የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
818 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 በህዝብ አቅም የተጀመረው ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ግንባታ!

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 በኅብረተሰብ ተሳትፎ የሚገነባ ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራ በይፋ መጀመሩ ተገልጿል።

ይህ ፕሮጀክት የ40/60 የጋራ መኖሪያና የንግድ ቤት ባለቤቶች ማኅበር ከወረዳው አስተዳደር ጋር በመተባበር እየተገነባ ሲሆን፣ ለወጣቶችና ለማኅበረሰቡ ጤናማ፣ ንቁ እና የተደራጀ ህይወት ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

ፕሮጀክቱ ወጣቶችን ከአደገኛ ባህሪያት በማራቅ ወደ ጤናማ እንቅስቃሴ ከመምራት ባሻገር በኅብረተሰቡ መካከል አንድነትንና መተባበርን በማጠናከር ረገድ ማኅበራዊ ፋይዳው ከፍተኛ ነው።

በግንባታ ወቅት የስራ ዕድሎችን በመፍጠር የአካባቢውን የንግድና አገልግሎት እንቅስቃሴን በመጨመር ለአካባቢው ነዋሪዎች ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ይሰጣል።

ይህ ፕሮጀክት የመንግሥት፣ የህዝብ እና የግል ተቋማትን ትብብር የሚያሳይ ተምሳሌት ሲሆን፣ በከተማችን ውስጥ የስፖርትና የልማት ባህልን ለማጠናከር እገዛ ያደርጋል።

#Bole #Woreda14 #SportForAll #AddisAbaba #CommunityPower
1👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
መንግሥት ሁሉንም የሃይማኖት ተቋማት በእኩልነት እንደ ዕሴቶቻቸውና አስተምህሯቸው በፍትሃዊነት ያገለግላል!

ከሌሎች የሀይማኖት ተቋማት ጋር እንዳደረግነው ሁሉ ዛሬ ከኢትዮጵያ ወንጌላውያን፣ ከካቶሊክ እና ከሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያናት መሪዎች ጋር “የሃይማኖት ተቋማት በመደመር መንግሥት እይታ” በሚል መሪ ሀሳብ ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል።
ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት፣ የካቶሊክ እና የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በሰላም፣ በልማትና በትውልድ ግንባታ ሂደት ውስጥ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እንዲዳብር፣ አንድነት እንዲጠነክር፣ ትውልድ እንዲማር ፣ በስነምግባር እንዲታነፅ ፣ ታሪክንና ቅርስን በመጠበቅ እንዲሁም ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና አበርክተዋል። በተጨማሪም ቴክኖሎጂን ወደ ሀገር በማስገባትና የሥራ ባሕልን በማበረታታት ረገድ ከሌሎች የሀይማኖት ተቋማት ጋር በመሆን ወሳኝ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

በታሪክ ብቻ ሳይሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታትም ተቋማቱ በከተማችን ሁለንተናዊ የሰላም ግንባታ፣ የልማት እና የብልጽግና ጉዞ ላይ እያበረከቱት ያለው ተሳትፎ ጉልህ ነው። በመድረኩ ለሕዝቦች ትስስር መጎልበት፣ በማኅበራዊ ልማትና በበጎ ፈቃድ ሥራዎች ተሳትፎ፣ የሥራ ባሕልን በማስረጽ፣ ትውልድን በሥነ ምግባር በመገንባት፣ የበጎነት ስራ መስራት እንዲለመድ በማድረግ፣ ለመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ መጎልበት እንዲሁም ሰላምን በማስፈንና ሕገወጥነትን በመከላከል ረገድ ለኢትዮጵያ ብልጽግና እና ለብሔራዊ ጥቅም በጋራ ለመቆም ጠቃሚ ውይይት አድርገናል።

በውይይታችን የተነሱ በስራ ሂደት ያጋጠሙ አንዳንድ ክፍተቶችን እና እንግልቶችን በቀጣይ በትብብር ለማረም የሚያስችል ምቹ መደላድል የፈጠረ ውጤታማ መድረክም ነበር። ይህ መድረክ በየክፍለ ከተማው ሲካሄዱ የቆዩ ውይይቶች ማጠቃለያ ሲሆን፣ የመንግሥትንና የሃይማኖት ተቋማትን ሚና እና ድርሻ በግልጽ ለይቶ ያስቀመጠ ነው።

ክቡራን የወንጌላውያን ፣ የካቶሊክ እና የኢትዮጵያ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን መሪዎች ላደረጋችሁት ከፍተኛ ተሳትፎና ለሰጣችሁት ገንቢ ሐሳብ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ባለፉት ሰባት ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የአካባቢ ልማትና ሰው ተኮር ተግባራት የነዋሪውን ተሳትፎ ማዕከል በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ከንፋስ ስልክ ላፍቶና ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የብሎክ ካውንስል አመራሮች ጋር ባካሄደው የሰባት ዓመታት የኅብረተሰብ ተሳትፎ ስኬቶች አራተኛ ዙር የግምገማ መድረክ፣ ፕሮጀክቶችን የሕዝብ አቅም በማስተባበር የመፈጸም ልምድ የከተማዋ መለያ እየሆነ መምጣቱ ተመላክቷል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወይዘሮ ፀሐይ ኪባሞ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ ስልጣን ሕዝብን ማገልገያ መሆኑን በተግባር በማረጋገጥ የኮሚሽኑ አመራሮች በቀን 24 ሰዓትና በሳምንት ሰባት ቀናት (24/7) ሊረባረቡ ይገባል። በሂደት የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን በመስበር መምራት እንደሚገባ ያሳሰቡት ምክትል ኮሚሽነሯ፣ ይህም ከተማዋን ወደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የሚያሸጋግርና የሕዝብን አቅም አስተባብሮ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ተግባራዊ ማረጋገጫ መሆኑን ጠቁመዋል።

የከተማዋ ዕድገት የሚለካው በነዋሪዎቿ ተሳትፎና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ መሆኑን የተናገሩት ወይዘሮ ፀሐይ በተለይም አቅመ ደካማ ወገኖችን ማዕከል ያደረጉ የበጎ ፈቃድ ስራዎችና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የከተማዋን እድገት ወደ ላቀ ከፍታ የሚያሸጋግሩ ተሞክሮዎች እንደሆኑ ገልፀዋል።

የብሎክ አመራሮች ባለፉት ሰባት ዓመታት የተገኙ ድሎችን መሰረት በማድረግ የአካባቢያቸውን ችግር በራሳቸው አቅም ለመፍታት የሚያደርጉትን ጥረት በማስቀጠል አዲስ አበባ “የራሷን ችግር በራሷ አቅም የምትፈታ ተምሳሌት ከተማ” ለማድረግ የተቀመጠውን ራዕይ በላቀ ቁርጠኝነት ማሳካት እንደሚገባ ምክትል ኮሚሽነሮ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ የብሎክ ካውንስል አመራሮች ጋር በአራት ዙር ሲካሄድ የቆየው የሰባት ዓመታት የኅብረተሰብ ተሳትፎ ስኬቶችና የቀጣይ አቅጣጫዎች የግምገማ መድረክ ዛሬ ተጠናቋል።
👍1
ዛሬ በኮሪደር ልማት የተገነቡ 315 የንግድ ሱቆችን፣ በቀበሌና በንግድ ቤቶች በኪራይ ሲሰሩ ለነበሩ የኮሪደር ልማት ተነሺዎች በዕጣ አስተላልፈናል።

በከተማችን ከዚህ ቀደም የመንግስት የቀበሌና የንግድ ቤቶችን ተከራይተው ሲሰሩ ለነበሩ ነዋሪዎች አስተዳደራችን ሁለት አማራጮችን አቅርቦ እንደየምርጫቸው በአክሲዮን ተደራጅተው ወደ ንግድ ሱቃቸው ገብተው ሥራ እንዲጀምሩ፣ ይህ ካልሆነም መንግስት የሚያቀርብላቸውን ሱቆች ተከራይተው እንዲሰሩ እድል ሰጥቶ ነበር።

አብዛኛዎቹ መንግስት ገንብቶ ያቀረብላቸውን ሱቆች ተከራይተው ንግዳቸውን የቀጠሉ ሲሆን፣ በአክሲዮን ተደራጅተው ወደ ንግድ ሱቃቸው ገንብተው ለመነገድ የመረጡም በርካቶች ነበሩ። ከእነዚህ በአክሲዮን እንዲደራጁና መሬት ተረክበው እንዲገነቡ ከተፈቀደላቸው ውስጥ የመገንባት አቅም በማጣታቸው በተለያዩ የውይይት መድረኮች ሌላ አማራጭ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ቆይተዋል።

በመሆኑም አስተዳደራችን ችግሩን ለመቅረፍ፤ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ ዳርቻ ልማት እና በመልሶ ማልማት ሥራዎች ምክንያት ለተነሱ ነዋሪዎች፤ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች በኮሪደር ልማቱ የተገነቡ 315 ዘመናዊ የንግድ ሱቆችን በዕጣ እንዲተላለፉላቸው አድርጓል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍1
ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ ከተሾሙት በኢትዮጵያ የጣሊያን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም አዲስ አበባ ከጣሊያን ከተሞች ጋር ያላትን ትብብር እና አጋርነት አጠናክሮ ለማስቀጠል፤ እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መካከል ያለውን የቆየ የታሪክ፣ የባህል እና የልማት ትብብር ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ምክክር አድርገዋል።

ኢትዮጵያና ጣሊያን የቆየ የታሪክ፣ የባህል፣ የልማት ትብብር እና የሁለትዮሽ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ያላቸው አገራት ናቸው።
3
ዛሬ ማለዳ የዒድ አል-ፈጥር በዓልን አስመልክቶ፣ ከ100 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖቻችን ማዕድ አጋርተናል።

ወትሮም በሌሎች በዓላት ላይ እንደምናደርገው ሁሉ ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ፣ ለአቅመ ደካሞች ፣ ለአካል ጉዳተኞች ፣ እንዲሁም ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው የከተማችን ነዋሪዎች የሚደረገው ይህ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር በሁሉም የከተማችን ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ የረመዳን ወቅትም 27 ሺህ ያህል ወገኖቻችን ወሩን በሙሉ በ28ቱም የምገባ ማዕከሎቻችን የአፍጥር ፕሮግራም ተዘጋጅቶላቸው ያለ ችግር እንዲያሳልፉ አድርገናል።

የማዕድ ማጋራት የምናደርገው ጊዜያዊ ችግርን ለመቅረፍ ብቻ ሳይሆን ለሕዝባችን ያለንን ክብር ለመግለጽ ሲሆን፤ ወንድማማችነትን እና የእርስ በእርስ መደጋገፍ እሴትን ለማጎልበት ነዉ።

እንደ ሁልጊዜውም በከተማችን በምናከናውናቸው የማዕድ ማጋራት ሥራዎች ላይ በማስተባበር፣ አቅመ ደካሞችን በጉልበታቸው በማገዝ ደፋ ቀና ለሚሉ የከተማችን ወጣቶችን፣ካላቸው ቆርሰው ለመስጠት ለማይሳሱ ባለሀብቶችና የከተማችን ነዋሪዎች በተጠቃሚዎች ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
በተለይም ዛሬ በከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያደረግነውን የማዕድ ማጋራት ለደገፉት ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለአቶ ጀማል አሕመድ እና የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ኤምባሲ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

በዓሉ የደስታና የመተሳሰብ እንዲሆን ከወዲሁ እመኛለሁ!
ዒድ ሙባረክ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
🥰4
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ከጠባቧ የቀበሌ ቤት ወደ ዘመናዊው አፓርታማ፦ የወይዘሮ ሀዋ ሸሪፍ የሕይወት ለውጥ

በልደታ ክፍለ ከተማ "ሳር ቤት" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለበርካታ ዓመታት በአንድ ጠባብ የቀበሌ ቤት ውስጥ ከአምስት የቤተሰብ አባላቶቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩት ወይዘሮ ሀዋ ሸሪፍ፣ "ከሞተ በላይ፣ በሕይወት ካለው በታች" ሆነው የመከራ ሕይወት ማሳለፋቸውን በምሬት ይናገራሉ።

ይኖሩበት የነበረው አንድ ጠባብ ክፍል ቤት ውስጥ አንድ ፍራሽ ብቻ ዘርግተው፣ ገሚሱ ቤተሰብ በራስጌ ገሚሱ ደግሞ በግርጌ ተፋፍገው ለማደር ይገደዱ እንደነበር ወይዘሮ ሀዋ ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

ከመኝታ ችግር ባለፈ፣ የዕድሜያቸውና የጤናቸው ሁኔታ ችግሩን ይበልጥ አክብዶት እንደነበር አንስተው፣ በሌሊት ወደ መፀዳጃ ቤት እንኳን ለመሄድ መነሳት የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ያወጋሉ፡፡

እንዴትም ብለው ለሊት ሲነሱም እንኳን፣ በልጆቻቸው ላይ እንዳይወድቁ ይፈሩ እንደነበር ያስታውሳሉ።

ቤቱ ለኑሮ ምቹ ባለመሆኑ እና በጠባብነቱ ምክንያት ልጆቻቸው እና የልጅ ልጆቻቸው በዓላትን አብረው ለማሳለፍ ይቸገሩ እንደነበርም ይናገራሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባከናወነው "ሰው ተኮር" የልማት ሥራ፣ ወይዘሮ ሀዋ ባለ አራት ወለል ዘመናዊ ህንፃ ላይ ሰፊና ምቹ መኖሪያ ቤት አግኝተዋል።

አሁን ያለሁበትን ሁኔታ ለመግለጽ ቃላት ያጥረኛል የሚሉት ወይዘሮ ሀዋ፣ ዘንድሮ ከልጅ ልጆቻቸው እና ከቅርብ ዘመዶቻቸው ጋር በአዲሱ ቤታቸው በደስታ የኢድ በዓልን ማሳለፋቸውን ገልጸዋል።

በዐረብ ሀገር ለብዙ ዓመታት ሠርታ የተመለሰችው ልጃቸውም፣ ቀደም ሲል ለእናቷ ያመጣቻቸውን እቃዎች ለማውጣት ትቸገር እንደነበር በማንሳት፣ አሁን ላይ ግን አውጥታ እናትና አባቷን ማሳመር በመቻሏ ታላቅ ደስታ እንደተሰማት ተናግራለች።

ወይዘሮ ሀዋ እና ቤተሰባቸው ይህንን እድል ላመቻቹ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ በተለይም ለከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ለባለሀብቶች ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ይህ ታሪክ በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች የዜጎችን ሕይወት እንዴት እንደሚቀይሩ የሚያሳይ ህያው ምስክር እንደሆነ የእድሉ ተጠቃሚዎች የሰጡት ምስክርነት ያረጋግጣል።

Via AMN