የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
826 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
አዲሱ የአራዳ ፓርክ፦ የታሪክ፣ የውበትና የዘመናዊነት መገናኛ !

የአራዳ ፓርክ የጉስቁልና ታሪክን፣ የቆሻሻና የብክለት ስጋትን እንዲሁም የአስከፊ ድህነትን ገጽታ የቀየርንበት ታላቅ ፕሮጀክት ነው። የባዕዳንን አሉታዊ የታሪክ አሻራዎች በመናድ፣ የኢትዮጵያን ውበትና የትውልድን አዲስ ታሪክ በጋራ በማተም አዲሱን ማንነታችንን ገንብተናል።

ከፒያሳ አካባቢ የተነሱ ነዋሪዎቻችንን ለሰው ልጅ ክብር ከማይመጥኑና ከተጎሳቆሉ መኖሪያዎች አውጥተን፤ እጅግ ጤናማ፣ ነፋሻማና ሰብአዊ ክብርን የሚመጥን መሰረተ ልማት የተሟላለት መኖሪያ “ቤት ለእምቦሳ” ብለን አስረክበናል። ማህበራዊ መስተጋብራቸው ሳይቋረጥ እድርና እቁባቸውን ጠብቀው በጋራ እንዲኖሩም አድርገናል። ፒያሳን መልሰን ስንገነባ እውነተኛ ስልጣኔንና አራድነትን በሚያሳይ መልኩ ነው። ወንዞቻችን ከቆሻሻና ከበሽታ አምጪነት ተላቀው ዛሬ የቱሪስት መዳረሻ፣ የተፈጥሮ ውበት መገለጫና የሥራ ዕድል መፍጠሪያ ሆነዋል።

የአራዳ ፓርክ በ40 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ የተቀናጀ የመሰረተ ልማትና የአገልግሎት ማዕከል ሲሆን፣ በውስጡ የሚከተሉትን ዋና ዋና አገልግሎቶች ይዟል፦
1. የትራንስፖርትና የመንገድ መሰረተ ልማቶች
• የአስፓልት መንገድ፦ 5 ኪ.ሜ. የሚረዝም የውስጥ ለውስጥ መንገድ።
• የእግረኛ መንገድ፦ 6 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ምቹ የእግር ጉዞ መስመር።
• የብስክሌት መስመር፦ 5 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው የሳይክል ሌን።
• የመሮጫ ትራክ፦ 5 ኪ.ሜ. የሚረዝም ለስፖርተኞች የተዘጋጀ መስመር።
2. የንግድና የፋይናንስ አገልግሎቶች
• የንግድ ሱቆች፦ ከፒያሳ ለተነሱ ነጋዴዎች ቅድሚያ የተሰጠባቸው 131 ዘመናዊ ሱቆች።
• ምግብና መጠጥ፦ 7 ካፌዎችና ሬስቶራንቶች።
• ግብይትና ባንክ፦ 1 ትልቅ ሱፐርማርኬት እና 1 የባንክ ቅርንጫፍ።
3. የስፖርት፣ የኪነ-ጥበብና የመዝናኛ መገልገያዎች
• ዘመናዊ የስፖርት አሬና፦ አንድ (1) ዘመናዊ የአካል ብቃት ማዕከል (Gym) እና 7 አዳራሾች።
• መድረኮች፦ 8 ፕላዛዎችና 3 አንፊ-ቴአትሮች (ለተለያዩ ኩነቶች ማዘጋጃ የሚውሉ)።
• ልዩ ውበት፦ በአይነቱ ልዩ የሆነ “ዳንሲንግ ፋውንቴን” (ተንቀሳቃሽ ፏፏቴ)።
• ብሔራዊ ምልክት፦ በሀገራችን ረጅሙ የሆነው ባለ 100 ሜትር የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ መስቀያ።
4. ለሕፃናትና ለቤተሰብ
• የሕፃናት መጫወቻ፦ 4 በሚገባ የተሟሉ ዘመናዊ የመጫወቻ ስፍራዎች።
• ትንሿ ከተማ፦ ሕፃናት ስለ ሀገራቸው እውቀት የሚቀስሙበትና የሚዝናኑበት ልዩ ስፍራ።
5. የተፈጥሮ ልማትና የንፅህና አገልግሎቶች
• አረንጓዴ ልማት፦ 15 ሄክታር መሬት በሳርና በተክሎች የተሸፈነ፣ በፓርኩ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ 22 የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች።
• ፓርኪንግ፦ በአንድ ጊዜ 131 መኪናዎችን መያዝ የሚችል ሰፊ ማቆሚያ ወዘተ አገልግሎቶችን አካትቷል።
የአራዳ ፓርክ የመሬት አጠቃቀምን በላቀ ደረጃ ጥቅም ላይ ያዋለ ፕሮጀክት ነው። መሬትን ከስር ለሱቅና ለአዳራሽ፣ ከላይ ደግሞ ለፕላዛ በመጠቀም ውስን የሆነውን የከተማ መሬት በብቃት ተጠቅመናል።

በተጨማሪም በአካባቢው የነበሩ ከ700 በላይ ቤቶችና ሕንፃዎች ታሪካዊ ይዘታቸውን ጠብቀው እንዲታደሱ ተደርጓል።
ይህ ፓርክ ከንግድ እስከ ስፖርት፣ ከቤተሰብ መዝናኛ እስከ ዓለም አቀፍ የኪነ-ጥበብ መድረኮችን አጣምሮ የያዘ የከተማዋ አዲስ የቱሪስት መዳረሻ ነው።
እንኳን ደስ አለን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
2👍1
የአዲስ አበባ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ በከንቲባ አዳነች አቤቤ የቀረቡለትን ሹመቶች አጽድቋል፡፡

በዚሁ መሰረት

1ኛ. አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ፣

2ኛ. አቶ አሰግደዉ ኃ/ጊዮርጊስ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ፣

3ኛ. አቶ ሰለሞን ዲባባ - የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነዉ ተሹመዋል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ለ2018 ዓ.ም 9 ነጥብ 94 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት አጽድቋል፡፡

ከዚህ ውስጥ 8 ነጥብ 5 ቢሊየን ብሩ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች በፌደራል መንግስት ለተሰጠ የደመወዝ ድጎማ እንዲሁም 996 ሚሊየን ብሩ ለከተማዋ የልማት ሥራዎች የሚውል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤው በጥቅሉ 9 ነጥብ 94 ቢሊየን ብር በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
3
ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ዕጩዎች ሹመትን አጸደቀ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤቱን የፍትሕና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን ዕጩዎች ሹመት አጽድቋል፡፡

አቶ በላይ ደጀን በምክር ቤቱ የፍትሕና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነዉ ተሹመዋል፡፡

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን አቅም እና ተደራሽነት ይበልጥ ለማጠናከር በቀረበዉ ሹመት መሰረት

1ኛ. አቶ ሞገስ ባልቻ - የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ

2ኛ. ነብዩ ባዬ - የሥራ አመራር ቦርድ አባል

3ኛ. አቶ ሠለሞን ካሳ - የሥራ አመራር ቦርድ አባል

4ኛ. ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ -የሥራ አመራር ቦርድ አባል

5ኛ. ሚኤሳ ኤሌማ (ዶ/ር)-የሥራ አመራር ቦርድ አባል

6 ኛ. ወ/ሮ ዘሃራ መሃመድ - የሥራ አመራር ቦርድ አባል ሆነዉ ተሹመዋል፡፡
4
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የተገነቡ የአቅመ ደካሞችና አረጋውያን ቤቶች ተመርቀው ለተጠቃሚዎች ተላለፉ።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር የተገነቡ 6 ልፍሎች ያሉት የG+1 ቤት ግንባታው ተጠናቆ ዛሬ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።

የህንፃው፦
* የቦታው ስፋት፦230 ካሬ ሜትር
* የክፍሎች ብዛት፦ 30 ቤተሰቦችን ተጠቃሚ ያደረጉ 6 መኖሪያ ክፍሎችን አካቷል።

ይህ ላለፉት ዓመታት በመንግስት ልዩ ትኩረት ሲሰራበት የቆየው የቤት ግንባታ ከቤት እድሳት ተግባር ተነስቶ ዛሬ ላይ ወደ በጎነት መንደር ግዙፍ ፕሮጀክቶች ያደገ ሲሆን ለማኅበራዊ ችግር የተጋለጡ ወገኖቻችንን ህይወት ለመቀየር የተደረገ የከተማችን ትልቅ ስኬት ነው።

አቅመ ደካሞችንና የሀገር ባለውለታዎችን ለመደገፍ ባለሀብቶችንና ማህበረሰቡን በማስተባበር የተጀመሩ ሰው ተኮር ስራዎቻች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል።

ለዚህ መልካም ተግባር መሳካት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እያበረከታችሁ ያላችሁ ባለድርሻ አካላት፣ ተቋማትና ድርጅቶች በሙሉ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን!

አብሮነትና በጎነት ይለምልም!

#kirkos #Voluntarism #HumanCenteredProjects #AddisAbaba #Ethiopia
በቦሌ ክፍለ ከተማ በህብረተሰብ ተሳትፎ በ112 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የጃክሮስ-ኢቢኤስ የአስፋልት መንገድ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ!

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ጃክሮስ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ኢንዱስትሪ መንደር በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ የተገነባው ዘመናዊ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተመርቋል።

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አደፍርስ ኮራን ጨምሮ አመራሮች፣ የአካባቢው ባለሀብቶችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ፕሮጀክቱ፦
* 1.35 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 10 ሜትር ስፋት
* ደረጃውን የጠበቀ የእግረኛ መንገድ እና የአረንጓዴ ስፍራዎችን
* እንዲሁም በኅብረተሰቡ አቅም 112 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል።
* የሕዝብ አቅምን ማስተባበር ከተቻለ ምን ያህል ታላላቅ ለውጦችን ማምጣት እንደሚቻል ማረጋገጫ ነው።
* የአካባቢው ነዋሪዎች ቀደም ሲል በጭቃና በአቧራ ምክንያት ይደርስባቸው የነበረውን እንግልት በዘላቂነት በመቅረፍ፣ ለአካባቢው የንግድና ኢንቨስትመንት መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

#BoleSubCity #Woreda7 #Infrastructure #RoadProject #AddisAbaba #Ethiopia
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነባ ባለሁለት ወለል ዘመናዊ ፖሊስ ጣቢያ ተመረቀ።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር በኅብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ እና በመንግስት ትብብር የተገነባ ዘመናዊ የፖሊስ ጣቢያ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። ባለሁለት ወለል (G+1) ህንፃ ሆኖ የተገነባው ይህ ጣቢያ፣ ለፖሊስ አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽነትና ቅልጥፍና ምቹ የሆኑ በቂ የአገልግሎት መስጫ ክፍሎችን አካቶ የያዘ ነው።

በዚሁ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ማህበረሰቡን በማስተባበር የህዝብን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ መመለስ መቻሉን አድንቀዋል። የፖሊስ ጣቢያው መገንባት ህብረተሰቡና ፖሊስ በወንጀል ቅድመ መከላከል ስራዎች ላይ ይበልጥ ተቀራርበውና ተቀናጅተው እንዲሰሩ ለማድረግ ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ በህዝብና መንግስት የጋራ ቅንጅት የተገኘው የላቀ ስኬት፣ በአካባቢው አስተማማኝ ሰላምና ልማትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ለተጀመረው ጉዞ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው። አዲሱ የፖሊስ ጣቢያ ወንጀልን ከመቀነስና የህዝብን ደህንነት ከመጠበቅ አንጻር የላቀ ሚና የሚጫወት ነው።

በህዝብና መንግስት ቅንጅት የአካባቢያችንን ሰላምና ልማት እናረጋግጣለን!

#KolfeKeranio #CommunityPolicing #PeaceAndSecurity #AddisAbaba #Ethiopia
👍31