የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
823 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት የሚረዱ የገቢያ ማዕከላት በአዲስ አበባ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአምስቱም የከተማይቱ መግቢያ በሮች የመሰረታዊ ሸቀጦችን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት የሚረዱ የግብርና ምርቶች መሸጫ ገቢያ ማዕከላት ገንብቶ ለአገልግሎት አውሏል፡፡ ማዕከላቱ በላፍቶ ቁጥር1 እና 2፣አቃቂ ቃሊቲ፣ ለሚ ኩራ እና ኮልፌ ክፍለ ከተሞች የተገነቡ እና ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ያላቸው ናችው፡፡

ከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ ያለውን የኑሮ ውድነትና ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት ችግሩን ለማስቀረትና ገበያውን ለማረጋጋት ከወሰዳቸው ዘርፈ ብዙ እርምጃዎች መካከል ግንባር ቀደም እና ለነዋሪው ትልቅ እፎይታን የሰጠ ተግባር ነው፡፡

በነዚህ የገቢያ ማዕከላት በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና ምርታማነትን በማሳደግ ህብረተሰቡ ከሸማችነት ወደ አምራችነት እንዲሸጋገር ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ተችሏል፡፡

በዚህም ህገወጥ ንግድና ደላላን በማስቀረት የመሰረታዊ ሸቀጦችን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት የሚረዱ የግብርና ምርቶች በገበያ ማዕከላቱ በስፋት እንዲሰራጩ አስችሏል፡፡
👍31
ከመሸጋገሪያ ወደ ማዘውተሪያ የተቀየረችው አዲስ አበባ

ከተማችን አዲስ አበባ ደረጃቸውን የጠበቁ ውብ የመዝናኛ የማዘውተሪያ ስፍራዎችን መገንባቷ ለቱሪስቱ አዲስ እይታን ለነዋሪው ደግሞ ውብ ማዘውተሪያን እያበረከተች ትገኛለች::

ይህ ደግሞ ከዚህ ቀደም ከተማዋ ወደሌሎች ሀገራት መተላለፊያ ብቻ አድርጓት የነበረውን ታሪክ በመቀየር መዳረሻ እሆነች እንድትመጣ አድርጓታል፡፡

ከታሪክና ከተፈጥሮ ባለፈ ወደ ልምድና መዳረሻ እየተቀየረች ያለችው ከተማችን የቱሪዝም ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ለቱሪዝም መነቃቃት የመጀመሪያው የባህልና የታሪክ ሀብት በመሆኑ ከተማችን ይህንን በተግባር እየገለጠች ሲሆን በተጨማሪም የደህንነትና የሰላም ዋስትና የመሰረተ ልማት ግንባታን በመገንባትና በማረጋገጥ ለቱሪስቶች ቆይታቸውን ማራኪ በማድርግ እንዲያራዝሙ እያደረገች ነው፡፡

በከተማዋ የተገነቡት እንደ አንድነት እና እንጦጦ ፓርክ ያሉ ፕሮጀክቶች ከተማዋን አረንጓዴ ከማልበሳቸው ባለፈ፣ የቱሪስቶችን ቆይታ የሚያራዝሙና ለቤተሰብ ምቹ የሆኑ የገጽታ ግንባታ ውጤቶች ሆነዋል፡፡

በተጨማሪም እንደ የሳይንስ ሙዚየምና የታሪክ ማዕከላት መገንባታቸው የኢትዮጵያን ጥንታዊ ጥበብ ከዘመናዊ የቴክኖሎጂ ግስጋሴ ጋር በማጣመር፣ ለጎብኚዎች የተሟላ እውቀትና መዝናኛ የሚሰጡ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስፍራዎች አድርጓቸዋል፡፡

ይህም ይህችን ውብ ከተማ በቱሪዝም እና በቱሪስት እንቅስቃሴ ከመሻጋገሪያ ወደ ማዘውተሪያ እየቀየራት መሆኑን እያስመሰከረች ነው፡፡
👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ዛሬ መጪውን የትንሳዔ በዓል ምክንያት በማድረግ፤ ለማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው የአገር ባለውለታ አረጋውያንና በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የመንግስት ሰራተኞች በአጠቃላይ  ከ233 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖቻችን ማዕድ አጋርተናል።

ይህ ተግባር በከተማችን የማዕከል መስሪያ ቤቶች፣ በሁሉም ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች እየተከናወነ  ያለ በጎ ተግባር ነው።
በሁሉም በዓላት የምናደርገው የማዕድ ማጋራት፤ ድጋፍ የሚሹ የከተማችን ነዋሪዎችን  “ምን ጎደለ?" ብለን  በመመልከትና በመጠየቅ ክፍተታቸውን የምንሞላበት  ለነዋሪዎቻችን ያለንን ክብር የገለፅንበት ሰው ተኮር ተግባር ነው።
ማዕድ ከማጋራት ባለፈ አሁን ላይ በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ግጭትና በነዳጅ እጥረት ሳቢያ የሚከሰተውን ጊዜያዊ የኑሮ ጫና ለማቃለልና የገበያ ጉድለትን ለመሙላት፣ ከፍተኛ በጀት መድበን መሰረታዊ ምርቶች በበቂ ሁኔታ እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ እያደረግን እንገኛለን። በዚህም የምርት እጥረት እንዳያጋጥም በሰራነው ሥራ፣ በከተማችን የተረጋጋ የገበያ ሁኔታ እንዲሰፍን ተደርጓል።

ወቅታዊ ችግሮችን ለመሻገር የምናከናውናቸው እነዚህ ተግባራት በሙሉ ከለውጡ ወዲህ የጀመርነው  የ"ሰው ተኮር" ሥራዎቻችን አካል ናቸው።
አዲስ አበባ ለሀብታሙም ለድሃውም፣ ለሁሉም እኩል የተመቸች ፣ ስራዎቻችንም  ማንንም ያልዘነጉ አካታች እንዲሆኑ እየሰራን ሲሆን፤ ከተማዋ እየተቀየረችና እየተለወጠችበት ያለው ልማት በሰዉ ኑሮና አኗኗር  ላይ ለውጥ  እያመጣ ያለ ነው።

"መስጠት አያጎድልም" ብለን ባደረግንላቸው ጥሪ መሰረት  በሁሉም ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ለሚደረገው ማዕድ ማጋራት ለተባበሩን ልበ ቀና ባለሀብቶች፣ እንዲሁም ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻቸው ሁሌም እየተሸከሙ  በጉልበታቸው በበጎ ፈቃደኝነት እያገለገሉ ላሉ ወጣቶቻችን በሙሉ በራሴና በነዋሪዎቻችን ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በተለይም ዛሬ በከንቲባ ፅ/ቤት ያካፈልነውን ያቀረቡልን  Jospong Trading 15 ሚሊዮን ብር፣. አቶ ጀማል (ሚድሮክ) 10 ሚሊዮን ብር፣ የኢትዮዽያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን 7 ሚሊዮን ብር፣ አቶ በላይነህ ክንዴ (BKG) 5 ሚሊዮን ብር፣. አትሌት ዮሐንስ ቢፋ  2.9 ሚሊዮን ብር፣ አቶ ተካበ ሙሉ 500 ሺህ ብር በመለገሳቸዉ ከልብ እናመሰግናለን።

የትንሳኤ በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ መዳን ፍቅሩን እስከ መስቀል የገለጸበት እና በትንሳኤ የምስራች የተበሰረበት በመሆኑ፣ በዓሉን ስናከብር በታላቅ ፍቅር፣ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን ያለንን መተሳሰብ በተግባር የምንገልጽበት አንዳችን ለሌላችን የደስታ፣ የሰላም፣ የአብሮነት  ምክንያት እንሁን እያልኩ፣  በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።
መልካም በዓል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በአዲስ አበባ የትንሳኤ በዓል ገበያ፣ በተተመነ ዋጋ ላይ ጭማሪ ባደረጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በአዲስ አበባ ከተማ ለትንሳኤ በዓል በተዘጋጁ የገበያ ማዕከላት ውስጥ በመንግስት ከተቀመጠው የዋጋ ተመን በላይ ሲሸጡ በተገኙ ሰባት የንግድ ድንኳኖች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የከተማዋ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ በከተማዋ በሚገኙ ስድስት የግብርና ምርት ማዕከላት፣ 246 የሰንበት ገበያዎች እና 11 ባዛሮች ላይ የንግድ ቢሮው የዋጋ ተመን አውጥቶ ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል።

ኃላፊዋ እንዳሉት፣ በ8588 ነፃ የስልክ መስመር በኩል ከህዝብ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በተደረገ ክትትል፣ ሰባት የንግድ ድንኳኖች በተለጠፈው የዋጋ ተመን ሳይሆን ከዚያ በላይ ሲሸጡ ተገኝተዋል። በዚህም የተነሳ፣ ሰባቱም የንግድ ድንኳኖች ከስራ እንዲታገዱ ተደርጓል። እነዚህ ነጋዴዎች ዳግም መሰል የገበያ አማራጮችና ባዛሮች ላይ እንዳይሳተፉ ተወስኖባቸዋል።

ወይዘሮ ሀቢባ አክለውም፣ ከተማ አስተዳደሩ ሰፊ በጀትና ጊዜ መድቦ የሸማቹን ማህበረሰብ ጫና ለመቀነስ እየሰራ ባለበት ወቅት፣ እንዲህ ያሉ ህገ-ወጥ ተግባራትን መፈጸም ተቀባይነት እንደሌለው አስገንዝበዋል።

ድርጊቱን እንደ ሀገር ክህደት ነው የምንቆጥረው ያሉት ኃላፊዋ፣ ለህገ-ወጥ ነጋዴዎች ምንም ዓይነት ትዕግስት እንደማይኖርና ፈጣን እርምጃ መውሰዱ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የንግድ ቢሮው ነዋሪዎች በማንኛውም የግብይት ሂደት ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ወይም ህገ-ወጥ ተግባር ሲያጋጥማቸው በ 8588 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ መስጠታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል። እያንዳንዱ ጥቆማ በአግባቡ ተፈትሾ አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድም ተገልጿል።
2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግም፣ ዛሬ ጠዋት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እና ጽሕፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው ሕጻናት ማዕድ አጋርተዋል።

On the occasion of the upcoming Easter holiday, Prime Minister Abiy Ahmed shared items this morning with low income staff members of the Office of the Prime Minister and also with orphaned children the PMO is helping to raise.

#PMOEthiopia
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የዓለም-አቀፍ ኮንፈረሶች የስህበት ማዕከል፥ አዲስ አበባ!

አዲስ አበባ፥ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና እና የዓለም-አቀፍ ስብሰባዎች ቀዳሚ መዳረሻ መሆኗን በተለያዩ ዘርፎች በተግባር እያረጋገጠች ትገኛለች። ከተማዋ ያላትን ጠንካራ የማስተናገድ አቅም፣ የሆቴል መሰረተ ልማት እና ልዩ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል፣ ለበርካታ ታላላቅ ጉባኤዎች ተመራጭ እንድትሆን አስችሏታል።

መዲናችን ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ተመራጭ እንድትሆን ካደረጓት ዋና ዋና ምክንያቶች፣  በከተማዋ ከ210 በላይ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ፅ/ቤቶች፣ ታላቁ የአፍሪካ ኅብረት እና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ መሆኗ እና በአጭር ጊዜ ያመጣችውን አስደማሚ የዕድገት መንገድ ተደምሮ ለአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ውሳኔዎች ቁልፍ ስፍራ አድርጓታል።

በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፥ ከተማዋ ለነዋሪዎቿም ሆነ ለጎብኚዎች ምቹ፣ ውብ እና ሳቢ ለማድረግ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ለዓለም አቀፍ ጉባኤዎች እና ጎብኚዎች ያላትን ተመራጭነት ይበልጥ አልቆታል።

በሌላ በኩል፥ ከተማዋን የቱሪዝም እና የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ የተገነባው “አዲስ ዓለም-አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል” ለከተማዋ ተጨማሪ የማስተናገድ አቅም የፈጠረ እና ለትላልቅ አለም አቀፍ ስብሰባዎችና ኤግዚቢሽኖችን ለማዘጋጀትም ዓቅም የፈጠረ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡ 

እንዲሁም “የዓድዋ ድል መታሰብያ ሙዝየም” ከታሪክና ቅርስ ማዕከልነቱ ባሻገር፣ በርካተ ስብሰባዎችን እና ኤግዚብሽኖችን በአንድ ጊዜ የማስተናገድ ማስተናገዱ ሌላው ለኮንፈረንስ ማዕከልነቷ ገፀ-በረከት ነው።

በአጠቃላይ አዲስ አበባ፣ በታሪክ ብቻ ከመኖር በአሁናዊ መሬት ላይ በፈጠረችው አስደማሚ የዕድገት እና ሁለንተናዊ ከፍታ፣ “ከሀገራችን ዋና ከተማነት ባሻገር" የዓለምን ቀልብ እየሳበች፣ በፈጣን ለውጥ ላይ ያለች እና ለዓለም-አቀፍ ባለሀብቶች፣ እንዲሁም ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ምቹ እየሆነች የመጣች ከተማ ናት።
👍21
የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ክቡር ኤቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ፤ በድንቅ ህዝቦቿና ባህሏ ወደ ምትቀበሎት ሀገሬ ኢትዮጵያ እንኳን በሰላም መጡ ስል በታላቅ ክብር ነው። ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ ጥልቅ የሆነ የወንድማማችነት እና የጋራ መከባበር ታሪክ ያላቸው ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘላቂ ትስስርም በከፍተኛ ሁኔታ እንደምናከብር ላስታውሶት እወዳለሁ። በዚህ ይፋዊ የስራ ጉብኝትዎ፣ ለወደፊቱ ያለንን የጋራ ትልም ወደ እውነት ለመቀየር በምናደርገው ጥረት፤ ቆይታዎ ግንኙነታችንን የበለጠ እንደሚያጠናክረው አልጠራጠርም። በድጋሚ እንኳን ወደ ሁለተኛ ቤትዎ በደህና መጡ ለማለት እወዳለሁ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ