የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በመዲናዋ በ9 ወራት ውስጥ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ለበርካታ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ተችሏል።
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸሙ ከ4.9 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ገንዘብ በርካታ የአካባቢ መሰረተ ልማት ጥያቄዎችን መመለስ ችሏል። ኮሚሽኑ በከተማዋ የነዋሪዎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻልና የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ በኪሎ ሜትር የሚለኩና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በስኬት አጠናቋል።
በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 188.5 ኪሎ ሜትር የሰቤዝ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለኮብልስቶን ንጣፍ ስራ ዝግጁ ተደርጓል። የኅብረተሰቡን ተሳትፎ በማስተባበር 57.6 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የውስጥ ለውስጥ የጠጠር መንገድ ግንባታ የተከናዎነ ሲሆን 174.5 ኪሎ ሜትር የድንጋይ ንጣፍ (Cobblestone) ጥገና ተጠናቋል።
ኮሚሽኑ የህዝብን አቅም ለአካባቢ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት በሚያስችል ስልት በመጠቀም 39 አነስተኛ ድልድዮችን፣ 42 የማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ማዕከላትን እንዲሁም 104 የጋራ መፀዳጃ ቤቶችን ገንብቶ ለተጠቃሚዎች አስተላልፏል።
በዘጠኝ ወራት ውስጥ 58.4 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ መብራት ዝርጋታ፣ 93.1 ኪ.ሜትር የቴራዞ መንገድ ግንባታ፣ 460.8 ኪዩቢክ ሜትር የድጋፍ ግንብ እንዲሁም 79 ኪሎ ሜትር የውኃ መፋሰሻ ቱቦ ግንባታ ስራ ተከናውኗል።
በተከናወኑ የአካባቢ ልማት ስራዎችም ከ1.7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የተፈታ ሲሆን 8 ሺህ 715 ስራ ፈላጎ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ እድል እና ከ771 ሚሊዮን ብር በላይ የገበያ ትሥስር አግኝተዋል።
#አዲስአበባ #የልማትዳታ #በጎፈቃድ #የመሠረተልማት #የ9ወራትሪፖርት #ኢትዮጵያዊነት

የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፤ በስራና ክህሎት ዘርፍ በለውጡ ዓመታት ኢትዮጵያ ያስመዘገበችውን ስኬቶች አብራርተዋል። ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት በማድረግና ብቁ የሰው ሀብት እንዲሁም ምቹ እና አስተማማኝ የሥራ ዕድል የተፈጠረባት ኢትዮጵያን ማየት የተለመው ይህ ዘርፍ፤ ከለውጡ በኋላ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የስራ ስመሪት እንዲሁም ዜጎች በቤት ውስጥ እና ባሉበት ሆነው በሚሰሯቸው ስራዎች አማካኝነት ለ19,872,846 ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል።
ይህን ታላቅ ስኬት ለማስመዝገብ ያስቻለው፤ ኢንተርፕርነር ተቋማትን በመፍጠር፣ ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር ተቋማት ጋር አጋርነት በመፍጠር፣ የቢዝነስ መስፋፋት እና የልህቀት ማዕከላት በማሳደግ፣ ቲቬት ዲጂታላይዜሽን በማረጋገጥ ሰፊ ስራዎች በመተግበራቸው የተገኘ ውጤት ነው።
#PMOEthiopia

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ዓበይት ስኬቶችን ባቀረቡት ሪፖርት፦ ዘርፉ ከለውጡ በፊት የነበሩ ክፍተቶችን በመለየት ካስመዘገባቸው ዋና ዋና ስኬቶች መካከል፤ ለ30 ዓመታት የቆየው የጤና ፓሊሲን በመከለስ፣ መከላከል ከሚለው መርህ በተጨማሪ አክሞ የማዳን ቁርጠኛ የፖሊሲ አመራር፣ የተቋም ግንባታ፣ የጤና መሠረተ ልማት ለውጦች፣ መድሃኒት፣ ክትባት እና የህክምና ግብዓቶች ምርት አቅርቦት እና ቁጥጥር ጭማሪ እንዲሁም የጤና ፋይናንስ እመርታ ቁልፍ እና ዋነኞቹ የለውጥ ስራዎች ናቸው።
በተለይም የወረርሽኝ ልየታ እና ቁጥጥር፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ፣ የጤና ባለሙያዎችን ማብቃትና ቁጥራቸውን ማሳደግ፤ የዲጂታል ጤና፣ በዘርፉ የተተገበሩ ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ኢትዮጵያ በጤና ዘርፍ ያስመዘገበቻቸው ግንባር ቀደም ስኬቶቿ ናቸው።
የጤና ዲፕሎማሲ ዘርፍ ከፍ ያሉ እመርታዎች የተመዘገበበት አንዱና ዋነኛው መስክ ሲሆን ኢትዮጵያ በተለያዩ መድረኮች ከአፍሪካ በቀዳሚነት ተመርጣ ድርድሮችን እና ንግግሮችን እንድትመራ አስችሏታል።

👍1
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በትምህርት ዘርፍ የተመዘገቡ ዓበይት ስኬቶችን አቅርበዋል።
ከለውጡ በፊት የትምህርቱ ዘርፍ በእጅጉ የተጎዳ፣ ሰፊ እና አፋጣኝ ተሀድሶ ከሚያስፈልጋቸው ዘርፎች አንዱ ነበር። ዘርፉን በእጅጉ ተጭነውት ከነበሩ ችግሮች መካከል፤ የመሠረተ ልማት ጥራትና የግብዓት እጥረት፣ የተማሪ-መምህር፣ የተማሪ-ክፍል ጥመርታ አለመመጣጠን፣ ለትምህርት ዓይነቶች ብቁ የሆኑ መምህራን አለመኖር፣ የስርዓተ ትምህርት አግባብነትና የመጻህፍት ተደራሽነት ችግሮች፣ ኢ-ፍትሃዊነትና ኢ-እኩልነት፣ የትምህርት ሴክተሩ ትክክለኛነት መዳከም፣ ዝቅተኛ የቅድመ መደበኛ ትምህርት መኖር ከብዙ ማነቆዎች ጥቂቶች ነበሩ።
በዚህም በጥናት በተደገፈ መልኩ፤ የትምህርት ዘርፉን ፍላጎቶች እና ተግዳሮቶች በመለየት ከተመዘገቡ ዋና ዋና ለውጦች መካከል፤ የሥርዓተ-ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ፣ የመፅሃፍት ህትመት ስርጭትና ተደራሽነት፣ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት፣ የቅድመ መደበኛ ትምህርትን ማሳደግ፣ የትምህርት ቤት ደረጃ ማሻሻል፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሪፎርም፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን እና ዲጂታል ትምህርት መስፋፋት፣ የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ዝግጅትና አስተዳደር መሻሻል፣ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማደግ ዋነኞቹ በለውጡ ተግባራዊ የሆኑና ውጤት ያስገኙ ሆነው ተመዝግበዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በሚኒስትር መስሪያቤታቸው የተመዘገቡ ዐበይት ስኬቶችን አቅርበዋል።
በዚህም ዘርፉ ከለውጡ በፊት ሲቸገርበት የነበሩ መጠነ ሰፊ ክፍተቶችን በመለየት ፈጣን መፍትሔ በመስጠት ሰፊ ስኬቶችን አስመዝግቧል።
ከተገኙ ስኬቶች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦
የፖሊሲና የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት የዜጎችን መብት ጥበቃ፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ። አደረጃጀቶችን በመደገፍና በማጠናከር መብትና ግዴታ በማወቅ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ የአቅመ ደካማ ዜጎችን የመደገፍና የማገዝ ባህል ማሳደግ ጥቂቶቹ ናቸው።
እነዚህ ስኬቶች ቁጥር ብቻ ሳይሆኑ በተጨባጭ 4,330,948 የሚሆኑ ወጣቶች እና 26,845,686 ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የተቻለበት ትልቅ ስኬትም ጭምር እንጂ! ከዚህ በተጨማሪም የሴቶችንና ወጣቶችን የፖለቲካ ተሳትፎን ከማሳደግ አኳያ ሰፊ ስራ ተሰርቶ ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
በተጨማሪም ዘርፉ ካስመዘገባቸው ስኬቶች መካከል የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አንዱና ዋነኛው ሲሆን በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ ተጋላጭ ሆነው ድጋፍ የተደረገላቸው ዜጎች፣ ከጎዳና ላይ የተነሱ ዜጎች፣ የተሀድሶ አገልግሎት ያገኙ አካል ጉዳተኞች፣ በማህበረሰብ እንክብካቤ ጥምረቶች የተሰበሰበ ሀብት ዋነኞቹ ስኬቶች ናቸው።

❤2
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ሹመት አጸደቀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
የቦርድ አባላቱን ሹመት አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት በምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ምህረቱ ሻንቆ (ዶ/ር) ተሿሚዎቹ በትምህርት ዝግጅት እንዲሁም ባዳበሩት ክህሎት የድርጅቱን ተልእኮ ማሳካት የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ብሔራዊ ጥቅምን መረዳት የሚችሉ እንዲሁም ተቋሙን ለስኬት እንደሚያበቁ የታመነባቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዚህም ፦
1፡- ብሌን ማሞ ....... የቦርድ ሰብሳቢ
2፡- ፈዲላ ቢያ ....... አባል
3፡- ተስፋዬ ዘውዴ ....... አባል
4፡- መሐመድ ካሳ ....... አባል
5፡- አፈወርቅ በደዊ ....... አባል
6፡- አስማ ረዲ ....... አባል
7፡- ዮናስ በቀለ ....... አባል
8፡- ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር ....... አባል
9፡- ኢሳያስ ካሳ (ዶ/ር)....... አባል ሆነው እንዲሾሙ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ምክር ቤቱ መርምሮ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
ተሿሚዎችም በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ-መሀላ ፈጽመዋል።

አዲስ አበባን “ እንደ ስሟ ውብ አዲስ አበባ “እናደርጋታለን ስንል ቅድሚያ የሰጠነው ለሰው ነው፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለሰዉ ትኩረት ሰጥተን ማህበራዊ ፍትሕን ለማንገስ በሰው አኗኗር እና በሰው የኑሮ ላይ ውጤታማ ስራ ሰርተናል።
የአዲስ አበባ ህጻናት ባዶ የምሳ እቃ ይዘው መራብ የለባቸውም ብለን ለልጆች ምግብና ዩኒፎርም በጀት በመመደብ ለትውልድ ግንባታ ሰርተናል። በመሆኑም ልጆች ሲማሩ ዋና ትኩረታቸው ትምህርት ላይ እንዲያደርጉ ደብተር፣ እስክርቢቶ፣ ቦርሳ፣ የኒፎርም የትምህርት ቁሳቁሶችን እንዲያገኙ በማድረግ በከተማችን የትምህርት ውጤት ከፍ እንዲል ማድረግ ተችሏል።
አረጋውያን፣ ለሀገር ውለታ የዋሉ፣ በተለያዩ ማህበራዊ ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን ምግብ ሊቸገሩ አይገባቸውም ብለን በከተማችን 30 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላትን በመገንባት እነዚህ ወገኖቻችን ረግመውን ሳይሆን እየባረኩን እንዲያልፉ የሚችል ስራ ተከናውኗል።
በከተማችን ሴተኛ አዳሪዎችን ህይወት ለመለወጥ በተገነባው ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ከአስከፊ ህይወት እንዲወጡና በተጨባጭ የሥራ ባለቤት እየሆኑ ነዉ።
#addisababa
#Ethiopia

❤1
የአራዳ ፓርክ አዲስ አበባን ለመለወጥ ያለንን ርዕይ በተግባር ያሳየንበት አንዱ ስራችን ነው። ቀደም ሲል ተዘንግቶና ለአደጋ ተጋልጦ የነበረው የአራዳ አካባቢ፣ ዛሬ ተመልሶ ተገንብቶ አስደናቂ የከተማ አካል መሆን ችሏል።
ኢትዮጵያ ለእኛ፤ በምናብ የምትሳል ህልም ብቻ ሳትሆን በተግባር የምትገነባ እውነታ ናት። ጤናማ፣ ጽኑ፣ ለመጭው ትውልድ ተስፋን ከተጨባጭ ሀብት ጋር የምትሰጥ፣ በአፍሪካ መሪ፣ በዓለም መድረክ ደግሞ ተወዳዳሪ የሆነች ሀገር እየገነባን እንገኛለን! በየቀኑም ይህንን ተስፋ ወደ እውነታ የመለወጥ ተግባራችንን እንቀጥላለን።
Once a neglected and hazardous area, the Arada district has been reimagined into a magnificent urban sanctuary.
For us, Ethiopia is not merely a dream to be envisioned, it is a reality to be built. We are building a nation that is healthy, resilient, and full of promise for future generations that is also a leader in Africa and a formidable competitor on the global stage. Each day, we continue to turn this promise into reality.

አዲሱ የአራዳ ፓርክ፦ የታሪክ፣ የውበትና የዘመናዊነት መገናኛ !
የአራዳ ፓርክ የጉስቁልና ታሪክን፣ የቆሻሻና የብክለት ስጋትን እንዲሁም የአስከፊ ድህነትን ገጽታ የቀየርንበት ታላቅ ፕሮጀክት ነው። የባዕዳንን አሉታዊ የታሪክ አሻራዎች በመናድ፣ የኢትዮጵያን ውበትና የትውልድን አዲስ ታሪክ በጋራ በማተም አዲሱን ማንነታችንን ገንብተናል።
ከፒያሳ አካባቢ የተነሱ ነዋሪዎቻችንን ለሰው ልጅ ክብር ከማይመጥኑና ከተጎሳቆሉ መኖሪያዎች አውጥተን፤ እጅግ ጤናማ፣ ነፋሻማና ሰብአዊ ክብርን የሚመጥን መሰረተ ልማት የተሟላለት መኖሪያ “ቤት ለእምቦሳ” ብለን አስረክበናል። ማህበራዊ መስተጋብራቸው ሳይቋረጥ እድርና እቁባቸውን ጠብቀው በጋራ እንዲኖሩም አድርገናል። ፒያሳን መልሰን ስንገነባ እውነተኛ ስልጣኔንና አራድነትን በሚያሳይ መልኩ ነው። ወንዞቻችን ከቆሻሻና ከበሽታ አምጪነት ተላቀው ዛሬ የቱሪስት መዳረሻ፣ የተፈጥሮ ውበት መገለጫና የሥራ ዕድል መፍጠሪያ ሆነዋል።
የአራዳ ፓርክ በ40 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ የተቀናጀ የመሰረተ ልማትና የአገልግሎት ማዕከል ሲሆን፣ በውስጡ የሚከተሉትን ዋና ዋና አገልግሎቶች ይዟል፦
1. የትራንስፖርትና የመንገድ መሰረተ ልማቶች
• የአስፓልት መንገድ፦ 5 ኪ.ሜ. የሚረዝም የውስጥ ለውስጥ መንገድ።
• የእግረኛ መንገድ፦ 6 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ምቹ የእግር ጉዞ መስመር።
• የብስክሌት መስመር፦ 5 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው የሳይክል ሌን።
• የመሮጫ ትራክ፦ 5 ኪ.ሜ. የሚረዝም ለስፖርተኞች የተዘጋጀ መስመር።
2. የንግድና የፋይናንስ አገልግሎቶች
• የንግድ ሱቆች፦ ከፒያሳ ለተነሱ ነጋዴዎች ቅድሚያ የተሰጠባቸው 131 ዘመናዊ ሱቆች።
• ምግብና መጠጥ፦ 7 ካፌዎችና ሬስቶራንቶች።
• ግብይትና ባንክ፦ 1 ትልቅ ሱፐርማርኬት እና 1 የባንክ ቅርንጫፍ።
3. የስፖርት፣ የኪነ-ጥበብና የመዝናኛ መገልገያዎች
• ዘመናዊ የስፖርት አሬና፦ አንድ (1) ዘመናዊ የአካል ብቃት ማዕከል (Gym) እና 7 አዳራሾች።
• መድረኮች፦ 8 ፕላዛዎችና 3 አንፊ-ቴአትሮች (ለተለያዩ ኩነቶች ማዘጋጃ የሚውሉ)።
• ልዩ ውበት፦ በአይነቱ ልዩ የሆነ “ዳንሲንግ ፋውንቴን” (ተንቀሳቃሽ ፏፏቴ)።
• ብሔራዊ ምልክት፦ በሀገራችን ረጅሙ የሆነው ባለ 100 ሜትር የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ መስቀያ።
4. ለሕፃናትና ለቤተሰብ
• የሕፃናት መጫወቻ፦ 4 በሚገባ የተሟሉ ዘመናዊ የመጫወቻ ስፍራዎች።
• ትንሿ ከተማ፦ ሕፃናት ስለ ሀገራቸው እውቀት የሚቀስሙበትና የሚዝናኑበት ልዩ ስፍራ።
5. የተፈጥሮ ልማትና የንፅህና አገልግሎቶች
• አረንጓዴ ልማት፦ 15 ሄክታር መሬት በሳርና በተክሎች የተሸፈነ፣ በፓርኩ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ 22 የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች።
• ፓርኪንግ፦ በአንድ ጊዜ 131 መኪናዎችን መያዝ የሚችል ሰፊ ማቆሚያ ወዘተ አገልግሎቶችን አካትቷል።
የአራዳ ፓርክ የመሬት አጠቃቀምን በላቀ ደረጃ ጥቅም ላይ ያዋለ ፕሮጀክት ነው። መሬትን ከስር ለሱቅና ለአዳራሽ፣ ከላይ ደግሞ ለፕላዛ በመጠቀም ውስን የሆነውን የከተማ መሬት በብቃት ተጠቅመናል።
በተጨማሪም በአካባቢው የነበሩ ከ700 በላይ ቤቶችና ሕንፃዎች ታሪካዊ ይዘታቸውን ጠብቀው እንዲታደሱ ተደርጓል።
ይህ ፓርክ ከንግድ እስከ ስፖርት፣ ከቤተሰብ መዝናኛ እስከ ዓለም አቀፍ የኪነ-ጥበብ መድረኮችን አጣምሮ የያዘ የከተማዋ አዲስ የቱሪስት መዳረሻ ነው።
እንኳን ደስ አለን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

❤2👍1
የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ ፕሮግራም ስኬቶች
https://youtu.be/55-1vnlnZGQ?si=4hnG6GxBMSynYHoC

YouTube
የተቀናጀ የሞዴል ብሎክ ልማት፡ የአዲስ አበባ አዲስ ገጽታ! (Kirkos Model Blocks)
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተተገበረ የሚገኘው የተቀናጀ የሞዴል ብሎክ ልማት ፕሮግራም የአካባቢን ውበት ከመጠበቅ ባለፈ የነዋሪዎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል። ይህ አጭር ቪዲዮ የፕሮግራሙን ዋና ዋና ስኬቶች እና በከተማዋ የፈጠረውን አዎንታዊ ተፅዕኖ ያሳያል።
The Integrated Model Block Development Program, currently being implemented…

የአዲስ አበባ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ በከንቲባ አዳነች አቤቤ የቀረቡለትን ሹመቶች አጽድቋል፡፡
በዚሁ መሰረት
1ኛ. አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ፣
2ኛ. አቶ አሰግደዉ ኃ/ጊዮርጊስ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ፣
3ኛ. አቶ ሰለሞን ዲባባ - የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነዉ ተሹመዋል፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ ለ2018 ዓ.ም 9 ነጥብ 94 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት አጽድቋል፡፡
ከዚህ ውስጥ 8 ነጥብ 5 ቢሊየን ብሩ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች በፌደራል መንግስት ለተሰጠ የደመወዝ ድጎማ እንዲሁም 996 ሚሊየን ብሩ ለከተማዋ የልማት ሥራዎች የሚውል መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤው በጥቅሉ 9 ነጥብ 94 ቢሊየን ብር በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

❤3
ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ዕጩዎች ሹመትን አጸደቀ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤቱን የፍትሕና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን ዕጩዎች ሹመት አጽድቋል፡፡
አቶ በላይ ደጀን በምክር ቤቱ የፍትሕና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነዉ ተሹመዋል፡፡
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን አቅም እና ተደራሽነት ይበልጥ ለማጠናከር በቀረበዉ ሹመት መሰረት
1ኛ. አቶ ሞገስ ባልቻ - የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ
2ኛ. ነብዩ ባዬ - የሥራ አመራር ቦርድ አባል
3ኛ. አቶ ሠለሞን ካሳ - የሥራ አመራር ቦርድ አባል
4ኛ. ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ -የሥራ አመራር ቦርድ አባል
5ኛ. ሚኤሳ ኤሌማ (ዶ/ር)-የሥራ አመራር ቦርድ አባል
6 ኛ. ወ/ሮ ዘሃራ መሃመድ - የሥራ አመራር ቦርድ አባል ሆነዉ ተሹመዋል፡፡

❤4
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የተገነቡ የአቅመ ደካሞችና አረጋውያን ቤቶች ተመርቀው ለተጠቃሚዎች ተላለፉ።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር የተገነቡ 6 ልፍሎች ያሉት የG+1 ቤት ግንባታው ተጠናቆ ዛሬ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።
የህንፃው፦
* የቦታው ስፋት፦230 ካሬ ሜትር
* የክፍሎች ብዛት፦ 30 ቤተሰቦችን ተጠቃሚ ያደረጉ 6 መኖሪያ ክፍሎችን አካቷል።
ይህ ላለፉት ዓመታት በመንግስት ልዩ ትኩረት ሲሰራበት የቆየው የቤት ግንባታ ከቤት እድሳት ተግባር ተነስቶ ዛሬ ላይ ወደ በጎነት መንደር ግዙፍ ፕሮጀክቶች ያደገ ሲሆን ለማኅበራዊ ችግር የተጋለጡ ወገኖቻችንን ህይወት ለመቀየር የተደረገ የከተማችን ትልቅ ስኬት ነው።
አቅመ ደካሞችንና የሀገር ባለውለታዎችን ለመደገፍ ባለሀብቶችንና ማህበረሰቡን በማስተባበር የተጀመሩ ሰው ተኮር ስራዎቻች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል።
ለዚህ መልካም ተግባር መሳካት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እያበረከታችሁ ያላችሁ ባለድርሻ አካላት፣ ተቋማትና ድርጅቶች በሙሉ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን!
አብሮነትና በጎነት ይለምልም!
#kirkos #Voluntarism #HumanCenteredProjects #AddisAbaba #Ethiopia

በቦሌ ክፍለ ከተማ በህብረተሰብ ተሳትፎ በ112 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የጃክሮስ-ኢቢኤስ የአስፋልት መንገድ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ!
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ጃክሮስ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ኢንዱስትሪ መንደር በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ የተገነባው ዘመናዊ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተመርቋል።
በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አደፍርስ ኮራን ጨምሮ አመራሮች፣ የአካባቢው ባለሀብቶችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ፕሮጀክቱ፦
* 1.35 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 10 ሜትር ስፋት
* ደረጃውን የጠበቀ የእግረኛ መንገድ እና የአረንጓዴ ስፍራዎችን
* እንዲሁም በኅብረተሰቡ አቅም 112 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል።
* የሕዝብ አቅምን ማስተባበር ከተቻለ ምን ያህል ታላላቅ ለውጦችን ማምጣት እንደሚቻል ማረጋገጫ ነው።
* የአካባቢው ነዋሪዎች ቀደም ሲል በጭቃና በአቧራ ምክንያት ይደርስባቸው የነበረውን እንግልት በዘላቂነት በመቅረፍ፣ ለአካባቢው የንግድና ኢንቨስትመንት መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
#BoleSubCity #Woreda7 #Infrastructure #RoadProject #AddisAbaba #Ethiopia