የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
822 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

ሁልጊዜም በበዓላት ወቅት እንደምናደርገው፣ ዛሬ በትንሣኤ በዓል ዋዜማ በከተማችን የተለያዩ አካባቢዎች በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር የገነባናቸውን 215 ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች፤ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ ለአቅመ ደካሞች፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአገር ባለውለታዎችና ለልማት ተነሺዎች ከሙሉ የቤት ቁሳቁስና ከበዓል መዋያ ጋር አበርክተናል።

በከተማችን የበጎ ፈቃድ ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተና ባህል እየሆነ መምጣቱ የሚያስደስት ነው። ይህንን በጎ ተግባር በተለያየ መልኩ ለደገፋችሁ ልበ ቀና በጎ ፈቃደኞች፣ ተቋማትና አመራሮች በሙሉ በተለይም ከ 80 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ላደረገው የኦሮሚያ ባንክ በተጠቃሚዎች ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

የትንሣኤ በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ በፍቅር ራሱን እስከ መስቀል የሰጠበት እና በትንሣኤ የምሥራች የተበሰረበት ነው። በመሆኑም በዓሉን ስናከብር በትሳኤን ዓላማ እና ምሳሌነት መሰረት በታላቅ ፍቅር እና መተሳሰብ ሊሆን ይገባል። ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን ያለንን መተሳሰብ በተግባር የምንገልጽበት፣ አንዳችን ለሌላችን የደስታ፣ የሰላም እና የአብሮነት ምክንያት የምንሆንበት በዓል እንዲሆንልን እመኛለሁ።
መልካም በዓል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ሰው ተኮር አመራር በተግባር፤ የዜጎች የልብ ስብራት ሲጠገን!

ዓመታት በፈተናና በትግል ቢታጀቡም፣ የሰው ልጅ ጽናት ግን የማይፈታ ስር እንዳለው የወ/ሮ መስከረም ታሪክ ምስክር ነው። በልጅነታቸው ከአልጋ ላይ ወድቀው በደረሰባቸው የአካል ጉዳት ምክንያት ህይወት ገና በጠዋቱ ዳገት የሆነባቸው ወ/ሮ መስከረም አዱኛ፣ ተስፋ ሳይቆርጡ ለቤተሰባቸው ደጀን በመሆን በሰው ቤት ልብስ እያጠቡ በጉልበታቸው እንጀራን፣ በጽናታቸው ደግሞ የቤተሰባቸውን ህልም ሲያቀኑ ኖረዋል።

ይሁን እንጂ ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ የገጠማቸው ህመም ካልጋ ላይ አውሏቸው፣ ያ ይተጉበት የነበረው ጉልበት ሲዝልና ቤት ተከራይቶ የመኖር ተግዳሮት ሲደራረብባቸው ህይወታቸው ዳግም በጨለማ ተዋጠ። ያሳለፉት መከራና የታገሉት ድህነት ጫናው ቢበረታም፣ በፈጣሪ ላይ ያላቸው እምነትና አንድ ቀን ነገሮች መልካም ይሆናሉ የሚለው ተስፋ ግን ከውስጣቸው እንዳልጠፋ ይናገራሉ።

ዛሬ ያ! የጨለመው ህይወቴ በድንገት በታላቅ የደስታ ብርሃን ተተክቷል ይላሉ በደስታ እንባ። ምክንያታቸው ደግሞ በስቃይ ይገፉት የነበረው የመከራ ዘመን አብቅቶ፣ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሆኑበት ታሪካዊ ቀን በመሆኑ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በትንሳኤው ዋዜማ የቤት ቁልፍ ሲያስረክቧቸው፣ የአመታት ሸክማቸው በቅፅበት ከጫንቃቸው ላይ ወረደ።

ወ/ሮ መስከረም ደስታቸውን ለመግለጽ ቃላት አጥተው እጃቸውን ወደ ላይ ዘርግተው ፈጣሪን እያመሰገኑ የሚያሳዩት ትዕይንት፣ ከመኖሪያ ቤት በላይ ትልቅ የሰብአዊነት ትርጉም አለው። "ሰው ተኮር" የሆነው የከተማ አስተዳደራችን ማህበራዊ ፕሮግራም ለአቅመ ደካሞች ምን ያህል የህይወት ትርጉም እንዳለውና የተሰበረን ልብ እንደሚጠግን የሚያሳይ ህያው ምሳሌ ነው። በዛሬው እለት ልክ እንደ ወ/ሮ መስከረም በከተማ አስተዳደሩ የትንሳኤ ገፀ በረከት የ215 አቅመ ደካሞች፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞችና የሀገር ባለውለታዎች የልብ ስብራት በበጎነት ተጠግኖ ተስፋቸው ለምልሟል።

በጎነት መልሶ ይከፍላል!

#በጎነት #ትንሳኤ #አዲስአበባ #ሰብአዊነት
2
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

የትንሣኤ በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ መዳን ያለውን ፍቅር እስከ መስቀል ሞት የገለጸበትና የሞት ድል የተበሰረበት ታላቅ ዕለት ነው። በመሆኑም በዓሉን ስናከብር በታላቅ ፍቅር፣ በትሕትና እና በመተሳሰብ ሊሆን ይገባል።

ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን ያለንን አጋርነት በተግባር የምንገልጽበት፣ አንዳችን ለሌላችን የደስታ፣ የሰላም እና የአብሮነት ምክንያት የምንሆንበት በዓል እንዲሆንልን እመኛለሁ።
መልካም በዓል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
2👍1
ዛሬ በጉለሌ ክፍለ-ከተማ ተገኝተን 27ኛውን የተስፉ ብርሃን የምገባ ማዕከል ስራ በማስጀመር ከማዕከሉ ተጠቃሚዎች ጋር የትንሳዔ በዓልን በጋራ አክብረናል።

በጉለሌ ክፍለከተማ ሶስተኛ ቅርንጫፍ የሆነውን ይህ 27ኛው የተስፉ ብርሃን የምገባ ማዕከል ስራ በማስጀመር፣ የምገባ ማዕከሉ ተጠቃሚ ከሆኑ ለማህበራዊ ችግር ከተጋለጡ ፣ አልባሽ አጉራሽ ለሌላቸው የሀገር ባለውለታ፣ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻች ፣ ከአረጋዊያን እና ከአካል ጉዳተኞች ወገኖቻችንን እንኳን አደረሳችሁ ብለን በዓሉን በጋራ አክብረናል።

በዓሉ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ያለአንዳች ልዩነት ለሰው ልጆች ሁሉ ራስን እስከ መስጠት ያሳየንን ፍቅር፣ በአብሮነት በፍቅና በመተሳሰብ ምሳሌነቱ በመከተል ልንኖር እንደሚገባ የሚስተምር በዓል ነው።

እኛም በ28ቱም የተስፉ ብርሃን የምገባ ማዕከል በዚሁ በትንሳኤ በዓል ብቻ ሳይሆን ሁሌም ወገኖቻችን ስንመግብ ለዜጐቻችን ክብራችንና ፍቅራችንን የምንገልጥበትና ማህበራዊ ፍትህን የምናነግስበት ተግባር ነው።
በዓሉን ምክንያት በማድረግ በሁሉም ክፍለ ከተሞች መዓድ የማቋደስ መርሐ-ግብር በማዕከላቱ እየተከናወኑ ይገኛሉ።

“መስጠት አያጎድልም” በሚል መርሕ የተደረገላቸዉን ጥሪ በመቀበል የገነቡት በጎ ፈቃደኛ “የአዲስ ቪው ሆቴል ባለቤት አቶ አብይ አበራ” እና በየቀኑ ለሚመመገብ የተረከበዉን “አኳስ ኮንስትራክሽን ፒ ኤል ሲ ባለቤት አቶ ወሰንን” በተጠቃሚዉ ወገን፣ በከተማ አስተዳደሩና በራሴ ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

በዓሉ የመተባበር፣ የመደጋገፍ እና የፍቅር በዓል ይሁንልን! መልካም በዓል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
2
የአካባቢያችንን ገጽታ ለመቀየርና የተሻለ የመኖሪያ አካባቢ ለመፍጠር የጀመርነው የተቀናጀ የልማት ስራ በነዋሪዎቻችን ንቁ ተሳትፎ ተጠናክሮ ቀጥሏል። እያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍል በጉልበቱ፣ በእውቀቱና በገንዘቡ እያደረገ ያለው ያልተቆጠበ ድጋፍ ለስራችን መሳካት ትልቁን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል።

ይህ በጋራ የመልማት ባህላችን የአካባቢያችንን የመሰረተ-ልማት ጥያቄዎች በራስ አቅም ለመፍታት እንደምንችል ትልቅ ማሳያ ነው። ዛሬ የምናደርገው ርብርብ ነገ ለልጆቻችን የምታምርና ምቹ የሆነች አዲስ አበባን ለማውረስ የሚደረግ ትልቅ ኢንቨስትመንት በመሆኑ ኩራት ይሰማናል።

በአንድነት ከቆምን የማንለውጠው ነገር የለም፤ የአካባቢያችን ልማት በጋራ እጃችን ነው!

#የህብረተሰብተሳትፎ #የአካባቢልማት #ልማትበጋራ #ኢትዮጵያ
በመዲናችን አዲስ አበባ በዚህ ሚያዝያ ወር ሶስት ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ኩነቶች ይከናወናሉ።

በዚህ ወር ከሚካሄዱ ሶስት ዓለምአቀፍ ስፖርታዊ ኩነቶች ውስጥ አንዱ በመጪው ቅዳሜ የሚካሄደው የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ የአንድ ቀን የአትሌቲክስ ውድድር ነው።

ይህ ውድድር በመዲናችን አዲስ አበባ ሲካሄድ የመጀመሪያው ሲሆን ለዘርፍ መንግስት በሰጠው ትኩረት የስፖርት መሰረተ ልማቶች መስፋፋት እንደ ምክንያት ሊገለጽ ይችላል።

ውድድሩ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ እና ብዙ ተከታይ ያላቸው አትሌቶች ይሳተፉበታል። የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ ሚያዝያ 10 በአዲስ አበባ ስታዲዮም የሚካሄድ ይሆናል።

በዚሁ ሚያዝያ ወር ከሚካሄዱ ውድድሮች ውስጥ ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኢሊሚኔተር ዓለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር እና ግራንድ ኢትዮጵያን ረን የሚካሄዱ ይሆናል።

ከተማ አስተዳደሩ ውድድሩን ለማሳካት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቂ ዝግጅቶች ከማድረግ በዘለለ በኢትዮጵያ ያሉትን የስፖርት መሰረተ ልማቶች ለማስተዋወቅ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።
👍2
ኢትዮጵያን የማኑፋክቸሪንግ ማዕክል የማድረግ ትልምን በተመለከተ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ ቀዳሚውን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለመሆን በቢሾፍቱ የሚገነባውን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ጨምሮ የሎጂስቲክስ መሠረተ ልማትን በማዘመን፣ እንደ ህዳሴ ግድብና ኒውክሌር ኢነርጂ ባሉ ፕሮጀክቶች አማካኝነት አስተማማኝና ንጹህ ኃይልን በማቅረብ፣ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ዝግጁነት ያለውን የወጣት የሰው ኃይል በሥልጠና በማብቃት ስልታዊ ሥራዎችን እያከናወነች ትገኛለች። በተጨማሪም የግሉን ዘርፍ የሚያነቃቁ ምቹ ፖሊሲዎችን በመቅረጽ፣ የፋይናንስ ሥርዓቱን በማሻሻልና ለስትራቴጂካዊ ምርቶች (እንደ ሶላር፣ ኤሌክትሮኒክስና መድኃኒት ያሉ) ትኩረት በመስጠት ሀገሪቱን የኢንዱስትሪና የማኑፋክቸሪንግ ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየተሠራ ነው።
ምርጫ ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ የሚያደርጉበት፣ ህዝቡ የሚመራውን አካል በነፃነት በመምረጥ የስልጣን ባለቤትነትን የሚያረጋግጥበት ዲሞክራሲያዊ መድረክ ነዉ፡፡

በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲኖር ማድረግ፣ ከምርጫ ባለፈ ለሀገር ግንባታና ለሰላም ያለው ፋይዳ እጅግ ከፍተኛ ሲሆን፣ በህግና በህዝብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሰላማዊ መንግስት ለማፅናት፣ ሀገር ከድህነት እና ከኋላቀርነት ለመታደግ የሚረዳ የስልጡን ዜጎች መገለጫ ነዉ።

ነፃና ፍትሃዊ በሆነ የምርጫ ሂደት የተመረጠ መንግስት፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት የሚኖረዉ ሲሆን፣ ይህም መንግስት የልማት ስራዎችን ለማከናወንና የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

በአጠቃላይ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለኢትዮጵያ የነፃነት፣ የፍትህና የዘላቂ እድገት መሰረት በመሆኑ፣ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶችና ፍላጎቶች በሚንፀባረቁበት በ7ኛዉ ሃገራዊ ምርጫ የሚበጅዎትን ለመምረጥ የሚያስችልዎትን የምርጫ ካርድ በመዉሰድ በድምፅዎ ወሳኝ ቢሆኑ ያተርፋሉ እንጂ ሃገርና ትዉልድን ኪሳራ ላይ አይጥሉምና ታሪካዊ ሃላፊነታችንን በጋራ እንወጣ !!!
አስተዳደሩ ባለፉት ስምንት ዓመታት 45 ሺህ 566 መኖሪያ ቤቶች በበጎ ፈቃድ ፕሮግራም ገንብቶ ለተጠቃሚዎች አስተላልፏል።

በከተማችን ለሚገኙ አቅመ ደካሞች፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞችና ለሀገር ባለውለታዎች ምቹ መኖሪያን ለመፍጠር የተጀመረው የተቀናጀ የቤት ግንባታ መርሃ ግብር ታላቅ ሰብዓዊ ድል አስመዝግቧል። ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ 45,566 ቤቶች በአዲስ መልክ ተገንብተው ለተጠቃሚዎች የተላለፉ ሲሆን፣ በዚህም ከ198,480 በላይ ቤተሰቦች የቤት ባለቤት መሆን ችለዋል። 

ይህ ግዙፍ የልማት ስራ በበጎ ፈቃደኞችና በባለሀብቶች ያልተቆጠበ ድጋፍ የተከናወነ ሲሆን ለቤት ግንባታው በወቅቱ በነበረው የገበያ ሁኔታ በገንዘብ ሲተመን ከ25.3 ቢሊዮን ብር በላይ በበጎ ፈቃድ ሞብላይዝ ተደርጓል። ይህም የማህበረሰባችን የመረዳዳት አቅም ምን ያህል ግዙፍ እንደሆነና በአብሮነት መቆም ያለውን ፋይዳ በግልጽ የሚያመላክት ውጤታማ ስራ ነው።  

ስኬቱ እውን እንዲሆን በገንዘብ፣ በቁሳቁስና በጉልበት ላገዛችሁ ባለሀብቶች፣ በጎ ፈቃደኞችና የልማት አጋሮቻችን በሙሉ ልባዊ ምስጋናችን እናቀርባለን። በቀጣይም ይህንን የበጎነት ጉዞ በማጠናከር ለብዙዎች መጠለያና ተስፋ መሆናችንን እንቀጥላለን።

#ቤትግንባታ #በጎፈቃደኝነት #ለወገንደራሽ #የአካባቢልማት #ኢትዮጵያ
1