የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
637 subscribers
2.17K photos
47 videos
267 links
Download Telegram
በቦሌ ክፍለ ከተማ በህብረተሰብ ተሳትፎ በ112 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የጃክሮስ-ኢቢኤስ የአስፋልት መንገድ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ!

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ጃክሮስ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ኢንዱስትሪ መንደር በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ የተገነባው ዘመናዊ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተመርቋል።

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አደፍርስ ኮራን ጨምሮ አመራሮች፣ የአካባቢው ባለሀብቶችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ፕሮጀክቱ፦
* 1.35 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 10 ሜትር ስፋት
* ደረጃውን የጠበቀ የእግረኛ መንገድ እና የአረንጓዴ ስፍራዎችን
* እንዲሁም በኅብረተሰቡ አቅም 112 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል።
* የሕዝብ አቅምን ማስተባበር ከተቻለ ምን ያህል ታላላቅ ለውጦችን ማምጣት እንደሚቻል ማረጋገጫ ነው።
* የአካባቢው ነዋሪዎች ቀደም ሲል በጭቃና በአቧራ ምክንያት ይደርስባቸው የነበረውን እንግልት በዘላቂነት በመቅረፍ፣ ለአካባቢው የንግድና ኢንቨስትመንት መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

#BoleSubCity #Woreda7 #Infrastructure #RoadProject #AddisAbaba #Ethiopia
👍1
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነባ ባለሁለት ወለል ዘመናዊ ፖሊስ ጣቢያ ተመረቀ።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር በኅብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ እና በመንግስት ትብብር የተገነባ ዘመናዊ የፖሊስ ጣቢያ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። ባለሁለት ወለል (G+1) ህንፃ ሆኖ የተገነባው ይህ ጣቢያ፣ ለፖሊስ አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽነትና ቅልጥፍና ምቹ የሆኑ በቂ የአገልግሎት መስጫ ክፍሎችን አካቶ የያዘ ነው።

በዚሁ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ማህበረሰቡን በማስተባበር የህዝብን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ መመለስ መቻሉን አድንቀዋል። የፖሊስ ጣቢያው መገንባት ህብረተሰቡና ፖሊስ በወንጀል ቅድመ መከላከል ስራዎች ላይ ይበልጥ ተቀራርበውና ተቀናጅተው እንዲሰሩ ለማድረግ ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ በህዝብና መንግስት የጋራ ቅንጅት የተገኘው የላቀ ስኬት፣ በአካባቢው አስተማማኝ ሰላምና ልማትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ለተጀመረው ጉዞ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው። አዲሱ የፖሊስ ጣቢያ ወንጀልን ከመቀነስና የህዝብን ደህንነት ከመጠበቅ አንጻር የላቀ ሚና የሚጫወት ነው።

በህዝብና መንግስት ቅንጅት የአካባቢያችንን ሰላምና ልማት እናረጋግጣለን!

#KolfeKeranio #CommunityPolicing #PeaceAndSecurity #AddisAbaba #Ethiopia
👍42
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በበጋ የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም የተገነቡ ከ20 በላይ የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላለፉ።

በክፍለ ከተማው በሚገኙ ልዩ ልዩ ወረዳዎች በጥቅሉ ከ20 በላይ የሚሆኑ የአቅመ ደካማና አረጋውያን መኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ለባለቤቶቻቸው ተረክበዋል።

የቤት ግንባታ ተጠቃሚ የሆኑት ወ/ሮ አሰገደች አሰፋ ከዚህ ቀደም ይኖሩበት የነበረው ቤት በጣም የተጎሳቆለ፣ ለዝናብና ለፀሀይ የተጋለጠ በመሆኑ ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገው እንደነበር ይናገራሉ። ዛሬ ቤታቸው በሚያስደስት ደረጃ ተገንብቶ በመረከባቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ለበጎ ፈቃደኞች ምስጋና አቅርበዋል።

ሌላኛው የቤት ግንባታው ተጠቃሚ አቶ አያሌው ይማም በበኩላቸው፣ ለብዙ ዓመታት ለመኖሪያነት ፍፁም በማይመችና ሙሉ በሙሉ ቆርቆሮ በቆርቆሮ በነበረ ጠባብ ቤት ውስጥ ይኖሩ እንደነበር ገልጸው፤ "ዛሬ ያ አሰቃቂ ታሪክ ተቀይሮ ቤታችን በብሉኬት ተሰርቶና ዘምኖ በመረከባችን የተሰማንን ደስታ በቃል መግለጽ ይከብዳል" ሲሉ አስተያየታቸውን መስጠታቸውን የላፍቶ ኮሙኒኬሽን ዘገባ ያመለክታል።

የክፍለ ከተማው ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ብዙአየሁ መኮንን ዛሬ ለተጠቃሚዎች የተላለፉት ቤቶች በበጋ ወቅት በልዩ ትኩረት በእቅድ ተይዘው ሲከናወኑ የቆዩ መሆናቸውን ጠቁመው ፕሮጀክቶቹ ከጅምር እስከ ፍጻሜ ስኬታማ እንዲሆኑ ከጎናቸው ላልተለዩ ቅን ባለሀብቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች ምስጋና አቅርበዋል።

በከተማችን ለአቅመ ደካሞች፣ ለአረጋውያን እንዲሁም ለሀገር ባለውለታዎች ደረጃቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ከመስጠት ባለፈ፤ የተዛመሙ ጎጆዎችን ባሉበት መልሶ በመገንባት ለኑሮ ምቹ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል።
👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በአዲስ አበባ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር 2,500 ቤቶች ሊገነቡ ነው

አዲስ አበባ| ሰኔ 15/2018 ዓ.ም፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተጀመረው የቤት ግንባታና የአካባቢ ማደስ ፕሮጀክት፥ የመንግስትን ፖለቲካዊ ቃል ኪዳን ወደ መሬት የመቀየር ስትራቴጂ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ። ከንቲባዋ "የመረጠንን ህዝብ የምናመሰግነው በቃላት ሳይሆን በተግባራዊ ምላሽ ነው" ያሉ ሲሆን፥ ይህም ብልፅግና ፓርቲ በምርጫ ዳግም ኢትዮጵያን ለመምራት ተጨማሪ የአምስት ዓመት እምነት በተሰጠው ማግስት የተጀመረ መሆኑን ገልጸዋል።

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በከተማ ደረጃ 2,500 ቤቶችን ለመገንባት የታቀደ ሲሆን፥ የዚሁ አካል የሆነውና ከከንቲባ ፅህፈት ቤት በስተጀርባ የሚገነባው የ“አራዳ የበጎነት መንደር” ግንባታ በይፋ ተጀምሯል። ይህ ሜጋ ፕሮጀክት ባለ 9 ወለል 8 ዘመናዊ የመኖሪያ ህንፃዎችን እና ባለ 4 ወለል ሁለት የገበያ ማዕከላትን ያካተተ ሲሆን፥ ለዘመናት የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን በመቀየር ለሰው ልጆች ክብር የሚመጥን ዘመናዊ የጋራ መገልገያ፣ አረንጓዴ ስፍራና የስፖርት ሜዳዎችን ያካተተ መንደር እንደሚሆን ተገልጿል።

ከቤት ግንባታው በተጨማሪ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብሩ አካባቢን የማጽዳት፣ የጎርፍ መከላከያ ግንባታ፣ አቅም ለሌላቸው ማዕድ የማጋራት፣ የደም ልገሳ እና የነፃ ህክምና አገልግሎቶች እንደሚሰጡ ከንቲባዋ አስታውቀዋል። በተጨማሪም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ፣ የተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እና የመንገድ ትራፊክ ማሳለጥ ስራዎችን በማከናወን ከተማዋን ለኑሮ ምቹ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቅሷል።

ለዚህ ታላቅ ግንባታ ስኬት የከተማዋ ባለሀብቶች ፈጣን ምላሽ የሰጡ ሲሆን፥ ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ በላይነህ ክንዴ እና ያደታ ጁነዲን እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ባለ 9 ወለል ህንፃ ለመገንባት ቃል ገብተዋል። በተመሳሳይ ቲኤንቲ ኮንስትራክሽን፣ ግራንድ ሌጋሲ ሃውስ፣ ኢቲ ኦንላይን፣ አብይ ማስረሻ፣ ዴማ ሪልስቴት፣ ቴምር ሪልስቴት፣ ስናፕ ትሬዲንግ፣ ጊፍት ሪልስቴት፣ መሃመድ አድናን እና አሚር በድሩ ቀሪዎቹን ህንፃዎች በጋራ ለመገንባት አጋርነታቸውን ማረጋገጣቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸው ምስጋና አቅርበዋል።
👍1
በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር 2,500 ዘመናዊ ቤቶች ይገነባሉ፡፡
አዲስ አበባ | ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተያዘው የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር 2,500 የመኖሪያ ቤቶች ይገነባሉ። የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብሩ አካል የሆነውን ይህንን የቤት ግንባታ ፕሮጀክት፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአራዳ ክፍለ ከተማ 8 ባለ ዘጠኝ ወለል ህንፃዎችን ያካተተ "የበጎነት መንደር" ግንባታን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት፣ "የመረጠንን ህዝብ የምናመሰግነው በቃላት ሳይሆን በተግባራዊ ምላሽ ነው" ያሉ ሲሆን፤ ይህ ሜጋ ፕሮጀክት ብልፅግና ፓርቲ በምርጫ ዳግም ኢትዮጵያን ለመምራት ተጨማሪ የአምስት ዓመት እምነት በተሰጠው ማግስት የተጀመረ መሆኑንም ገልጸዋል።
ይህ ታላቅ ፕሮጀክት ከዘመናዊ የመኖሪያ ህንፃዎች በተጨማሪ ባለ 4 ወለል ሁለት የገበያ ማዕከላትን ያካተተ ነው። የበጎነት መንደሩ ለዘመናት የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን በመቀየር ለሰው ልጆች ክብር የሚመጥን ዘመናዊ የጋራ መገልገያዎችን፣ አረንጓዴ ስፍራዎችን እና የስፖርት ሜዳዎችን ያካተተ ይሆናል።
የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በ16 ዓበይት ፕሮግራሞችና በ19 ንዑስ መርሃ ግብሮች የሚተገበር ሲሆን፣ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 5,846 ቤቶችን በመገንባት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ 38,898 ነዋሪዎች ማስተላለፍ ተችሏል።
የዘንድሮው የክረምት የቤት ግንባታ መርሃ ግብር ከሌላው ጊዜ የሚለየው፣ የሚገነቡት 2,500 ቤቶች በሙሉ ከሁለት ወለል በላይ መሆናቸው ነው።
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
“በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ!”
በአዲስ አበባ ከተማ የ2018 ዓ.ም ዐበይት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራሞችና ዝርዝር መርሀ ግብሮች፤
1) ሰብዓዊና ማህበራዊ አገልግሎት፤
· ቤት ግንባታ መርሀ-ግብር፡- 2500 ቤቶችን በመገንባት ለ12,500 አረጋውያን ፣ አቅመ ደካሞች ፣ አካል ጉዳተኞችን ፣ የሀገር ባለውለታዎች እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ይደረጋሉ፤ በቤት ግንባታ ስራ 7,500 በጎ ፈቃደኞችን ይሳተፋሉ፤
· ማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር፡ 8,150 በጎ ፈቃደኞችን ማሳተፍ፤ 205,000 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
· የትስስር መርሀ ግብር፡- በአንድ ቤተሰብ ለአንድ ሰው የትስስር መርሃ ግብር 33,000 የህብረተሰብ ክፍሎችን ቢያንስ ለ3 ወራትና ከዚያ በላይ የሚዘልቅ ትስስር ይፈጠራል፤ 220 ወላጆቻቸውን ያጡና ለችግር የተጋለጡ ህፃናት አማራጭ ድጋፍ  ይመቻችላቸዋል፡፡
2) ልዩ ፍላጎት አገልግሎት፤
· ለ12 የአምዕሮ ህሙማን፣ የአረጋዊያንና የህፃናት መርጃ ማዕከላት በመጎብኘ  የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ 4800 ወገኖች ተጠቃሚ ይሆናሉ፤
· በ11 ልዩ ፍላጎት የሚሹ ወገኖች ክብካቤ ማዕከላት፣ ተቋማት/ማህበራት  1,100 በጎ ፈቃደኞችን በማሳማራት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡
3)አረንጓዴ አሻራና አካባቢ ጥበቃ አገልግሎት፤
· በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር፡- 400,000 የተለያዩ በጎ ፈቃደኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተሳታፊ ማድረግ፡፡
· በአካባቢ ጽዳት፣ ማስዋብና እንክብካቤ መርሀ ግብር፡- 100,000 የተለያዩ በጎ ፈቃደኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ፡፡
4) ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት፤
· በህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና በኮሪደር ልማት ጥበቃና ማስተባበር መርሀ-ግብር፡-  1,100 በጎ ፈቃደኞችን ይሳተፋሉ፡፡
5) ትምህርት እና ስልጠና አገልግሎት፤
· በክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት መርሀ ግብር፡- በ5 ዋና ዋና የትምህርት ዓይነቶች 41,800 ተማሪዎችን ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
· በአጫጭር የክህሎት ስልጠና መርሀ ግብር፡- በመሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠናና በአጫጭር የክህሎት ስልጠናዎች ላይ 6,600 ተማሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል፡    
· በጎልማሶች ትምህርት መርሀ ግብር፡- 5,500 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል፡፡
6) የጤና አገልግሎት፤
· በነፃ ህክምና አገልግሎት  መርሀ ግብር፡- የመንግስትና የግል የህክምና ተቋማትንና የህክምና ቡድኖችን በማሳተፍ ለ110,000 የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ይሰጣል፡፡
· በጤና መድህን ደጋፍ መርሃ ግብር፡- ለ 5500 ያህል አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ዓመታዊ የጤና መድህን ሽፋን ድጋፍ ያገኛሉ፤
· በደም ልገሳ መርሀ ግብር፡- 25,000 ዩኒት ደም ይሰበሰባል፤
· በበጎነት በሆስፒታልና በጤና ጣቢያ መርሀ ግብር፡- 3,300 በጎ ፈቃደኞች የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ይሰማራሉ፤ በ12 የመንግስት ሆስፒታሎች ለ1200 ህሙማን የተለያዩ ድጋፎች ይደረጋሉ፡፡
· የመድኃኒት ድጋፍ መርሃ ግብር፡- በህመም ላይ ሆነው የገንዘብ አቅም ለሌላቸው 2,200 የህበረተሰብ ክፍሎች ከግል ፋርማሲዎች ጋር ትስስር በመፍጠር የመድኃኒት ድጋፍ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡
7) የስፖርት ንቅናቄ አገልግሎት፤
· 1,100 በጎ ፈቃደኛ የስፖርት ባለሙያዎችን በማሳተፍ የተለያዩ ስፖርታዊ ስልጠናዎችን እንዲሰጡ ይደረጋል፤
8)የመንገድ ትራፊክ ደህንነት አገልግሎት፤
· በተመረጡ አደባባዮች ላይ 10,000 በጎ ፈቃደኞን በማሰማራት የትራፊክ አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡
9)በተቋማት የበጎ ፈቃድ ድጋፍ አገልግሎት፤ 
· ተገልጋይ በሚበዛባቸው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት 10,000 በጎ ፈቃደኞች አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡
10)የሙያ በጎ ፈቃድ አገልግሎት፤
· 22,000 በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ በጎ ፈቃደኞች በሙያቸው አገልግሎት እንዲሰጡ ይይረጋል፤ (መምህራን፤ ሃኪሞች፣ ሌሎች)
11)የትውልድ ግንባታ አገልግሎት፤
· በህይወት ልምድ ማካፈል መርሀ ግብር፡- 1,100 ወጣት በጎ ፈቃደኞች ፤ በተለያየ ዘርፍ ስኬትን ካስመዘገቡ ታላላቅ ኢትዮጵያዊያን አርበኞች፣ ከስኬታማ ወጣቶች የህይወት ልምድና ተሞክሮ እንዲማሩ ይደረጋል፡፡
· በቤተ መፅሐፍት ድጋፍ መርሀ ግብር፡- በጎ ፈቃደኞችንና ማህበረሰቡን በማንቀሳቀስ 5,500 መጻህፍትን ለማሰባሰብና ለ11 የትምህርት ቤት መፅሐፍት ቤቶች ድጋፍ ለማድረግ ታቅዷል፡፡
12)   የሰላም እሴት ግንባታ አገልግሎት፤
· በሐይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት ላይ 50,000 በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ እንዲያሰተባብሩና የሰላም እሴት ግንባታ ስራዎችን እንዲሰሩ ይደረጋል፡፡
13) ማኅበራዊ ሚዲያ ለበጎነት አገልግሎት፤
· ማህበራዊ ሚድያ ለበጎ ተግባር እንዲውል 12,000 ወጣቶችን ስልጠናና ግንዛቤ በመፍጠር በማህበራዊ ሚድያው በጎ ተፅኖ እንዲፈጥሩ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል፡፡
14)   የአደጋ ቅድመ - መከላከል አገልግሎት፤
· ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት የሚሰሩ 2,200 ቅድመ ስልጠና የወሰዱ የአደጋ ተከላካይ በጎ ፈቃደኞች ይሰማራሉ፤
· 110 በጎ ፍቃደኞች በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ወቅት የመጀመሪያ እርዳታ አሰጣጥ ስልጠና ይወስዳሉ፡፡
15)   የከተማ ግብርና ልማት አገልግሎት፤
· 11,000 በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ በህዝብ ተቋማትና በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ክፍት ቦታዎችን ወደ ምርታማ የጓሮ አትክት ስፍራ የመለወጥ ስራ ይከናወናል፡፡
· 550 በግብርና ሙያ የተመረቁ ተማሪዎችና ባለሙያዎች በከተማ ግብርና ሳይንስ ዙሪያ ግንዛቤ እንዲሰጡ ይደረጋል፤፤
16)ወሰንና ድንበር የለሽ አገልግሎት፤
·  በወሰን የለሽ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር፡- 1,500 በጎ ፈቃደኞችን በተመረጡ ክልሎች በማሰማራት የከተማችንን የበጎ ፈቃድ ተሞክሮ የማስፋፋት ስራ ይከናወናል፡፡
· በስጦታዬ ለሀገሬ መርሀ ግብር፡- የተለያዩ የትምህርት መሳሪያዎችን፣ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችንና አልባሳትን በማሰባሰብ ለ5,200 የክልል እና አጎራባች አካባቢ ተማሪዎችማ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ይደረጋል፡፡
· በድንበር የለሽ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር፡- 30 በጎ ፍቃደኞችን በአጎራባች ሃገራት በአረንጓዴ አሻራ  ተግባር ላይ በማሳተፍ በቀጠናው ያለውን ወንድማማችነትና የህዝብ ለህዝብ ትስስር  የማጠናከር ስራ ይሰራል፡፡
“በጎነት፤ ለአዲስ አበባ ከፍታ!”
መንግሥት በቀጣይ 5 ዓመታት 1.5 ሚ.
ቤቶችን ለመገንባት ማቀዱ ተገለጸ

የዜጎችን የቤት አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 1.5 ሚሊዮን አዳዲስ ቤቶችን ለመገንባት መዘጋጀቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ይፋ አደረጉ። ሀገሪቱ ባለፉት ሰባት ዓመታት 1.2 ሚሊዮን ቤቶችን መገንባቷን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አዲሱ ግዙፍ ዕቅድ በመንግሥት፣ በግል ዘርፉ እንዲሁም በመንግሥትና የግል አጋርነት (PPP) አማራጮች የሚተገበር መሆኑንና ለዚህ የሚረዳው ፖሊሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መጽደቁን አብራርተዋል።

ይህንን ግንባታ በከተሞችም ሆነ በገጠር በከፍተኛ ፍጥነት ለማሳካት የ3D ቴክኖሎጂን ጨምሮ አዳዲስ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂዎች፣ የሀገር ውስጥ ግብዓት አምራች ፋብሪካዎችና የሰለጠነ የሰው ኃይል በስፋት እየተዘጋጁ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

የቤት ግንባታው በተለይ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ሲሆን፣ የፋይናንስ አቅርቦቱን ለማመቻቸት መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ዜጎች ከሚያገኙት ገቢ ላይ እየቆጠቡ በረጅም ጊዜ ክፍያ የቤት ባለቤት የሚሆኑበት ዘመናዊ ሥርዓት እየተዘረጋ ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ መግዛት ለማይችሉ ወገኖች ደግሞ የመከራየት አማራጭ የሚቀርብበት አሠራር ይመቻቻል ተብሏል።

#ኢትዮጵያ #የቤትግንባታ #ዐቢይአሕመድ #የቤትልማት #ቴክኖሎጂ #Ethiopia #HousingProject #PMAbiyAhmed #3DPrinting #AffordableHousing
1