የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ቅድሚያ ለሴቶች!
ሴቶች በጥበብ ይኖራሉ፤ በራስ መተማመን ይሠራሉ፤ በራስ መተማመን ይሮጣሉ፤ ይችላሉም! ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን የአገራችንን ብልፅግና እናረጋግጣለን።
ዛሬ ማለዳ 16 ሺህ ሴቶች የሚሳተፉበትን የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በድምቀት አስጀምረናል። በታላቁ ሩጫ አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚካሄደው ይህ ውድድር፤ ዘንድሮ በኮሪደር ልማታችን አማካኝነት እጅግ ውብ፣ ምቹ እና ለከተማችን አዲስ ዘመናዊ መልክ ባላበሰው በቦሌ - አትላስ - ኡራኤል መንገድ ላይ በልዩ ድምቀት ተከናውኗል።
እንኳን ደስ አላችሁ!
ሁላችሁም አሸናፊዎች ናችሁ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

👍2
ዛሬ በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ መልሶ ማልማት ፎረም የእኛ ሚኒስትሮች እና የጣሊያ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትርና የዓለምቀፍ ትብብር ሀላፊ በተገኙበት አስጀምረናል።
አሁን ላይ በመዲናችን የንግድ እንቅስቃሴ እያደገ፣ የኢንቨስትመንት ፍሰቱም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል። አዲስ አበባ በፍጥነት እየተለወጠች በመሆኗ፣ ይህ የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ መልሶ ማልማት ፎረም መካሄዱ ወቅታዊ፣ ትክክለኛና እጅግ አስፈላጊ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለግል ዘርፉና ለኢንቨስትመንት መስፋፋት ትልቅ ድጋፍ ያደርጋል። የጣሊያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በዚህች በተለወጠች ከተማ ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
አዲስ አበባ የተለወጠችው በገፅታ ብቻ ሳይሆን ቢዝነስ ለመስራት አመቺና ቀላል በመሆኗም ጭምር ነው። ኢንቨስት ለማድረግ ስትመጡ በፈጣንና ቀልጣፋ አሰራር ለማስተናገድ እንደ ‘መሶብ’ ያሉ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎቶች ዝግጁ ናቸው። አስተዳደራችን የግል ዘርፉን ለመደገፍ እጅግ ቁርጠኛ ሲሆን፣ ይህ ፎረም ለዚህ ግብ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው እርግጠኞች ነን።
ክቡራን የፎረሙ ተሳታፊዎች፤ በአዲስ አበባ የሚኖራችሁ ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን እመኛለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

👍2❤1
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ከሚገኘው የመጀመሪያው የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን ፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ መልሶ ማልማት ፎረም ጎን ለጎን፣ ከጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ማሪያ ትሪፖዲ ጋር በመሆን ከእንጦጦ እስከ አራዳ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ጎብኝተናል።
ክብርት ማሪያ ትሪፖዲ፤ ለነበረን ፍሬያማ ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ክብርት ማሪያ ትሪፖዲ፤ ለነበረን ፍሬያማ ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
❤2👍1
ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር መፈፀም ተከታታይነት ያለው የማያቋርጥ ተግባር ሆኗል።
ዛሬ በከተማችን 4ኛውን የቂርቆስ ቅርንጫፍ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት በይፋ ሥራ አስጀምረናል።
የቂርቆስ ቅርንጫፍ አዲስ የመሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት 20 ተቋማት፣ በ85 የአገልግሎት መስኮቶች፣ 112 የተለያዩ የሕዝብ አገልግሎቶችን በአንድ ስፍራ ለተገልጋይ ያቀርባል። ይህም የመንግሥት አገልግሎትን በማላቅ፤ ደላላን ፣ ሌብነትን፣ አድሎ እና እንግልትን በማስወገድ፣ ተደራሽነትን እና የዜጎችን እርካታ በማሳደግ፣ በተቋማት መካከል የነበረውን የተበታተነ አገልግሎት በማቀናጀት እንዲሁም ኅብረተሰቡ አገልግሎት ለማግኘት የሚያጠፋውን ጊዜና ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ፍትሐዊ አገልግሎት የሚያሰፍን ይሆናል ።
የተቀናጁ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የመንግሥት አገልግሎት አፈጻጸም ቁልፍ የክዋኔ መለኪያ እና አጠቃላይ የዜጎች እርካታን እያመጡ፣ አካታች እና ፍታዊ ተጠቃሚነት ማጎልበቻ ስርአት እየሆሙ ነው። ማዕከሉ ለአጠቃላይ ተገልጋዩ ማህበረሰብ ምቹ ሲሆን፤ በተለይም አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ፣ እንዲሁም ለሠራተኞች ምቹ የሥራ አካባቢን የፈጠረ ነው።
የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል አቀናጅቶ የማቅረብ መርሃ ግብር ስኬት እና በተሟላ መንገድ ተግባራዊ እንዲሆን አስቀድመን በኮሪደር ልማት የዘረጋናቸው መሠረተ ልማቶች ወሳኝ ሚና እያበረከቱ ይገኛሉ ።
ይህንን ለሕዝባችን እሮሮ መነሻ ሆኖ የቆየ አገልግሎት አሰጣጥ ችግር መሰረታዊ መፍትሄ ወደ ሥራ እንዲገባ በፍጥነትና በትጋት ሌት ተቀን ለሠራችሁ፣ የሕዝባችንን የአገልግሎት ጫና ላቀለላችሁ ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
አዲስ አበባ —መጋቢት 17/2018 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በመዲናዋ ማህበራዊ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በጋራ ለመከወን የሚያስችላቸውን ታሪካዊ የመግባቢያ ሰነድ በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል።
የፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ የተከናወነው በጉባኤው ጽሕፈት ቤት ሲሆን፣ ስምምነቱ በዋናነት በከተማዋ የሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን ይበልጥ የተቀናጁና ውጤታማ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በስምምነቱ ወቅት የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ እንደተናገሩት፣ በቅዱሳት መጻሕፍት አስተምህሮ መሠረት ለሰው ልጆች በጎነትን ማድረግ የሐይማኖት ተቋማት ቀዳሚ ተግባር ነው።
ምድራችን በብዙ ተፈጥሯዊ ሀብት የታደለች በመሆኗ፣ ይህንን ሀብት ለማህበራዊ በጎ ስራዎች በማዋል ማኅበረሰባችንን ማገልገል ይገባል" ያሉት መጋቢ ታምራት፣ ቤተ ዕምነቶች በየዓመቱ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት እያከናወኑት ያለውን የበጎ አድራጎት ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል፣ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አስራት ንጉሴ፣ ስምምነቱ የከተማዋ ነዋሪዎች በበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉና የእርስ በእርስ መረዳዳት ባህል እንዲጎለብት ትልቅ መሠረት እንደሚጥል ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለት የተፈራረምነው ሰነድ የሐይማኖት ተቋማት እያበረከቱ ያለውን ሚና ይበልጥ የሚያጠናክርና ትውልድን በሥነ-ምግባር ለመገንባት የሚያግዝ ነው ብለዋል ምክትል ኮሚሽነሯ።
ሁለቱ ተቋማት ይህንን የመግባቢያ ሰነድ ተግባራዊ በማድረግ በመዲናዋ የሚታዩ ማህበራዊ ችግሮችን በጋራ ለመቅረፍ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።

❤3👍1
በአዲስ አበባ ከተማ ማኅበረሰቡን በስፋት ያሳተፉ የአካባቢ መሠረተ ልማት ግንባታዎች በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በተያዘው የበጀት ዓመት የታቀዱ የሰቤዝ መንገድ ልማት ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ፣ በአሁኑ ወቅት የኮብልስቶን ንጣፍ ሥራዎች በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች በስፋት እየተተገበሩ ነው።
እነዚህ የልማት ሥራዎች "የራስን ችግር በራስ የመፍታት" ከተማ አቀፍ እሳቤን በተግባር እያሳዩ ያሉ ውጤቶች ናቸው። ፕሮጀክቶቹ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው በሚከናወኑ የልማት ተግባራት ላይ በቀጥታ እንዲሳተፉ በማድረግ፣ የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማቸውና የጋራ ችግሮቻቸውን በጋራ ጥረት እንዲፈቱ ዕድል ፈጥረዋል። ይህም ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ይበልጥ ተስማሚ የማድረግ ስትራቴጂ አንዱ አካል ነው።
የአካባቢው ማኅበረሰብ ከልማት ጠባቂነት መንፈስ ወጥቶ የራሱን አካባቢ ለማልማት እያሳየ ያለው ተነሳሽነት፣ ለዓመታት ሲስተዋሉ የነበሩ የመልካም አስተዳደርና የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመመለስ አስችሏል። ነዋሪዎች በገንዘባቸው፣ በእውቀታቸውና በጉልበታቸው እያደረጉት ያለው ንቁ ተሳትፎ የልማት ሥራዎች እንዲፋጠኑና ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ እያደረገ ይገኛል።
የመንግሥትና የሕዝብ ቅንጅት ይበልጥ እንዲጠናከር ለማድረግም፣ መንግሥት ለነዚህ የሕዝብ ተሳትፎ ፕሮጀክቶች የ35 በመቶ የፋይናንስ ድጎማ እያደረገ ይገኛል። ይህ ድጋፍ ማኅበረሰቡ የጀመራቸው የልማት ጥረቶች ግባቸውን እንዲመቱና የፋይናንስ ክፍተቶች እንዳያጋጥሙ ትልቅ አቅም ሆኗል።

❤4👍1
የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ማዕከላትን ለአገልግሎት ምቹ የማድረግ ስራ እየተከናወነ ነው
📌 የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በከተማዋ የሚገነቡ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ማዕከላት ደረጃቸውን የጠበቁ እና ለህዝብ አገልግሎት ምቹ እንዲሆኑ እየሰራ መሆኑን ገለጸ።
📌 በከተማዋ ባሉ 4,350 ብሎኮች ውስጥ ከ834 በላይ ማዕከላት የሚገኙ ሲሆን፣ አንድ ማዕከል ከ1 እስከ 6 የሚደርሱ ብሎኮችን በማቀፍ የጸጥታና የሰላም ስራዎችን ያከናውናል።
📌 የማዕከላቱ ዋና ዋና ጥቅሞች፦
👉ለማህበረሰቡ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት መስጠት፣
👉የአካባቢን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ፣
👉የወንጀል ድርጊቶችን አስቀድሞ መከላከልና ጥቆማዎችን መቀበል፣
👉ማህበራዊ አንድነትንና የህዝብ ተሳትፎን ማጠናከር።
📌 ኮሚሽኑ ማዕከላቱን ገንብቶ የማስረከብ፣ ከብሎክ አመራሮችና ከነዋሪዎች ጋር የማስተሳሰር እንዲሁም የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን በቅንጅት እንደሚሰራ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ፀሀይ ኪባሞ ገልጸዋል።
#የማህበረሰብ_አቀፍ_ፖሊስ #ሰላምና_ጸጥታ #የህብረተሰብ_ተሳትፎ #አዲስ_አበባ

❤3
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የበጎነት ብርሐን በሰው ተኮር ልማት ሲገለጥ!
ወይዘሮ ዙፋን ገብረመስቀል በእርጅና አጎንብሳ፣ የጉስቁልና ጥላ ባጠላባት ደሳሳ ጎጆ ውስጥ ሆና፣ በጨለማው ስንጥቅ በኩል የነገን ፋና የምታማትር የትዕግሥት ተምሳሌት ነች። ኑሮዋን በጉሊት ንግድ ስታቃና የኖረችው ይህች ብርቱ ሴት፣ በምስቅልቅል ሕይወት ውስጥ ሆና የነገን ብርሃን ትናፍቅ ነበር።
ይሁን እንጂ የከተማዋ መሪዎችና የበጎነት መላእክት የሆኑት በጎ ፈቃደኞች፣ ይህችን በፈራረሰ መጠለያ ውስጥ ያለች ነፍስ በሰብዓዊነት ዓይን ተመለከቷት። የከተማዋ አስተዳደር "ሰው ተኮር" ልማት ለሰውነት ቅድሚያ የሚሰጥ በመሆኑ፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለጋስ እጆች የተገነባውን የዘመናዊ መኖሪያ ቤት ቁልፍ ለወይዘሮ ዙፋን አስረከቡ። በዚያች ቅጽበት፣ ለዘመናት በድህነት የታጠረው ዓለሟ በድንገት በብርሃን ተጥለቀለቀ፤ ያ ያዘመመና የጎሰቆለ ሕይወቷም ለታሪክ ማጣቀሻነት ተሸኝቶ ወደ ክብር ማማ ተሸጋገረች።
በጎነት የተሰበረን ልብ የሚጠግንና የወደቀን ሕይወት የሚያቀና የሰብዓዊነት ድልድይ እንደሆነ ዙፋንና መሰል በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ሕያው ምስክሮች ናቸው። ዛሬ ወይዘሮ ዙፋን በኩራት ቀና ብላ የምትራመድ፣ የነገ ተስፋ የሆኑ ልጆቿን በጥበብ የምታሳድግ ብርቱ እናት ሆናለች። ይህም በጎነት በልዩ ልዩ አቅጣጫዎች እየፈሰሰ፣ እንደ ዙፋን ያሉ ብዙዎችን ከጉስቁልና አዘቅት አውጥቶ ወደ ክብር አሸጋግሯቸዋል።
የሰው ልጅ ቀና ልብና ርኅራኄ ሲታከልበት፣ ልማት ከኮንክሪትና ከድንጋይ ድርደራ አልፎ የሕይወት እስትንፋስን የሚዘራ ሰውን የሚያስቀድም ይሆናል። የከተማችን የልማት ስልትም በጎ ፈቃድን በዜጎች ማህበራዊ መስተጋብር ውስጥ እንደ ባህል በማፍሰስ፣ የማኅበረሰቡን የኑሮ ሸክም የሚያቀልና ሰብዓዊነትን የሚያነግሥ ጥልቅ ፍልስፍና ነው። በዚህም መሠረት ዙፋንን ያነሳው በጎነት፣ የከተማዋን ሰብዓዊ ልማት ወደ ላቀ ከፍታ የሚያሻግር የድል አርማ ሆኖ ይቀጥላል።
በጎነት ይለምልም!
#አዲስአበባ #በጎፈቃድ #የኅብረተሰብተሳትፎ #ኢትዮጵያ #Volunteerism #AddisAbaba #SocialImpact

ከቤት እድሳት ወደ በጎነት መንደር ምስረታ ያደገ እምርታ!
የአንዲት ከተማ ትልቁ ሀብቷ የመሰረተ ልማት ግንባታዎቿ ብቻ ሳይሆኑ በውስጧ የሚኖሩ ዜጎች ሰብአዊ ክብርና ደህንነት ነው። የከተማ አስተዳደሩ "ሰው ተኮር" ልማትን የስትራቴጂው ማዕከል በማድረግ፣ ነዋሪዎችን ከችግርና ከጎስቁልና ህይወት የሚያወጡ ግዙፍ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። ይህ ስራ ዛሬ ላይ ከመደበኛ የቤት እድሳት ተነስቶ፣ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ "የበጎነት መንደሮችን" ወደ መገንባት ተሸጋግሯል።
የዚህ ታላቅ ፕሮጀክት አነሳሽ (Initiative) ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሲሆኑ በአዋሬ አካባቢ ለዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ቤት በመገንባት ከተጀመረው ተግባር ነው። ይህ አርአያነት ያለው ተግባር በከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ተሰጥቶት፣ ወደ ላቀ አፈፃፀምና ውጤት በመቀየር ዛሬ ላይ በመላው ከተማዋ ከ5 በላይ ግዙፍ የበጎነት መንደሮች እንዲፈጠሩ መሰረት ሆኗል።
ለዚህ ስኬታማ የልማት አቅጣጫ የልደታ በጎነት መንደርን እንደ ዋነኛ አብነት መጥቀስ ይቻላል። በተለምዶ "ቆርቆሮ ሰፈር" በሚል ስያሜ ይታወቅ የነበረውና ለኑሮ እጅግ ምቹ ያልነበረው አካባቢ፣ ዛሬ በሰው ተኮር ልማት አማካኝነት መልክ ቀይሮ የትውልድ አሻራ ወደሚያርፍበት ዘመናዊ መንደርነት ተቀይሯል። ይህ ለውጥ የአካባቢውን ገጽታ ብቻ ሳይሆን የነዋሪዎቹን የስነ-ልቦና እና የማህበራዊ ህይወት ደረጃ ከፍ ያደረገ ነው።
በዚህ በልደታ በጎነት መንደር ውስጥ እያንዳንዳቸው ዘጠኝ ወለል ያላቸው 11 ዘመናዊ ህንፃዎችና 967 ቤቶች ተገንብተው ለነዋሪዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል። ግንባታው ዜጎች በሰውነታቸው ሊያገኙ የሚገባውን ክብርና ምቾት እንዲያገኙ ታስቦ የተሰራ ነው። እነዚህ ፕሮጀክቶች የከተማ አስተዳደሩ ለዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍል ያለውን ፅኑ ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳዩ ህያው ምስክሮች ናቸው።
የከተማ አስተዳደሩ እየተከተለው ያለው የልማት አቅጣጫ ሰውን ያላገለለና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ነው። ከአዋሬ የተጀመረው የበጎነት ጥንስስ፣ ዛሬ በልደታና በሌሎችም አካባቢዎች በግዙፍ ህንፃዎችና በተሟላ መሰረተ ልማት ታጅቦ "የበጎነት መንደር" ሆኖ አብቧል። ይህ ጉዞ ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹና በጎነት ባህል የሆነባት የሰብአዊነት መገለጫ ወደመሆን ከፍ ያደረጋት ታሪካዊ ክንውን ነው።

❤2
❤2