የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
810 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
ባለፉት 6 ወራት በንግዱ ዘርፍ የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች በተመለከተ

የገበያ መረጋጋት እና የምርት አቅርቦት
👉የሰብል አቅርቦት 688,153 ኩንታል በላይ ፤
👉አትክልትና ፍራፍሬ 3,899,375 በላይ ፤
👉ዳልጋ ክብት እና በግና ፍየል 2,127,208 በላይ ማቅረብ የተቻለ ሲሆን፤
👉በተጨማሪም የድጐማ ምርቶች በተለይ በየቀኑ በሚሊዮኖች የዳቦ አቅርቦትን በመጨመር፣
👉12,601,755 ሊትር የምግብ ዘይትና 242,892 ኩንታል ስኳር በማቅረብ የከተማችንን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ ተጨባጭ ስራዎች አከናውነናል ፡፡

👉የንግድ መሠረተ ልማት እና ቁጥጥር
የደላላን ሰንሰለት ለመበጠስና ሸማቹን ከአምራች ጋር በቀጥታ ለማገናኘት ሰፊ ስራዎች ተሰርተዋል፦
👉የገበያ ማዕከላት፦ በአምስቱም የከተማ መግቢያዎች ከተገነቡት በተጨማሪ የላፍቶ ቁጥር 2 ገበያ ማዕከል ወደ አገልግሎት ገብቷል።
👉የቅዳሜና እሁድ ገበያ፦ የገበያ ቦታዎች ቁጥር ከ219 ወደ 245 ከፍ እንዲል ተደርጓል።
👉ህጋዊነትን ማስፈን፦ በ230,013 ድርጅቶች ላይ ክትትል ተደርጎ፣ 12,139 ጥፋተኞች ተለይተዋል። ከእነዚህም ውስጥ 10,496 ነጋዴዎች ወደ ህጋዊ መስመር ተመልሰዋል።
👉መደበኛ ያልሆነ ንግድ፦ 7,400 መደበኛ ያልሆኑ አነስተኛ ንግዶችን ህጋዊ እውቅና በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል።
ባለፉት 6 ወራት በጤናው ዘርፍ የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች ባጭሩ፦
1. የጤና ጥራትና ዲጂታላይዜሽን
👉የሞት ምጣኔ፦ የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ሞትን በመቀነስ የ2030 የዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) ተሳክተዋል።
👉ወረቀት አልባ አገልግሎት፦ ሁሉም ሆስፒታሎችን ጨምሮ 67 የጤና ተቋማት የኤሌክትሮኒክ መረጃ አያያዝ (EMR) መተግበር ጀምረዋል።
2. የጤና መድህንና ተደራሽነት
👉ተጠቃሚነት፦ 2.7 ሚሊዮን አባላት ያሉት ሲሆን፣ 1.49 ሚሊዮን ዜጎች በጤና መድህኑ ታክመዋል።
ድጋፍ፦ መንግስት በዓመት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ይመድባል።
3. መሰረተ ልማትና ሆስፒታሎች
👉አዳዲስ ተቋማት፦ 9 አዲስ ጤና ጣቢያዎች ተገንብተዋል፤ 13ቱ ላይ የማስፋፊያ ስራ ተሰርቷል።
ግዙፍ ፕሮጀክቶች፦ የኮልፌ መንዲዳ፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ እና የገላን ትራውማ ሆስፒታሎች ግንባታ ተጠናቆ ወደ ስራ ለመግባት ተዘጋጅተዋል።
👉ራስን መቻል፦ ሁሉም ሆስፒታሎች የራሳቸው የኦክስጅን ማምረቻ እንዲኖራቸው ተደርጓል።
4. የህጻናት ልማትና አልሚ ምግብ
👉እንክብካቤ፦ 1.3 ሚሊዮን ህጻናትን ታሳቢ ያደረገ ፕሮግራም ተቀርጿል፤ 1,000 ማቆያዎች ተገንብተዋል።
👉በካሳንቺስ 5 ሄክታር ላይ "የህጻናት አለም" እየተገነባ ነው።
👉አካላዊ እድገት ውስኑነት ለታየባቸው 185 ህጻናት ችግራቸውን ታሳቢ ያደረግ የዊልቼር ድጋፍ ተደርጓል።

👉ምክርና ድጋፍ፦ ለ245,803 ቤተሰቦች የቤት ለቤት ምክር ተሰጥቷል፤ ለ15,000 እናቶችና ህጻናት የአልሚ ምግብ ድጋፍ ተደርጓል።
👉ውጤት፦ የህጻናት እድገት ሁኔታ 2.7% መሻሻል አሳይቷል።
ቱሪዝም በተመለከተ

የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት የቱሪዝም ኢንዱስትሪው ለከተማዋ ዕድገት ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አስተዋፆኦ ለማሳደግ በርካታ የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲለሙ ተደርጓል፡፡

በዚህም ወደ ከተማችን የሚመጡ ቱሪስቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል፡፡
• ባላፉት ስድሰት ወራት ከተማችንን ይጎበኛሉ ተብሎ ከታቀዱ 4.7 ሚሊየን የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች 4.9 ሚሊየን ቱሪስቶች መዲናችንን ጎብኝተዋል፡፡
•በከተማችን ላይ ሲከበሩ የነበሩ ህዝባዊ እና ሃይማኖታዊ ባህላዊ የአደባባይ በአላት፤ እንዲሁም የስፖርትና የጤና ቱሪዝም መስፋፋት ከፍተኛ አበርክቶ ነበራቸው፡፡ን መጎብኘት ችለዋል፡፡

ይህም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃጸር በ15 ፐርሰንት ብልጫ አሳይቷል፡፡ ከተማችንን የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማእከል ለማድረግ የተከናወኑ በርካታ የልማት ስራዎችና ሜጋ ፕሮጀክቶች ፍሬ በማፍራት በከተማችን ውስጥ የሚደረጉ ኩነቶች ጨምረዋል፡፡
•ባለፉት ስድት ወራት 150 የሚሆኑ አለማቀፍና አህጉር አቀፍ ኩነቶች አዲስ አበባ ላይ ተካሂደዋል፡፡ ይህም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃጻር የ50 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

በአጠቃላይ ከሀገር ውስጥ እንዲሁም
• በተመሳሳይ 699,761 ቱሪስቶች ከተማችንከውጪ ሀገር የቱሪስት ፍሰት ባለፉት ስድት ወራት 155 ቢሊየን ብር ወደ ኢኮኖሚ ፈሰስ ማድረግ ተችሏል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኪነ-ጥበብ ዘርፍን በተመለከተ

በኪነ-ጥበብ የዘርፉን አቅምና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ሊያሳድጉ የሚችሉ 380 የሥነ ጽሁፍ ሥራዎችን ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ መፈፀም ተችሏል፡፡በዚህም እጅግ ዘመናዊ የትያትርና ፊልም ማእከላትን በመገንባት ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል፡፡

25 የሚሆኑ የዕይታዊ ጥበባትና ክውን መልቲ-ሚዲያ ሥራዎች የስዕል ኤግዚቢሽኖች፣ ቶክ-ሾውና ስልጠናዎችን ተካሄደዋል፡፡

እንዲሁም በከተማዋ መንግስታዊ ኩነቶችን ተከትሎ 245 የሚሆኑ የኪነ-ጥበብ መድረኮችና ኩነቶችን ማዘጋጀትና ማስተባበር ታቅዶ 100% መፈፀም ተችሏል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
1
ትራንስፖርት ዘርፍ በተመለከተ፤-

ባለፉት 6ወራት 14,133 ተሸከርካሪዎችን በማሰማራት በቀን በአማካይ 3.98 ሚሊየን ህዝብ በማጓጓዝ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ማሳለጥ ተችሏል፡፡

የብዙኃን ትራንስፖርት ድርሻ ከነበረበት 36 በመቶ ወደ 42 በመቶ ማሳደግ ተችሏል፤

የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ከማስፋፋት አኳያ የከተማውን የትራንስፖርት ችግር በወሳኝነት ሊቀርፍ የሚችል የፈጣን አውቶብስ ትራንዚት የBRT B2 ፕሮጀክት የ15.6 ኪ.ሜ የመንገድና የዴፖ ግንባታ ስራም ተጀምሯል፡፡

የሞተር አልባ ትራንስፖርትን ከማስፋፋት አኳያ በኮሪደር ልማት የተገነቡትን 241 ኪ/ሜትር የብስክሌት ኦፕሬሽን ስራ ለማስጀመር 10 ኦፕሬተሮች የምዝገባ ፍቃድ ወስደው ሶስቱ ብስክሌቶችን ከውጪ የማስገባት ስራ እየተሰራ ነዉ፡፡

ባልተገባ የመንገድ አጠቃቀም የሚከተሉ አሽከርካሪዎችና እግረኛ የመንገድ ተጠቃሚዎችን የመቆጣጠርና አስተማሪ እርምጃዎችን የመዉሰድ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

የትራፊክ ቁጥጥር እና የፓርኪንግ አስተዳደር ክፍያ ስራዎችን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ አገልግሎቱን ማዘመንና ማሻሻል ተችሏል፡፡
👍1
የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት በተመለከተ

👉የቆየውን የሲስተም መቆራረጥ ችግር የሚፈታ አዲስ ቴክኖሎጂ ወደ ሥራ ገብቷል።

👉በዚህም ለ 805,432 ነዋሪዎች ቀልጣፋ የነዋሪነት አገልግሎት ተሰጥቷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ክህሎት በተመለከተ
👉ቋሚ ሥራ፦ ለ 195,112 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ::
👉ጊዜያዊ ሥራ፦ በኮሪደር እና በቤት ግንባታ ፕሮጀክቶች 250,000 በላይ ሰዎች ጊዜያዊ ሥራ አግኝተዋል።
👉የዘርፍ ድርሻ፦ የአገልግሎት ዘርፍ (71%) ትልቁን ድርሻ ሲይዝ፣ ኢንዱስትሪ (21%) እና ግብርና (8%) ይከተላሉ።
👉ስልጠና፦ 266,962 ሰልጣኞች በክህሎት መር አጫጭር ስልጠናዎች ሰልጥነዋል።
👉ተጠቃሚዎች፦ ሴቶች 53.7%፣ ወጣቶች 49.25%
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍1
አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ:-

የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን ዲጂታላይዝ ለማድረግ በተሰራው ስራ 23 አዳዲስ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በማስደገፍ 370 አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ ታግዘው እንዲሰጡ ማድረግ ተችሏል።

በ"መሶብ" የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲለሙ በማድረግ፤ ጊዜንና ወጪን በመቀነስ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይን እርካታ 94.2% ማድረስ ተችሏል።

በአገልጋዩ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ከተነሱ የተገልጋይ ጥያቄዎች መካከል 86% የሚሆኑት ችግሮች መፈታታቸውን በመስክ ምልከታ ማረጋገጥ ተችሏል።

በተቋማት ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር 183 የህጻናት ማቆያ፣ 1ዐዐ የሰራተኞች ካፊቴሪያ እና 166 የሸማቾች ሱቆች አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡

ተጠያቂነት ከማስፈን አንፃር በ61 አመራሮች፤ በ126 ዳይሬክተር፤ ቡድን መሪዎችና ከ3ሺ በላይ ሰራተኞች በአገልግሎት አሰጣጥ በፈፀሙት ጥፋት ተጠያቂ ተደርገዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍2
የገቢ ግብር አሰባሰብን በተመለከተ

95% የግብር ከፋዮች ግብራቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ የተደረገ ሲሆን በ6 ወራት ለመሰብሰብ ከታቀደው 176.03 ቢሊዮን ብር ውስጥ 162.72 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 92.4% መፈፀም ተችሏል፡፡ ይህም ከ2017 ጋር ሲነፃፀር 51.12 ቢሊዮን ብር ( 45.8%) የገቢ ጭማሪ አሳይቷል ::

የግማሽ ዓመት ወጪ አፈጻጸም በተመለከተ ከጠቅላላ ወጪ፡ 148.9 ቢሊዮን ብር የካፒታል ወጪ ድርሻ 70.14% ፤ በማህበራዊ ድጋፍ ቀጥታ ድጎማ 18.72 ቢሊዮን ብር ፤ እንዲሁም ለተማሪ ምገባ ፣ ለዩኒፎርም፣ ለጤና መድህንና ለትራንስፖርት 55.7 ቢሊዮን ብር ወጪ በማድረግ 59.7% የእድገት መጠን ማሳየት ተችሏል፡፡

የቅሬታ አያያዝና አገልግሎት ክትትል በተመለከተ ከከንቲባ ጽ/ቤት ጀምሮ ግልፅ የቅሬታ ስርዓት በመዘርጋት፤ በብልሹ አሰራርና ሌብነት የተሳተፉ 282 ሰራተኞች ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ ተወሰዷል፡፡

በቴክኖሎጂ በተደገፈ የቁጥጥር ስራ በ7,678 ግብር የሚሰውሩ ነጋዴዎችና በ2,261 የጭነት መኪናዎች ያለ ደረሰኝ ምርት ሲያጓጉዙ በመገኘታቸው ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡

ከተማዋ በገቢ አሰባሰብና በጀትን በአግባቡ ከመጠቀም አንፃር ከአፍሪካ ከተሞች ጋር በተካሄደ ጥናት ምዘና መሰረት ከተማችን ቀዳሚ በመሆን ልምዷን አካፍላለች፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
1👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የመሬት ልማት እና አስተዳደርን በተመለከተ፡-

የኦንላይን አገልግሎትን ለማሳለጥ ባለፉት ስድስት ወራት በተሻሻለው ሲስተም 10,528 ካርታዎች ታትመው ተሰራጭተዋል፡፡

የለማ መሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ሥርዓትን ከማሻሻል አንፃር ለተለያዩ አገልግሎቶች 341 ሄክታር መሬት ለማዘጋጀት ታቅዶ 465 ሄ/ር መሬት ማዘጋጀት ተችሏል፡፡

ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል የከተማዋን ፍላጎት መሠረት ያደረገ 294 ሄክታር መሬት ለማስተላለፍ ታቅዶ 483 ሄ/ር ማስተላለፍ ተችሏል፡፡

የቅድመ ማልማት ጥያቄ ላቀረቡ 54 ባለይዞታዎች በይዞታቸው ላይ ማልማት እንዲችሉ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

በግማሽ ዓመቱ ለልማት ተነሺዎች 7.4 ቢሊዮን ብር በላይ ካሣ መክፈል የተቻለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ በልማት ምክንያት ለተነሱት ልማት ተነሺዎቻችን ለመሠረተ ልማት ዝርጋታ (ለመብራት) አገልግሎት ከ 400 ሚሊዮን ብር በላይ ከፍያ ተፈጽማል፡፡

የአርሶ አደር መብት ፈጠራ አፈፃፀምን በሚመለከት 6,122 ካርታዎች የታተሙ ሲሆን እስካሁን ድረስ 10,873 ካርታዎች ታትመው አርሶ አደሩ እጅ እንዲደርሱ ተደርጓል፡፡

ለ50 አርሶ አደሮች በይዞታቸዉ ላይ እንዲያለሙ ዉሳኔ ተሰጥቶ ወደ ልማት እንዲገቡ ማድረግ ተችሏል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት 41,454 ይዞታዎች ለመመዝገብ ዕቅድ ተይዞ 34,802 ማከናወን ተችሏል፡፡ እንዲሁም ለሚቀርቡ የመብት ምዝገባና የመስክ አገልግሎት ጥያቄዎች ለ84,996 ተገልጋዮች ምላሽ ለመስጠት ታቅዶ ለ94,927 በላይ ማሳካት ተችሏል፡፡

ለ7,310 ተገልጋዮች አዲስ እና አዝ ቢዊልት የግንባታ ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ ለ7,150 ገንቢዎች ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡

ለ1,990 ተገልጋዮች የግንባታ ማሻሻያ፤ ማራዘሚያ እና ማፍረሻ ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ ለ2,477 ገንቢዎች ፈቃድ መስጠት ተችሏል፡፡

ለ12,634 ተገልጋዮች የእድሳት እና ጊዜያዊ የግንባታ ፈቃድ ፣ ለ13,451 ገንቢዎች ፈቃድ በመስጠት በርካታ ሕንፃዎች ታድሰዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍1
ባለፉት 6 ወራት በኢንቨስትመንት በተመለከተ
የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ

የኢንቨስትመንት ፍቃድ አሰጣጥ ከታቀደው በላይ አፈጻጸም አሳይቷል፦

አዲስ ፈቃድ፦ 1,750 ታቅዶ ለ 2,549 ባለሀብቶች ፈቃድ ተሰጥቷል።

ማስፋፊያ፦ ማስፋፊያ ፈቃድ 140 ታቅዶ ለ 162 ተሰጥቷል።

ዕድሳት፦ ለ981 የኢንቨስትመንት ፈቃዶች እድሳት ተደርጓል።

የውጭ ዜጎች የስራ ፈቃድ፦ ለ42 የውጭ ዜጎች የስራ ፈቃድ ተሰጥቷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍1
የወጣቶችና ስፖርት ዘርፍ በተመለከተ

ወጣቶችን በልማትና በጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ለማሳተፍ የተመዘገቡ ውጤቶች፦
👉በጎ ፈቃድ አገልግሎት፦ 1,445,745 ወጣቶች በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ስራዎች (አረንጓዴ አሻራ፣ ደም መለገስ፣ ፅዳት...) ተሳትፈዋል። ይህም በገንዘብ ሲተመን 217.7 ሚሊዮን ብር ያወጣል።
👉ግንዛቤ መፍጠር፦ ለ 874,460 ወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮችና በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ ግንዛቤ ተፈጥሯል።
👉 ስፖርትና ማዘውተሪያ፦
👉32 አዳዲስ የስፖርት ሜዳዎችና ማዘውተሪያዎች ተገንብተዋል።
👉84,683 ታዳጊዎች በ723 ጣቢያዎች ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ።
👉17 ታዳጊዎች ለአገርቱ ብሔራዊ ቡድን እንዲመረጡ ተደርጓል።
👉በማህበረሰብ አቀፍ ስፖርት 3.7 ሚሊዮን ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍1
በውኃ ልማት ዘርፍ በተመለከተ

👉የከተማዋን የውኃ አቅርቦት ሽፋን በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በቀን በ60ሺህ ሜ.ኩብ የሚያሳድጉ የተለያዩ የውሃ ልማት ሥራዎች ተቀርጸው ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከዚህ አንጻር ፤-
👉ባለፉት 6 ወራት በቀን 37,996 ሜ.ኩብ ውሃ መስጠት የሚያስችሉ የ21 ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ በማጠናቀቅ በቀን 3,996 ሜ.ኩብ ውሃ መስጠት የሚያስችሉ 3 ጉድጓዶች ወደ ስርጭት ሲስተም እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
👉በቀን 100ሺህ ሜ.ኩብ ውኃ ማምረት ከሚያስችለው የጭቋላ ዌል ፊልድ የውሃ ልማት ፕሮጀክት ጋር ተያይዞ የ20 ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ወደ ስርጭት ሲስተም ለማስገባት እየተሰራ ይገኛል፡፡
👉የዘመናዊ ፍሳሽ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ 8 ፕሮጀክቶች በቀን 20ሺህ ሜ.ኩብ ፍሳሽ የማጣራት አቅም በመፍጠር እስከ 235ሺህ የሚደርስ የህብረተሰብ ክፍል የዘመናዊ ፍሳሽ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
👉የኮዬ ፈጬ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክት 75% ፤በቀን 106ሺህ ሜ.ኩብ ፍሳሽ የማጣራት አቅም የሚኖረው የምሰራቅ ተፋሰስ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ 30% ማድረስ ተችሏል፡፡
👉በሌላ በኩል 20.02 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ከመኖርያ ቤቶች የሚፈጠረውን ፍሳሽ ቆሻሻ በመስመር እና በተሸከርካሪ በማሰባሰብ 19.73 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገድ ተችሏል፡፡
ከብቲባ አዳነች አቤቤ
👍4
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የቤት ልማት አቅርቦትን በተመለከተ

በመንግስት በጀት እና በበጎ አድራጎት 11,550 መኖሪያ እና 707 ንግድ ቤቶች በድምሩ 12,257 መኖሪያ እና ንግድ ቤቶችን ለልማት ተነሺዎች፣ ለአገር ባለውለታዎች፣በጨረታና በመልካም አስተዳደር ማስተላለፍ ተችሏል፡፡

በመንግስትና የግል አጋርነት እና በከተማው በጀት ሊገነቡ ከታቀዱ 100 ሺ ቤቶች ላይ 97,000 ቤቶች ወደ ግንባታ ሂደት የገቡ ሲሆን ሁሉንም በተያዘላቸው ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው፡፡

በግል እና ሪል ስቴት የተገነቡ ቤቶች 13,517 ሲሆን በኮሪደር የለሙ 810 የንግድ ቤቶችን በልማት ለተነሱ አነስተኛ ነጋዴዎች ተላልፏል፡፡

በመንግስት እና በግል አጋርነት በተሰራው ዘርፈ ብዙ ስራ ከ70 በላይ ፕሮጀክቶችን ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል፡፡ በዚህም ከብር 1.3 ትሪሊዮን በላይ ካፒታል ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል፡፡

በ65 ህብረት ሥራ ማህበራት ለተደራጁ 5,110 ቤት ገንቢዎች ጠንካራ ድጋፍ በመደረጉ 42 ማህበራት ወደ ግንባታ ምዕራፍ ተሸጋግረዋል::

ከለውጡ ወዲህ 45,566 ቤቶች የተገነቡ ሲሆን በዚህ 6 ወር ደግሞ 4,990 ቤቶች ተገንብተዋል፡፡

ባለፉት 6 ወራት ብቻ 1.5 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ ለባንክ ተመላሽ በማድረግ የቦንድ ብድር ጫናን መቀነስ የተቻለ ሲሆን በአጠቃላይ ከለውጡ በፊት ለጋራ መኖሪያ ቤቶች መገንቢያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተወሰደው የቦንድ ብድር ከወለዱ ብር 61.2 ቢሊየን ከለውጡ ወዲህ መክፈል ተችሏል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍1
የመንገድ መሰረተ ልማት በተመለከተ
የመንገድ ሽፋን፣የትራፊክ ፍሰትና ደህንነትን ለማሻሻል የተሰሩ ስራዎች
👉17.5 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ለመንገድ ልማት ዘርፍ በመመደብ
👉የመንገድ ግንባታ 134.8 ኪ.ሜ.
👉የመንገድ ጥገና 573.54 ኪ.ሜ.
👉ባለፉት 6 ወራት በመንገድ መሰረተ ልማት 708.34 ኪ.ሜ. ማከናወን ተችሏል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የሴቶችና ማህበራዊ ዘርፍ በተመለከተ(ዘርፈ ብዙ አገልግሎት)
ማህበራዊ ስብራትን ለመጠገንና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች፦
👉ተሳትፎ፦ 46,265 ሴቶች በሰላም ግንባታ፣ 144,580 ሴቶች ደግሞ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፈዋል።
የነገዋ የሴቶች ማእከል፦
👉በ3ኛው ዙር 812 ተጋላጭ የነበሩ ሴቶች በክህሎት ሰልጥነው ወደ ሥራ ገብተዋል።
👉በ4ኛው ዙር 1,000 ሴቶች ስልጠናቸውን እያጠናቀቁ ይገኛሉ።
የህብረተሰቡ ተሳትፎና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተመለከተ

👉ከህብረተሰቡና ከባለድርሻ አካላት ለአከባቢ ልማትና ለማህበራዊ ሀላፊነትን በመወጣት ረገድ አገልግሎት የሚውል በጥሬ ገንዘብ ፣ በአይነትና በጉልበት በተደረገ አስተዋፅኦ፤-
• 4,99ዐ የአቅመ ደካማ ቤቶችን፣
• 81 ኪ.ሜ ኮብል ስቶን ጥገና፣
• 30 አነስተኛ ድልድይ ግንባታ ፣
• 28 የኮሚኒቲ ፖሊስ ግንባታ ፣
• 35 የውስጥ ለውስጥ መንገድ መብራት ዝርጋታ ፣
• 68 የጋራ መጸዳጃ ቤቶች ግንባታ ፣
• 36 ኪ.ሜ ጠጠር መንገድ ግንባታ እና
• 60 ኪ.ሜ የቴራዞ መንገድ ግንባታ ተከናውኖ ለአገልግሎት በቅቷል፡፡

👉ብሎኮችን ለነዋሪው ምቹ ከማድረግ አንፃር 648 ብሎኮችን ሞዴል ማድረግ ተችሏል፡፡

👉በ6ወራት ውስጥ ለ881,559 የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ ማጋራት ተችሏል፡፡

👉በአጠቃላይ ባለፉት ስድስት ወራት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት 13,136,434,921 ብር እና በህብረተሰብ ተሳትፎ የአከባቢ ልማት ስራዎች 2,200,466,477.74 በድምሩ 15,336,901,398 ብር በማሰባሰብ ለህዝብ ጥቅም ማዋል ተችሏል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍5