ማግስት የተጀመረ መሆኑን ገልጸዋል።
በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በከተማ ደረጃ 2,500 ቤቶችን ለመገንባት የታቀደ ሲሆን፥ የዚሁ አካል የሆነውና ከከንቲባ ፅህፈት ቤት በስተጀርባ የሚገነባው የ“አራዳ የበጎነት መንደር” ግንባታ በይፋ ተጀምሯል። ይህ ሜጋ ፕሮጀክት ባለ 9 ወለል 8 ዘመናዊ የመኖሪያ ህንፃዎችን እና ባለ 4 ወለል ሁለት የገበያ ማዕከላትን ያካተተ ሲሆን፥ ለዘመናት የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን በመቀየር ለሰው ልጆች ክብር የሚመጥን ዘመናዊ የጋራ መገልገያ፣ አረንጓዴ ስፍራና የስፖርት ሜዳዎችን ያካተተ መንደር እንደሚሆን ተገልጿል።
ከቤት ግንባታው በተጨማሪ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብሩ አካባቢን የማጽዳት፣ የጎርፍ መከላከያ ግንባታ፣ አቅም ለሌላቸው ማዕድ የማጋራት፣ የደም ልገሳ እና የነፃ ህክምና አገልግሎቶች እንደሚሰጡ ከንቲባዋ አስታውቀዋል። በተጨማሪም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ፣ የተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እና የመንገድ ትራፊክ ማሳለጥ ስራዎችን በማከናወን ከተማዋን ለኑሮ ምቹ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቅሷል።
ለዚህ ታላቅ ግንባታ ስኬት የከተማዋ ባለሀብቶች ፈጣን ምላሽ የሰጡ ሲሆን፥ ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ በላይነህ ክንዴ እና ያደታ ጁነዲን እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ባለ 9 ወለል ህንፃ ለመገንባት ቃል ገብተዋል። በተመሳሳይ ቲኤንቲ ኮንስትራክሽን፣ ግራንድ ሌጋሲ ሃውስ፣ ኢቲ ኦንላይን፣ አብይ ማስረሻ፣ ዴማ ሪልስቴት፣ ቴምር ሪልስቴት፣ ስናፕ ትሬዲንግ፣ ጊፍት ሪልስቴት፣ መሃመድ አድናን እና አሚር በድሩ ቀሪዎቹን ህንፃዎች በጋራ ለመገንባት አጋርነታቸውን ማረጋገጣቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸው ምስጋና አቅርበዋል።

በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር 2,500 ዘመናዊ ቤቶች ይገነባሉ፡፡
አዲስ አበባ | ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተያዘው የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር 2,500 የመኖሪያ ቤቶች ይገነባሉ። የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብሩ አካል የሆነውን ይህንን የቤት ግንባታ ፕሮጀክት፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአራዳ ክፍለ ከተማ 8 ባለ ዘጠኝ ወለል ህንፃዎችን ያካተተ "የበጎነት መንደር" ግንባታን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት፣ "የመረጠንን ህዝብ የምናመሰግነው በቃላት ሳይሆን በተግባራዊ ምላሽ ነው" ያሉ ሲሆን፤ ይህ ሜጋ ፕሮጀክት ብልፅግና ፓርቲ በምርጫ ዳግም ኢትዮጵያን ለመምራት ተጨማሪ የአምስት ዓመት እምነት በተሰጠው ማግስት የተጀመረ መሆኑንም ገልጸዋል።
ይህ ታላቅ ፕሮጀክት ከዘመናዊ የመኖሪያ ህንፃዎች በተጨማሪ ባለ 4 ወለል ሁለት የገበያ ማዕከላትን ያካተተ ነው። የበጎነት መንደሩ ለዘመናት የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን በመቀየር ለሰው ልጆች ክብር የሚመጥን ዘመናዊ የጋራ መገልገያዎችን፣ አረንጓዴ ስፍራዎችን እና የስፖርት ሜዳዎችን ያካተተ ይሆናል።
የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በ16 ዓበይት ፕሮግራሞችና በ19 ንዑስ መርሃ ግብሮች የሚተገበር ሲሆን፣ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 5,846 ቤቶችን በመገንባት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ 38,898 ነዋሪዎች ማስተላለፍ ተችሏል።
የዘንድሮው የክረምት የቤት ግንባታ መርሃ ግብር ከሌላው ጊዜ የሚለየው፣ የሚገነቡት 2,500 ቤቶች በሙሉ ከሁለት ወለል በላይ መሆናቸው ነው።

“በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ!”
በአዲስ አበባ ከተማ የ2018 ዓ.ም ዐበይት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራሞችና ዝርዝር መርሀ ግብሮች፤
1) ሰብዓዊና ማህበራዊ አገልግሎት፤
· ቤት ግንባታ መርሀ-ግብር፡- 2500 ቤቶችን በመገንባት ለ12,500 አረጋውያን ፣ አቅመ ደካሞች ፣ አካል ጉዳተኞችን ፣ የሀገር ባለውለታዎች እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ይደረጋሉ፤ በቤት ግንባታ ስራ 7,500 በጎ ፈቃደኞችን ይሳተፋሉ፤
· ማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር፡ 8,150 በጎ ፈቃደኞችን ማሳተፍ፤ 205,000 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
· የትስስር መርሀ ግብር፡- በአንድ ቤተሰብ ለአንድ ሰው የትስስር መርሃ ግብር 33,000 የህብረተሰብ ክፍሎችን ቢያንስ ለ3 ወራትና ከዚያ በላይ የሚዘልቅ ትስስር ይፈጠራል፤ 220 ወላጆቻቸውን ያጡና ለችግር የተጋለጡ ህፃናት አማራጭ ድጋፍ ይመቻችላቸዋል፡፡
2) ልዩ ፍላጎት አገልግሎት፤
· ለ12 የአምዕሮ ህሙማን፣ የአረጋዊያንና የህፃናት መርጃ ማዕከላት በመጎብኘ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ 4800 ወገኖች ተጠቃሚ ይሆናሉ፤
· በ11 ልዩ ፍላጎት የሚሹ ወገኖች ክብካቤ ማዕከላት፣ ተቋማት/ማህበራት 1,100 በጎ ፈቃደኞችን በማሳማራት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡
3)አረንጓዴ አሻራና አካባቢ ጥበቃ አገልግሎት፤
· በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር፡- 400,000 የተለያዩ በጎ ፈቃደኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተሳታፊ ማድረግ፡፡
· በአካባቢ ጽዳት፣ ማስዋብና እንክብካቤ መርሀ ግብር፡- 100,000 የተለያዩ በጎ ፈቃደኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ፡፡
4) ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት፤
· በህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና በኮሪደር ልማት ጥበቃና ማስተባበር መርሀ-ግብር፡- 1,100 በጎ ፈቃደኞችን ይሳተፋሉ፡፡
5) ትምህርት እና ስልጠና አገልግሎት፤
· በክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት መርሀ ግብር፡- በ5 ዋና ዋና የትምህርት ዓይነቶች 41,800 ተማሪዎችን ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
· በአጫጭር የክህሎት ስልጠና መርሀ ግብር፡- በመሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠናና በአጫጭር የክህሎት ስልጠናዎች ላይ 6,600 ተማሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል፡
· በጎልማሶች ትምህርት መርሀ ግብር፡- 5,500 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል፡፡
6) የጤና አገልግሎት፤
· በነፃ ህክምና አገልግሎት መርሀ ግብር፡- የመንግስትና የግል የህክምና ተቋማትንና የህክምና ቡድኖችን በማሳተፍ ለ110,000 የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ይሰጣል፡፡
· በጤና መድህን ደጋፍ መርሃ ግብር፡- ለ 5500 ያህል አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ዓመታዊ የጤና መድህን ሽፋን ድጋፍ ያገኛሉ፤
· በደም ልገሳ መርሀ ግብር፡- 25,000 ዩኒት ደም ይሰበሰባል፤
· በበጎነት በሆስፒታልና በጤና ጣቢያ መርሀ ግብር፡- 3,300 በጎ ፈቃደኞች የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ይሰማራሉ፤ በ12 የመንግስት ሆስፒታሎች ለ1200 ህሙማን የተለያዩ ድጋፎች ይደረጋሉ፡፡
· የመድኃኒት ድጋፍ መርሃ ግብር፡- በህመም ላይ ሆነው የገንዘብ አቅም ለሌላቸው 2,200 የህበረተሰብ ክፍሎች ከግል ፋርማሲዎች ጋር ትስስር በመፍጠር የመድኃኒት ድጋፍ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡
7) የስፖርት ንቅናቄ አገልግሎት፤
· 1,100 በጎ ፈቃደኛ የስፖርት ባለሙያዎችን በማሳተፍ የተለያዩ ስፖርታዊ ስልጠናዎችን እንዲሰጡ ይደረጋል፤
8)የመንገድ ትራፊክ ደህንነት አገልግሎት፤
· በተመረጡ አደባባዮች ላይ 10,000 በጎ ፈቃደኞን በማሰማራት የትራፊክ አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡
9)በተቋማት የበጎ ፈቃድ ድጋፍ አገልግሎት፤
· ተገልጋይ በሚበዛባቸው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት 10,000 በጎ ፈቃደኞች አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡
10)የሙያ በጎ ፈቃድ አገልግሎት፤
· 22,000 በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ በጎ ፈቃደኞች በሙያቸው አገልግሎት እንዲሰጡ ይይረጋል፤ (መምህራን፤ ሃኪሞች፣ ሌሎች)
11)የትውልድ ግንባታ አገልግሎት፤
· በህይወት ልምድ ማካፈል መርሀ ግብር፡- 1,100 ወጣት በጎ ፈቃደኞች ፤ በተለያየ ዘርፍ ስኬትን ካስመዘገቡ ታላላቅ ኢትዮጵያዊያን አርበኞች፣ ከስኬታማ ወጣቶች የህይወት ልምድና ተሞክሮ እንዲማሩ ይደረጋል፡፡
· በቤተ መፅሐፍት ድጋፍ መርሀ ግብር፡- በጎ ፈቃደኞችንና ማህበረሰቡን በማንቀሳቀስ 5,500 መጻህፍትን ለማሰባሰብና ለ11 የትምህርት ቤት መፅሐፍት ቤቶች ድጋፍ ለማድረግ ታቅዷል፡፡
12) የሰላም እሴት ግንባታ አገልግሎት፤
· በሐይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት ላይ 50,000 በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ እንዲያሰተባብሩና የሰላም እሴት ግንባታ ስራዎችን እንዲሰሩ ይደረጋል፡፡
13) ማኅበራዊ ሚዲያ ለበጎነት አገልግሎት፤
· ማህበራዊ ሚድያ ለበጎ ተግባር እንዲውል 12,000 ወጣቶችን ስልጠናና ግንዛቤ በመፍጠር በማህበራዊ ሚድያው በጎ ተፅኖ እንዲፈጥሩ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል፡፡
14) የአደጋ ቅድመ - መከላከል አገልግሎት፤
· ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት የሚሰሩ 2,200 ቅድመ ስልጠና የወሰዱ የአደጋ ተከላካይ በጎ ፈቃደኞች ይሰማራሉ፤
· 110 በጎ ፍቃደኞች በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ወቅት የመጀመሪያ እርዳታ አሰጣጥ ስልጠና ይወስዳሉ፡፡
15) የከተማ ግብርና ልማት አገልግሎት፤
· 11,000 በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ በህዝብ ተቋማትና በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ክፍት ቦታዎችን ወደ ምርታማ የጓሮ አትክት ስፍራ የመለወጥ ስራ ይከናወናል፡፡
· 550 በግብርና ሙያ የተመረቁ ተማሪዎችና ባለሙያዎች በከተማ ግብርና ሳይንስ ዙሪያ ግንዛቤ እንዲሰጡ ይደረጋል፤፤
16)ወሰንና ድንበር የለሽ አገልግሎት፤
· በወሰን የለሽ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር፡- 1,500 በጎ ፈቃደኞችን በተመረጡ ክልሎች በማሰማራት የከተማችንን የበጎ ፈቃድ ተሞክሮ የማስፋፋት ስራ ይከናወናል፡፡
· በስጦታዬ ለሀገሬ መርሀ ግብር፡- የተለያዩ የትምህርት መሳሪያዎችን፣ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችንና አልባሳትን በማሰባሰብ ለ5,200 የክልል እና አጎራባች አካባቢ ተማሪዎችማ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ይደረጋል፡፡
· በድንበር የለሽ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር፡- 30 በጎ ፍቃደኞችን በአጎራባች ሃገራት በአረንጓዴ አሻራ ተግባር ላይ በማሳተፍ በቀጠናው ያለውን ወንድማማችነትና የህዝብ ለህዝብ ትስስር የማጠናከር ስራ ይሰራል፡፡
“በጎነት፤ ለአዲስ አበባ ከፍታ!”

መንግሥት በቀጣይ 5 ዓመታት 1.5 ሚ.
ቤቶችን ለመገንባት ማቀዱ ተገለጸ
የዜጎችን የቤት አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 1.5 ሚሊዮን አዳዲስ ቤቶችን ለመገንባት መዘጋጀቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ይፋ አደረጉ። ሀገሪቱ ባለፉት ሰባት ዓመታት 1.2 ሚሊዮን ቤቶችን መገንባቷን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አዲሱ ግዙፍ ዕቅድ በመንግሥት፣ በግል ዘርፉ እንዲሁም በመንግሥትና የግል አጋርነት (PPP) አማራጮች የሚተገበር መሆኑንና ለዚህ የሚረዳው ፖሊሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መጽደቁን አብራርተዋል።
ይህንን ግንባታ በከተሞችም ሆነ በገጠር በከፍተኛ ፍጥነት ለማሳካት የ3D ቴክኖሎጂን ጨምሮ አዳዲስ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂዎች፣ የሀገር ውስጥ ግብዓት አምራች ፋብሪካዎችና የሰለጠነ የሰው ኃይል በስፋት እየተዘጋጁ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
የቤት ግንባታው በተለይ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ሲሆን፣ የፋይናንስ አቅርቦቱን ለማመቻቸት መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ዜጎች ከሚያገኙት ገቢ ላይ እየቆጠቡ በረጅም ጊዜ ክፍያ የቤት ባለቤት የሚሆኑበት ዘመናዊ ሥርዓት እየተዘረጋ ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ መግዛት ለማይችሉ ወገኖች ደግሞ የመከራየት አማራጭ የሚቀርብበት አሠራር ይመቻቻል ተብሏል።
#ኢትዮጵያ #የቤትግንባታ #ዐቢይአሕመድ #የቤትልማት #ቴክኖሎጂ #Ethiopia #HousingProject #PMAbiyAhmed #3DPrinting #AffordableHousing

❤1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በመዲናዋ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር 10 ሺህ በጎ ፈቃደኞች አገልግሎት በሚበዛባቸው የመንግስት ተቋማት ይሰማራሉ።
በከተማችን የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት በየጊዜው እያደጉ መምጣታቸውን የሚያሳይ "በጎነት በገልግሎት ሰጪ ተቋማት!" የተሰኘ የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር ተጀምሯል። ዛሬ በተካሄደው መድረክ፣ አገልግሎት በሚበዛባቸው የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ውስጥ ተሰማርተው ህዝባቸውን የሚያገለግሉ በጎ ፈቃደኞች የስራ ስምሪት ተሰጥቷቸዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ይመር ከበደ ለበጎ ፈቃደኞች የስራ መመሪያና አቅጣጫ ሰጥተዋል። ዋና ኮሚሽነሩ በንግግራቸው "በጎ ፈቃደኞች በሚሰማሩባቸው ተቋማት ሁሉ ዓለም አቀፍ የበጎ ፈቃድ መርሆዎችን በጥብቅ መከተል ይኖርባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማ ለማድረግ የተቋማቱን የአሰራር እሴቶችና ስነ-ምግባር አክብሮ መስራት ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አስራት ንጉሴ በበኩላቸው፣ በከተማዋ የበጎነት ባህል እንዲዳብርና የህብረተሰቡ የጋራ እሴት እንዲሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ዘርፈ ብዙና አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። ይህ የዛሬው የስምሪት መርሃ-ግብርም የዚሁ ስኬታማ ጉዞ አካል መሆኑን ጠቁመዋል።
የበጎ ፈቃደኞቹን የስራ አካባቢ ምቹ የማድረግና የመደገፍን አስፈላጊነት ያነሱት ደግሞ በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ የቢሮው አማካሪ አቶ አቡበክር ሀሽም ናቸው። አቶ አቡበክር በመንግስት ተቋማት ውስጥ ለሚሰማሩት ለእነዚህ በጎ ፈቃደኞች ተቋማቱ አስፈላጊውን ድጋፍና ቀጣይነት ያለው ክትትል እንደሚያደርጉላቸው አረጋግጠዋል።
ታዋቂው የስራ ፈጣሪና በጎ ፈቃደኛ ኢንጂነር ቢጄአይ ናይከር እና በመከላከያ ሰራዊትነት ለረዥም ጊዜ አገራቸውን ያገለገሉት 50 አለቃ ብርሃኑ አማረ በመድረኩ ተገኝተው ለበጎ ፈቃደኞቹ የረጅም ዘመን የስራ፣ የህይወትና የሀገር ፍቅር ልምዳቸውን አጋርተዋል።
ታዋቂ ግለሰቦች ያጋሩት ልምድና የተሰጣቸው የስራ አቅጣጫ ወደ አገልግሎት ከመግባታቸው በፊት የስነ-ልቦና ዝግጅት እንዲያደርጉ እንዳገዛቸውና መነሳሳት እንደፈጠረላቸው በጎ ፈቃደኞቹ ገልፀዋል።
ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በዜጎች መካከል የመረዳዳትና አብሮነትን የማጠናከር ትልቅ አገራዊ ፋይዳ ይኖረዋል።

👍3❤2
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የኅብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ስራዎች የለውጡ እሳቤ በተግባር የተገለጠባቸው መሆናቸው ተገለጸ።
አዲስ አበባ| ሰኔ 11/2018 ዓ.ም ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ የኅብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ውጤቶች የለውጡ እሳቤ በተግባር የተገለጠባቸው ተግባራት መሆናቸውን የአዲስ አበባ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ ተናገሩ። ምክትል ኮሚሽነሯ ይህንን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያካሄደ በሚገኘው የ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃጸም ግምገማ መድረክ ወቅት ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም እና ያለፉት 5 ዓመታት የስራ አፈፃጸም ግምገማ ከሰኔ 10/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት እየተካሄደ ይገኛል። በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የኮሚሽኑን የስራ አፈፃጸም አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ፤ ባለፉት 5 የለውጥ ዓመታት የህዝብ ተሳትፎን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ረገድ በርካታ ዘርፈ ብዙና ሰው ተኮር የሆኑ ተግባራት ስኬታማ በሆነ መንገድ መከናወናቸውን አስገንዝበዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ቀዳሚ መሪነት የተጀመረው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤት የመገንባት ስራ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ውስጥ ትልቅ እምርታ ማሳየቱን ምክትል ኮሚሽነሯ አብራርተዋል። ይህ የበጎ ፈቃድ ንቅናቄ ቀደም ሲል ከነበረበት የግለሰብ ቤቶች እድሳት ደረጃ በመውጣት፣ በአሁኑ ወቅት ሰፋፊ የሆኑ የ"በጎነት መንደር" ግንባታዎችን ወደ ማካሄድ መሸጋገሩንና በከፍተኛ ደረጃ መስፋቱን አስረድተዋል።
ባለፉት 5 የለውጥ ዓመታት ውስጥ ብቻ በዚህ በጎ እሳቤ ተመርቶ በተከናወነ የተቀናጀ ስራ የዜጎችን ማኅበራዊ አኗኗር የሚመጥኑና የከተማዋን ገጽታ ያዘመኑ ከ46 ሺህ 441 በላይ መኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ለተጠቃሚዎች መተላለፋቸውን ወ/ሮ ፀሐይ ገልጸዋል። አያይዘውም ይሄው አበረታች የበጎ ፈቃድ ስራ በሚቀጥለው የ2019 በጀት ዓመትም ከከተማዋ ሁለንተናዊ እድገትና ለውጥ ጋር ተመጋጋቢ በሆነ መንገድ፣ ይበልጥ በላቀ የሰው ተኮር እሳቤ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በተያዘው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 2 ሺህ 500 አዳዲስ መኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞችና ለችግረኛ ወገኖች ለመገንባት ታቅዶ ርብርብ እየተደረገበት እንደሚገኝና ስራዎችም በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ። በተቋሙ "በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል የሚመሩት እነዚህ ማኅበራዊ አገልግሎቶች የነዋሪውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ያለሙ ናቸው።
#በጎነት_ለአዲስ_አበባ_ከፍታ
#የበጎ_ፈቃድ_አገልግሎት
#humanitarian
#አዲስ_አበባ
#Ethiopia

👍2
የመምህርነት የስራ ቅጥር ምዝገባ ማስታወቂያ!
(ሀምሌ 13/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ10/11/2018 ዓ.ም ያወጣው የመምህርነት የስራ ቅጥር ማስታወቂያ ምዝገባ ከዛሬ ማለትም ከ13/11/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚከናወን ይሆናል፡፡
የመምህርነት የስራ ቅጥር መመዝገቢያ ሊንክ
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfszWEujUr29knX3mhUsQJfzvosKBGCg7Jw2WznB0EsBMybGQ/viewform?usp=publish-editor
(ሀምሌ 13/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ10/11/2018 ዓ.ም ያወጣው የመምህርነት የስራ ቅጥር ማስታወቂያ ምዝገባ ከዛሬ ማለትም ከ13/11/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚከናወን ይሆናል፡፡
የመምህርነት የስራ ቅጥር መመዝገቢያ ሊንክ
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfszWEujUr29knX3mhUsQJfzvosKBGCg7Jw2WznB0EsBMybGQ/viewform?usp=publish-editor
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ኤካ ኮተቢው አጠቃላይ ሆስፒታል በክረምት በጎ ፈቃድ መርሀ ግብር ከ200 ሺህ በላይ ዜጎችን ነፃ የሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚ አደረገ።
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም
በየካ ክፍለ ከተማ የሕክምና ወጪ መሸፈን ለሚቸገሩ በርካታ ነዋሪዎች እፎይታን ሲሰጥ የቆየውና ከ200 ሺህ በላይ ነፃ የሕክምና አገልግሎቶች የተሰጡበት የ11 ቀናት የበጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር ዛሬ ተጠናቋል። በጤና ሚኒስቴር፣ በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል እና በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትብብር የተዘጋጀው ይህ ነፃ የሕክምና አገልግሎት፣ የብዙዎችን የጤና ችግር በመቅረፍና ለዜጎች አስፈላጊውን የሕክምና ድጋፍ ተደራሽ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተገልጿል።
በማጠናቀቂያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የሜዲካል ሴንተሮች መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢሊባቡር ቡኖ እንደተናገሩት፣ በዘንድሮው ዓመት ብቻ በመላ ሀገሪቱ ከ20 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የዚህ ነፃ የሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ። የኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር መገርሳ አለሙ በበኩላቸው፣ ባለፉት 11 ቀናት ለሕብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት በመቻሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ለህክምናው መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ የጤና ባለሙያዎችና አጋር አካላት ምስጋና በማቅረብ መሰል ሰብዓዊ አገልግሎቶች ወደፊትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ኢምሮ፣ ላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የሕክምና ወጪ መሸፈን ለማይችሉ ወገኖች አገልግሎት ሲሰጥ ለቆየው ለኤካ ኮተቤ ሆስፒታልና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል። በዚህ የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር ላይ እንደ ዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተር፣ ላንሴት ሆስፒታል እና ጂአይቪ ሆስፒታል ያሉ የግል ተቋማትም በመሳተፍ የዜጎችን ህይወት ለመታደግ በተደረገው ጥረት ድጋፍ አድርገዋል ሲል የዘገበው የካ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ነው።