የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
822 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ከቤት እድሳት ወደ በጎነት መንደር ምስረታ ያደገ እምርታ!

የአንዲት ከተማ ትልቁ ሀብቷ የመሰረተ ልማት ግንባታዎቿ ብቻ ሳይሆኑ በውስጧ የሚኖሩ ዜጎች ሰብአዊ ክብርና ደህንነት ነው። የከተማ አስተዳደሩ "ሰው ተኮር" ልማትን የስትራቴጂው ማዕከል በማድረግ፣ ነዋሪዎችን ከችግርና ከጎስቁልና ህይወት የሚያወጡ ግዙፍ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። ይህ ስራ ዛሬ ላይ ከመደበኛ የቤት እድሳት ተነስቶ፣ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ "የበጎነት መንደሮችን" ወደ መገንባት ተሸጋግሯል።

የዚህ ታላቅ ፕሮጀክት አነሳሽ (Initiative) ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሲሆኑ በአዋሬ አካባቢ ለዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ቤት በመገንባት ከተጀመረው ተግባር ነው። ይህ አርአያነት ያለው ተግባር በከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ተሰጥቶት፣ ወደ ላቀ አፈፃፀምና ውጤት በመቀየር ዛሬ ላይ በመላው ከተማዋ ከ5 በላይ ግዙፍ የበጎነት መንደሮች እንዲፈጠሩ መሰረት ሆኗል።

ለዚህ ስኬታማ የልማት አቅጣጫ የልደታ በጎነት መንደርን እንደ ዋነኛ አብነት መጥቀስ ይቻላል። በተለምዶ "ቆርቆሮ ሰፈር" በሚል ስያሜ ይታወቅ የነበረውና ለኑሮ እጅግ ምቹ ያልነበረው አካባቢ፣ ዛሬ በሰው ተኮር ልማት አማካኝነት መልክ ቀይሮ የትውልድ አሻራ ወደሚያርፍበት ዘመናዊ መንደርነት ተቀይሯል። ይህ ለውጥ የአካባቢውን ገጽታ ብቻ ሳይሆን የነዋሪዎቹን የስነ-ልቦና እና የማህበራዊ ህይወት ደረጃ ከፍ ያደረገ ነው።

በዚህ በልደታ በጎነት መንደር ውስጥ እያንዳንዳቸው ዘጠኝ ወለል ያላቸው 11 ዘመናዊ ህንፃዎችና 967 ቤቶች ተገንብተው ለነዋሪዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል። ግንባታው ዜጎች በሰውነታቸው ሊያገኙ የሚገባውን ክብርና ምቾት እንዲያገኙ ታስቦ የተሰራ ነው። እነዚህ ፕሮጀክቶች የከተማ አስተዳደሩ ለዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍል ያለውን ፅኑ ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳዩ ህያው ምስክሮች ናቸው።

የከተማ አስተዳደሩ እየተከተለው ያለው የልማት አቅጣጫ ሰውን ያላገለለና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ነው። ከአዋሬ የተጀመረው የበጎነት ጥንስስ፣ ዛሬ በልደታና በሌሎችም አካባቢዎች በግዙፍ ህንፃዎችና በተሟላ መሰረተ ልማት ታጅቦ "የበጎነት መንደር" ሆኖ አብቧል። ይህ ጉዞ ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹና በጎነት ባህል የሆነባት የሰብአዊነት መገለጫ ወደመሆን ከፍ ያደረጋት ታሪካዊ ክንውን ነው።
2
ስምንት ዓመታት፤ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሽግግር ወደ ዘመናዊ እና ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚ

#EthiopiaDelivers
#PMOEthiopia
2
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ለበጎነት የተዘረጉ ለጋስ እጆች!

በከተማችን የጤና ተቋማት ውስጥ ሌት ተቀን የሚታይ አንድ ትልቅ እውነት አለ፤ እርሱም የሕክምና ባለሙያዎቻችን ለሕሙማን ፈውስ የሚያሳዩት ተከታታይነት ያለው ትጋትና ርኅራኄ ነው። ሆኖም በነዚህ የፈውስ ማዕከላት ውስጥ ሕክምናውን በጽናት የሚከታተሉ፣ ነገር ግን በቁሳቁስና በአስታማሚ እጥረት የሚፈተኑ ጥቂት ወገኖች መኖራቸው አይካድም። ይህን ክፍተት ለመሙላትና የሐኪሞችን ድካም በበጎነት ለማገዝ የቆረጡ ተቋማትና በጎ ፈቃደኞች መኖራቸው ደግሞ ለከተማችን ትልቅ ኩራት ነው።

ከነዚህም መካከል ታፍ ኢነርጂስ ይጠቀሳል። ታፍ ኢነርጂስ ነዳጅና ቅባቶችን በማቅረብ ብቻ የሚታወቅ ተቋም አይደለም፤ ከዚያ ይልቅ የሰውን ልጅ ችግር ተረድቶ "ለወገኔ ምን ላድርግ?" የሚል የቆሰሉ ልቦችን ጠጋኝ እንጂ። ዛሬ ላይ ተቋሙ 80 አቅመ ደካሞችን በቋሚነት ይደገፋል። ከእነዚህም መካከል ነገ የአገር ተረካቢ የሆኑ 10 ሕፃናት ይገኙበታል። እነዚህ ሕፃናት ዛሬ የታፍ ኦይልን እጅ ይዘው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ፣ አረጋውያኑም የዕለት ጉርሳቸውን ሳያጡ በክብር ሲኖሩ ማየት የተቋሙ ትልቁ ትርፍ ነው።

ድርጅቱ ረዳትና አስታማሚ አጥተው በዘውዲቱ ሆስፒታል ለሚገኙ ሕሙማን ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፣ የተቋሙ ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ መቅደስ አሰፋ "ረዳት የሌላቸውን ወገኖች መርዳት መቻላችን ትልቅ የሕሊና እርካታ ሰጥቶናል" ሲሉ ታፍ ኢነርጂስ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ ተረድቶ በተግባር የሚፈጽም ተቋም መሆኑን አረጋግጠዋል። ታፍ ኢነርጂስ ማኅበራዊ ኃላፊነትን እንደ ግዴታ ሳይሆን እንደ ሰብአዊ ጥሪም በመቁጠር፣ ሌሎች የግል ተቋማት የዚህ ቅዱስ ተግባር ተካፋይ እንዲሆኑ አርአያነቱን በተግባር አሳይቷል።

ኮሚሽኑ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ባከናወናቸው ከ15 በላይ በሚሆኑ የበጎ ፈቃድ ፕሮግራሞች በርካቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወይዘሮ አስራ ንጉሴ እንደ ታፍ ኢነርጂስ ያሉ ልበ-ቀና ድርጅቶችን በማስተባበር ለአቅመ ደካሞች ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን ከመገንባት ጀምሮ እስከ ሕሙማን ድጋፍ ድረስ የተከናወኑት ተግባራት የማኅበረሰቡ የመረዳዳት ዕሴት ማደጉን አመላካች እንቅስቃሴ መሆኑን በአንክሮ ገልጸዋል።
በጎነት ዛሬ የምንዘራውና ነገ የምናጭደው የሰላም ሰብል ነው ያሉት ኮሚሽነሯ፤ ሁላችንም በጋራ ከቆምን፣ በአዲስ አበባ ውስጥ ማንም አቅመ ደካማ ብቻውን አይሆንም፤ ማንም ሕመምተኛም ያለ ረዳት አይቀርም ሲሉ አክለዋል፡፡

የዘውዲቱ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ቴዎድሮስ አቡሌ በበኩላቸው በጤና ተቋማት ውስጥ ረዳት ለሌላቸው ወገኖች የሚደረግ ማንኛውም ድጋፍ ከመድኃኒት እኩል ፋይዳ እንዳለው ጠቅሰው፣ ይህ በከተማ አስተዳደሩና በበጎ ፈቃደኞች የሚከናወነው "በጎነት በሆስፒታል" ንቅናቄ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

#በጎነት #አዲስአበባ #ታፍኢነርጂስ #TaffEnergies #ሰብአዊነት #ኢትዮጵያ #AddisAbaba
3👍2
እባክዎን ከሐሰተኛ ዜናዎች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ስርጭት ይጠበቁ!

‎ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተብሎ የሚደርስዎትን ማንኛውም ‎ይፋዊ መልዕክት ከማጋራትዎ በፊት ሁልጊዜም በጽሕፈት ቤቱ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና ድህረ-ገጽ በመግባት፣ ትክክለኛነቱን እንዲያረጋግጡ እናሳስባለን።

Please remain vigilant against the spread of fake news and misinformation.

To ensure authenticity, always cross-check any official messages attributed to the Office of the Prime Minister (PMO) against the office’s official social media pages and website before sharing.

Facebook: https://www.facebook.com/share/1DbRTPiYUF/?mibextid=wwXIfr

X: https://x.com/pmethiopia?s=21

Website: https://pmo.gov.et

#PMOEthiopia
3👍1
ከትግራይ ክልል ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ የምክክር ኮምሽን የአጀንዳ ልየታ ጉባኤ ተሳታፊዎች የአዲስ አበባ የልማት ሥራዎች ጎበኙ!

በምክክር ኮምሽን አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው የሶስት ቀናት ውይይት ሲጠናቀቅ፤ በአጀንዳ ልየታው ለመሳተፍ ከትግራይ ክልል የመጡ ከሶስት መቶ (300) በላይ የሚሆኑ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ተሳታፊዎች፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ ኮርደር ልማት፣ ሳይንስ ሙዝየም፣ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና በመልሶ ማልማት የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

ጎብኝዎቹ በአጭር ጊዜ የተገነቡ የልማት ስራዎች የከተማዋን ውበት ከማሳደግ ባሻገር ዓለምዓቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን የሚያስችላት መሆኑን ገልፀዋል ። እንዲሁም “ይህን መሰል የመሰለ የልማት ስራ በተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች መድገም እንደሚያስፈልግ፣ ይህንኑ ሃላፊነትም ወጣቱ ትውልድ ወስዶ የመፈፀም ሃላፊነት እንዳለበት” በቁጭት ገልፀዋል።

ተሳታፊዎቹ፥ “ሰላም የሁሉም መሰረት እንደሆነ፣ ለዚህ በቂ ማሳያም የላቀ የስራ ባህል በመገንባት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ በማምጣት፣ አለማቀፍ ተፅዕኖ መፍጠር የቻለውን አዲስ አበባ እና በሌሎች አካባቢዎች እየታዩ ያሉ የልማት ስራዎች በቂ ማሳያ ነው” ሲሉ ገልፀዋል። በአዲስ አበባ በተመለከቱት ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች መደሰታቸውንም አብራርተዋል።
በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሳይንስ ሥነ-ምሕዳር ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከል ዛሬ መርቀን ከፍተናል።
‎በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባው ይህ ዘመናዊ ተቋም ከመሠረተ ልማት ግንባታ ባለፈ፤ ራሷን የቻለችና ጤናማ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚተጋ የላቀ የዕውቀት ማዕከል ነው።

የምርምር ማዕከሉ 40 ላቦራቶሪዎችን፣ የላቁ የጂኖሚክስ (genomics) እና የባዮኢንፎርማቲክስ (bioinformatics) ቦታዎችን፣ እንዲሁም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራትና ብቃት የሚያረጋግጥ የባዮኢኩዊቫለንስ (bioequivalence) ማዕከልን አካትቷል። በተጨማሪም ተቋሙ ለድንገተኛ አደጋዎች ዝግጁነትና ምላሽ የመስጠት አቅምን በመገንባት ረገድ እንደ ማገር ሆኖ ያገለግላል።
‎ምርምርን ወደ ፖሊሲ፣ ፈጠራን ደግሞ ወደ ተግባራዊ መፍትሔ በመቀየር፤ ይህ ማዕከል በመድኃኒት ምርት ራሳችንን ለመቻል፣ ዘላቂ የጤና ደህንነትን ለማረጋገጥ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ እስካሁን ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች ይበልጥ ለማሳደግ የሚረዳ ትልቅ እርምጃ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍31
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦላቸው በውጤቶቹ ላይ ግምገማ እና ውይይት ተደርጓል።

Via PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የአቅርቦት ችግር በመቅረፍ ረገድ የሸማቾች ማህበራት ዋነኛ መፍትሄ ናቸው- አቶ ጃንጥራር አባይ

በልደታ ክፍለ ከተማ የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ አምራችና ሸማቹን የሚያገናኝ ባዛር እና የገበያ ማዕከል የመክፈቻ መርሐ ግብር ተከናውኗል ፡፡

ባዛሩን ከፍተው ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ የአቅርቦት ችግር በሚኖርበት ወቅት የሸማቾች ማህበራት ዋነኛ መፍትሄ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ግጭትና በነዳጅ እጥረት ምክንያት የትራንስፖርት ዋጋ መጨምሩን ተከትሎ፣ በህዝቡ ላይ የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስ አስተዳደሩ ጥረት እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመዲናችን አዲስ አበባ መጪው የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የንግድና ባዛር መርሀ ግብር በዛሬው እለት በይፋ ተከፈተ

በመዲናችን በ11ዱም ክፍለ-ከተሞች መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ የንግድና ባዛር መርሀ ግብር በዛሬው እለት በይፋ ተከፍቷል፡፡

ንግድና ባዛሩ የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለማቃለል እና የገበያ ዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ያለመ ይህም ከተማ አሰተዳደሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸዉ ተግባራት አንዱ እና ተጠናክሮ የቀጠለ ዉጤታማ ስራ ነዉ፡፡

በተጨማሪም ህብረተሰቡ በአቅራቢያው የበዓል መጠቀሚያ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ የሚያስችል ሲሆን ህብረተሰቡን ካላስፈላጊ ወጪ ለማዳን በከተማዋ በአምስቱ የገበያ ማዕከላት ጭምር የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በጥራት እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡

ነጋዴው ማህበረሰብ የተፈጠረለትን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ጥራት ያለዉ ምርት እንዲያቀርብ እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸጥ ሸማቹም አቅሙን ባገነዘበ መልክ በተዘረጋለት ፍትሃዊ የግብይት ስርዓት ተጠቃሚ እንዲሆን ከተማ አስተዳደሩ ጥሪዉን ያቀርባል፡፡