የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
809 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
"በ2018 በጀት ዓመት የ 6 ወር እቅድ አፈፃፀማችን በአማካይ 95.3% ማሳካት ችለናል፡፡" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በመዲናችን አዲስ አበባ በ2018 በጀት ዓመት በ6 ወራት ዉስጥ በሁሉም ዘርፎች በ24/7 የስራ መርህ በተሰራዉ ስራ በአማካይ 95.3% ማሳካት ችለናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በአቀረቡት ሪፖርት ገልፀዋል፡፡
የደንብ ማስከበርና የሕገ-ወጥነት መከላከል በተመለከተ
በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችና ህገወጥ ተግባራትን ለመከላከል ፣ ለመቆጣጠርና ተፈፅሞም ሲገኝ ማረም እንዲቻል ብቁ በስነምግባር የታነጹ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮችን በ9 ዙሮች በማሰልጠን በስነ-ምግባር የታነጹ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ሰልጥነው ወደ ሥራ ገብተዋል።

የደንብ መተላለፍ ቁጥጥር ላይ በመሬት ወረራ፣ በሕገ-ወጥ ግንባታ፣ በጎዳና ንግድ፣ በሕገ-ወጥ እርድና ማስታወቂያ፣ እንዲሁም በደረቅና ፍሳሽ አወጋገድ ዙሪያ የሚታዩ ሕገ-ወጥ ተግባራትን የመከላከልና የማረም ሥራ ተከናውኗል።

አዋኪ ድርጊቶች፤ ህገ-ወጥ የመንገድ አጠቃቀም በመከላከል ረገድ አበረታች ስራ ተከናዉኗል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ሰላም እና ፀጥታ በተመለከተ

የበዓላት አከባበር ላይ ከነዋሪዎች፣ ከሃይማኖት ተቋማትና ከጸጥታ አካላት ጋር በተደረገ ቅንጅት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች የተሳተፉባቸው የአደባባይ በዓላት (ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ሕዝባዊ) ያለምንም የጸጥታ ችግር በድምቀት ተከብረዋል።

የሰላም ሰራዊት ተሳትፎ ከማሳደግ አኳያ ከ22 ሺህ በላይ አዳዲስ የሰላም ሰራዊት አባላትን በመመልመልና በማሰልጠን ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት በየቀኑ ለከተማዋ ሰላም አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ተደርጓል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የፍትሕ ሥርዓት ማስከበር በተመለከተ

የወንጀል ምጣኔ ከመቀነስ አኳያ ከህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፤ ከህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ ከዝርፊያና፣ ደረቅ ወንጀሎች ጋር የተያያዙ በርካታ እርምጃዎች የመውሰድ ስራ ተሰርቷል፡፡

በፍትሀብሔር ጉዳዮች የከተማ አስተዳደሩንና የነዋሪውን መብትና ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር በፍርድ ቤት ክርክር የቀረቡ 4,140 መዝገቦች ውስጥ በፍ/ቤት ውሳኔ ካገኙ 1,491 መዝገቦች 1,382 ለአስተዳደሩ ማስወሰን በመቻሉ ማስከበር የተቻለ የመንግስት እና ሕዝብ መብትና ጥቅም በገንዘብ 3 ቢሊዬን ብር በላይ ሲሆን፣ በአይነት ደግሞ 101 ቤቶች፣ 19 ሼዶች እንዲሁም 178.62 ሄክታር መሬት ህጋዊነት ማስከበር ተችሏል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የትምህርት ዘርፍ በተመለከተ

የከተማ አስተዳደሩ ባለፉት የለውጥ አመታት ለትምህርት ዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ባደረገው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት መሰረት አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን በበጀት ዓመቱ በ 6 ወራት በተሰራዉ ስራ

ከተማሪዎች ውጤት አንጻር፤ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና 50% በላይ ያመጡ ተማሪዎች 2015 ዓ.ም ከነበረበት 80.2% በአሁን ወቅት 95% ማድረስ ተችሏል::
የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና 50% በላይ ያመጡ ተማሪዎች 2010 ዓ.ም ከነበረበት 36.1% በአሁን ወቅት ወደ 88.8% ከፍ ብሏል።

12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና 50% በላይ ያመጡ ተማሪዎች 2013 ዓ.ም ከነበረበት 25.45% በአሁን ወቅት 31% ከፍ ማለቱ እና በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች መካከል የነበረውን የውጤት ልዩነት በከፍተኛ ደረጃ ተቀራራቢ የአፈጻጸም ውጤት እንዲመዘገብ አስችሏል፡፡

የትምህርት ተሣትፎና ፍትሐዊነት በማሳደግ በዕውቀትና በሥነ- ምግባር የታነፀ ትውልድን ለማፍራት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አጠቃላይ ተማሪ ቅበላ ከነበረበት 1,253,737 ወደ 1,334,830 የደረሰ ሲሆን ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የተማሪ ቁጥር 81,093 ዕድገት አሳይቷል።

የትምህርት ፍትሃዊነትና አካታችነትን ለማስፈን በተደረገው ጥረት በሁሉም ት/ቤቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት በጥቅሉ 124 ማእከላትን ማድረስ ተችሏል፡፡

በ80 ት/ቤቶች ራምፕ ጥገና እና ራምፕ በሌላቸው 4 ት/ቤቶች በአዲስ መልክ የመገንባት ሥራ ፤ ለአይነ ስውራን ተማሪዎች የብሬል መፅሃፍ ህትመት በማከናወን ስራ እንዲሁም ለ36 ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች እና ለመምህራኑ ስፈላጊ ሆኑ ግበዓቶች እንዲሟሉ ተደርጓል::

የት/ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል ባለፉት 6 ወራት “ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ በተሰራው ሥራ ተለያዩ ባለድርሻ አጋር አካላትን በትምህርት ጥራት ላይ ተሳትፎአቸዉን በማጠናከር በጥሬ ገንዘብ 637,253,857፤ በዓይነት 1,137, 493,918፤ በጉልበት 211,388,874፣በዕቀውት 243,478,637 በድምሩ 1.32 ቢሊየን ለመሰብሰብ ታቅዶ ክንውን 2.23 ቢሊየን (100% በላይ) ሀብት ማሰባሰብ ተችሏል፡፡

በተማሪዎች ምገባ፤- በቅድመ አንደኛ እና አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ላይ 940,329 በላይ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ እንዲመገቡ እየተደረገ ሲሆን የተማሪ ዩኒፎርም፣ የትምህርት ቁሳቁስ እና የመምህራን ጋዋን በወቅቱ እንዲደርሳቸው በማድረግ በኢኮኖሚያዊ ጫና ምክንያት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች (መጠነ ማቋረጥ)፤የሚደግሙ (ተማሪዎች መጠነ መድገም) ጉልህ በሆነ መልኩ መቀነስ እንዲሁም በተማሪዎች መካከል የእኩልነት ስሜት በማዳበር የስነ ልቦና ጫናን መቀነስ ተችሏል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍2
ባለፉት 6 ወራት በንግዱ ዘርፍ የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች በተመለከተ

የገበያ መረጋጋት እና የምርት አቅርቦት
👉የሰብል አቅርቦት 688,153 ኩንታል በላይ ፤
👉አትክልትና ፍራፍሬ 3,899,375 በላይ ፤
👉ዳልጋ ክብት እና በግና ፍየል 2,127,208 በላይ ማቅረብ የተቻለ ሲሆን፤
👉በተጨማሪም የድጐማ ምርቶች በተለይ በየቀኑ በሚሊዮኖች የዳቦ አቅርቦትን በመጨመር፣
👉12,601,755 ሊትር የምግብ ዘይትና 242,892 ኩንታል ስኳር በማቅረብ የከተማችንን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ ተጨባጭ ስራዎች አከናውነናል ፡፡

👉የንግድ መሠረተ ልማት እና ቁጥጥር
የደላላን ሰንሰለት ለመበጠስና ሸማቹን ከአምራች ጋር በቀጥታ ለማገናኘት ሰፊ ስራዎች ተሰርተዋል፦
👉የገበያ ማዕከላት፦ በአምስቱም የከተማ መግቢያዎች ከተገነቡት በተጨማሪ የላፍቶ ቁጥር 2 ገበያ ማዕከል ወደ አገልግሎት ገብቷል።
👉የቅዳሜና እሁድ ገበያ፦ የገበያ ቦታዎች ቁጥር ከ219 ወደ 245 ከፍ እንዲል ተደርጓል።
👉ህጋዊነትን ማስፈን፦ በ230,013 ድርጅቶች ላይ ክትትል ተደርጎ፣ 12,139 ጥፋተኞች ተለይተዋል። ከእነዚህም ውስጥ 10,496 ነጋዴዎች ወደ ህጋዊ መስመር ተመልሰዋል።
👉መደበኛ ያልሆነ ንግድ፦ 7,400 መደበኛ ያልሆኑ አነስተኛ ንግዶችን ህጋዊ እውቅና በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል።