የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
826 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እንኳን ደስ አለዎት!

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው በመሾምዎ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እንኳን ደስ አለን ለማለት እወዳለሁ።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን የጥረታቸው ፍሬ በአፍሪካ ደረጃ እውቅና አግኝቶ ለዚህ ሹመት መብቃታቸው ለኢትዮጵያን ሁሉ ኩራት ነው ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ !
3👍1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ከሰአት በኋላ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀብለዋል። የመሪዎቹ ግንኙነት ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር በኢትዮጵያ የሚያደርጉት የሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት አካል ነው። የመሪዎቹ ውይይት በሁለትዮሽ ግንኙነቶች እና የወል የትብብር መስኮችን በማጠናከር ላይ እንደሚያጠነጥን ይጠበቃል።

Prime Minister Abiy Ahmed receives H.E. Salva Kiir Mayardit, President of the Republic of South Sudan, at the National Palace this afternoon. The meeting takes place as part of President Kiir’s two-day official visit to Ethiopia. Discussions are expected to focus on bilateral relations and advancing areas of mutual cooperation.

#PMOEthiopia
2
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ቅጠል ተራን  ወደ ውብ መኖሪያ ሥፍራ!

ለመኖር እጅግ ምቹ ያልሆነ፤ ለሰው ልጅ ክብር በማይመጥን፤ በጣም የቆሸሸ፣ የተፋፈገ እና የተጨናነቀ እንዲሁም ከተማ እምብርት ላይ ሆነው በተተበተበ ለአደጋ አጋላጭ  የሆነ የኤሌክትሪክ  መስመር ብሎም በኩራዝና  በሻማ የሚጠቀሙ ነዋሪዎች ይኖሩበት የነበረውን የቅጠል ተራ ሰፈርን፣ ወደ ውብ መኖሪያ አካባቢነት ለመቀየር ዛሬ ባለ 8 ወለል የሆኑ ብዛታቸው 9 ህንጻዎች ከ500 በላይ ቤቶችን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠናል።

ይህ ፕሮጀክት አካባቢው መንገድ ያልነበረው፣ እንደ ሸረሪት ድር የተጠላለፉ ገመዶች የበዙበት፣  ነዎሪዎች በድህነት ምክንያት ኑሯቸውን ለመደጎም ቤታቸው ውስጥ ቆጥ ሰርተው አልጋ  የሚያከራዩበትና ሰዎች ላይ ቆልፈው በሚሄዱበት ጊዜ በሚፈጠር የእሳት አደጋ የሰዎች ህይወት የሚጠፋበት፣ ንብረት የሚወድምበት፣ እጅግ ብዙ ገመናዎችን የያዘ  አስከፊ  የሰው ህይወትን  የሚቀይር  ፕሮጀክት ነው።

አካባቢው የከተማ እምብርት ሆኖ ሳለ፣ ነገር ግን በብዙዎቹ  የገጠር አካባቢዎች እንኳን የቀረውን ሻማ እና ኩራዝ የሚጠቀም ነዋሪ ያለበት አካባቢ ነው።

መርካቶ አካባቢ ብዙ  “ተራ”  የሚል ስያሜ የተሰጣቸው - ቅጠል ተራ፣ ጭድ ተራ፣ ገብስ ተራ፣ ሳር ተራ፣  ቦንብ ተራ … ጠጋ ብለን ስናያቸው የነዋሪዎቻችን የአኗኗር ሁኔታ እና ገፅታውን የሚያሳዩ ናቸው። እንደዚህ ዓይነት ችግሮችን ደጋግመን በማውራት ነዋሪው ሆድ እንዲብሰው ማድረግ ሳይሆን፣ መፍትሄው ሰርተን ህይወቱ እንዲቀየር እና ለሰው ልጆች የሚመጥን የክብር ኑሮ እንዲኖር እዚያው የመኖሪያ ቤት እና የንግድ ቦታዎች እንዲያገኝ ማድረግ ነው ።

በከተማችን ዋነኛ የስራዎቻችንን ማዕከል ሰው ተኮር ስራዎች አድርገን እየሰራን እንገኛለን ።
በቅጠል ተራ ያስጀመርነው የቤት ግንባታ 10ሺህ ካሬ ላይ ያረፈ፤ ተገንብቶ ሲጠናቀቅም ከ20,000  በላይ ሰዎችን ንፁህ፤  ለሰው ክብር የሚመጥን ዘመናዊ አኗኗር ያለው መኖሪያ ቤት  ተጠቃሚ የሚያደርግ ትልቅ ፕሮጅክት ነው ።

ፕሮጀክቱ ልጆች ቦርቀው እንዲያድጉ የስፖርት ሜዳ እንዲሁም የንግድ ሱቆች እና  ሊሎች አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ ተሟልተውለት  በጥራት እና በፍጥነት ተገንብቶ ይጠናቀቃል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
1
የከተማ አስተዳደራችንን የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረናል።

በበጀት ዓመቱ በእቅድ ከያዝናቸው ተግባራት 96 በመቶ መፈፀም ችለናል።

ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የግምገማ መድረክ በበጅት ዓመቱ ለመፈፀም ካቀድናቸው ውስጥ በ9 ወራት በጥብቅ ክትትል የተከናወኑትን የምንገመግምበት እና በቀሪ ወራት የትኩረት ማዕከል አድርገን የምንፈፅማቸው በመልካም አስተዳደር ተለይተው ያልተመለሱትን ምላሽ በመስጠት ማጠናቀቅ፣ የኑሮ ውድነትን የሚያባብሱ ችግሮችን በመቀነስ የዋጋ ንረትን መከላከል፣ የገበያ ማዛባት ችግሮችን መከላከል፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በመሶብ ዲጅታል የአንድ ማዕከል የመንግስት አገልግሎት የጀመርነውን ውጤታማ ስራ በቀሪ ወራት በተሟላ ሁኔታ በማጠናቀቅና ወደ ስራ ማስገባት እንዲሁም ቀሪ አገልግሎቶችን ዲጅታላይዝ አድርጎ ወደ መሶብ ማስገባት፣ ተጀምረው በዚህ ዓመት መጠናቀቅ ያለባቸውን ፕሮጀክቶች በፍጥነትና በጥራት ማጠናቀቅ የአፈፃፀም ግምገማ ማዕከላችን ይሆናሉ።

ባለፋት አምስት ዓመታት የእቅድ አፈፃፀማችን ከ90 በመቶ በላይ እያደገ መጥቶ በ2018 ደግሞ 96 በመቶ የደረሰበት ውጤታማ አፈፃፀም መኖሩን በመገምገም፣ ይህንን እያደገ የመጣ የመፈፀም ልምድ አጠናክረን መቀጠል እንድንችል በትኩረት እንገመግማለን ።

በተጨማሪም 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ነፃ፣ ተዓማኒና ገለልተኛ ሆኖ እንዲከናወን ሁሉም አመራራችን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ትልቅ ሃላፊነት መወጣት እንዲችሉ የግምገማ አቅጣጫን አስቀምጠናል።

የነበሩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል፣ ጉድለቶችን በመሙላት በቀሪዎች ወራት በላቀ መፈፀም የግምግማችን ማዕከል ይሆናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍3
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በመዲናዋ በ9 ወራት ውስጥ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ለበርካታ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ተችሏል።

አዲስ አበባ | ሚያዚያ 2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸሙ ከ4.9 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ገንዘብ በርካታ የአካባቢ መሰረተ ልማት ጥያቄዎችን መመለስ ችሏል። ኮሚሽኑ በከተማዋ የነዋሪዎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻልና የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ በኪሎ ሜትር የሚለኩና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በስኬት አጠናቋል።

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 188.5 ኪሎ ሜትር የሰቤዝ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለኮብልስቶን ንጣፍ ስራ ዝግጁ ተደርጓል። የኅብረተሰቡን ተሳትፎ በማስተባበር 57.6 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የውስጥ ለውስጥ የጠጠር መንገድ ግንባታ የተከናዎነ ሲሆን 174.5 ኪሎ ሜትር የድንጋይ ንጣፍ (Cobblestone) ጥገና ተጠናቋል።

ኮሚሽኑ የህዝብን አቅም ለአካባቢ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት በሚያስችል ስልት በመጠቀም 39 አነስተኛ ድልድዮችን፣ 42 የማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ማዕከላትን እንዲሁም 104 የጋራ መፀዳጃ ቤቶችን ገንብቶ ለተጠቃሚዎች አስተላልፏል።

በዘጠኝ ወራት ውስጥ 58.4 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ መብራት ዝርጋታ፣ 93.1 ኪ.ሜትር የቴራዞ መንገድ ግንባታ፣ 460.8 ኪዩቢክ ሜትር የድጋፍ ግንብ እንዲሁም 79 ኪሎ ሜትር የውኃ መፋሰሻ ቱቦ ግንባታ ስራ ተከናውኗል።

በተከናወኑ የአካባቢ ልማት ስራዎችም ከ1.7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የተፈታ ሲሆን 8 ሺህ 715 ስራ ፈላጎ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ እድል እና ከ771 ሚሊዮን ብር በላይ የገበያ ትሥስር አግኝተዋል።

#አዲስአበባ #የልማትዳታ #በጎፈቃድ #የመሠረተልማት #የ9ወራትሪፖርት #ኢትዮጵያዊነት
የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፤ በስራና ክህሎት ዘርፍ በለውጡ ዓመታት ኢትዮጵያ ያስመዘገበችውን ስኬቶች አብራርተዋል። ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት በማድረግና ብቁ የሰው ሀብት እንዲሁም ምቹ እና አስተማማኝ የሥራ ዕድል የተፈጠረባት ኢትዮጵያን ማየት የተለመው ይህ ዘርፍ፤ ከለውጡ በኋላ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የስራ ስመሪት እንዲሁም ዜጎች በቤት ውስጥ እና ባሉበት ሆነው በሚሰሯቸው ስራዎች አማካኝነት ለ19,872,846 ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል።

ይህን ታላቅ ስኬት ለማስመዝገብ ያስቻለው፤ ኢንተርፕርነር ተቋማትን በመፍጠር፣ ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር ተቋማት ጋር አጋርነት በመፍጠር፣ የቢዝነስ መስፋፋት እና የልህቀት ማዕከላት በማሳደግ፣ ቲቬት ዲጂታላይዜሽን በማረጋገጥ ሰፊ ስራዎች በመተግበራቸው የተገኘ ውጤት ነው።

#PMOEthiopia
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ዓበይት ስኬቶችን ባቀረቡት ሪፖርት፦ ዘርፉ ከለውጡ በፊት የነበሩ ክፍተቶችን በመለየት ካስመዘገባቸው ዋና ዋና ስኬቶች መካከል፤ ለ30 ዓመታት የቆየው የጤና ፓሊሲን በመከለስ፣ መከላከል ከሚለው መርህ በተጨማሪ አክሞ የማዳን ቁርጠኛ የፖሊሲ አመራር፣ የተቋም ግንባታ፣ የጤና መሠረተ ልማት ለውጦች፣ መድሃኒት፣ ክትባት እና የህክምና ግብዓቶች ምርት አቅርቦት እና ቁጥጥር ጭማሪ እንዲሁም የጤና ፋይናንስ እመርታ ቁልፍ እና ዋነኞቹ የለውጥ ስራዎች ናቸው።

‎በተለይም የወረርሽኝ ልየታ እና ቁጥጥር፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ፣ የጤና ባለሙያዎችን ማብቃትና ቁጥራቸውን ማሳደግ፤ የዲጂታል ጤና፣ በዘርፉ የተተገበሩ ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ኢትዮጵያ በጤና ዘርፍ ያስመዘገበቻቸው ግንባር ቀደም ስኬቶቿ ናቸው።

የጤና ዲፕሎማሲ ዘርፍ ከፍ ያሉ እመርታዎች የተመዘገበበት አንዱና ዋነኛው መስክ ሲሆን ኢትዮጵያ በተለያዩ መድረኮች ከአፍሪካ በቀዳሚነት ተመርጣ ድርድሮችን እና ንግግሮችን እንድትመራ አስችሏታል።

#PMOEthiopia
👍1
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በትምህርት ዘርፍ የተመዘገቡ ዓበይት ስኬቶችን አቅርበዋል።

ከለውጡ በፊት የትምህርቱ ዘርፍ በእጅጉ የተጎዳ፣ ሰፊ እና አፋጣኝ ተሀድሶ ከሚያስፈልጋቸው ዘርፎች አንዱ ነበር። ዘርፉን በእጅጉ ተጭነውት ከነበሩ ችግሮች መካከል፤ የመሠረተ ልማት ጥራትና የግብዓት እጥረት፣ የተማሪ-መምህር፣ የተማሪ-ክፍል ጥመርታ አለመመጣጠን፣ ለትምህርት ዓይነቶች ብቁ የሆኑ መምህራን አለመኖር፣ የስርዓተ ትምህርት አግባብነትና የመጻህፍት ተደራሽነት ችግሮች፣ ኢ-ፍትሃዊነትና ኢ-እኩልነት፣ የትምህርት ሴክተሩ ትክክለኛነት መዳከም፣ ዝቅተኛ የቅድመ መደበኛ ትምህርት መኖር ከብዙ ማነቆዎች ጥቂቶች ነበሩ።

በዚህም በጥናት በተደገፈ መልኩ፤ የትምህርት ዘርፉን ፍላጎቶች እና ተግዳሮቶች በመለየት ከተመዘገቡ ዋና ዋና ለውጦች መካከል፤ የሥርዓተ-ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ፣ የመፅሃፍት ህትመት ስርጭትና ተደራሽነት፣ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት፣ የቅድመ መደበኛ ትምህርትን ማሳደግ፣ የትምህርት ቤት ደረጃ ማሻሻል፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሪፎርም፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን እና ዲጂታል ትምህርት መስፋፋት፣ የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ዝግጅትና አስተዳደር መሻሻል፣ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማደግ ዋነኞቹ በለውጡ ተግባራዊ የሆኑና ውጤት ያስገኙ ሆነው ተመዝግበዋል።

#PMOEthiopia
👍1
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በሚኒስትር መስሪያቤታቸው የተመዘገቡ ዐበይት ስኬቶችን አቅርበዋል።

‎በዚህም ዘርፉ ከለውጡ በፊት ሲቸገርበት የነበሩ መጠነ ሰፊ ክፍተቶችን በመለየት ፈጣን መፍትሔ በመስጠት ሰፊ ስኬቶችን አስመዝግቧል።

‎ከተገኙ ስኬቶች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦
‎የፖሊሲና የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት የዜጎችን መብት ጥበቃ፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ። አደረጃጀቶችን በመደገፍና በማጠናከር መብትና ግዴታ በማወቅ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ የአቅመ ደካማ ዜጎችን የመደገፍና የማገዝ ባህል ማሳደግ ጥቂቶቹ ናቸው።

እነዚህ ስኬቶች ቁጥር ብቻ ሳይሆኑ በተጨባጭ 4,330,948 የሚሆኑ ወጣቶች እና 26,845,686 ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የተቻለበት ትልቅ ስኬትም ጭምር እንጂ! ከዚህ በተጨማሪም የሴቶችንና ወጣቶችን የፖለቲካ ተሳትፎን ከማሳደግ አኳያ ሰፊ ስራ ተሰርቶ ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል።

በተጨማሪም ዘርፉ ካስመዘገባቸው ስኬቶች መካከል የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አንዱና ዋነኛው ሲሆን በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ ተጋላጭ ሆነው ድጋፍ የተደረገላቸው ዜጎች፣ ከጎዳና ላይ የተነሱ ዜጎች፣ የተሀድሶ አገልግሎት ያገኙ አካል ጉዳተኞች፣ በማህበረሰብ እንክብካቤ ጥምረቶች የተሰበሰበ ሀብት ዋነኞቹ ስኬቶች ናቸው።

#PMOEthiopia
2
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ሹመት አጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

የቦርድ አባላቱን ሹመት አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት በምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ምህረቱ ሻንቆ (ዶ/ር) ተሿሚዎቹ በትምህርት ዝግጅት እንዲሁም ባዳበሩት ክህሎት የድርጅቱን ተልእኮ ማሳካት የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ብሔራዊ ጥቅምን መረዳት የሚችሉ እንዲሁም ተቋሙን ለስኬት እንደሚያበቁ የታመነባቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።

በዚህም ፦
1፡- ብሌን ማሞ ....... የቦርድ ሰብሳቢ
2፡- ፈዲላ ቢያ ....... አባል
3፡- ተስፋዬ ዘውዴ ....... አባል
4፡- መሐመድ ካሳ ....... አባል
5፡- አፈወርቅ በደዊ ....... አባል
6፡- አስማ ረዲ ....... አባል
7፡- ዮናስ በቀለ ....... አባል
8፡- ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር ....... አባል
9፡- ኢሳያስ ካሳ (ዶ/ር)....... አባል ሆነው እንዲሾሙ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ምክር ቤቱ መርምሮ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

ተሿሚዎችም በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ-መሀላ ፈጽመዋል።