የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ከጠባቧ የቀበሌ ቤት ወደ ዘመናዊው አፓርታማ፦ የወይዘሮ ሀዋ ሸሪፍ የሕይወት ለውጥ
በልደታ ክፍለ ከተማ "ሳር ቤት" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለበርካታ ዓመታት በአንድ ጠባብ የቀበሌ ቤት ውስጥ ከአምስት የቤተሰብ አባላቶቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩት ወይዘሮ ሀዋ ሸሪፍ፣ "ከሞተ በላይ፣ በሕይወት ካለው በታች" ሆነው የመከራ ሕይወት ማሳለፋቸውን በምሬት ይናገራሉ።
ይኖሩበት የነበረው አንድ ጠባብ ክፍል ቤት ውስጥ አንድ ፍራሽ ብቻ ዘርግተው፣ ገሚሱ ቤተሰብ በራስጌ ገሚሱ ደግሞ በግርጌ ተፋፍገው ለማደር ይገደዱ እንደነበር ወይዘሮ ሀዋ ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።
ከመኝታ ችግር ባለፈ፣ የዕድሜያቸውና የጤናቸው ሁኔታ ችግሩን ይበልጥ አክብዶት እንደነበር አንስተው፣ በሌሊት ወደ መፀዳጃ ቤት እንኳን ለመሄድ መነሳት የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ያወጋሉ፡፡
እንዴትም ብለው ለሊት ሲነሱም እንኳን፣ በልጆቻቸው ላይ እንዳይወድቁ ይፈሩ እንደነበር ያስታውሳሉ።
ቤቱ ለኑሮ ምቹ ባለመሆኑ እና በጠባብነቱ ምክንያት ልጆቻቸው እና የልጅ ልጆቻቸው በዓላትን አብረው ለማሳለፍ ይቸገሩ እንደነበርም ይናገራሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባከናወነው "ሰው ተኮር" የልማት ሥራ፣ ወይዘሮ ሀዋ ባለ አራት ወለል ዘመናዊ ህንፃ ላይ ሰፊና ምቹ መኖሪያ ቤት አግኝተዋል።
አሁን ያለሁበትን ሁኔታ ለመግለጽ ቃላት ያጥረኛል የሚሉት ወይዘሮ ሀዋ፣ ዘንድሮ ከልጅ ልጆቻቸው እና ከቅርብ ዘመዶቻቸው ጋር በአዲሱ ቤታቸው በደስታ የኢድ በዓልን ማሳለፋቸውን ገልጸዋል።
በዐረብ ሀገር ለብዙ ዓመታት ሠርታ የተመለሰችው ልጃቸውም፣ ቀደም ሲል ለእናቷ ያመጣቻቸውን እቃዎች ለማውጣት ትቸገር እንደነበር በማንሳት፣ አሁን ላይ ግን አውጥታ እናትና አባቷን ማሳመር በመቻሏ ታላቅ ደስታ እንደተሰማት ተናግራለች።
ወይዘሮ ሀዋ እና ቤተሰባቸው ይህንን እድል ላመቻቹ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ በተለይም ለከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ለባለሀብቶች ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ይህ ታሪክ በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች የዜጎችን ሕይወት እንዴት እንደሚቀይሩ የሚያሳይ ህያው ምስክር እንደሆነ የእድሉ ተጠቃሚዎች የሰጡት ምስክርነት ያረጋግጣል።
Via AMN

ውቧ አዲስ አበባ፦
በሴቶች ቆራጥነት በውጤት ተምሳሌትነት እየተገነባች ያለችው የሁላችን ከተማ አዲስ አበባ!
#በመላ ኑሪ፣ በኮንፊደንስ ሩጪ!" ሴቶች 5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ
በሴቶች ቆራጥነት በውጤት ተምሳሌትነት እየተገነባች ያለችው የሁላችን ከተማ አዲስ አበባ!
#በመላ ኑሪ፣ በኮንፊደንስ ሩጪ!" ሴቶች 5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ቅድሚያ ለሴቶች!
ሴቶች በጥበብ ይኖራሉ፤ በራስ መተማመን ይሠራሉ፤ በራስ መተማመን ይሮጣሉ፤ ይችላሉም! ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን የአገራችንን ብልፅግና እናረጋግጣለን።
ዛሬ ማለዳ 16 ሺህ ሴቶች የሚሳተፉበትን የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በድምቀት አስጀምረናል። በታላቁ ሩጫ አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚካሄደው ይህ ውድድር፤ ዘንድሮ በኮሪደር ልማታችን አማካኝነት እጅግ ውብ፣ ምቹ እና ለከተማችን አዲስ ዘመናዊ መልክ ባላበሰው በቦሌ - አትላስ - ኡራኤል መንገድ ላይ በልዩ ድምቀት ተከናውኗል።
እንኳን ደስ አላችሁ!
ሁላችሁም አሸናፊዎች ናችሁ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

👍2
ዛሬ በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ መልሶ ማልማት ፎረም የእኛ ሚኒስትሮች እና የጣሊያ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትርና የዓለምቀፍ ትብብር ሀላፊ በተገኙበት አስጀምረናል።
አሁን ላይ በመዲናችን የንግድ እንቅስቃሴ እያደገ፣ የኢንቨስትመንት ፍሰቱም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል። አዲስ አበባ በፍጥነት እየተለወጠች በመሆኗ፣ ይህ የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ መልሶ ማልማት ፎረም መካሄዱ ወቅታዊ፣ ትክክለኛና እጅግ አስፈላጊ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለግል ዘርፉና ለኢንቨስትመንት መስፋፋት ትልቅ ድጋፍ ያደርጋል። የጣሊያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በዚህች በተለወጠች ከተማ ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
አዲስ አበባ የተለወጠችው በገፅታ ብቻ ሳይሆን ቢዝነስ ለመስራት አመቺና ቀላል በመሆኗም ጭምር ነው። ኢንቨስት ለማድረግ ስትመጡ በፈጣንና ቀልጣፋ አሰራር ለማስተናገድ እንደ ‘መሶብ’ ያሉ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎቶች ዝግጁ ናቸው። አስተዳደራችን የግል ዘርፉን ለመደገፍ እጅግ ቁርጠኛ ሲሆን፣ ይህ ፎረም ለዚህ ግብ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው እርግጠኞች ነን።
ክቡራን የፎረሙ ተሳታፊዎች፤ በአዲስ አበባ የሚኖራችሁ ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን እመኛለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

👍2❤1
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ከሚገኘው የመጀመሪያው የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን ፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ መልሶ ማልማት ፎረም ጎን ለጎን፣ ከጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ማሪያ ትሪፖዲ ጋር በመሆን ከእንጦጦ እስከ አራዳ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ጎብኝተናል።
ክብርት ማሪያ ትሪፖዲ፤ ለነበረን ፍሬያማ ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ክብርት ማሪያ ትሪፖዲ፤ ለነበረን ፍሬያማ ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
❤2👍1
ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር መፈፀም ተከታታይነት ያለው የማያቋርጥ ተግባር ሆኗል።
ዛሬ በከተማችን 4ኛውን የቂርቆስ ቅርንጫፍ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት በይፋ ሥራ አስጀምረናል።
የቂርቆስ ቅርንጫፍ አዲስ የመሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት 20 ተቋማት፣ በ85 የአገልግሎት መስኮቶች፣ 112 የተለያዩ የሕዝብ አገልግሎቶችን በአንድ ስፍራ ለተገልጋይ ያቀርባል። ይህም የመንግሥት አገልግሎትን በማላቅ፤ ደላላን ፣ ሌብነትን፣ አድሎ እና እንግልትን በማስወገድ፣ ተደራሽነትን እና የዜጎችን እርካታ በማሳደግ፣ በተቋማት መካከል የነበረውን የተበታተነ አገልግሎት በማቀናጀት እንዲሁም ኅብረተሰቡ አገልግሎት ለማግኘት የሚያጠፋውን ጊዜና ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ፍትሐዊ አገልግሎት የሚያሰፍን ይሆናል ።
የተቀናጁ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የመንግሥት አገልግሎት አፈጻጸም ቁልፍ የክዋኔ መለኪያ እና አጠቃላይ የዜጎች እርካታን እያመጡ፣ አካታች እና ፍታዊ ተጠቃሚነት ማጎልበቻ ስርአት እየሆሙ ነው። ማዕከሉ ለአጠቃላይ ተገልጋዩ ማህበረሰብ ምቹ ሲሆን፤ በተለይም አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ፣ እንዲሁም ለሠራተኞች ምቹ የሥራ አካባቢን የፈጠረ ነው።
የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል አቀናጅቶ የማቅረብ መርሃ ግብር ስኬት እና በተሟላ መንገድ ተግባራዊ እንዲሆን አስቀድመን በኮሪደር ልማት የዘረጋናቸው መሠረተ ልማቶች ወሳኝ ሚና እያበረከቱ ይገኛሉ ።
ይህንን ለሕዝባችን እሮሮ መነሻ ሆኖ የቆየ አገልግሎት አሰጣጥ ችግር መሰረታዊ መፍትሄ ወደ ሥራ እንዲገባ በፍጥነትና በትጋት ሌት ተቀን ለሠራችሁ፣ የሕዝባችንን የአገልግሎት ጫና ላቀለላችሁ ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
አዲስ አበባ —መጋቢት 17/2018 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በመዲናዋ ማህበራዊ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በጋራ ለመከወን የሚያስችላቸውን ታሪካዊ የመግባቢያ ሰነድ በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል።
የፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ የተከናወነው በጉባኤው ጽሕፈት ቤት ሲሆን፣ ስምምነቱ በዋናነት በከተማዋ የሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን ይበልጥ የተቀናጁና ውጤታማ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በስምምነቱ ወቅት የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ እንደተናገሩት፣ በቅዱሳት መጻሕፍት አስተምህሮ መሠረት ለሰው ልጆች በጎነትን ማድረግ የሐይማኖት ተቋማት ቀዳሚ ተግባር ነው።
ምድራችን በብዙ ተፈጥሯዊ ሀብት የታደለች በመሆኗ፣ ይህንን ሀብት ለማህበራዊ በጎ ስራዎች በማዋል ማኅበረሰባችንን ማገልገል ይገባል" ያሉት መጋቢ ታምራት፣ ቤተ ዕምነቶች በየዓመቱ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት እያከናወኑት ያለውን የበጎ አድራጎት ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል፣ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አስራት ንጉሴ፣ ስምምነቱ የከተማዋ ነዋሪዎች በበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉና የእርስ በእርስ መረዳዳት ባህል እንዲጎለብት ትልቅ መሠረት እንደሚጥል ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለት የተፈራረምነው ሰነድ የሐይማኖት ተቋማት እያበረከቱ ያለውን ሚና ይበልጥ የሚያጠናክርና ትውልድን በሥነ-ምግባር ለመገንባት የሚያግዝ ነው ብለዋል ምክትል ኮሚሽነሯ።
ሁለቱ ተቋማት ይህንን የመግባቢያ ሰነድ ተግባራዊ በማድረግ በመዲናዋ የሚታዩ ማህበራዊ ችግሮችን በጋራ ለመቅረፍ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።

❤3👍1
በአዲስ አበባ ከተማ ማኅበረሰቡን በስፋት ያሳተፉ የአካባቢ መሠረተ ልማት ግንባታዎች በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በተያዘው የበጀት ዓመት የታቀዱ የሰቤዝ መንገድ ልማት ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ፣ በአሁኑ ወቅት የኮብልስቶን ንጣፍ ሥራዎች በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች በስፋት እየተተገበሩ ነው።
እነዚህ የልማት ሥራዎች "የራስን ችግር በራስ የመፍታት" ከተማ አቀፍ እሳቤን በተግባር እያሳዩ ያሉ ውጤቶች ናቸው። ፕሮጀክቶቹ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው በሚከናወኑ የልማት ተግባራት ላይ በቀጥታ እንዲሳተፉ በማድረግ፣ የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማቸውና የጋራ ችግሮቻቸውን በጋራ ጥረት እንዲፈቱ ዕድል ፈጥረዋል። ይህም ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ይበልጥ ተስማሚ የማድረግ ስትራቴጂ አንዱ አካል ነው።
የአካባቢው ማኅበረሰብ ከልማት ጠባቂነት መንፈስ ወጥቶ የራሱን አካባቢ ለማልማት እያሳየ ያለው ተነሳሽነት፣ ለዓመታት ሲስተዋሉ የነበሩ የመልካም አስተዳደርና የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመመለስ አስችሏል። ነዋሪዎች በገንዘባቸው፣ በእውቀታቸውና በጉልበታቸው እያደረጉት ያለው ንቁ ተሳትፎ የልማት ሥራዎች እንዲፋጠኑና ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ እያደረገ ይገኛል።
የመንግሥትና የሕዝብ ቅንጅት ይበልጥ እንዲጠናከር ለማድረግም፣ መንግሥት ለነዚህ የሕዝብ ተሳትፎ ፕሮጀክቶች የ35 በመቶ የፋይናንስ ድጎማ እያደረገ ይገኛል። ይህ ድጋፍ ማኅበረሰቡ የጀመራቸው የልማት ጥረቶች ግባቸውን እንዲመቱና የፋይናንስ ክፍተቶች እንዳያጋጥሙ ትልቅ አቅም ሆኗል።

❤4👍1