የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
826 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የተገነቡ የአቅመ ደካሞችና አረጋውያን ቤቶች ተመርቀው ለተጠቃሚዎች ተላለፉ።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር የተገነቡ 6 ልፍሎች ያሉት የG+1 ቤት ግንባታው ተጠናቆ ዛሬ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።

የህንፃው፦
* የቦታው ስፋት፦230 ካሬ ሜትር
* የክፍሎች ብዛት፦ 30 ቤተሰቦችን ተጠቃሚ ያደረጉ 6 መኖሪያ ክፍሎችን አካቷል።

ይህ ላለፉት ዓመታት በመንግስት ልዩ ትኩረት ሲሰራበት የቆየው የቤት ግንባታ ከቤት እድሳት ተግባር ተነስቶ ዛሬ ላይ ወደ በጎነት መንደር ግዙፍ ፕሮጀክቶች ያደገ ሲሆን ለማኅበራዊ ችግር የተጋለጡ ወገኖቻችንን ህይወት ለመቀየር የተደረገ የከተማችን ትልቅ ስኬት ነው።

አቅመ ደካሞችንና የሀገር ባለውለታዎችን ለመደገፍ ባለሀብቶችንና ማህበረሰቡን በማስተባበር የተጀመሩ ሰው ተኮር ስራዎቻች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል።

ለዚህ መልካም ተግባር መሳካት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እያበረከታችሁ ያላችሁ ባለድርሻ አካላት፣ ተቋማትና ድርጅቶች በሙሉ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን!

አብሮነትና በጎነት ይለምልም!

#kirkos #Voluntarism #HumanCenteredProjects #AddisAbaba #Ethiopia
በቦሌ ክፍለ ከተማ በህብረተሰብ ተሳትፎ በ112 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የጃክሮስ-ኢቢኤስ የአስፋልት መንገድ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ!

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ጃክሮስ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ኢንዱስትሪ መንደር በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ የተገነባው ዘመናዊ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተመርቋል።

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አደፍርስ ኮራን ጨምሮ አመራሮች፣ የአካባቢው ባለሀብቶችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ፕሮጀክቱ፦
* 1.35 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 10 ሜትር ስፋት
* ደረጃውን የጠበቀ የእግረኛ መንገድ እና የአረንጓዴ ስፍራዎችን
* እንዲሁም በኅብረተሰቡ አቅም 112 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል።
* የሕዝብ አቅምን ማስተባበር ከተቻለ ምን ያህል ታላላቅ ለውጦችን ማምጣት እንደሚቻል ማረጋገጫ ነው።
* የአካባቢው ነዋሪዎች ቀደም ሲል በጭቃና በአቧራ ምክንያት ይደርስባቸው የነበረውን እንግልት በዘላቂነት በመቅረፍ፣ ለአካባቢው የንግድና ኢንቨስትመንት መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

#BoleSubCity #Woreda7 #Infrastructure #RoadProject #AddisAbaba #Ethiopia
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነባ ባለሁለት ወለል ዘመናዊ ፖሊስ ጣቢያ ተመረቀ።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር በኅብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ እና በመንግስት ትብብር የተገነባ ዘመናዊ የፖሊስ ጣቢያ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። ባለሁለት ወለል (G+1) ህንፃ ሆኖ የተገነባው ይህ ጣቢያ፣ ለፖሊስ አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽነትና ቅልጥፍና ምቹ የሆኑ በቂ የአገልግሎት መስጫ ክፍሎችን አካቶ የያዘ ነው።

በዚሁ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ማህበረሰቡን በማስተባበር የህዝብን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ መመለስ መቻሉን አድንቀዋል። የፖሊስ ጣቢያው መገንባት ህብረተሰቡና ፖሊስ በወንጀል ቅድመ መከላከል ስራዎች ላይ ይበልጥ ተቀራርበውና ተቀናጅተው እንዲሰሩ ለማድረግ ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ በህዝብና መንግስት የጋራ ቅንጅት የተገኘው የላቀ ስኬት፣ በአካባቢው አስተማማኝ ሰላምና ልማትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ለተጀመረው ጉዞ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው። አዲሱ የፖሊስ ጣቢያ ወንጀልን ከመቀነስና የህዝብን ደህንነት ከመጠበቅ አንጻር የላቀ ሚና የሚጫወት ነው።

በህዝብና መንግስት ቅንጅት የአካባቢያችንን ሰላምና ልማት እናረጋግጣለን!

#KolfeKeranio #CommunityPolicing #PeaceAndSecurity #AddisAbaba #Ethiopia
👍31